Thursday, May 15, 2014

ኢህአዴግ በምርጫ 2007 በቀይ ካርድ መባረር አለበት
Share/Bookmark


የአዲስ አበባ ንሮ
ግማሽ በልቶ ግማሽ ጦም አድሮ
ግማሽ ጠጥቶ ግማሽ ተጠምቶ
ግማሽ በርቶ ግማሽ ጠፍቶ
ግማሽ ተደስቶ ግማሽ ተማርሮ

ሰሞኑን ውሃ የለም፡፡በተለይም ከቀጨኔ መድሃኒአለም አንስቶ እስከ አራዳው ጊዮርጊስ ደረስ ውሃ ከጠፋ ቆይቷል፡፡ትናንት ደሞ የውሃው ችግር ለገሃር ወደ ሚገኘው መስራቤታችን ተከትሎን መጣና መፀዳጃ ቤቶች በጣም ከመቆሸሻቸው የተነሳ ገምተው ስራ መስራት ከልክለውን ውሏል፡፡

በምግብ ቤቶች ገብቶ ምግብ በልቶ ውሃ ማግኘት እርም ሆኗል፡፡በውሃ መጥፋት አሳብበው በፕላስቲክ የታሸገ ውሃ እንድትገዛ የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ከቀን ወደ ቀን እየተባባሱ በመምጣታቸው በካፌዎችና ሬስትራንቶች ውሃ በነፃ ማግኘት ታሪክ ወደ መሆን እየተቃረበ ነው፡፡
1.   የቤት ክራይ ዋጋ ከልክ በላይ መናር
2.   የትራንስፖርት እጥረት
3.   የውሃ ችግር
4.   የመብራት መቆራረጥ
5.   የንሮ ውድነት ናቸው፡፡

የእነዝያ ችግሮች ዛሬም መፍትሔ አልተበጀላቸውም፡፡ህዝቡ ዛሬም ቤት ወደ ስራ እንዲሁም ከስራ ወደ ቤት ሲመላለስ በየመንገዱ ብያንስ ሩብ ሰዓት ተሰልፎ መቆሙ ግዴታው ሆኗል፡፡በየጊዜው በውሃና በመብራት መቆራረጥ ንሮው እንደተቃወሰ ይገኛል፡፡የቤት ክራይ ንረትም ከቁጥጥራችን ከወጣ ቆይቷል፡፡ስራችን ሰርቶ ለቤት አከራዮች ማስረከብ ሆኗል፡፡የድሮው ርስተ ጉልታዊ ስርዓት መልኩን ቀይሮ እያስገበረን ነው፡፡

ከዚህ የምንረዳው ይህ መንግስት ስራውን መስራት እንዳልቻለ ነው፡፡የህዝብ ችግሮችን ለመፍታት ፍላጎትም ሆነ ቁርጠኝነት እንደሌለው ነው የምንረዳው፡፡በመሆኑም ይህ መንግስት ከስልጣን መባረር አለበት፡፡የኢህአዴግ ቀልዶችና ተረት ተረቶች ለዓመታት ሰምተን ሰልችቶናል፡፡ነገረ ስራው ሁሉ ‹‹አበበ በሶ በላ›› ሆኗል፡፡ወሬው ‹‹አበበ በሶ በላ›› ነው፣ስራውም ‹‹አበበ በሶ በላ›› ነው፡፡እናም ይብቃው፡፡ከዚህ በላይ መታገስ አንችልም፡፡

ኢህአዴግን እንዴት ከስልጣን እናባርረው?


በመርጫ! ምርጫ 2007 ደርሳለች አይደል? ኢህአዴግ በቀይ ካርድ መባረር አለበት፡፡በግርግር ሳይሆን( ኢህአዴግን በግርግር ማባረር አይቻልም…ተሸናፊው ህዝብ ነው የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም ኢህአዴግ ሌባ ነው፤ ግርግር ደሞ ሌለይባ ይመቻል ‹‹የገበያ ግርግር ለለይባ ይመቻል›› እንዲሉ) በምርጫ…በድምፅ ብልጫ…ኢህአዴግን ወክለው የሚወዳደሩ ሁሉ አንዳችም ድምፅ ማግኘት የለባቸውም፡፡እሮሯችን አልሰሙማ፣ ችግሮቻችን አልፈቱልንማ፣ ህዝቡን እንደፈጉት ለማድረግ የተሾሙ ከበርቴዎች እንጂ የህዝብ አገልጋሊዎች አደሉማ፡፡ከዚህ በላይ ምን ምን ዓይነት ማስረጃ እንፈልጋለን፡፡

እኛ ነን ተስፋ ያልቆረጥነው እንጂ ኢህአዴግ እማ ዜሮ መሆኑን ሺ ጊዜ ደጋግሞ አረጋግጦልናል፡፡አንዴ ከቻይና፣ሌላ ጊዜ ደሞ ጃፓን፣ አንዴ ከአውሮፓ፣ደሞ ከአሜሪካ አደዲስ የእንግሊዘኛ ቃላት እየኮረጀ መደጋገም እንጂ ምን አዲስ ነገር አመጣ? BPR፣ Transformation፣ change army፣command post፣quality circle፣Kaizen….ከዛስ፡፡

ደሞ አያፍርም! ‹‹ተማሪዎች በሃገራዊ ፈተናዎች እየተኮራረጁ ነውና ማቆም›› አለባቸው ይለናል፡፡ሲጀምር ሃገራችንን የኩረጃ ሃገር ያደረጋት ማን ሆነና ነው ኢህአዴግ ስለኩረጃ መጥፎነት የሚሰብከው? ወይስ እንደ አንዳንዶቹ አመንዝራ ሰባኪዎች ‹‹የምናገረው እንጂ የማደርገውን አትመልከቱ›› ሊለን ፈልጎ ነው?

አዎ! ይህ ከኩረጃ በስተቀር ምንም የማያውቅ ኮራዥ መንግስት ምርጫ 2007ን ማለፍ የለበትም፡፡በፈተና ላይ ሲኮረጅ የተገኘ ተማሪ የፈተና ወረቀቱን በቀይ እስክርቢቶ ምልክት ተደርጎበት ከመፈተኛ አደራሽ ይባረራል፣ውጤቱም ይሰረዛል፡፡ኢህአዴግም እንዲሁ ከፈተና አዳራሽ(ከኢትዮጵያውያን ጫንቃ) መባረር አለበት…በቀይ ካርድ!


4 comments:

 1. ጓደኜ የነዚህ መንሰኤ ምን መሆኑ ታውቃለህ:እድገት እድገት እድገት ነው ቡዙ ማማረር የለብህም ድሮ የነዝህ ችግር ይቅርና በሰላም የምትኖርበት፣ይምትበላበት ፣እንደንተ የፈለገሀው የምትናገርበት ግዜ አልነበረምና ወደኋላ ማስታወስ አለብህ….

  ReplyDelete
  Replies
  1. እድገት ችግሮችን ይቀርፋል እንጂ የችግሮች ምንጭ አይሆንም Muez Bugssa፡፡አልፎ አልፎ የችግሮች ምንጭ መሆን የሚችለው ደሞ የለምንም ቁጥጥር በደመነፍስ የሚከናወን ከሆነ ብቻ ነው፡፡ስለዚህ አሁንም ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ብቃት የለውምና በቀይ ካርድ መባረር አለበት፡፡

   Delete
  2. so who do you want to rule the country? our oppositions are bunch of useless people who are organized not to create an alternatives but to condemn the government. Do you think we are blind not to see the problems we face every day?? No every one is well aware of that, but who can we choose with a better alternative? None. our opposition are there to insult and condemn the gov, which even civilians could do it. I wonder why we need such opposition? to do the things that we can do, blame, insult, condemn or because they have a better option??

   Delete
  3. Mr/ Mis Anonymous, I do share your concern. The oppositions are another gangs of cheats. But for how long can we be under the tyranny of EPRDF? For how long can we be at the mercy of EPRDF foxes? Haven't we had enough of them? At least the oppositions should have enough seat on the parliament... no matter who they are, though that may mean just varieties of monkeys.

   Delete