Sunday, January 18, 2015

ቀፃሊ ጉዕዞ ህዝቢ ትግራይን ህወሓትን ናበይ የምርሕ?




ህዝቢ ትግራይ ብውድብ ህወሓት ካብ ዝምራሕ 40 ዓመታት ተቖፂሮም ኣለው፡፡ደርጊ ብዘይካ ከተማታትን ከባቢአንን መብዛሕቲኡ ከባቢታት ትግራይ ንምምሕዳር ዕድል ኣይነበሮን፡፡ብስሩ እውን እቲ ጉጅለ(ኮሚቴ) ብዛዕባ እንታይነት ህዝባዊ ምምሕዳር ዘይተሰቖሮ ስለዝነበረ ኣፍካ መሊእኻ መንግስታዊ ምምሕዳር መስሪቱ ነይሩ ንክትብል ዘፀግም እዩ፡፡
ህወሓት ግን ብረታዊ ቃልሲ ምስ ጀመረት እያ ህዝቢ ክተመሓዳደር ዝጀመረት፡፡እዚ ክብሃል ከሎ ግን እቲ ህዝቢ ሓንጎፋይ ኢሉ እዩ ተቐቢልዋ ማለት ኣይኮነን፡፡ኣብቲ ሻዓኡ እዋን ዝነበሩ ምሁራትን ንኡሳን መሳፍንትን ይቃወሙዋ ከም ዝነበሩን እታ ውድብ ድማ ብዘይንሕስያ ከም ዝቐፅዐቶምን ፀሓይ ዝወቕዖ ሓቂ እዩ፡፡ብፍላይ ግን፣ እቶም እናዓፈነት ናብ 06 ዝወሰደቶም ተጋሩ ክሳብ ሐዚ ኣበይ ከም ዝነጠቡ ኣይፍለጥን፡፡

ዝኾነ ኾይኑ ግን፣ መብዛሕቲኡ ከባቢታት ትግራይ ኣብ ኢድ ቁፅፅር ህወሓት ከም ዝነበረን ሐዚ እውን ከም ዘሎን ብዙሕ ዘካትዕ ኣይኮነን፡፡እቲ ወድዓዊ ጉዳይ እዚ ካብ ኾነ፣ ኣብዚ ሐዚ እዋን፣ እንተውሓደ እዞም ዝስዕቡ ሕቶታት ክልዓሉን ግቡእ መልሲ ክረኽቡን ኣለዎም ዝብል መርገፂ ኣለኒ፡፡
1.  ቅድሚ አርባዓ ዓመታት መነባብሮ ህዝቢ ትግራይ እንታይ ይመስል ነይሩ?
2.  ሐዚ ኸ ኣብ ምንታይ ኩነታት  ይርከብ?
3.  ኣንፈት ቀፃሊ ጉዕዞኡ ኸ ናበይ የምርሕ?

ውድብ ህወሓት ነቲ ዝመፅእ ዘሎ መበል 40 ዓመት ምጅማር ብረታዊ ቃልሲ ብድምቀት ንምኽባር ኣብ ምሽብሻብ ትርከብ፡፡ይኹን እምበር፣ እቲ ብዓል ካብቶም ዝሓለፉ ብዓላት ብምንታይ ከም ዝፍለ ዝተፈለጠ ነገር የለን፡፡ወይከዓ ብውልቀይ ዝፈልጦ የብለይን፡፡እዚ ክብል ከለኹ ግን ንህወሓት ዝህልዎ ረብሓ ጠፊእኒ ከይኮነስ ኣብ መነባብሮ ህዝቢ ትግራይ ዘምፅኦ ርኡይ ለውጢ እንታይ እዩ? ንባል እየ ደልየ፡፡

እቲ ወግሐ ፀብሐ ብሬድዮን ተለቪዥንን እናተጋነነ ዝጋዋሕ ዘሎ ስርሒት ፕሮፓጋንዳ ኣብ መሬት ከም ዘይርከብ ኣብቲ ዝሓለፈ ወርሒ ናብቲ ክልል ኣምሪሖም ዝነበሩ ጋዜጠኛታትን ከየንትን በቢገፆም ኣቃሊዖሞ እዮም፡፡ኣማሓዳሪ እቲ ክልል ዝኾኑ ፕረዚደንት ኣባይ ወልዱ እውን ንምስክርነት እቶም ጋዜጠኛታትን ከየንትን ዘጠናኽር ርእይቶ እዮም ዝሃቡ፡፡እቲ ‹‹ገባር ትግራይ 100 ምኢታዊ ሞዴል›› ከም ዝኾነ ብጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ዝተአወጀ ኣዋጅ ሻዕኡ ናበይ ከም ዝሃፈፈ ግን እንድዒ፡፡

Friday, January 16, 2015

የኢትዮጵያ ህዝብና መሪዎቹ፡እንቁራሪትና ጊንጥ




ጊንጥና እንቁራሪት አፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ ከሚገማሸር ውንዝ ዳር ተገናኙ፡፡ጊንጥ ወደ እንቁራሪት ጠጋ ብላ በጀረቧን አዝላ ወንዙን እንድታሻግራት በትህትና ጠየቀቻት፡፡የጊንጦች አመል ጠንቅቃ የምታውቀው እንቁራሪት ‹‹ወንዙን ባሻግርሽ ደስ ባለኝ፤ ግን ትነድፊኛለሽ›› ስትል መለሰችላት፡፡
ጊንጥ ‹‹በጭራሽ አላድርገውም፤ አልነድፍሽም፤ እባክሽን ወንዙን አሻግሪኝ›› በማለት እንቁራሪቷን 
ተመፀነቻት፡፡
‹‹
አይ፣ አይሆንም፤ እንደማትነድፊኝ እርግጠኛ የምሆንበት መንገድ የለም››መለሰች እንቁራሪት፡፡

‹‹ሙች! አልነድፍሽም፤ የግድ መሻገር ስላለብኝ እባክሽን ተባበሪኝ›› ጊንጥ ተማፀነች፡፡በመቀጠልም ‹‹እስኪ አስቢው፤ ከነደፍኩሽ እኮ ትሰምጪያለሽ፤ እናም እኔም እብሬሽ እሰምጣለሁ ማለት ነው፡፡የምፈልገው ግን ወንዙን በሰላም መሻገር እንጂ ሰምጬ መሞት አይደም፡፡ዓላማየ እንደሱ ቢሆንማ አንችን ለምን አስቸግርሻለሁ? ቢሳካልኝም ባይሳካልኝም፣ ወደ ጎርፉ ዘልዬ አልገባም?›› በማለት እንቁራሪትዋን ለማሰመን አበክራ መጎተቻት፡፡

እንቁራሪት የማትሰማማበት አሳማኝ ምክንያት አልነራትምና ጊንጥዋን አመነቻት፡፡ጊንጢ በእንቁራሪትዋ ጀርባ ተፈናጠጠችና ተዛዝለው ወደ ጎርፉ ገቡ፡፡በወንዙ መሃል እንደደረሱ፣ ጊንጥ ሆዬእንቁራሪትዋን ነደፈቻትና ተያይዘው መስመጥ ጀመሩ፡፡እንቁራሪቷ ለመሞት እያጣጣረች እያለች ‹‹ለምን?›› ስትል ጊንጥዋን ጠየቀቻት፡፡የጊንጧ 
መልስ ‹‹ጊንጥ እኮ ነኝ፤ ከጊጥ ሌላ ጠብቀሽ ነበር?
በቃ፣ ተፈጥሮዬ ስለሆነ ነደፍኩሽ›› የሚል ነበር፡፡

ይህ አስገራሚ ተረት ተረት የኤሶፕ እንደሆነ ይነገራል፡፡የሃገራችን ታሪካዊና ነባራዊ ሁኔታዎችን ጥርት አድርጎ የሚያሳይ ሆኖ ስላገኘት እንደ መንደርደርያ ልጠቀምበት ወደድኩ፡፡እንቁራሪትዋ የኢትዮጵያ ህዝብ ነች፡፡ጊንጥዋ ደሞ ድሮና ዘንድሮ በኢትዮጵያ የነገሱ አምባገነኖችና ሹመኞቻቸውን ትወክላለች፡፡

ሲጀመር መሪዎች መሪ መሆን ያለባቸው የሚመሩት ህዝብ ይሁንታ ሲሰጣቸው ብቻ ነው፡፡የህዝብ ይሁንታ ሊያገኙ የሚችሉት ድሞ ህዝቡን እየመሩ የህይወት ወንዝን ሊያሻግሩት እንደሚችሉ ሲታመንባቸው ነው፡፡ለተወሰኑ ዓመታት ተፈትነው ህዝቡን የህይወት ወንዝን ሊያሻግሩት የማይችሉ መሆናቸውን ሲረጋገጥም በሌሎች መተካት አለባቸው፡፡በአጭሩ መሪዎች ህዝብን ለማገልገል በህዝቡ ፍቃድ የሚሸሙ እንጂ በጉልበታቸው በህዝቡ ጫንቃ የሚፈናጠጡ ጊንጦች መሆን አልነረባቸውም፡፡

በሃገራችን የነበረውና ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግን የዚሁ ግልባጭ ነው፡፡መሪዎቹ ህዝቡን መርተው ወንዙን ማሻገር ሲገባቸው ህዝቡ መሪዎቹን ተሸክሞ ኢንዲያሻግራቸው ያስገድዱታል፡፡የጊንጥዋን ያህል እንኳን ለጊዜው አሳማኝ ምክንያቶች ማቅረብ አይችሉም፡፡ህዝቡ የግድ እንዲሸከማቸው ያስገድዱታል፡፡ተሸከሞ የህይወት ወንዙን ሊያሻግራቸው ከጎሩፉ በሚታገልበት ወቅት ግን ጀርባውን ይነድፉታል፡፡ከዛም ህዝቡም መሪዎቹም አብረው ይሰምጡና ጎርፍ ይወስዳቸዋል፡፡ለምን ቢባል፣ የመሪዎቹ ተፈጥሮ እንደዛ ሰለሆነ፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ የሚታወሱ ነገስታት እንዳለ ከዚህ የተለየ መንገድ አልተከተሉም፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ አፄ ኃይለሥላሴን ለ40 ዓመታት ተሸክሟቸዋል፡፡በነዝያ ዓመታት ግን የህዝቡን ጀርባ ሲነድፉ ነው የኖሩት፤ በመጨረሻም ከህዝቡ ጋራ ጎርፍ ወሰዳቸው…የአብዮት ጎርፍ፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ የደርግ ስርዓትንም ለ17 ዓመታት በጀርባው ተሸክሞ የኑሮ ወንዙን ለመሻገር የቻለውን ሁሉ አድርጓል፡፡መክፈል የነበረበት መስዋእት ሁሉ ከፍሏል፡፡

ደርግ ግን የህዝቡን ጫንቃ ነደፈውና አብረው ሰጠሙ፤ የኑሮ ጎርፍም ወሰዳቸው፡፡አሁን ያለው ስርዓትም ለ24 ዓመታት ተሸክመን የችጋር ወንዙን ለመሻገር በመጣጣር ላይ እንገኛለን፡፡በጎርፉ መሃል እያለን በተደጋጋሚ ጀርባችንን ነድፎናል፡፡ሆኖም ግን ሰውነታችን ለንድፍያዎች አዲስ ባለመሆኑና ያለፉት ስርዓቶች ከተውብን ጠባሳዎች ጋራ በመላመዱ ብቻ ተዝለፍልፈን ልንወድቅ አልቻልንም፡፡ለወደፊት ግን ይህ ነገር ቀጣይነት የሚኖረው አይመስለኝም፡፡አንድም ተናዳፊ መሪዎቹን ከችጋር ወንዙ ውሰጥ ጥሎ ወደ ብልፅግና ጎዳና ይሻገራል አልያም እንደ ድሮው አብረው ይሰምጣሉ፡፡

እንደኔ እምነት ከሆነ፣ ህዝቡ ከታሪክ መማር አለበት፡፡ከነገስታት አክሱም፣ላሊበላ፣ጎንደር፣ትግራይና ሽዋ ጋር አብሮ በጎርፍ በመወሰዱ ከዓለም የብልፅግና ቁንጮነት ተንከባልሎ ወርዶ ወርዶ ወርዶ… ዛሬ ላለበት የድህነትና የኋላ ቀረነት ተምሳሌትነት ደርሰዋል፡፡ከዚህ በታች ግን መውረድም መዋረድም አይችልም…መሞትና ጨርሶ ከምድረ ገፅ መጥፋት እንጂ፡፡ይህ እንዳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ጊንጦችን አምኖ መሸከም የለበትም፡፡በየዋህነቱ ተታልሎም ይሁን ተገድዶ የተሸከማቸው ጊንጦችም ተባብሮ ከጫንቃው አሽቀንጥሮ ሊወረውራቸው ይገባል፡፡ጊንጦችን ተሸክሞ ያደገው ጉዞ ስኬት አልባ ነበር፡፡ጊንጦችን በጊንጦች መቀያየርም ከንድፍያ አልታደገውም፡፡

ከአሁን ወድያ ግን በቃኝ ማለት አለበት…አሁን ያለውን የምርጫ ጭላንጭል ተጠቅሞ ከዘመኑ ጋራ አብረው መራመድ የሚችሉ መሪዎቹን መምረጥ አለበት፡፡የፈለገው ቢመጣም ጦረኛ ጊንጦችን ማመን የለበትም፡፡በጠብ መንጃ አፈሙዝ ዙፋን የተቆናጠጡ ሁሉ ጊንጦች እንደሚሆኑ ከታሪክ ተምረናል፡፡ስለሆነም፣ ነፍጥ አንግበው ህዝቡን ከጭቆና ቀንበር አላቅቀን፤ የነፃነት፣የሉዓላዊነትና የዲሞክራሲ ባለቤት እናደርጋለን የሚሉ ሁሉ ግባቸው የስልጣን ኮርቻን መቆናጠጥ ብቻ መሆኑን ልንስተው አይገባም፡፡ጦረኛ ነፃ አውጪ ሊኖር አይችልም፡፡

ጦርነት የነበረውን ያወድማል እንጂ የሚጨምረው ነገር እንደማይኖር ከታሪክ ተምረናል፡፡በጦርነት ዘመናዊ የስልጣን ሽግግር ሊኖር አይችልም፡፡በታሪካችን የተከሰቱት የስልጣን ሽግግሮች ዘመናዊ ስላልነበሩ አሁን ለለንበት የድህነትና የኋላ ቀርነት ተምሳሌትነት ተዳርገናል፡፡ከአሁን በኋላ ግን ይብቃው፤ እባቦችና ጊንጦች በእርግቦች ይተኩ፡፡



Sunday, January 11, 2015

ሰበር ዜና፡ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በአሳት ቃጠሎ ወደመ




እቴጌጣይቱ ሆቴል
በወርሐ ነሐሴ 1898 ዓ.ም የተቋቀመውና የ109 ዓመታት የዕድሜ ባለፀጋው እቴጌ ጣይቱ ሆቴል የእሳት ቃጠሎ ሰለባ ሆነ፡፡

ሆቴሉ በማሐል ፕያሳ(አራዳ) የሚገኝና በእቴጌ ጣይቱ እንደተመሰተ የሚነገርለት በኢትዮጵያ ቀዳሚው ሆቴል ነው፡፡

የተለያዩ ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶችን በማቆያነት እንዲያገለግል ተስቦ የቋቋመው፣ የሃገራችን አንጋፋና ታሪካዊ ሆቴል ከጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን አጠገብ ከሚገኘው የእሳት አደጋ ድርጅት ድንጋይ ወርውሮ ሊደርስበት በሚችል ርቀት የሚገኝ ቢሆንም በጊዜ ደርሶ ከቃጠሎው ሊታደገው አልቻለም፡፡

ድርጅቱ የእሳት ቃጠሎው እንደተነሳ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ቢደወልለትም ከአንድ ሰዓት በኋላ ደርሶ ሆቴሉ ብዙ ውድመት ከደረሰበት በኋላ ‹‹በቁጥጥር ስር›› እንዳዋለው ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ፣ድርጅቱ በደቂቃዎች ሳይሆን በሳዓቶች እየዘገየ የሚደርስ በመሆኑ የአዲስ አበባ ኗሪዎች ሁሌም እንደ ተማረሩበት ነው፡፡
አዲስ አበባ በየዓመቱ የሰው ህይወትና በሚሊዮን የሚቆጠር ንብረት በእሳት አደጋ የሚወድምባት ከተማ ነች፡፡

ባለፈው ዓመት(ታሕሳስ ወር 2006 ዓ.ም) መርካቶ አከባቢ በተለምዶ ጆንያ ተራ እየተባለ በሚጠራው ሰፈር የደረሰው የእሳት አደጋ በ32 ሰዎች ላይ አደጋ እንዳደረሰ፤ 40 ሱቆች ሙሉ በሙሉ እንዳወመና አምስት መጋዝኖች ዶግ አመድ እንዳደረገ የሚታወስ ነው፡፡

Sunday, January 4, 2015

‹‹ምርጫው በዴሞክራሲና በአምባገነንነት መኻል ነበር›› ገብሩ አስራት



google pitures
የታጋይ ገብሩ አስራት መፅሐፍ(ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ) አነበብኩት፡፡ይህ መፅሐፍ አንብቤ እንደጨረስኩ በአሁኑ ሰዓት ህወሓት የሚባል ድርጅት አለመኖሩን ተገንዝብያለሁ፡፡የህወሓት ታሪክ ያከተመው በ1993 ዓ.ም ነበር፡፡
ለዚሁ ድምዳሜ ያደረሱኝ ብዙ ምክንያቶች መደርደር እችላለሁ፡፡ለጊዜው ግን ሁለቱን ብቻ ለስቀምጥ፡፡
አንደኛው ምክንያት፣ የህወሓት ህገ ደምብ በ93 ዓ.ም ተሽሯል፡፡ተሻሽለዋል አላልኩም፤ ሙሉ በሙሉ ተሽሯል! ማን አፈረሰው? ቢባል፣ አሁን በስልጣን ያለው ቡድን፡፡በስምምነት ሳይሆን በወታደራዊ እርምጃ!
‹‹የህወሓት ህገ ደምብ ውስብስብ ሁኔታውችንን በሚገባ ስለማያገናዝብ ቆሻሻ መጠራቀምያ ውስጥ መጣል አለበት፤ ሠገራ ነው››(መለስ ዜናዊ ገፅ፡298)
‹‹ድርጅቱ ለአደጋ በተጋለጠበት ወቅት ሕገ ደምብ ብሎ ነገር የለም፤በእንዲህ ያለ የድርጅት ቀውስ ወቅት አሳሳቢ የሚሆነው የድርጅቱ ህልውና እንጂ የሕገ ደምቡ መከበር አይደለም››(ስዩም መስፍን ገፅ፡308)

እነዚህ ሰዎች እያሉን ያሉት ‹‹በመፈንቅለ መንግስት(ኩዴታ) ስልጣን ለብቻችን ተቆጣጥረናል›› ነው፡፡ህገ ደምብ ከሌለ ድርጅት ብሎ ነገር የለም፡፡ምክንያቱም ምትግባበትም ሆነ የምትለያይበት መርሕ አይታወቅም፡፡እንደ ድርጅት የምትመራበት ደምብ ከሌለ ማንኛውም ስልት ብትጠቀም ትክክል ነው፡፡ይህ ደሞ ማፍያ(ሽፍታ) እንጂ ድርጅት አይደለም፡፡አሁኑ ቡድን የኸው ነው፡፡
ሁለተኛው ምክንያት፣ ህወሓት የታገለው ቤተ መንግስቱን የሚቆጣጠሩት ሰዎች ለመለወጥ ሳይሆን ወታደራዊ ስርዓቱን በህዝባዊ ስርዓት ለመቀየር ነበር፡፡ነበር ባይሰበር፡፡ዛሬ ህዝባዊ የሚለው ቃል በተግባር የለም፤ በቃል ደረጃ እማ ደርግም ይጠቀምበት ነበር፡፡

የአሁኑ ቡድን መነሻና መድረሻው ስልጣንና ስልጣን ብቻ ነው፡፡ስለ ህዝብ ቅንጣት ታህል ስሜት የለውም፤ ስለ ሃገር የሚያገባው ነገር የለም…ስልጣንና ገንዘብ እስካተረፈባት ድረስ ኢትዮጵያ እንደለ ከመሸጥ ወደ ኋላ እንደማይል በተግባር አስመስከሯል፡፡ዴሞክራሲ ብሎ ቀልድ አያውቅም፡፡ስለሃገርና ህዝቦቿ ደንታ የሌለው ቡድን በማንኛውም መለክያ ህወሓትን ሊወክል አይችልም፡፡
ህወሓትን በመፈንቅለ መንግስት የደመሰሰው ቡድን የድህንነት፣የፖሊስና የወታደር መዋቅር ተጠቅሞ ስልጣኑን አስጠብቋል፡፡ የእነ ተወልድ-ስዬ ቡድን ግን ህገ ደምቡን ብቻ ተከትለው የሃገር ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ለማስከበር ታግሏል፡፡የድርጅቱ ህዝባዊነት እንዲቀጥል በነበራቸው አቋም ወታደራዊ እርምጃ እንደ አማራጭ ከመጠቀም ተቆጥበዋል፡፡