Monday, April 29, 2013

Why "NO ENOUGHS"?

                        



In our country there is no enough electricity. No enough tape water. No enough transpiration. No enough justice. No enough rent houses to live in.No enough freedom of expression. No! No! No!..

We have more than enough of  NO ENOUGHS. The only thing we have in excess is shortage of basic things for life. More than 50 percent of our society is illiterate. And over 24 percent of the population is unemployed.Over 39 percent live blow poverty line.  Hence, our country is labeled  POOR. If the so called  educated and hence employed are challenged this far to survive, I don't know what kind of life our unemployed compatriots are leading. 

But why?
Our country is poor not due to lack of resources. Our country is poor not due to a curse of some superpower. Our country 'Ethiopia' is poor neither due to invasion, aggression nor due to foreign manipulation. We are poor only because our rulers are mentally and spiritually poor.They are not strong enough to overcome their personal egos. Their ego has blocked their vision. They cannot think beyond their bellies. The longest vision they are capable of is up to their nose. 

But we are blessed that they cannot limit the amount of air inhale and exhale. We are blessed they cannot blackout the sun, the moon, and the stars. We are blessed they cannot turn on and off our body parts as they please. We are blessed they cannot limit our life span.

You are Blessed, that you are reading this text right now. You are lucky that you are not among the 50 percent illiterate compatriots. And I am more than blessed that I am able to write it to express my internal feeling.

Thursday, April 25, 2013

የሴቶች አገዛዝ





ድሮ ሴቶችን እማውቃቸው በአይነ ዓፈርነታቸው ነበር። አብሮኝ ያደገው የክፍለ ሃገር ውቦች መሽኮርመም ከህሊናየ መቸም አይጠፋም። ትኩር ብለህ ብታያቸው ፊታቸው ወደ ሌላ አቅጣጫ ይመልሳሉ፣ አንገታቸውን ሰበር ያደርጋሉ።እንኳንስ ልጃገረዶች እናቶቻችንም  አይነ ዓፋሮች ናቸው። ባላቸውን በስሙ ለመጥራት አይደፍሩም፤ ከጠሩም አንቱ በማለት ነው።

ምክንያቱ ይላል አንድ ህፃን እያሎህ የሰማሁት ተረት ተረት፡ ድሮ የዓለም መሪዎች ሴቶች ነበሩ።መቼ? የሰው ልጅ እርሻ ከመጀመሩ በፊት… እንደ ወፈ ሰማይ ሳይዘራ ያጭድ በነበረበት ዘመን።ያኔ ጫካው፣ሜዳው፣ ዳገቱና ቁልቁለቱ ሁሉ በሴቶች ግዛት ነበር።ምክንያቱም፣ ያኔ የእናቶች እናትነት እንጂ የወንዶች የአባትነት እውቅና አልተሰጠም ነበር። እናም አባቶችም ሆነ ልጆች የእናቶቻቸው ተገዢ ወይም ታዛዥ ነበሩ፤ ልክ እንደ ነገስታት ሰራዊት(ወንዶች የሴቶች ሎሌ ነበሩ)።

እናም የሰው ልጅ በዚህ ዓይነት ስርዓት ይተዳደር በነበረበት ዘመን ሶስት ሴቶች ሁነው አንድ ምስኪን መንገደኛ ያገኙና አስገድደው ይደፍሩታል። ተራበተራ እያሉ አደከሙት ሶስቱም ስሜታቸው እስኪረካ ድረስ። ይባስ ብሎ ግን እየተመላለሱ ዱቄት ካደረጉት በኋላም ለሚቀጥለው ቀን እንዲጠቅማቸው በማሰብ ከአንዱ ዛፍ ጋር አጣብቀው ሁሉት እጆቹን ኋሊት ጠፍረው ያስሩታል።

ፀሓይ ጠለቀች፤ መሬት የጨለማ ብርድልብሷን ለበሰች። የአውሬዎች ክፍለ ጊዜ ታወጀ፤ ከያሉበት በመጠራራት ተሰባሰቡና ጉዞ ጀመሩ። ሲጓዙ አምሽተው ያ የፈረደበት ምስኪን መንገደኛ ተስሮ አገኙትና የመስቀል ቅርጫ ያደርጉታል። ይህን ግፍ ሲመለከት የነበረው የእግዚሔር መልአክም በሴቶቹ ተግባር በጣም ይናደዳል። እናም የሶስቱም ፊት በጥፊ ለመምታት እጆቹን ሲወረውር ፊቶቻቸውን መለስ፣ ዓይኖቻቸውን ሰበር ያደርጋሉ።ያኔ ነበር ታድያ እህቶቻችን አይነ ዓርነትና በወንዶች መመራት የተጀመረው።



አሁን ግን የከተማ እህቶቻችን ያ የድሮው ስልጣናቸው ለመመልስ በመታገል ላይ ያሉ ይመስላል። ድፍረታቸው ጉድ ያሰኛል … አይናውጣ ሁኗል። ገላቸውን አራቁተው መታየቱን እንደ ፋሽን ይቆጥሩታል። የነሱ ራቆትነት ታድያ የወንዶች አንገት እያስደፋ ይገኛል። ብዙ አይነ ዓፈራ ወንዶች እሚገቡበት ሲያጡ ይታያል፤ በተለይ ታክሲ ውስጥ። እንሱ በሚያስተዳድሮት ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ወንዶች ወየውላቸው። በተለይ፣ በተለይ ሽንት ቤትና ሻወር የጋራ ከሆነ።




ከላይ የሚታየው ፎቶ የተነሳው በአንድ የጋራ ሻወር ውስጥ ነው። ምናልባት ሰሙኑን ውሃና መብራት በተደጋጋሚ ይጠፋ ስለነበር ፓንታቸውን የሚያጥቡበት ውሃ አጥተው ይሆናል። ቢሆንም ግን ግፍ ነው፤ ጡር ነው እህቶች። ድሮ ወንዶች ነበሩ በጫማ ሽታና በሰውነት ንፅህና ጉድለት የሚታሙት አሁን ግን እንጃ። ሴቶች በሚገዙት ቦታ ሁሉ እንዲህ ይሆን?የአዲስ አበባ ጭዋ ልጆች ምን ትላላችሁ? እንደ እኔ በገጠር ተወልደው የደጉ እህቶቼ እንኳን በጣም እንደሚገረሙ አልጠራጠርም።







ትርፍ ሰዎች


                               



የአዲስ አበባ የትራንስፖርት እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት ይገኛል።በታክሶች መነሻና መድረሻ ቦታዎች ቆሞ የሚጠብቀው ህዝብ ብዛቱ ለጉድ ነው። እንደው በተራ አስከባሪዎች ምክንያት ጋብ አለ እንጂ ታክሲ ለመያዝ ይደረግ የነበረው ግፍያና ሩጫ ለህይወትና ለንበረት በጣም አስጊ ነበር። አብዛኛው ተጓዥ ብዙ ከጠበቀ በኋላ በምትመጣው ታክሲ ተሳፍሮ ካሰበበት ቦታ በጊዜ ለመድረስ ሲጋፋ ሞባይሉ በኪስ አቂዎች የተዘረፈው ብዙ ነው።

ታክሲዎች ትራፊክ ፖሊሶች በሚያዘወትሩበት አከባቢ ትርፍ አይጭኑም፤ ጭነው ከተገኙም የቀጣሉ።ስለሆነም ከብዙ ልፍያና ግፍያ የገባው ተሳፋሪ «ትርፍ ነሽ ወይም ነህ ውረድ/ጂ» ይባላል፤ የተለመደ ነው ።ትራፊከ ፖሊሶች በማይኖሩበት ቦታ ግን ሰው በሰው ላይ ይጫናል፤ ታክሲው በሰው ይታጨቃል።

የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ግን ትርፍ ቢጭኑም ባይጭኑም ስለማይቀጡ ችግር የለባቸውም።ገብቶ መቆም የቻለ ሁሉ ትርፍ አይባልም፤ ጉዞው ይቀጥላል።ከእግር እስከራሱ እየተሻሽ፣እየተፋተገ ትንፋሽ ለትንፋሽ እየተለዋወጠ።

ይህች ዓለምም በታክሲዎችና በአውቶብሶች ልንመስላት እንችላልን።አብዛኛው ጊዜ በሰው ይታጨቃሉ።አውቶብሶችና ሀይገሮች ቻይ ነገር ይመስሉኛል፤ እስከቻሉት ድረስ ብዙ ሰው ይጭናሉ።ታክሲዎች ግን ሲያሻቸው ይጭናሉ ከልተመቻቸውም ትርፍ ነህና ውረድ በማለት ያስወርዳሉ።

ዓለማችንም እንዲሁ ነች።ሲያሻት በሰዎች ትክሻ ታዝለን እንድንኖር ጭምር ትፈቅድልናለች።ሲያሻት ደሞ ቦታ እያለም ትርፍ ነህና ውረድ ትለናለች።ወያለው ከታክሲው አስገድዶ እንደሚያስወርደን ሁሉ ዓለምም ከጀርባዋ አሽቀንጥራ ትወረውረናለች።እኛ ገና ነን፣ ጊዜና ቦታ አለን ብለን ተንደርደረን ለመግባት ስንሞክር በድንገት «ትርፍ አልጭንምና ውረድ» እንባላለን።

እስኪ አስቡት፣ ስንት ሰዎች ናቸው «ትርፍ» ተብለው ከዚች ዓለም የተንሰናበቱት? ለመቁጥረ ይከብዳል። እንደው የቅርቡን እናንሳ ብንል በጣም የምንወዳቸው ብዙ የጥበብ ሰዎች አጥተናል። ዓለም ያንቀጠቀጡ፣በእንብርክክ ያስኬዱ፣ትርፍ ነህ ትረፍ ነሽ በማለት ከዚች ምድር በጉልበት ያሰናበቱ አንጋፋ የሃገር መሪዎችም ጊዜው ሲደር ትርፍ ተብለው ከሚስገበገቡለት ስልጣናቸውና በዙዎችን እንደ ጥሬ ፈጭተው እንደ በረት አቅልጠው ከገዙባት ሃገር ተሰናብተዋል። ወደው ሳይሆን ተገደው «ትርፍ» ተብለው።

«ትርፍ» መባል ብንሮ ደረጃ፣በዘር፣በሃይማኖት፣በስልጣን፣በመልክ፣በቁመት ወዘተ. አይወሰንም።ሁሉም ሰው በጊዜው ትርፍ ይሆናል።ለጊዜው ግን በሌሎች ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ያላቸውን ሁሉ እየመጠጠ በህይወት መርከብ ወድያ ወዲህ ይላል።ነገር ግን የመርከብዋ ጉዞ ሁሌም ሰላማዊ አይሆንም።«ለሁሉም ጊዜ አለው» ተብለዋልና በሰላም ስትቀዝፍ የኖረችው መርከብ በወጀብ ስትናወጥ ብዙዎችን «ትርፍ» በማለት ወደ ውቅያኖሱ ትወረውራለች።

የአሁኑ የፌስቡክ ወሬ ስለየቀድሞው የኢትዮጵያ ወታደራዊ አምባገነን ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም ሁነዋል።አንዴ ሞቱ ተቀበሩ ይላሉ፣ መልሰው ደግሞ «የወያኔ ወሬ ነው» አልሞቱም በማለት ነገር ያምታታሉ። ምንግስቱ የተለየ ሰው አይደም፤ የተለይ ታሪክ የለውም። ማመዛዘን የማይችል፣ እንደ እንስሳ በደመነፍስ የሚንቀሳቀስ ሬሳ ነበር። የፌስቡክ ወረኞች ጊዜዊ ወናፈም አይግደለውም ከሞትም አያድነውም።ሬሳ ነበር ሬሳ ይሆናል፤ በእርግጠኝነት።

የፕሮፖጋንዳ ወናፈ ከየትም በላይ በፌስ ቡክ ይልቃል።ግን ለውጥ አይኖረውም፤ «ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ» ብቻ።ለሃገራዊ ለውጥ የሚደረገው ትግል የሚያቀጭጭ፣ ለጊዜው በተጫኑ «ትረፍ» ሰዎች የሚነፋ፣ የጆሮ ታምቡር የሚቀድ ሻጋታ ወሬ ነው።የቆሻሻ ፖለቲከኞች የዜሮ ድምር ጨዋታ።ልክ «እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል» አለች አህያ እንደሚባለው።

እነዚህ ትርፍ ሰዎች ያልተባለ፣ያልታየና የሌለ ነገር አለ፤ በዓይኔ አየሁት፣በጆሮየ ሰማሁት በማለት ይጮሃሉ። ጭሆቱን መልሰው በማስተጋባትም ውሸቱን እውነት ለማስመሰል ስራየ ብለው ይተጋሉ። ለትርፍ ሰዎች ትርፍ ነገር ማውራት የተለመደ ነውና። 



Tuesday, April 23, 2013

Blackout In Addis Ababa


Yesterday(22/04/2013), the power gone off in a critical work time, a deem-light replaced the bright daylight. The blackout continued through the afternoon, actually accompanied by an uproar of generators as they turn off and on time and again, till they ultimately silenced for unknown reason. All office workers in the whole block could do nothing...went here and there aimlessly. And some would simply pop up their heads out of the windows to look out what the hell was going on.

Most staff members including high ranking officials left. Offices were almost empty. This reminded me a common joke while I was a university student.Social science students would call Computer Science " A Department that turns off whenever power goes off." It might have been so during collage life, but not now...in employed life.Yesterday was a proof. When the power went off all offices became empty.

Just after work, I went to AAU to attend a night class session. Fortunately, there was light till the session was over, but it went off at the end of the class. Then I had to go home through the dark street. It seemed a kind of jungle I saw on AVATOR movie. I bought a couple of candles to light my home till the power outage comes to life. Alas! I spent the remaining evening lighting a candle without any special purpose.

Eventually, I slept without blowing out the candle. Around mid night, I woke up soaked in sweat. Good God, my home was brighter than ever. The bulb was shining straight over me, and the candle was gleaming. I thought for a moment how lucky I was;otherwise, the candle could ignite a fire and I would be brunt to ash.

I questioned myself where the hydro powers being generated from Tekeze, Gibe II, Tana Beles, Ashegoda and others has gone. It is said that my country Ethiopia is exporting electric power to Djibouti and Sudan...100MW each. Why is then, Addis Ababa is suffering from recurrent blackouts? May be, our self appointed lords want to save more power to export so that they could amass the Dollars coming over. These greedy monkeys could do anything to fill their hallowed belly, their oceanic pockets.

I pondered like so for sometime. And finally I turned off the light and slept again.

Monday, April 22, 2013

ዝግመተ ለውጥ(አለማዮህ ገላጋይ)



«እንጋባ» ሲል ጠየቃት፣ አሳምነው።
አልተቀበለችውም አስማሩ። «ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል» አለችው።
ተስማሙ።
ቤቷ እየመጣ ይጠይቃታል።
ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፣ካላት ታቀርባለች - ይበላሉ።
አውግተው ይለያያሉ።
የትዳር ነገር ዳግም አለተነሳም።                       

አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ፀሐይ መጣ።
እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውለቆ አስቀመጠ።ስለሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ።
አስማሩ አሳምነው ረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት።
ዳግም ሲመጣ ደርቦ ደራርቦ ነበርና የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም።
ጃኬቱን አውልቆ ሄደ።
አስማሩ እሱንም አጥባ አኖረችው።
ሱሪውን ደርቦ መጣ «ወበቀኝ» አወለቀው።
አስማሩ አጥባ አኖረችው፣
ካፖርቱን ጥሎ ሄደ፣
አጥባ አኖረችው።
አንድ ቀን በጠራራ ፀሐይ ብርድ ልብሱን ለብሶ መጣ፣
አስማሩ «ምነው?» አለቸው።
«በጠራራ ፀሐይ ብረድ ሆዴ ገባ» አላት።
«ምች ይሆናል፣ አለችው። የምች መድኃኒት ብታሽለት ተሻለው።
ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም ጥሎት ሄደ።
አስማሩ አጥባ አኖረችው።
ትንሽ ቆይቶ፣ ፈራሹን ተሸክሞ መጣ።
«ምነው?» አለችው።
«ላሳድሰው መሄዴ ነው።አይቼሽ ልለፍ ብዬ ነው» አላት።
አመነችው።
ጨዋታው ደራ፣ ፍራሹን እረስቶት ሄዶ ኖሮ እኩለ ሌሊት ቢመጣ አስማሉ ቦታ ስላጣች ፍራሹን ላይ ደርባው ደረሰ። ያኔ «ተነሽ» ከማለት «ጠጋ በይ» ማለት ቀልሎ ተገኘ።



                       ማስታወሻ፡ ይህ ፅሑፍ ኩርቢት ከተባለ የአለማዮህ ገላጋይ መፅሓፍ የተወሰደ ነው።

Saturday, April 20, 2013

የቢሆንስ ዜና



                            

የፌስቡክና የክፍል ጓደኛየ ሄኖክ ፍቃዱ፣ የሚከተለው ዜና እውን እንደሆነ በማሰብ እንዲፅፍ በአስተማሪው ታዝዞ ነበር።የቢሆን ዜናው  «የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብዱን ለማሰልጠን ተስማሙ» ይላል።የስነ ፅሑፍ ችሎታው በጣም የሚያስደንቅ ነው።በተለይ የአነባብ ክህሎቱና መረዋ ድምፁ የሃገራችን ጋዜጠኞችን ያስንቃል።የዕለቱ እስተማሪም ከሌሎች ተማሪዎችን በተለየ ከተቀመጠበት ተነስቶ በማጨብጨብ አድናቆቱን ገልፆለታል።እስኪ እኔ ደሞ ለውድ አንባቢዎቼ «እንደ ወረደ» ላቅርብላችሁና የተሰማችሁን ሁሉ በሉ ወይም አድርጉ።

                    የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብዱን ለማሰልጠን ተስማሙ

ዕለቱ አርብ ነው፣ ቀኑ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ሚያዝያ 11፣ 2013 ዓ.ም፣ ስፔን ዴ- ማድሪድ አዳራሽ። የዓለም የስፖርት ጋዜጠኞች የተናጋሪውንና የአውሮፓ ሻምፔንስ ሊግ፣የእንግሊዝ ፕሪመር ሊግና የስፔን ላሊ ሻምፔኑን የ38 አመቱን አሰልጣኝ ይጠብቃሉዘ። ሁሌም ከአንደበቱ አዲስ ነገር የሚፈልጉት ጋዜጠኞች መድርኩን በፈገግታ ያጅቡለታል፣ አሰልጣኝ ጆሴ ደሳንቶስ ሞሪንሆ።


በዕለቱ ከበርካታ ጋዜጠኞች ጥያቄዎችን ከተቀበለ በኋላ ስዓቱን ተመለከተ።ከሰጣቸው ደቂቃ አንደም ማሳለፍ የማይፈልገው አሰልጣኝ የመጨረሻ እድሉን ለአንድ ጀርመናዊ ጋዜጠኛ ሰጠ።ጥያቄውም እንዲህ ይል ነበር፣«ከ33 ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አፍሪካ ወንጫ ያለፈችን አገር ለማሰልጠን ተስማምቷል ይባላል፣ እውነት ነው?» አለ።


በስፔን ዴ-ማድሪድ አደረሽ የነበሩ ጋዜጠኞች በሙሉ ማለት ይቻላል የስላቅ ድምፅ ያሰሙ ጀመር። የአንድ ወንድና የእንደ ሴት ልጆች አባት የሆነውን፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ከአራት የተለያዩ ክለበቦች ጋር ከአስር ዎንጫዎችን በላይ የሰበሰበ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ግን መልሱን ከመመለሱ በፊት ፈገግ አለ።ወደ ማይኩ ጠጋ ሲልም የጥያቄውን መልስ የሚጠብቁ ጋዜኞች በአደራሹ ድምፃቸውን አጠፋው።


«ስሟ ኢትዮጵያ ይባላል፣የብዙ አትሌቶች ማፍለቅያ ናት፣ብዙ ታሪክም አላት» ሲል ነበር ማብራረያውን የጀመረው።አንድ ኢትዮጵያዊ ስለሃገሩ ከሚሰጠው መግለጫ የማይተናነስ በሚመሰል መልስ ንግግር አደረገ።« እግር ኳስ ወዳዱን ህዝቧን በቴለቪዥን መስኮት ብቻ ሌላ ቡድን እየደገፉ የዓለም ዋንጫን እንዲመለከቱ ማን ገደባቸው?» ይላል ተጠያቂው አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ሲጠይቅ።


ከእንግሊዝ እስከ ስፔን፣ ከጣልያን እስከ ጀርመን፣ በተለያዩ ታላለቅ ክለቦች ሲታደን የነበረው ፣በታላላቅ የእር ኳስ ሀያላን አገሮች «ካዝናችንን ሰብረን እናስፈርምህ» ጥያቄ የጎረፈለት የአውሮፓ ታላላቅ ዋንጫዎች በሙሉ በስሙ ያሉት፣ ቆፍጣናውና ልዩ ሰው ነኝ ባዩ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ፣ አሁንም ልዩ ሰው መሆኑን ለማሳየት የምስራቅ አፍሪካዊቷን አገር ኢትዮጵያን መርጧል። በመጋቢት 17 ቀን፣ 2013 ዓ. ም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጋር ብሄራዊ ቡድኑን ለሶስት ዓመታት ለማሰልጠን ሲስማማ በሪያል ማድሪድ በአመት ከሚያገኘው ሶስት ሚልዬን ዶላር በአራት እጥፍ ተጨማሪ ክፍያ ይቀበላል። ለስራውንም በኢስ አበባ ምድር ነሀሴ 22 ኢትዮጵያ ከሶማልያ ጋር በምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ በይፋ ይጀምራል።

ጆሴ ሞሪንሆ እውነትም «ልዩ ነው» ባይነኝ፣ በጣም አደንቀዋሎሁ። እንደውም የእግር ኳስ ችሎታም ሆነ ፍቅር ባይኖረኝም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያሎሁ በርሱ ምክንያት ለተወሱኑ ዓመታት የቼልሲ ጨዋታዎችን መከታተል ጀምሬ ነበር።ቅሉ ቼልስን ለቆ ወደ ጣልያን በማምራት ኢንተር ሚላንን ማሰልጠን ሲጀምር የእግር ኳስ ስሜቴ «እንኳን ዘንቦብሽ…» ነበረና ጭራሹን አቆምኩት እንጂ።ከላይ ያነበባችሁት የሄኖክ የቢሆን ዜና እውን ቢሆን ግን የአዲስ አበባ ስቴድዮም ቋሚ ተሰላፊ ከመሆን ወደ ኋላ አልልም ነበር።


Monday, April 15, 2013

ይድረስ ለዲያስፖራው ወዳጄ ባለህበት





የሀገሬ የወንዜ ልጅ፤ ሰሞኑን ከወትሮው በተለየ መልኩ አብዝተህ “ጤንነቴን” የጠየቅከኝ ያለ ምክንያት እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ ያቀረብክልኝ ሠላምታ ሥጋት አለበት፡፡ መቼመ ሆነ የትም፣ ምንም ይሁን ምን፣ ኑሮ ቢሳካም ባይሳካልህም፣ ቢደላህም ባይደላህም ስለወገን እና ስለሃገርህ ማሰብህ ተገቢ ነው፡፡ ደግሞም አለማሰብም አይቻልህም፡፡ የማያስበው የሞተ ብቻ ነውና፡፡ 

ወዳጄ ልቤ፡- በአካል ከተለያየን ከብዙ ዓመታት በኋላ “ገፅ ለገፅ” ለመነጋገር የበቃነው በቅርቡ ነው፡፡ በ“ፌስ ቡክ” ከተጋመድን አንድ ዓመት እንኳ የሞላን አይመስለኝም፡፡ ከዚያ ጊዜ ወዲህ፤ በተለያየ ጊዜ፣ በተለያየ ሁኔታ፣ በተለያየ ምክንያት ሀገራቸውን ጥለው ለሥደት የተዳረጉ አንተን መሰል እህትና ወንድሞቼን ተጎዳኝቻለሁ፡፡ ከግል ጉዳይ አንስቶ እስከማህበራዊ፣ ከዚያም አልፎ ሃገራዊ እና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮችን ስሰልቅም ከርሜያለሁ፡፡ በተለይ ከአንተ ጋር ያላወጋነው፣ ያልከረተፍነው፣ ያልሰነቅለው ጉዳይ የለም፡፡ 

2005 ዓም ከገባ ወዲህ ግን ከአንተ በኩል የሚሰደድልኝ መልዕክት በመጠይቅ ብቻ የታጀለ ሆነ፡፡ የኑሮ ውድነቱ፣ ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት መታጣቱ፣ መንግስት በዜጎቹ ላይ መክፋቱ፣ ዲሞክራሲ የሚባል ከነአካቴው መጥፋቱ፣ ወዘተ ስለምን ነው ብለህ በጥያቄ ወጠርከኝ፡፡ እኔም እንዳንተው ቢጨንቅኝ፣ ይኸው ሃሳብ እያነጎለኝ አለሁ፡- መኖር ከተባለ፡፡

የሀገሬ ልጅ፡- እናልህ!... ሀሳብ እያነጎለኝ ለጥቂት ዘመናት ታሪክን የኋሊት እያስቃኘ አነፈረኝ፡፡ የሀገሬ ፖለቲካ አበሸቀኝ፡፡ ብሽቅ!! የምር ነው የምልህ የኛ ሀገር ፖለቲካ ብሽቅ ነው፡፡ የብሽቅ ብሽቅ!! ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ “ባህላችን” ነው፡፡እንደው በደፈናው የዛሬው የፖለቲካ ባህላችን “የእኛው ውጤት ነው” ወደሚል ድምዳሜ ደርሻለሁ፡፡ “የአንድ ሀገር እና ሕዝብ የሚሆነውና የሚያገኘው፣ መሆን ያለበትንና ማግኘት የፈለገውን ያህል ነው” ያለው ማን ነበር!? ረሳሁት እንጂ ይህንን ያለው የሆነ ሰው ነው፡- ፈነንጅ ነው መሰለኝ፡፡ ያው ፈረንጅ ያለው ሁሉ ትክክል ነው ብለን ስለምናምን እንጂ አስቀድመን ያልነው እኛ ኢትዮጵያኖች ሳንሆን አንቀርም፡፡
(ሣቅ በሣቅ) …
እየቀለድኩ እንዳይመስለህ!! ታሪካችን መመርመር አለበት፤ ባህላችን መመርመር አለበት፡፡ “የትኛውም ሕዝብ የሚያገኘው ወይም የሚኖረው የሚፈልገውን አይነት መሪ እና ኑሮ ነው” የተባለው ምንም ህፀፅ የለው፡፡


ወዳጄ ልቤ፡- ይኼንን አባባል በምሳሌ ባስረዳህ ነው የሚሻለው፡፡ ለወጋችን ያህል የእኔና የአንተን ዕድሜ አስላውማ!!? 40 ዓመት ደፈንን፡፡ ዕድሜን ለመቁጠር እንጂ ለመኖር አልታደልንም መቼም፡፡ በእነዚህ ዓመታት ሁለት መንግስታት አይተናል፡፡ ኢህአዴግን እና ደርግን፡፡ የአጼውም መንግስት ብዙም አልራቀንም፡፡ ከቀደምት የሀገራችን መንግስታት በተሻለ የአፄውን ዘመን ታሪክ እናውቀዋለን፡፡ ሶስቱም መንግስታት አንድ አይነት ናቸው፡፡ አፄ ኃይለስላሴ አምባገነን ነበሩ፡፡ ደርግ አምባገነን ነበረ፡፡ ኢህአዴግ አምባገነን ነው፡፡ የሚለያቸው ዘመን እና አምባገነንነታቸው የተገለፀበት (የሚገለፅበት) ሁኔታ ነው፡፡ የሚለያቸው የሚከተሉት የአምባነንነት ስልት ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ሶስቱም የእኛው ውጤቶች ናቸው፡፡ የባህላችን ስሪቶች ናቸው፡፡ 
 ምን ለማለት ፈልጌ መሰለህ?! አሁን ላይ ሆኜ ያለፍነውን እና ያለንበትን ዘመን ሁኔታ በጥሞና ሳብሰለስለው፤ የመናገርን ወይም ሀሳብን በነፃነት መብታችንን የተነፈግነው በሕፃንነት ዘመናችን ነው ብዬ ወደማመን ደርሻለሁ፡፡ ገና በጨቅላነታችን ነው የመናገር ነፃነታችንን የተነፈግነውና ያጣነው፡፡ በአስተዳደግ “ባሕላችንን” ክፋት የተነሳ፡፡ 

ወዳጄ ልቤ፡- እዚችጋ በትውስታ ወደህፃንነት ዘመን ልመልስህ፡፡ ያኔ ጨቅላ ሳለን፣ ሕፃን ሳለን፣ እንቦቀቅላ ሳለን፣ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ሳለን፣ ክፉና ደጉን ለይተን በማናውቅበት ጮርቃነታችን ዘመን፣ እኔም ሆንን አንተ እየተገረፍን፣ እየተቀጣን ነው ያደግነው፡፡ አንዳንዴ አጥፍተን፣ አንዳንዴ ደግሞ ሳናጠፋ ነበር የምንቀጣው፡፡ ታዲያ ይኼ ከጉዳያችን ጋር ምን ያገናኘዋል? ትለኝ ይሆናል፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ያርቁ ዘንድ ግድ ነው ትለኝ ይሆናል፡፡ በእርግጥም ወላጆች ልጆቻቸውን ከስህተታቸው ሊያርሙ ይገባል፡፡ ሊቀጡም ሊቆጣል ይገባል፡፡ ነገር ግን ከቀጡህ እና ከተቆጡህ በኋላስ?!....ታለቅሳለህ፡፡ ስታልቅስ ይብስባቸዋል፡፡ “አፍህን ያዝ!!” እያሉ ግርፊያቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እንዳታለቅስ እንኳ ይከለክሉሃል፡፡ ይኼ አታልቅስ ማለትታቸው እኮ በራሱ ያስለቅሳል፡፡

ትዝ ይለሃል ያኔ ሀ፣ሁ ስንማር? ፊደል ስንስት ስንሳሳት? መምሬ አያሌው አንተን እንዴት እንደበጠበጠቡህ? ሰውነትህ እስኪጉረበረብ ዠልጠውህ፣ ዠልጠውህ ሲያበቁ “ፀጥ በል፣ ትንፍሽ እንዳትል፣ ድምጥህን (“ጥ” እንጂ “ፅ” የሚል ድምፀት አይችሉም ነበር) እንዳልሰማ” እያሉ አሳርህን ያስቆጠሩህ!?፡፡ ከዚያች ቀን በኋላ አይደል እሳቸው ጋ ፊደል መቁጠር ያቆምከው!? እስከአፍላነት እድሜ ድረስ እንዴት ትጠላቸው እንደነበር ታወሰህ? ይኸውልህ እንግዲህ ወላጆቻችንም፣ የጨቅላነት መምህሮቻችን በጨቅላነታችን የቀረፁን በዚህ አይነት ባህል ነው፡፡ የእኛ ሀገር መሪዎችም በዚህ ክፉ ባህል ውስጥ ነው ያለፉት፡፡

የደርጉን ኮ/ል መንግስቱን ውሰድ፡፡ የለየላቸው አምባገነን ነበሩ፡፡ የሚመሩት ሥርዓት የለየለት አፋኝ ነበረ፡፡ ጨካኝ፡፡ እንኳንስ ማልቀስ፣ ትንፍሽ ማለት አይቻልም ነበረ፡፡ እሳቸውን የተኩት የኢህአዲጉ አቶ መለስም አምባገነን ነበሩ፡፡ (ነፍስ ይማር) እነዚህ መሪዎች በሕፃንነታቸው አጥፍተውም ሆነ ሳያጠፉ ተገርፈው (ተቀጥተው) ሲያለቅሱ፤ “አታልቅሱ፤ አፋችሁን ያዙ” በሚል ባህል ውስጥ ያደጉ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው የሀገር መሪ ሲሆኑ፣ ብሶታችንን መናገር እንኳ የነፈጉን፡፡ ማልቀስ እንኳ የከለከሉን፡፡
እነዚህ መሪዎች በስልጣን ዘመናቸው የሚመሩትን ሕዝብ “አፍህን ያዝ አልልም” አለማለት አይችሉም፡፡ ምክንያቱም በሥልጣን መንበራቸው ዙሪያ ያሰባሰባቸው ሹሞቻቸው “አፍህን ያዝ” ተብለው የታነፁ ናቸው፡፡ ቁንጮዎቹ መሪዎች ሕዝቡ “አፍህን ያዝ” ማለት ባይፈልጉ እንኳ፣ “አፉን ይያዝ እንጂ” ብለው የሚመክሩ ናቸው፡፡ ቁንጮው መሪ፣ ካለ ሹሞቹ ምንም ኃይል ስለማይኖረው “አፉን ይያዝ” ከማለት ውጪ ምንም ምርጫ የለው፡፡ ሕዝቡም አፉን ከመያዝ በቀር ምንም ነገር ለማድረግ የማይደፍረው፣ አሳዳጊዎቹ ወይም አሳዳሪዎቹ ያነፁት በዚያው መጠን ስለሆነ ነው፡፡
እንደው በአጭሩ የመናገር ነፃነታችንን የተነፈግነው “በባህላችን ክፋት” የተነሳ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ የደረስኩት ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ ነው መሪዎቻችንን የፈጠርነው እኛው ነን የምልህ፡፡ (ቤተሰብ የሕብረተሰብ መሠረት ነው የሚለውን ሀቅ እንዳትዘነጋብኝ)… የሆነ ሆኖ በሀገራችን ያየነው፣ የኖርነው፣ የምንኖረው ዕውነት ይኸው ነው፡- “አታልቅስ አፍህን ያዝ” እየተባልን፡፡ ይኸው እኔም አታልቅስ የሚሉት ፈሊጥ እያስለቀሰኝ እንዳለሁ አለሁ፡፡


የሀገሬ ልጅ፡- በል እንግዲህ ይህን ያህል ካልኩህ ይበቃል፡፡ የቀረውን ሃሳቤን ሌላ ጊዜ አወጋሀለሁ፡፡ እስከዚያው ባለህበት ቦታ ሁሉ ሠላምና ጤና ካንተ ጋር ይሆን ዘንድ እመኛለሁ፡፡ በተረፈ ካንተው ጋር ላሉ ለሃገሬን ልጆች ሁሉ (ለሴቱም ለወንዱም፣ ለታናናሾችም ለታላላቆችም፣ ለሊቆቹም ለደቂቆቹም) የከበረ ሠላምታ አድርስልኝ፡፡ “እኔ እንዳለሁ አለሁ፤ እናንተ እንዴት ናችሁ” በልልኝ፡፡


ተፃፈ፡- በ2005 ዓ.ም፤
ከዓመቱም በስምንተኛው ወር (ሚያዝያ)
ከወሩም በመጀመሪያው ቀን፡፡


ወዳጅህ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን

አዲስ አበባ፡፡ 

አባትህ ማን ነው?





ድሮ ህፃን እያሎሁ ነበር እቺ ጥያቄ ጨቅላው አእምሮየን ማስጨነቅ የጀመረችው።ከዕለታት በአንዱ ቀን እኔ በለቅሶ ቤተሶቦቼ በደማቅ ዕልልታ በማጀብ ወደዚች ዓለም መምጣቴን አበሰርን።ለዕድሜ እረኝነት እንደደረከስኩኝ የሆነ ነገር አያቴን ማስጨነቅ ጀመረ።ከእኩዮቼን ተለይቼ የቤት እስረኛ ሆኜ መኖር እንደማልችል ብታምንም እውነታውን እንዴት አፍረጥርጣ ትንገረኝ? እንዳትነገረኝ ንፁህ አእሞሮየን ማቆሸሹን አልዋጥልሽ አላት።ምስጢሩን ደብቃ ዝም እንዳትለኝ ደሞ እንድያ ባለማድረጓ ሊደርስ የሚችለው አደጋ እስፈራት።ሁለት አስቀያሜ አማራጮች ግን ደሞ የግድ አንዱን መምረጥ ነበረባት።

ለብዙ ቀናት ብዙ ካሰበች በኋላ አንዱን ልትነግረኝ ወሰነች።እናም እረኝተነት ውዬ ቤት እንደገባሁ ሁሌም እንደምታደርገው መክሰሴን ሰጠችኝና ትኩር ብላ ዓይን ዓይኔን ታይን ጀመር።መክሰሴን በልቼ እንደጨረስኩ ከእኩዮቼ ጋር ለመጫወት ከቤት ልወጣ ስል ጠጋ ብላ ፆግሬን እያሻሸች አውነቱን ነገረችን።እንዴት? ለምን? እኔ ምን አጠፋሁ? በጥያቄዎች ወቅያኖስ ሰምጬ ፍርሃት አይሉት ጭንቀት  እንደ ዥዋዥዌ ወድያ ወዲህ ያላጋኝ ገባ።አያቴ ለጥያቄዎቼ መልስ ሳይሆን ሌላ ተጨማሪ ጥያቄ ነበር የሰጠችኝ።
«ይስፋው ወደይ፣ ድሕር ደጊም አቦኻ መን እዩ ተቢሎምኻ ቐሺ ብርሃኑ ኢኻ ልትብል።ትምሕል ተለኻለ ስጋ ቓሺ ኢኻ ልትብል።ወዲ ገዳሙ እየ ተቢልኻ ናቦኻ ፀለእቲ ክቐትሉኻ እዮም። ድሕሪ ደጊም ገዳሙ አቦኻ የኾነይ፤ተጠንቀቕ» አለቺኝ ።ትርጉሙም እንደሚከተለው ይመስላል።«ይስፋው ልጄ፣ ከአሁን በኋላ አባትህ ማን ነው ብለው ቢጠይቁህ ቄስ ብርሃኑ ነው መናገር ያለብህ።ስትምልም ቄስ ብርሃኑ ይሙት ማለት ይጠበቅብሃል። የገዳሙ ልጅ ነኝ ካልክ የሱ ጠላቶች ይገድሉሃል።ከአሁን ወድያ አባትህ አይደለም፣ ተጠንቀቅ»

የተባልኩት ሁሉ ተግባራዊ ባደርግም ከጭንቀትና ፍርሐት የሚገላግለኝ ግን አላገኘሁም።የምወዳት አያቴ ምክር አላባከንኩትም።በእውነተኛው አባቴ ስም የሚጠራኝ ሁሉ በድንጋይ ለመፈንከት ወደኋላ አልለም፤ ፆታ፣ዕድሜ፣ የሰውነት አቋም አያስጨንቀኝም።የሚያሽንፈኝ መሆኑን ካመንኩ በማይደርስብኝ ቦታ ሁኜ በወንጭፍ! ያተግባሬ ከእርግማንና ጥላቻ ውጪ ምንም አልፈየደልኝም።

ያባቴ ጠላቶች በተግባር ባይፈፅሙትም እኔን ለመግደል እንደ አሞራ እያዣበቡብኝ መሆኑን ባማስነገር ሽብር ይለቁብኝ ጀመር።እኔ ባላውቃቸውም እነሱ ግን በዋልኩበት ባመሽሁበት ሁሉ እየተከታተሉኝ መሆኑን በዘመዶቼ አማካኝነት ያሳውቁኛል።ቀን ባይመጡብኝም ለሊት በሕልሜ ያሳድዱኛል።አያቴ በነገረችን ተረት ተረቶች ያሉ ጭራቆች ረዣዥምና ስለታም ገጀራዎች፣ትላልቅ መፍለጫዎች፣ ጎራዴ፣ቢላዋ፣ ማጭድ… አስፈሪ የሚባል ስለታም ነገር ሁሉ በእጃቸው የያዙ ሰዎች ያባርሩኛል።
በመጨረሻ ብዙ ሩጬ፣ሩጬ፣ ሩጬ በማላውቀው አካባቢ ስደርስ እገሮቼን ማንሳት ያቅተኛል። ደክሞኝ ተዝለፍለፌ ስወድቅ አንዱ በያዘው ትልቅ መፍለጫ ግንባሬን ሲፈነክተኝ «ኡ…ዪ!» በማለት የተኛሁበት ቤት በጭሆት ሳቀልጠውና ከእንቅልፌ ብንን ብዬ ስነቃ አንድ ይሆናል።የገጠር ንሮ ለሊት ለሊት ጭለማ ስለሆን ለተወሰነ ጊዜ መረጋጋት ያቅተኛል።ያኔ አያቴ በጭንቀት ልታብድ ትደርሳለች።በየፀበሉ ትወስደኛለች፤የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፀበል፣የአቡነ ተክለሃይማኖት ፀበል፣የሚካኤል፣የገብሪኤል፣ የጊዮርጊስ… ብዙ ተጠመቅኩ።ፀበሉ ይሁን እያደግኩ ስለመጣሁ እንጃ ቅዠቱ እየለቀቀኝ መጣ።

ነገር ግን ጤናየ መታወክ ጀመረ።እምባላውም ሆነ እምጠጣው አይስማማኝም።አንዴ ቀርጠት፣በሌላ ጊዜ ፍልጠት፣ ራስምታት፣ተውካት፣ውጋት… የበሽታዎች ዓይነት መረማመጃ ሆንኩኝ። ሞት መዳከሜን ሲያውቅ እኔን ችላ ብሎ ሌሎችን እያሳደደ አፈር ያስግጣቸዋል።ብዙ ሰዎች ገደለ፤ አያቴ፣አክስቴ፣አጎቴ፣ታናሽ እህቴ… አረ ስንቶች! ከነዚህ ሁሉ በላይ የአያቴ ሞት ነበር በዚች ዓለም ተስፋ እንድቆርጥና ራሴን ለማጥፋት እንዳስብ ያደረገኝ። አላደረኩትም። ይህን ሁኔታየን የታዘበች እናቴ ከባሏ(የእንጀራ አባቴ) መፋጠጥ ጀመረች።ጧት ማታ ጭቅጭቅ ንትርክ ሆነ…በኔ ምክንያት።« እኔ በህይወት እያሎሁ ልጄ በጣም የሚወደው ትምህርቱን አቋርጦ ማይት አልፈልግም» በማለት የማይዛነፍ አቋሟን አሳወቀችው፤ እቅጩን ነገረችው።

ያኔ የስምንተኛ ብሔራዊ ፈተና ወስጀ ወደ ዘጠኛ አልፌሎሁ። ችግሩ ታድያ 35 ኪሎ ሜትሮችን አቋርጬ ሳልጓዝ መማር አልችልም ነበር።ስንቅ የሚልክልኝና የቤት ክራይ የሚከፍልልኝ ያስፈልገኛል።ጭንቅ ሆነ፤ እናቴ ከባሏ ልትፋታ አፋፍ ላይ ደረሰች። ይህን ስረዳ አንቺ ተፋተሽ የስደስት ሰዎች ህይወት ከሚመሰቃቀል እኔ ትምህርቱን አቁማሉሁ፤ እትቸገሪ አልኳት።በንዲህ ዓይነት አስጨናቂ ሁኔታ እያለን ነበር የትግራይ ማሕበር ልማት መቐለ በሚገኘው ቓላሚኖ የሚባል አዳሪ ትምህርት ቤት ልታስተምረኝ መሆኑን ያሳወቀቺኝ።ያ ዕድል በህይወቴ በጣም ወሳኝ ምዕራፍ ነበር።አዛ በኋላ ከመቃብር በላይ ትምህርት ማቋረጥ የማይታሰብ ሆነ።

ነገር ግን የጤናየ ጉዳይ ከመሻሻል ይልቅ አሳሳቢ እየሆነ መጣ።ወደ ክልኒክ መመላለስ አበዛሁ፣ ብዙ የመድሃኒት እንክብሎች እንደ ጉድ ዋጥኩኝ።የሽሮፕ ዓይነቶች ጠጣሁኝ።በመጨረሻ የበላሁት ሁሉ እንደ እሳት ሆዴን ያቃጥለኝ ጀመር።የመረመሩኝ ሐኪሞች ጨጓራ ነው አሉኝ።በቃ፣ ወጥ የነካው ምግም መብላት ጭራሹን አቆምኩ።ምግቤ ዳቦ ብቻ ሆኑ።በጣም ከሳሁ፤ ግልበት አጣሁ።እንዳልበላ ያመኛል፤ዝም እንዳልል ይርበኛል… ሌላ የህይወት ፈተና።

በዚህ ግዚ ነበር «አባትህ ማን ነው?» የሚለው ህፃን እያሎሁ የተጠየኩት ጥያቄ መልሼ ራሴን መጠየቅ የጀመርኩት።ቀኑን ባላስታውሰውም በ1990 ዎቹ መጨረሻ የፃፍኳት ትንሽየ መጣጥር ይህችትና።
ውድ አንባቢሆይ ፣ የልደት ቀንህን በትክክል ታወቀዋለህ? መልስህ አዎ ነው? እርግጠኛ ነህ? እንድያማ ከሆነ ስትወለድ ታውቅ ነበር ማለት ነዋ።እንድም «ጂኔስ» ነህ አልያም ዕድለኛ። ታድለህ፣ በየዓመቱ የልደት ቀንህን ታከብራለህ ማለት እኮ ነው።እኔ ግን እንኳንስ ላከብረው ጭራሹንም ትዝ አይለኝም።

ዓመተ ምህረቱን ባታውቀውም ዕለተ ቀዳሜ፣ ጥር 23 ቀን እንደ ተወለድኩኝ እናቴ ነግራኛለች።የተወለድኩበት ዓመተ ምህረት ባማወቅዋ ቅር አይለኝም።ምክንያቱም እናቴ እንደኔ ተምራ ማንበብና መፃፍ የምትችልበት ዕድል አላገኘችም። ብያንስ በኩር ልጇን ለመገላገል ያማጠችበትን ቀን አልረሳችም።አባቴ መሆኑን አስራ ምናምን ዓመት ሲሞላኝ ሰዎች ያስተዋወቁኝ ሰውዬ ቀኑም ሆነ ዓመተ ምህረቱን አያውቀውም።ግንኮ ፊደል የቆጠረ ሊቅ ነው እየተባለ የሚወራለት ከባላባቶች የሚወለድ ቀጭን ጌታ ነው።የቀኛዝማች ልጅ ስለኔ ምንም ነገር አያውቅም።

አበራሽ የምትባል ታናሽ እህት ነበረችኝ።ነገር ግን የዚህ ዓለም ፈተና ማለፍ ስላልቻለች በትክክል መናገር እንኳን ሳትችል ነበር ዳግም ላትነሳ ያንቀላፋችው።በጣም ውብ ነበርች።እግዚሔር ቀናተኛ ነው ይባል የለ? ውበቷ አማልሎት እንደ እምቡጥ ፅጌ ረዳ ሙሉ በሙሉ ሳታብብ ቀጥፏት ይሆናል። እኔን ግን አይወደኝም፤ እንዲወስደኝ ብዙ ጊዜ አባብየው አሻፈረኝ ብሎኛል።

እግዚሔር ሁሉም አዋቂ፣ሁሉም ቻይ፣ ጊዜና ቦታ እንደማይወስነው ይነገራል።ደሞ ቀናተኛና በቀለኛ ነውም ይበላል።ታድያ ከኔው በምን ይሻላል? ያለጥፋቴ፣ ያለሐጥያቴ ሲያሳድዱኝ ከነበሩ ሰዎችስ በምን ይለያል? እኔስ ቅናት፣ንዴትና ቂም አይደሉም ቆሽቴን የሚያቃጥሉት? አባቴ ባጠፋው ጥፋት እኔን ለመግደል ሲያሴሩ የኖሩት በቀለኞች ስለሆኑ አይደለም?

 ቀናተኛ፣ምቀኛ፣ቁጡ፣ርህሩህ ወዘተ እያሉ የሚሽቆጠቆጡለት አምላክ የኔ አምላክ ሊሆን አይችልም።ምክንያቱም ከልክ በላይ ስሜታዊና ግልፍተኛ ነገር ነው።በስሜት እንጂ በምክንያት አያምንም።ድስ ላሰኘው፣ «በኢጎው» ለተጫወተበት የሾማል፣ ባለሃብትና ጥበበኛ ያደርጋል…እስራኤን ያወርሳል፤ከዛም ወደ ገነት። ላስቀየመው ግን ያሳድዳል፣ያሰቃያል፣ባርያ ያደርጋል።ይበቀላል፤ ወደ ግሃንመ እሳት በመወርወር።በቀሉ እስከ ሰባት ትልዶች ያቀጥላል።

ስማ አንተ፣ ከዛሬ ጀምሮ አላመልክህም፤ ከፈለግክ አሁንኑ ፈንግለኝ።ችሎታህ ይህ ነውና።ዘላለማዊ ህይወት ትሰጣለህ ሲባል ብሰማም እህቴን ዓይኖቿን ሳትገልጥ፣አፍዋን ሳትከፍት ነበር የቀጨሀት።እንኳንስ ዘላለማዊነት የአንድ ሰው ዕድሜ ለመስጠትም በፍጥረታት ደም የተጨማለቁ እጆችህ አልተፈቱም።

የኔ አምላክ ፍፁም ነው።ቁጣ፣ቅናት፣ምቀኝንት ወዘተ የሚባሉ የደካሞች ባህርያት አይገልፁትም።ደግሞ«አባትና እናትህን እክብር» ትለኛለህ፤ ከአስርቱ ትእዘዛትህ በአራተኛው።ቆይ አባቴ የት አውቀዋሎሁና ነው እማከብረው?እናቴስ? አሳዳጊዎችህ ለማለት ፈልገህ ከሆነ ንገረኝ።አለዚያ ወልደው ለአሳዳጊዎች የሚያስረክቡ በጣም ብዙ መሆናቸውን ታውቅ የለ?ሰዎች ይሀውና አባትህ ይህ ነው ስላሉኝ ብቻ አሜን ብዬ መቀበል አለብኝ? በምን እርግጠኛ እሆናለሁ?

ወይጉድ! ደሞ «ዲኤንኤ» ምርመራ ምናም ልትለኝ ይሆናል።ታድያ የመመርመርያ መሳርያው ሳትፈጥር ለምን በሰባተኛው ቀን ተኛህ ጃል?ይህን ግኝትስ ውሸት መሆኑን የሚያረጋግጥ ሌላ ግኝት አለመኖሩን እንዴ እርግጠኛ መሆን እንችላለን?«እናትና አባትህ በሚያደርጉልህ ልዩ እንክብካቤ ወላጆችህ መሆናቸውን ማወቅ ትችላለህ» ያልከኝ መሰለኝ።ታድያ ሁሉም የጉዲፊቻ አሳዳጊዎች መጥፎናቸው ያለህ ማን ይሆን? በመስተንግዶ በጣም የተወራላቸው ሐበሾች ይቅርና በቀለም የማይመሳሰሉን ፈርንጆች በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት በጉዲፊቻ ለማሳደግ እየተሻሙ መሆኑን አታውቅም?

ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ የኔ እምነት ሰው የዘራውን ያጭዳል የሚል ይሆናል።አዎ! የፈለግከውን ማድረግ ትችላለህ፤እስላሙ፣ክርስትያኑ፣ቡድሂስቱ፣የሁንዲዝም ተከታዩ፣የአይሁድ አማኙ፣ ኢአማኙ ሁሉም እኩል ናቸው።የተረገመ ወይም ተባረከ ዘር ብሎ ነገር የለም።ባርያ፣ቡዳ፣ጭዋ … ወዘተ የሚሉ ኋለ ቀር ታርጋዎች በሰው ልጆች ላይ መለጠፍ ጅልነት ነው። ሰዎች ያው ሰዎች ናቸው፤ የዘሩትን ያጭዳሉ በቀጥታም ሆነ በዘወርዋራ።አለዚያ ላንዱ አንግሰህ ሌላውን ባርያ ማለትህ አምባገንነት ነው፤አጥብቄ እቀወመዋለሁ።ስለዚህ አባትና እናቴን እማከብረው ሲያከብሩኝ ብቻ ነው።ካልሆነ ግን እንሱ እንደጎዱኝ እኔም ባልጎዳቸውም ያልዘሩትን እንዲያጭዱ አልፈቅድላቸውም።

ማንኛውም ሰው ወልዶ ማሳደግ የማይችል ከሆነ መውለድ የለበትም።እግዚሔር ያውቅል፣በዕድሉ ይደግ ብሎ ነገር መቆም አለበት።ከወለደ አፈር ልሶ ስራስር ምሶም ቢሆን ማሳደግ አለበት፤ ግዴታ ነው።እኔ ፈጣሪ ብሆን ንሮ ወልደው የማያሳድጉትን ሁሉ ብልቶታቸውን ሽባ አደርግባቸው ነበር።ወለደው የሚያሳድጉትንም በተቃራኒው የማይደበዝዝ ዘላለማዊ ፍቅር እሰጣቸው ነበር።

«የጀነቲክስ» ወይም ዘረ መል ባለሞያዎች ፍቅር የጅኖች የተፅዕኖ ውጤት ነው ይላሉ።አንዲት እናት የእርግዝናን ድካም ለዘጠኝ ወራት ችላ፣ የምጥ ስቀይ ተቋቁማ ወልዳ፣ጡቶቿን አጥብታ እንድታሳድግ የሚያስገድዳት የጅኖች ዘርን የመተካት ጫና ነው በማለት ይሞግታሉ።ምክንያቱም የዘረመሎች(ጅኖች) ተፈጥራዊ ልዩ ባህሪ ራስን መተካት ነው።ይህ ራስን የመተካት ግብታዊ ሀይል ነው እንግዲህ ወንድና ሴት በፍቅር አማካኝነት አጣምሮ፣ ወልደው ከብደውና የሞቀ ቤተሰብ መስርተው እንዲያልፉ የሚያስገድደው።

ሳይንሱ የፈለገው ማለት ይችላል፤ እውነትም ይሁን ውሸት ግድየለኝም።ይህን ሁሉ ምሬቴን በፅሑፍ የዘከዘኩት ከአስር ዓመታት በፊት ነው።ከምችለው በላይ ከፍቶኝ በንበረበት ጊዜ ስለነበር ከአሁኑ እምነቴ ጋር በጠኑም ቢሆን የሚጋጩ ሐሳቦች አሉ።ሆኖ ግን እንደዚያ እንዳስብ ያደረገኝ የቤተሰብ የፍቅር እጦት ስለነበር እንናንተ ልጆቻችሁ በፍቅርና በእንክብካቤ ያሳደጋችሁና በማሳደግ ላይ ያላችሁ፣ እንዲሁም ወልዳችሁ በቻላችሁት መጠን አቀማጥላችሁ ለማሳደግ የቆረጣችሁ ሁሉ በልጆቻችሁ ስም እጅግ በጣም አድርጌ አመስግናቿሎሁ።በልጆቻችሁ አማካኝነት ፍቅር የዘራችሁ ሁሉ የፍቅር አዝመራ ይበርክትላችሁ።

                                                                            
                                                                            
                               እለተ እሁድ፣ ማዝያ 6 ቀን 2005 ዓ.ም

Sunday, April 14, 2013

የቀን ውሎ






ዓርብ ማታ



ከአከራዮቼ ልጆች አንዷ ጴንጤ ነች።የሰላሳዎቹ የዕድሜ ክልል አጠናቅቃ ወደ አርባዎቹ የተጠጋች ትመስላለች።ነገር ግን ልጅም ሆነ ባል የላትም።ፀገሯ ልክ እንደ ቁመቷ አጭርና ሳሳ ያለ ነው።በዊግ ቀጣጥላ ረዥምና ብዙ ለማስመሰል ብትጣጣርም የባሰ ያስጠላባታል።አሻንጉሊት ያስመስላታል።ገፅታዋ«ጠይም ዓሳ መሳይ» ነገር ነው፤ቢሆንም ግን በኮስሞቲክስ ብዛት ሳይሆን አይቀርም ወዘናው ጠፍቷል።አብዛኛው ጊዜ ደግና ርህሩህ ብጤ ነች፤አመለ ሸጋና ሆደ ባሻ ነገር።

 ቤተ ክርስትያን ( እርሷ church ነው የምትለው) ሂዳ «የእየሱስ ቃል» ሰምታ ስትመጣ ግን የተለየ ባህሪ ታመጣለች።የእየሱስ ስም ደጋግማ በማንሳት አንዱን እያነሳች ሌላው እየጣለች፣ራሷ ጠይቃ ራሷ እየመለሰች፣አንዱ የጴንጤ ሞዝሙር ክፍታ የቴፑ ድምፅ ሙሉ በሙሉ እየለቀቀች፣ ደግሞ ያኛው ሳያልቅ በሌላ እየቀየረች…በቃ የምትሆነው ታጣለች።ወደ ቤቷ ትገባና መልሳ ደግሞ አፍታኳን ሳትቆይ ትወጣለች።ሽንት ቤት ትገባና በመስታወቱ ፊት ለፊት ተገትራ ራሷን ስታይ ቆይታ ስለ ሽንት ቤቱ መቆሸሽ፣ ማን ገብቶ እንደወጣ፣ «ምን ዓይነት እንስሳ ነው በየሱስ ስም» በማለት ትጠይቃለች፣ደጋግማ ትምላለች፣ እንዲሁም ትገዝታለች።ያኔ ማንም ተከራይም ሆነ ሌላ ትንፍሽ አይልም፤ እናቷም ጭምር። ዓለም በአንድ እግሯ የቆመች ነው የሚመስለው።ዓርብ ማታ እንዲሁ ነበር ስትሆን ያመሸችው።

መጀመርያ በነሱ ግቢ ተከራይቼ ስገባ አንድ ታላቅ ወንደሟ ስለነበረ አንዲት ቃል አትተነፍስም ነበር።ጭራዋን በሁለት እግሮቿ መሃል ሽሽጋ የምትሸሽ ውሻ ነበር የምትመስለው።« አንቺ ጴንጤ!» ይላታል፤በወጣ በገባ ቁጥር።ያን ጊዜ እምትገባበት ታጣ ነበር።እርሱ ተከራይቶ ይሁን ወደራሱ ቤት ከወጣ ወዲህ ግን እናትና ልጅ እየተፈራረቁ ግቢው ሰላም አሳጥተውታል።በግቢው ውስጥ አንድ ወንድና ስድስት ሴቶች ይኖራሉ፤ ከሶስት ተከራዮች ጋር።የቤቱ ፈላጭ ቆራጮች ግን እማወራዋና ጴንጠዋ ናቸው።ሌሎቹ ሰዎች ሲወጡና ሲገቡ እንጂ አንዳችም ቃል ሲተነፍሱ አይሰማም።


ቅዳሜ ጧት


የቤቱ እማወራ ሁል ጊዜ እንደሚያደርጉት በ200 ሜትር ርቀት የሚገኘው የዮሐንስ ቤተ ክርስትያን ተሳልመው መጥቷል።እርሳቸውም ልክ እንደ ጴንጠዋ ልጃቸው ዓይነት ባህሪ ነው ያላቸው።በመልክ፣በቁመናና በሴትነት መዓርግ ግን የትም አይገናኙም።በርሷ ዕድሜ እያሉ ይቅርና ሽማግሌ በሚባል ዕድሜ ሁነውም በጣም ይበልጧታል።በአብዛኛው ጊዜ በግ ነገር ናቸው።ነጭ በነጭ በሆነ የሐበሻ ባህላዊ አለባበስ አሸብርቀውና ነጭ እርግብ መስለው ወደ ቤተ ክርስትያን ይበራሉ።
አንዳንዴ ግን የጂኒ ፈረስ ይመስላሉ።ቀንድ ያበቅላሉ።በሆነው ባልሆው ይጮሐሉ፣ያራገማሉ፣ ይገለፍጣሉ።እርሳቸውም ልክ እንደ ልጃቸው የሽብር ክፍለ ጊዜው አዘጋጅና አቅራቢ ይሆኑና መሬት ቆውጢ ያደርጓታል።

የርሳቸው የቁጣ መዓት ተጠቂ የቤት ሰራተኛቸው ነች።ሆድ ሲብስባቸው ከምንም ተነስተው እንጀራው አያምርም፤ዓይን የለውም፣ቀጠነ፣ወፈረ፣ አረረ ምናም፤ ወጡ አይጣፍጥም፣ጨው የለውም ወይም በዛበት… እያሉ የእርግማንና የስድብ እያሪኮ ያወርዱባታል።ሰራተኛዋ ግን ትንፍሽ አትልም።ሰምታ እንዳል ሰማች ዝም ጭጭ።ድሮ በየሳምንቱ ነበር የቤት ሰራተኛ የሚቀያይሩት፤እንዲህ አንዳቸው ሲጮሁባቸው ቤቱን ጥለው ይወጣሉ።የአሁኗ ግን ገራገር ነገር ነች፤በመጣባቸው ቁጥር ልጅና እናት በሚያቀጣጥሉት የእሳት ወላፈን እየተጠበሰች እንደ አመጣጡ እየቻለች ወራት ብቻ ሳይሆን ዓመትም ሳታስቆጥር አትቀርም።ዓርብ ማታና ቅዳሜ ጥዋት ከልጅና ከእናት የተወረወሩት የቃላት ቦምቦች ብታስተናግድም ይሀው ዛሬም አለች።


ቅዳሜ ከስዓት


በፌስቡክ እየተናፈሱ ያሉ «የበሬ ወለደ» ወሬዎች ከልክ በላይ ተሰላችቼሎህ።ፖለቲከኞችና ደጋፊዎቻቸው ቁንጫውን በሬ፣በሬውም ተራራ በማስመሰል የቀሽሞች ፕሮፖጋንዳ ይነፋሉ።ጉንበት ሰባቶች ኢህወዴግ-ዲ ተመስረቷል ይላሉ።ኢህወዴጎች ደግሞ ጉንበት ሰባት-ዲ ተፈጥሯል በማለት የመልስ ምት ይሰጣሉ።ተቃዋሚዎችና የመንግስት ደጋፊዎች ሁለቱም እንደ በዶ ቤርሜሎች ትንሽ በተነኩ ቁጥር ከፅናፍ እስከ አፅናፍ ያስተጋባሉ።የገደል ማሚቶው ከአንዱ ፅንፈኛ ወደ ሌላው ፅንፈኛ ሲያስተጋባ በአከባቢው የሚገኙ ሰላማዊ ዜጎችን ሰላም ይነሳል፤ ያቅለሸልሻል።

«ሃይማኖተኞቹ» «ከአንዱ ጫፍ የእምነት ነፃነታችን ተነጠቅን» በማለት ይጮሃሉ።በሌላው ጫፍ ደሞ «ነብዪ አልያስ አራት ኪሎ ይገኛል።ቡና ሲጠጣ አግንቼው ለምእመኑ እንዲህ ብዬ እንደናገር አዞኛል።» የሚል ጭሆት ያስተጋባል።ጭሆቱ አሁንም ይቀጥልና « በዓሉ ግርማ በህይወት አለ፤ዓለም በቀኝ ብሎ በጣና ሃይቅ በሚገኝ አንድ ገዳም በምናኔ ይኖራል።ዴርቶ ጋዳ፣ራማቶራ፣ዣንቶዣራ፣ተልሚድና ሌሎቹም መፃሕፍት ፅፎ በይስመዓከ ወርቁ ስም አማከኝት እንዲ ወጡ ያደረገው እርሱ ነው።» ይላል።

ፖለቲከኞችና ሃይማኖተኞች እንደ ሃይለኛ ጠጪ ፊኛ በውሸት ተወጥረዋል።በዚህም በዚያም በየቀኑ የሚቃዠው ቁጥር እንደ አሸን ፈልቷል።አንዱ የቃዠው ሌላው ቅዠታም በማጋነን ያስተጋባዋል።ውሸታሞችና ቅዠታሞች ለትልቅ ሽልማት የሚፎካከሩ ነው የሚመስለው።ጨዋታው ማን ደግ ሰራ ማንስ ተሳሳተ አይደለም፤ የማን ቀደዳ ከአድማስ አድማስ አስተጋባ ነው።በዚህ ምክንያት በፌስቡክ የማጠፋው ጊዜ ከቀን ወደ ቀን እየተመናመነ ይገኛል።እንደውም ራሴን ሳላጠፋ አልቀርም።ታድያ ከዚች ዓለም አለመሆኑን ይታወቅለኝ፤ራሴን እማጠፋው ከፌስቡክ ብቻ ነው።

ቅዳሜ ጧት በነዚህና በሌሎች የሐሳቦች ማዕበሎች ግራና ቀኝ ስናጥ አርፍጄ ከሰዓት ለመማር ወደ ክፍል («ክላስ») አመራሁ።አንደኛው ክፍለ ጊዜ የተማሪዎች «ፕረዘንቴሽን» ነበር።አንዷ ተማሪ አሮንጓዴ ሱሪ፣አሮንጓዴ የጥፍር ቀለምና በግራና ቀኝ ክንፍያለው የሚመስል ግራጫ ሸሚዝ አድርጋ ዊግ ምናም ስትል ደረስኩ።መጀመርያ ትንሽ ግር ብሎኝ ነበር፤የፀጉር አሰራር ዓይነቶች ያምታወራ መስሎኝ።
ሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ከአስር የሚያዝ ፈተና ተፈተንን።ምን ዓይነት ፈተና? ሌላ ጊዜ እመለስበታሎሁ።

በሶስተኛው ክፍለ ጊዜ አስተማሪው ላፕቶፑን አየጎረጎረ ትንሽ ጊዜ ስለወሰደ አንዱ ተማሪ ከምፒተሩ አስክት ከፍት ድረስ የሆነ ነገር እናውራ ብሎ ስለተማፀነ የሰሙኑን የፌስቡክ በሬ ወለደ ተነሳ።የበዓሉ ግርማ በጣና ሐይቅ ከሚገኙ ገዳሞች በአንዱ ሞንክሶ መኖር ለማሳመን ሰንካላ የሆኑ ምክንያቶች ተነሱ።ልክ እንደ ፌስቡክ አንዱ እውነት ነው ወይም ሊሆን ይችላል ይላል ሌላው መሰረተ ቢስ ውሸት ነው በማለት ይሞግታል።ነገር ግን ስምምነት ላይ ሳይደረስ ወደ መደበኛው የትምህርቱ ርእስ ተገባ።

በዕለቱ የተወያየንባቸው ርእሶች እውነት ስለመናገር፣ማንኛውም ነገር በትክክል ስለመግለፅ፣ራስን ችሎ በራስ አቋም ስለመመራት፣ስለተጠያቂነት፣ስለፍትሐዊነት ወዘተ የሚያወሱ ነበሩ።
በጣም ያስገረመኝ ግን በፌስቡክ ስለሚናፈሱ አልቧልታዎች ብያኔ መስጠትና አቋም መያዝ አቅቶን ስለእውነት፣ፍትሕና እኩልነት ምንነት መዘባረቀችን ነው።አንዱን በጭፍን እየተቃወሙና ሌላውን በጭፍን እየደገፉ እንዴት ነው እውነት መናገር የሚቻለው?ፍትሕና እኩልነትስ ከየት ይመጡ? አንዱ ከመሬት ተነስቶ ሲገላፍጥ ሌላውም ያንኑን የሚያስተጋባ ከሆነ መማራችን ምን ዋጋ አለው?ለዝያውማ ተራሮች አሉ አይደል? «አረ ጉድ ነው፣ጉድ ነው፣ጉድ ነው…» ያለው ማን ነበር?
  



                                                                                  ቅዳሜ ማታ፣ መጋቢት 5 ቀን 2005 ዓ.ም

Sunday, April 7, 2013

የኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይነት?




ሁሌም ነው በተለያዩ የምድያ ቶቋማት ሲደጋገም የምሰማው።የኢትዮጵያ ህዝብ ሰው አክባሪ፣እንግዳ ተቀባይ ነው ይባላል።የገጠር ልጅ ነኝና አዲስ አበባ ከመምጣቴ በፊት አባባሉ ለአፍታም ቢሆን አልጠራጠረውም ነበር።ይባላል ብቻ ሳይሆን በእርግጠኝነት «ነው» ማለት እችላለሁ።«ደጉ ባላገሩ» ይባል የለም?ዘፈን ብቻ እንዳይመስልህ እውነት ነው።ካላመንከኝ ምናልባ የአዲስ አበባ ልጅ ነህ እና ወደ ክፍለ ሃገር ጎራ ብለህ ማረጋገጥ ትችላለህ። የባላገር ንሮ የጋራ ነው፤በጋራ ይሰራል፣በጋራ የበላል፣በጋራ ይኖራል።በቃ!በሐዝንም ሆነ በደስታ ንሮው በጋራ ነው።

በክፍለ ሃገር የሰው ልጅ ያው ሰው ነው…ለማዳና አውሬ ወይም የቤትና የበረሐ፣ ፋራና አራዳ ተብሎ አይከፋፈልም፤ እንግዳም ቢሆን።የንሮ ልዩነቱም ብትል ተመሳሳይ ሁኖ ነው የሚጠብቅህ።ብያንስ ብያንስ በክፍለ ሃገር ጎደና አደሮች አታገኝም፤ሁሉም ሰው ቤት ውስጥ ይኖራል፤አለቀ።የቤቶች ልዩነት ቢኖር ቢበዛ ጣርያቸው በሳር ወይም በቆርቆሮ የተከደነ መሆኑን ብቻ ነው። ሃብታሙ ብዙ የቤት እንስሳትና ላቅ ቢልም ወፍጮቤት ወይም አይሱዝ መኪና ሊኖረው ይችላል።ነገር ግን የቤቱ አጥር «Denger! አደገኛ» የሚል ፅሑፍ የተንጠርለጠለበት የኤሌትሪክ ሽቦ የታጠረና በብረት መዝግያ የተቸነከረ አይደለም።ለጎረቤት፣ለወገን ዘመድ እንዲሁም ለእንግዳ ሁሌም ክፍት ነው።

አዲስ አበባ መኖር ከጀመርኩ ወዲህ ግን  የሰዎች ልዩነት የሰማይና የመሬት ያህል የተራራቀ መሆኑን ተገንዚቤለሁ፤ጥርሱን ያገጠጠ፣ዓይኑን ያፈጠጠ ሰፊ ልዩነት።የሰው ልጅ በእምነት(ሃይማኖት)፣በፖለቲካ፣በዘር፣በሃብት፣በብሔር፣በሰፈር፣በፆታ ወዘተ  የተቆራረጠ ይመስላል።ሰው አክባሪነትና እንግዳ ተቀባይነት የሚሉቃላት በወሬ እንጂ በተግባር አላጋጠሙኝም።ስለሆነም «ይባላል» እንጂ «ነው» ለማለት አልደፍርም።ምክንያቱም ሲባል ከመስማት በስተቀር ሲደረግ አላየሁም።
አዲስ አበቤዎች ለውጭ ሃገር ዜጎች እንጂ ለሐበሾች ሲበዛ ክፉ ናቸው።ፈረንጆች ወይም ከንፈራቸው ወፈር፣ፊታቸው ጠቆር ያሉ አፍሪካውያን ካዩ ሳይላኩ ወድየት፣ ሳይጠሩም አቤት ይላሉ።ተጨማሪ ክፍያ ልያገኙም ላያገኙም ይችላሉ።ግን አለ አይደል፣ እንዲሁ አመል ሆኖባቸው ነው መሰለኝ ማሽቃበጥ ያበዛሉ፤ሲበዛ ይሽቆጠቆጣሉ።ሐበሻ ከሆነስ? አይጣል ነው። ለማንኛውም አገልግሎት እንግልት ይደርስበታል፤ይጉላላል፣ይዋከባል።ድርጅቱ የመንግስትም ሆነ የግለሰብ ለውጥ የለውም።

ይህ ነገር ወሬ ብቻ እንዳይ መስልህ እመነኝ! እውነት ነው።ካላመንከ ፈረንጆችና ሐበሾች ወደ ሚስተናገዱባቸው ሆቴሎች፣ኤርፖርቶች(የኤርፖርቶች ደምበኛ አይደለሁም ግን ለሐበሾች አስቸጋሪ መሆኑን ይታወቃል) ፣የዜግነትና የስደተኞች ጉዳይ ምኒስተር መስራ ቤት ጎራ በል።ጉድ ታያለህ። ፓስፖርት ለማውጣት ብያንስ ለሶስት ወራት ትንከራተታለህ።ፈረንጅ ከሆንክ ግን አንድ ቀንም አይፈጅብህም።ሆቴሎች ሐበሻ ለመስተናገድ ብያንስ ግማሽ ሰዓት ይፈጅባቸዋል።ለፈረንጅስ?ቢበዛ በአንድ ደቂቃ!እናም በቀላሉ አንድ ሐበሻ የሚስተናገደው ከርሱ በኋላ የመጡ 27 ፈረንጆች ከተስተናገዱ በኋለ ነው።በመንግስት ድርጅቶች፣በተለይ በቴሌ ፈረንጆች አይፈተሹም፤ምስኪን ሐበሻ ግን በደምብ ይታሻል… ከላይ እስከታች።

በአከራይና ተከራይ መካከል ያለው ግንኙነት እግዚኦ! የሚያስብል ነው፤በተለይ ለሴቶችና ለባለ ትዳሮች(ለወለዱ በጣም ይከፋል)።ሽንት ቤት ቢቆሽሽ፣ ውሃ ቢፈስ፣መብራት ከሶስት ሰዓት በኋላ ከበራ ወዘተ መዓት ይወርድብሃል…ድርጅቱ የተፈፀመው ባንተ ላይሆን ይችላል፤ የሆነ ሁኖ ግን ተጠያቂ ነህ።
እዚች ጋ አንዲት ቀልድ ትዝ አለችኝ።ድሮ ነው አሉ(«አሉ ነው እንግዲህ» አለ የፌስ ቡክ ፀሐፊ) የሆነ ሰው በእንግድነት ወደ አንዱ ቤት ይሄዳል።ወሩ ጥቅምት ነበር።ወርሐ ጥቅምት ደሞ የእሸት ወር መሆኑን ይታወቃል።እንደ አጋጣሚ ሁኖ የቤተሰቡ እራት የተለያዩ ዓይነት ሰብሎች እሸት ነበር፤ የበቆሎ፣የአተር፣የአኩሪ አተር እሸት እንደጉድ የጠበሳል፣የቀቀላል…ይበላል ። እራት ከተበላ በኋለ የእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሆድ እንደ ባሉን ተነፋ።ትንሽ ቆይቶ ቤቱ በፈስ ድምፅ የጦር አውድማ መስሎ ቁጭ አለ።መጀመርያ አከባቢ የቤቱ አባወራና እማወራ ለድምፅ ብክለቱ በሳቅ ያለፉት ነበር።እየቆየ ሲመጣ ግን እየሆነ ያለው ነገር አሜን በለው ለመቀበል የሚያስቸግር ሆነባቸው።

አባወራ አከታትለው ለቀቁት፤ቀደድ፣ቀደደድ፣ቡም።ተንሰተው ሂደው ትንሹኝ ልጃቸው «ይድፋህ»በማለት በጥፊ አጮሉት።
እማወራ ቀጠሉ፤ቀደድ፣ቦጭ፤ቦጨጭ፤ቦጨጨጭ።እናትም ተነሱና «ምናባቱ ይህ ባለጌ ሰዳቢ እንደ አህያ ይለቀዋልሳ» ብለው ለልጁ በጥፊ ደረገሙበት።ልጁ አንዴ ፈርዶበታልና ምንም አላለም፤ጭጭ፣ዝም።
በመጨረሻ እንግዳው፤ስጢጥ፣ስ…ጢ…ጥ፣ኡቭ፣ቋ…ቅ(በጣም የታፈነ የፈስ ድምፅ አሰሙ)።ማን ይቀራል ታድያ? እንግዳም ተነሳ።
አባወራ ጠየቁ፤ወዴት ነው ጌታየ?
እንግዳ መለሰ፤ ወደፈረደበት ልጅ።
የአዲስ አበባ ተከራይም እንዲህ ነው፤የማንም ፈሳም ማሳበብያ።

ወንደ ላጤ ሁነ በዕድሜ ገፋ ያሉ ሴቶች ያሉበት ግቢ ውስጥ ከተከራየህ ግን ያን ያህል አትቸገርም።እንደውም ቡና ጠጣ ምናምን ትባላለህ።በሰበብ አስባቡ ከሴቶቹ ጋር እንደትተዋወቅ ጥረት ይደረጋል፤ያው በአረዶች አባባል «ጠበሳ» መሆኑን ነው።

ባንዱ ቤት ያጋጠመኝ ግን የተለየ ነበር።የአክስቴ ልጅ በሳሪስ አቦ አከባቢ ተከራይቶ ይኖራል።እናም ባለቤቱ ስለወደች ለመጠየቅ ሄድኩኝ።ቤቷ በጣም ጠባብ ነች፤ቆርቆሮ በቆርቆሮ።ለይመሰል በውስጥ በኩል በፕላሰቲክና በመዳበርያ ተሸፋፍኛለች።ቢሆንም ግን እጅግ በጣም ትሞቃለች፤እንግዶቹም ሆነ የቤቷ ተከራዮች ላብ በላብ ሁኗል።ይባስ ብሎ ግን ዓይን የሚያስለቅስ፣አፍንጫ እየሰረሰረ አሁንም አሁንም የሚያስነጥስ ነገር በቤቷ በር በኩል መግባት ጀመረ።እሁድ ቢሆንም አከራይዋ ሴትዮ በቤቷ አጠገብ(ወደ በር ተጠግታ)  በርበሬ እየወቀጠች ነው። አንዱ «እጥሾ!» ይላል፤እንባው መንታ መንታ ቦይ ሰርቶ ፊቱን እያጠበ ይወርዳል።ሌላውም እንዲሁ ይከተላል።ሰባት ሰዎች!ንጥሻ በንጥሻ፣እንባ በእንባ ሁኗል።አይኖች ቀልቷል፤ያለ ማቋረጥ እንባ ያፈሳሉ።አፍንጮች አብጧል፤ደጋግመው ይናፈጣሉ።

ሴትዮዋ ግን ስራውን አለቆመችም።አይን የለም፣ጆሮ የለም …ርህራሄ አይታሰብም።አንድ በአንድ እየተናፈጥን፣አያነባን ቤቷን እየለቀቅን ወደየመጣንበት።ይገርማል! የአዲስ አበባ መስተንግዶ በርበሬ ማጠንም ይጨምራል።በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይነት አዲስ አበባን ሳይጨምር መሆን አለበት።ምክንያቱም አዲስ አበቤዎች በእንግድነት ቀርቶ በተከራይነትም መኖር ይህን ያህል አስቸጋሪ ነው።በተከራየህበት ቤት እንግዶች መቀበል በርበሬ እስከማጠን ደረስ እያስቀጣ ነው።"ወይ ዘንድሮ" አለ ዘፋኙ?


Thursday, April 4, 2013

Fanaticism at its best






Many centuries ago, Aristotle said, “The two extremes are always vices." He might have been obsessed with the fanatics of his time. That's why he introduced the idea of Golden Mean; though, it is not faultless, it still is an enlightening thought to this very day.

But, are we saved from the vices or evils of radicals, fundamentalists, extremists and even worse fanatics? The answer is boldly NO. Unless we are unable to curve the wild beast in us, we will continue dwelling on the oppositely charged poles of baseless ideologies. Such foolish ideologies are the result of Machiavellian and Goebbelean brainwashing. They are meant to breakdown social bonds and replace them with antagonistic feelings.

As such hatred intensifies, societies start killing one another savagely. For the canning propagandists, such social catastrophes are as profitable as a vampire movie. In the meantime, the Iagos are busy amassing everything whatever their ego demands them. They take everything the society possess: social, economic and political power. They dedicate their life for social respect, economic freedom and political prestige... dead or alive.

On the other hand, they are busy preaching the society how poorly they live. Their self-prophesy for holding power is that they are pleaded to stay in power just to change the life of their society. They work day in and day out, directly and indirectly simply to prove that they are born to lead. Their media organizations indulge themselves in systematically producing and distributing fictitious miracles.

This is what has happened and is still going on in our country. Our governors, late and present, have the culture of attaching themselves with some ethnic groups and they viciously claim that the ethnic group is leading the others, whether the system of governance is autocratic, dictatorship or democratic it does not matter.

However, this is a fatal misconception as no society can ever lead another. Even in a dynastic rule, only a family  is beneficiary politically, socially and economically. From Emperor Tewodros to Haileslase and from Mengistu to Meles no clan or ethnic group enjoyed life but their immediate family and themselves. Thus, all of them, no matter how they ruled, lived and died to quench their egos...just for their belly. 
The rest of all lived and still live in political, social and economic destitute unless they are blind loyalists of the respective rulers. And above all, no matter the effect (positive or negative), the past generation can never represent this generation and this generation to the next and so on.  

As a result, Ethiopians are subdivided in three main groups at this time. Those pro and against the ruling class and those who are either fad up with dirty politics of contemporary Ethiopia or waiting for the mighty judge...time. Such glaring diversion prevailed after the death of the late Prime minster. You can look at the picture shared above. To translate it roughly, it means: If you don't love Meles, that means you are a traitor who never reciprocates his (Meles') good deeds. This is nothing but absurd fanaticism. It is logically fallacious.

For his staunch supporters, Meles was charismatic, visionary, wise, compassionate, passionate, great communicator, daring, disciplined, persistent, and honest leader Ethiopia ever has had in its entire history. Such superlative words have been everywhere describing his personality and glorifying him beyond the gods of ancient Athens. Well, in our culture, the dead is faultless. The eulogy is written only in favor of the deceased individual, all misdeeds have zero chance. Yet, history should be free of cultural emotions... it should entertain the weaknesses and strengths equally.

However, for his archenemies, Meles was a traitor, a dictator, and self-aggrandizing, public enemy...just list down the exact opposites of the superlative words that praise his personality like an angel or saint. Some wrote that he was "a devil incarnate" that turned the country hundred years backward. Others danced on his funeral day in ecstasy chanting and ululating frantically; though uncommon culture wise. 

Nevertheless, whatever the pros and antis may say, Meles lived like other humans. He was neither perfect nor hundred percent faulty. Meles was not a saint (and I hope he won't be) and he was not a devil either. Those who either aggrandize or demonise him are both equally fallacious... they are saying or doing like so because they are in the opposite ends of a charged pole.

Therefore, one has the right and a chance as well, settle in the middle of the pole; though, the measurably imperfect. It is up to the individual either to join the chaos groups or not. Both groups are good for nothing other than polluting the status quo.


Tuesday, April 2, 2013

የመጽሐፍ ሻጩ ሙግት





…ማንበብ እወዳለሁ።ከምንም ነገር በላይ ያዝናናኛል፤ነፍሴ ነው።በተለይ የማነበው ነገር ይዘት ከራሴ የህይወት ፍልስፍና ከተገጣጠመ አምብቤ ለመጨረስ የማደርገው ትግል ልዩ ነው።ያኔ የሚኖረኝ ትጋትና ትዕግስት ያስገርመኛል።ምነው በሁሉም ስራዎቼም እንደዚህ ያለ ጉጉትና ጥልቅ ተመስጦ በኖረኝ የሚል ምኞት ይፈጥርብኛል።

በዚህ የተነሳ ለመፅሐፍ  መግዣ የማወጣው ወጪ አያስጨንቀኝም።በጣም የተወራለት ወይም ደስ ያለኝ መጽሐፍ ካገኘሁ ቢወደድም ከመግዛት ወደ ኋላ አልልም።ሳላቅማማ እገዛዋለሁ።በቂ ጊዜ ካገኘሁ እሰዮ ነው ተረጋግቼ አነበዋለሁ።ካልሆነ ግን የእንቅልፍ ሰዓቴም ጭምር እየቀጣሁ እጨርሰዋለሁ።አንዳንዴም ለሌላ ጊዜ ይቀመጣል።ምክንያቱም የገዛሁት መጽሐፍ ሳላነበው እንደማልቀር ከልምድ ተምሬለሁና ነው።

ስለሆነም በአዲስ አበባ ጎደናዎች የእግር ጉዞ ሳደርግ ዓይኖቼ የሚንከራተቱት ከመልከ መልካሞቹ ወጣት ሴቶች ይልቅ በየአስፓልቱ ዳር የተዘረጉት መጻሕፍት ላይ ነው።አንዳንዴ ወጣትነቴ ጥሎኝ የሸሸ መስሎ ይሰማኛል።ነገር ግን ድሮውም ለሴቶች ያን ያህል አልነበርኩም።ማለት ካንቺ ወድያ ዓለም ለምኔ ብሎ እንደመነነው በዛብህና ለሮዛ ሲል ህይወቱን አሳልፎ እንደሰጠው የታይታኒኩ ተዋናይ ዓይነት ስሜት ንሮኝ አያውቅም።

እናም የሰፈረኝ የመጻሕፍት ፍቅር እንደ ለማዳ እንስሳ እየነዳ ወደ አንዱ መጻሕፍት ሻጭ ወስዶ እንደ ሐወልት ገተረኝ።ወጣት ነው፤ በሃያዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኝ ይመስለኛል።ሁል ጊዜ አንድ ዓይነት ነው፤አንድ ዓይነት ልብስ፣አንድ ዓይነት ጫማ፣በጫት የተወጠቀ አንድ ዓይነት ጉንጭ።ልጁ እንደነገረኝ ከሆነ አባቱም ዕደሜ ልካቸው መጽሐፍ ሻጭ ነበሩ ።ብዙ ጊዜ ስለምመላለስ ከልጁ ጋር ተላምደናል።አንብቤ እንደ መልስለት በቀን አንድ ብር ሒሳብ ያከራየኛል።በጣም የምፈልገው መጽሐፍ ሲነረውም እገዛዋለሁ፤በተመጣጣኝ ዋጋ።የዛሬ አመጣጤም አንድም ለመግዛት አልያም ለመከራየት ነበር።ነገር ግን ሳናስበው ቅልጥ ባለ ሙግት ውስጥ ገባን።

እንደ ልማዴ እስኪ ዛሬ ደግሞ አንድ ጥሩ ነው የምትለው መፅሐፍ መርጠህ ስጠኝ አልኩት።
«ይህ መፅሐፍ አንብበኋል?» አለኝ።ራሴን ግራና ቀኝ በማወዛወዝ አለማንበቤን ነበርኩት።
«አንብበው አሪፍ መፅሐፍ ነው።» አለኝ።አንተስ አንብበኋል? ብየ ጠየቅኩት።
«እኔ እኮ መሸጥ እንጂ ማንበብ አልወድም።አባቴ ጎበዝ አንባቢም ሻጭም ስለነበር አንብብ እያለ ይወተውተኝ ነበር።ነገር ግን በማንበብ ሳይሆን በመሸጥ ብቻ ነበር ንሯችን ሲዶጉም የነሮው።»

እና ካባትህ አንተ እንደምትሻል እየነገርከኝ ነው? 

«አይ እንደዛ ለማለት ፈልጌ ሳይሆን።አባቴ አንብቦ ምን አገኘ ነው እምልህ።በእርግጥ በገንዘብ አያያዝ አልደርስበትም፤እሱ ያገኛት ሁሉ ይዞ ወደ ቤት ነበር የሚገባው።ነገር ግን ከጥቂት አሮጌ መፅሐፎች በቀር ያወረሰኝ ነገር የለም።» አለኝ።
አንተስ ለልጅህ ወይም ልጆችህ ምን ለማውረስ ተዘጋጅተሃል? የኔ ጥየቄ ነበር።በመፅሐፍ ሽያጭ ከምያገኘው ገቢ ከጫት መግዣ ተርፎት ምንያህል ማጠራቀም እንደሚችል በአእምሮየ እያሰላሰልኩ።

«ከዚች ያርከበ ሱቅ ተለቅ የለ የመፃሕፍት መሸጫ መደብር እማወርሳቸው ይመስለኛል።ያም ሆነ ይህ ግን አንብቡ እያልኩ አላስቸግራቸውም።»

ለምን? የሚል ጥያቄ አስከተልኩለት።የተለየ ምስጢር ይነገረኛል ብየ ሳይሆን ወሬውን ለማስቀጠል ያህል።

«ምክንያቱም ማንበብ እንድታስብ ይገፋፋል።አስበው ብዙ መፅሐፍ ባነበብክ ቁጥር ብዙ ታስባለህ።ብዙ ማሰብም ጭንቀት ያመጣል።ብዙ መጨነቅ ጀመርክ ማለት ችግር ውስጥ ላይ ነህ ማለት ነው፤ አንድ ቀን ልትነቅል ትችላለህ።በአሁኑ ዘመን ብዙ አሳሳቢ ነገሮች አሉ።እንኳንስ ከልክ በላይ አንብበህ ሳተነብም ልታብድ ትችላለህ።»

ግን ደሞ «ጥሩ ፃሐፊ ለመሆን ጥሩ አንባቢ መሆን የግድ ነው» ይባላል።ለምሳሌ አንተ የምትሸጣቸው መፅሕፍት በሙሉ መስረታቸው ከደራስያን እንጂ ከመፃሕፍት ሻጮች አይደለም።ደራስያኑ ባይፅፉ ንሮ በዚች ክዮስክ ውስጥ አንድ መፅሐፍ አናገኝም፤እኔም አላውቅህም ነበር።«ማንበብ እንድታስብ ይገፋፋል» የሚለው አባባልህ አኔም እጋራዋለሁ።ነገር ግን «ብዙ ማሰብ ጭንቀት ያስከትላል፤ጭንቀት ደግሞ ሊያሳብድ ይችላል» ካልከው አባባል ጋር አልስማማም።ማሰብ ለሰው ልጅ መሰረታዊ ነገር ነው።ልክ እንደ መለያው ልትቆጥረው ትችላለህ፤የማሰብ ችሎታ ባይነሮው ንሮ ሰው አይባልም ነበር።ደግሞ ለጭንቀትም ሆነ ለዐብደት የሚያደርስ ክፋት የለውም።ማሰብ የአእምሮ«ጂምናስቲክ» ነው፤ሌላው አካላችን በስፖርት እንደሚዝናናውና እንደሚጠነክረው ሁሉ አእምሯችንም በማሰብ የዝናናል፤የጎለብታልም። በማለት ላሳምነው ሞክሬ ነበር፤ልጁ ግን በቀላሉ እጅ የሚሰጥ አልነበረም።አንድ መጽሐፍ ገዢ ከስተናገደ በኋላ ክርከሩን ቀጠለ።

«ወዳጄ፣ መፅሐፍ የሚያነቡም ሆነ ብሎም የሚፅፉ ሰዎች ለኛ ለሻጮች፣ለአሳታሚዎችና ሌሎች አንባቢዎች አስበው እንደይመስለህ።እንሱም ልክ እንደኔ በሱስ ስለተለከፉ ነው።አንዴ አዲስ ነገር ለመሞከር ሲሉ ማንበብ ጀመሩ፤ከዛም በዛው ገፉበትና ሱስ ሆነባቸው።እናም ሱሳቸውን ለማስታገስ ሲሉ ያነባሉ፤ምርቃናውን እንዲሽርላቸውም ባገኙት ወረቀት ላይ መሞነጫጨር ይጀምራሉ።ከዛም ሳያስቡት ወደ ደራሲነት ዓለም ይገባሉ ማለት ነው።ልክ የሽጋራ ሱሰኛ አጭሶ መርካት ሲያቅተው ሐሽሽ ማጨስ እንደሚጀምረው ሁሉ።»

በሾርኔ ሱሰኛ ነህ እያለኝ መሆኑን ገብቶኛል፤ሆኖም ግን እንዲነቃብኝ እድል አልሰጠሁትም።ግን እኮ ማሕበረሰባችን በጣም ያደንቃቸዋል፤ያከብራቸዋልም።እንደሱሶኞች ተቆጥረው አያውቁም፤እንደ አዋቂዎች እንጂ።የማሐበረሰባችን ምስጢሮች ሳይቀር አፍረጥርጠው ስለሚፅፉ ለእውነት፣ለእኩልነትና ለፍት በብዕራቸው የሚዋጉ አርበኞች እንደሆኑ ነው የሚታወቀው።አይደለም እንዴ?

«ትክክል ነህ።ነገር ግን አብዛኛው ጊዜ ተዋቂነትም ሆነ ክብር የሚያገኙት በህይወት እያሉ ሳይሆን ከሞቱ በኋላ ነው።እንደውም ብዙዎቹ ለሰላማዊ ንሮ አልታደሉም።እነሱ በብዕሮቻቸው ይሞግታሉ ባለንጦቻቸው ደግሞ ከተቻለ ዝም እንዲሉ ይመክሯቸዋል።በምክር ካልተመለሱ አንድም በማዋከብ አገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ የገፋፏቸዋልቸ፣አልያም ያለፍርድ እስር ቤት ውስጥ ተቸንክረው እንዲማቅቁ ያደርጋሉ።እንዚህ ሁሉ አማራጮች ሞክረው ካልሆነም አንገታቸውን በመጠምዘዝ እስከወድያኛው እንዲያሸልቡ ያደርጋሉ።መቸስ የአቤ ጉበኛና የበዓሉ ግርማ ታሪክ አታውቅም የሚል እምነት የለኝም።ይህን ስልህ ግን የደራስያን አድናቂ አይደለሁም እያልኩህ አይደለም።በአጠቃላይ እውነተኛ የጥበብ ሰዎችን ከምንም በላይ አድንቃለሁ፤አከብራለሁ።በተለይም ትእግስታቸውና ስስት አልባ ህይወታቸው።አየህ እነሱ በህይወት እያሉ በአስርና አስራምስት ብር ታትሞ ለገበያ የወጣው ምርጥ መፅሐፍ አሁን በመቶዎች እየተቸበቸበ ይገኛል።»

የበዓሉ ግርማና የአቤ ጉበኛ ስም ሲያነሳ አንጀቴ በሐዘን ተላወሰ።ሃገር በጅቦች ጭቆና በነበረችበት ዘመን ሁለቱም ለእውነት የቆሙ ምርጥ የኢትዮጵያ አርበኞች ነበሩ።ታድያ የአርበኝነታቸው መሳርያ ብእርና ወረቀት ብቻ ነበር፤ማንንም አላቆሰሉም፣አልገደሉምም።ቢሆንም ግን ሁለቱም ገዳያቸው ሳይታወቅ በወጡበት ቀሩ።
አዎ፣ ገዢዎች አሰራራቸው የፈለገው ያህል ቢረቀም ምንጊዜ ከህዝብ እይታ የተሰወረ አይደለም።ወንጀለኞቹ የተቀበረ ሚስጥር ነው ብለው የሚያስቡት ሁል ለህዝቡ ንፋስ ያብጠለጠለው የመንደር ወሬ ነው።የስንቶቹን ዓይኖች አጥፍተውና የስንቶቹን ጀሮ ዘግተው ይዘልቁት ይሆን?

ከልጁ ጋር መከራከሩን ትቼ ወደ ቤቴ ጉዞ ጀመርኩ።በፖለቲከኞችና በጥበብ ሰዎች መካከል ያለው የሰማይና የመድር ልዩነት እያሰላሰልኩ።የጥበብ ሰዎች ብርሃን ናቸው፤ፖለቲከኞች ግን(ሁሉም ለማለት ባልደፍርም) በአብዛኛው ጨለማ ናቸው።ብርቱ ጥበበኛ በለበት ሁሉ ብርሃን አለ።ብርሃን ካለም ጨለማ አይኖርም።ህይወት እንደ ወተት ነጭ ነች፤ፖለቲከኞች ቡና በመጨመር ያጠቁሯታል።

  

                         እለተ እሁድ መጋቢት 22፣2005 ዓ.ም