የፌስቡክ ግምባር ቁጥር አንድ ተዋጊ ነው፡፡ በፈለገው ዓይነት መሳርያ ያለርህራሄ ወደ ህወሓት በመተኮስ ይታወቃል፤ ሌላው ቀርቶ ጅምላ ጨራሻ መሳርያም ሳይነረው አይቀርም የሚሉ ወገኖች አይጠፉም፡፡የመሳርያው ምንጭ
ግን አይታወቅም፡፡የመቐለ ዩኒቨርሲቲ
የስነ ምግባርና የስነ ዜጋ አስተማሪው ይዋሻል ተብሎ ስለማይታሰብ የተናገረው ሁሉ እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ወይም ቅዱስ ቁርዓን ያለ ማንገራገር መታመን አለበት ብሎ ያምናል፡፡ ለዛም ነው በህወሐት ላይ እያነጣጠረ ለሚተኩሳቸው መሳርያዎች ምንጭ ሲጠቅስ የማይታየው፡፡ባለፈው ጊዜ
‹‹ጋዜጠኛ አይደለሁም›› ሲል ፅፎ(ተኩሶ) ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ያልሆነ ሁሉ የውሸት ቦምቦች እንዳሻው ማፈንዳት ይችላል ያለው ማን ነው? የስነ ምግባርና የስነ ዜጋ መምህር ያለ ምንም ገደብ ‹‹መቅደድ›› ኣለበት እንዴ?ለማንኛውም ያለ ምንም ምንጭ የፈለገው ዓይነት ሮኬት መወንጨፉ፣ቦምብ ማፈንዳቱ፣የአየር መቃወምያ መሳርያ መጠቀሙ ጠቀመው እንጂ አልጎዳውም፡፡በከፍተኛ ሹመት
ወደ አዲሱ ዓመት እንዲሸጋገር ረድቶታል፡፡በጳጉሜ ሁለትና
ሶስት በተካሄደው የዓረና ትግራይ ሶስተኛው ድርጅታዊ ስብሰባ የማእከላይ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ አባልና ሆኖ ተመርጧል፡፡ለእርሱ ይመቸው
እንጂ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት እማ መሆን አያቅተኝም፡፡
እኔስ የስነ ምግባርና የስነ ዜጋ መምህር ነው ያሉኝ ጊዜ ከማንም ጋር ሳይወግን ለህዝብ ነፃነትና ፍትሕ ብቻ የሚታገል መሲህ መስሎኝ ነበር፡፡ዓረና እማ
የስም ለውጥ እንጂ ከህወሓት የተለየ የአስተሳሰብና የተግባር
ውጤት እንደማይኖራት እናውቃለን፡፡አቶ ገብሩ አስራት የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳደር እያሉ ህዝቡ እንዳሻቸው ይረማመዱበት አልነበረም እንዴ? የትግራይ ህዝብ ተቆርቋሪ ከሆኑ ያኔ ቀበታቸውን ጠበቅ አድርገው በመስራት ንሮውን እንዲቀየር አይረዱትም ነብር?የህወሓቶች አደናቃፊ አሰራር ስራየን እንዳልሰራ ከልክሎኛል ብለው የሚያምኑ ከሆነስ ከህወሓት ጋር ተወዳጅተው በትግራይ ህዝብ ላይ ባደረሱት በደል ተፀፅተው ይቅርታ የማይጠይቁት ለምንድነው? አሁን ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ የህዝብ አለኝታ ለመምሰል ከመሞከር ይልቅ ኤርትራ ወደቦቻችን ይዛ እብስ እንደት ለምን ፋቀዱላት? የተፈጥሮ ሃብታችን እንዳሻት ስታደርግስ ለምን ነበር ከአምስታ ዓመታት በላይ የታገሷት? ለካ መምህር አብርሃም የነዚህ ሰዎች ተላላኪ ነበሩ፡፡‹‹ሰው ማመን ቀብሮ ነው›› ያለው ማን ነበር?
ዓረናዎች ህወሓትን ለመውቀስ የሚያስችል ብቃትም ሆነ ሞራል የላቸውም፡፡የነሱ ነገር
‹‹ልነቓዕስያ ስባር ትመየኖ›› የሚባል የትግርኛ አባባል በደምብ ይገልፀዋል፡፡ዓረና እምሽክሽክ
ብሎ፤ ተሰባብሮ ከጥቅም ውጭ የሆነ ድርጅት ነው፡፡ህወሓት ግን
ነቃ(ለመሰበር ትንሽ ቀረው) እንጂ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ አልሆነም፡፡ ህወሓቶች ድክመቶቻቸውን ምንም
ሳያንገራግሩ በመቀበል ለመሻሻል ጠንክረው ከሰሩ ከዓረናዎች እንደሚሻሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ምክንያቱም የትግራይ
ህዝብ አሁንም ድረስ ጨርሶ ተስፋ አልቆረጠባቸውምና፡፡ልክ እንደ
ድሮው(በራሃ እያሉ እንደነበራቸው የህዝብ
ፍቅር) ራሳቸውን እየነቀፉ ስህተቶቻቸውን ለማረም
ቢሞክሩ የሚሳካላቸው ይመስለኛል፡፡ድክመታቸው አላ ሻሽልም ብለው ራሳቸው ለውድቀት ቢጋብዙ እንኳን ከዓረናዎች የሚብሱ አይመስለኝም፡፡
በቃ፤ አብርሃ ደስታም እንደ ሌሎቹ የህዝብ ተሟጋች ነን ባዮች መነሻውና መድረሻው ስልጣን ሳይሆን አልቀረም፡፡ለዛም ሳይሆን
አይቀርም ለአቅመ ስልጣን ከበቃ ወዲህ የፌስቡክ ትግሉም የተቀዛቀዘው፡፡ወይስ አዲስ
የማጥቃት ስልት በመቀየስ ላይ ነው?‹‹ልነቓዕስያ ስባር ትመየኖ!›› ዓረና ከህወሓት በምን መስፈርት ነው የተለየ የሚሆነው? በቃ፤ ከአሁን በኋላ የህዝብ ተቆርቋሪ ለመምሰል የሚደረገው
ጥረት ፉርሽ ሆነዋል፡፡የእህል ወሃ ጉዳይ ነው በየፌስቡኩ እያስጨሆኝ ያለው ማለት አለበት፤ በድፍረት፡፡
የሆነ ሁኖ የትግራይ ህዝብ ችግሮች በተሻለ መልኩ ሊቀረፉ የሚችሉት በህወሓትና በዓረና ሳይሆን ፐለቲካው ከነዚህ ድርጅቶች ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ በሌላቸው የአዲሱ ትውልድ ስብስቦች የመመራት ዕድል ቢኖረው ይመስለኛል፡፡ምክንያቱም እነዚያ
ድርጅቶች ዓላማቸውን አሳክቷል፡፡ዓላማቸው የትግራይን
ከደርግ አገዛዝ ‹‹ነፃ ማውጣት›› ነበር፤ልማትና ዲሞክራሲ
ግን ለስልጣን ከበቁ በኋላ የመጡ አዳዲስ ሐሳቦች ናቸው፡፡ለዛም ነው
ከውጭ የተኮረጁ መሰረተ ሐሳቦች የታለመውን ያህል ውጤት ሲያመጡ የማይታዩ፡፡እነ ቢፒአር፣ካይዘን፣ጂቲፒ ወዘተ. የስብሰባና የመገናኛ ብዙሓን አጀንዳ ከመሆን በላይ አመርቂ ውጤት የማያስገኙት፡፡
ለማንኛውም አብራሃ ደስታ የተመኘውን አግኝተዋልና እንኳን ደስያለህ፤ስልጣን ያዳብር
ልለው እወዳለሁ፡፡አዲሱ ዓመት የዓረነ ትግራይ ማእከላይ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ አባል አድርጎ ተቀብሎታልና፡፡እሱም ስልጣን
ከመያዛቸው በፊት ራሳቸው እንደ መሲህ ከሚቆጥሩና በትረስልጣን ከጨበጡ በኋላ ግን የውሸት ጭምብላቸውን አውለቀው እውነተኛ አምባገነን
እንደሚሆኑ ወገኖቹ እንዳይሆነም ላሳስበው እፈልጋለሁ፡፡

እግዚሄር ይሃበካ አስፋው እታ ዘላ ኩላ ገሊፅካያ
ReplyDeleteBravo Abrish....enkuwan des aleh..
ReplyDeleteEngidih zem belo mayet new
ReplyDeleteI agree with you, the guy is a power hungry, I specially understand him from the beginning , he is not an activist rather he wants to be a politician b/se he is blind to lies and poisons claims if it is from the side he wants to be. I told him/commenting many times but didn't get a reply from him positively or negatively. but i didnt agree with ' TPLF is better than Arena ' TPLF is the worst party that it betrayed our brother sacrifice. TPLF has a debt of the Tigray people a debt of life that it should give us back, rather it is group of families that it works for a very specific family groups. I am more than happy with your claims that the Ethiopian problem specially tigrean problem can only solved with those has no relation with the expired groups TPLF or ARENA.
ReplyDeletemaking choices b/n TPLF or ARENA is a wast of time.