| ዶክተር እንጅነር ሳሙኤል ዘሚካኤል |
ሬድዮ ፋናቢሲ በዛሬው ዕለት የጥዋት የ90 ደቂቃ ዝግጅቱ እጅግ በጣም አስገራሚ ዜና አስደምጦናል፡፡
እራሱን ዶክትረ እንጅነር እያለ የሚጠራውና በድህነት ማቅቆ ቢያድግም ‹‹በጥረትና እልህ አስጨራሽ›› ስራ የብዙ ድርጅቶች ባለቤት
እንደበቃ በኩራት የሚናገረው ሳሙኤል ዘሚካኤል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደማያውቀው ተረጋግጧል፡፡በመሆኑም ከአዲስ አበባ አራት ኪሎ ግቢ በስቪል
እንጂኔሪንግ በመጀመርያ ድግሪ ያልተመረቀ መሆኑን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡
ይህ ፎርጅድ ሰውየ በሚያዝያ 27 ቀን 2006 ዓ.ም ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ረዥምቃለ መጠይቅ ማንነቱን እንሚከተለው ስፍሮ ይገኛል፡፡
‹‹ዶ/ር ኢ/ር ሳሙኤል ዘሚካኤል በሙያው መሃንዲስ ነው፡፡ በ1995 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቴክኖሎጂ ፋኩልቲ የትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪውን በሲቪል ኢንጂነሪንግ አገኘ፡፡ ሁለተኛ ዲግሪውን በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት በ2000 ዓ.ም ከአውስትራሊያ ካምቢራ ዩኒቨርሲቲ፣ ሦስተኛ (ዶክትሬት) ዲግሪውን ደግሞ በአርባን ፕላኒንግ በቅርቡ ከአሜሪካ ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ መቀበሉንና ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንደተሰጠው ተናግሯል፡፡››
ከላይ ለተገለፀው እጅግ ለላቀው የትምህርት ደረጃና መዓርግ እንዴት እንደደረሰ የሚተርከው ደሞ እንዲህ በማለት ነው፤‹‹አቃቂ ከተማ ውስጥ በፈረስ ጋሪ የጠዋት ተማሪ ስሆን ከሰዓት፣ የከሠዓት ተማሪ ስሆን ጠዋት እየሰራሁ ነው የተማርኩት፡፡ ሰው ቤት በእረኝነት ተቀጥሬ ከብቶች እየጠበቅሁና እያጠብኩ፣ አዛባቸውን እየጠረግሁ አበሳ አይቼ ነው የተማርኩት፡፡››
‹‹ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ››
እንደሚባለው ሰሙኤል ዘሚካኤል ሁለገብ ባለሙያና ከባዶ ተነስቶ የብዙ ድርጅቶች ባለቤት እንደሆነ ነው እራሱን የሚገልፀው፡፡ያ ህሉ
ትርክትና መዓርግ ግን ግዜውን ጠብቆ ተረት ተረት መሆኑን ግልፅ ሆኗል፡፡ ሳሙኤል በ“ላይፍ ኮች ኤንድ ሞቲቬሽን ስፒከር” የመጀመርያ ድግሪ እንዳለው በማስወራት ሰዎች የላቀ ስብእናና መንቃቃት እንዲኖራቸው ሲያስተምር
ኖሯል፡፡ አሁን ግን የገፀ ባህሪው ማንነት ልበወልዳዊ ፈጠራ መሆኑ ነው ሬድዮ ፋና የዘገበው፡፡
አዲስ አድማስ እንደሚከተለው
ነበር ያያኔውን ዶክትር እንጂኔር ሳሙኤል ዘሚካኤልን የህይወት ታሪክ ያስነበበው፤ ‹‹ የዛሬ 35 ዓመት አንድ ሕፃን ከድሃ ቤተሰብ በጋንዲ ሆስፒታል ተወለደ፡፡ ያ
ሕፃን ከተቀሩት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት የተለየ ችሎታ አልነበረውም፡፡ ቤተሰቦቹ ድሃ ስለነበሩ በእንክብካቤና በቅምጥል አላደገም፡፡ አባቱን አያውቃቸውም፡፡ የአምስት ወር ህፃን ሳለ ነው በሞት የተለዩት፡፡…›› የሰውየው ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ያደረገው ቃለ
መጠይቅ ሙሉውን ለማንበብ የጋዜጣውን ድረ ገፅ ይጎብኙ፡፡ለጊዜው ግን የቃለመጠይቁ ጭብጥ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡፡
ü ከደሀ ቤተሰብ ተወልዶ ብችጋር ማደጉን በሄደበት ሁሉ ያወራል፡፡
ü ‹‹ያ ከድሃ ቤተሰብ የተወለደው ሕፃን፤ በእልህ አስጨራሽ ትግልና ጥረት፣ በከፍተኛ የእውቀት ፍቅርና ትጋት ድህነትን ድል ነስቶ፣ ከራሱ አልፎ ለሌሎች ለመትረፍ በቃ፡፡›› እያለ በገናኛ ብዙሓን የውሸት ማንነቱን ያስነግራል፡፡
ü እራሱን እንደ አፍሪካዊ ባለራዕይ ይቆጥራል፡፡
ü በ1998 ዓ.ም የመንግስት ስራውን ሲለቅ ደሞዙ 22ሺ
ብር እንደነበር
ይናገራል፡፡
ü በኮንስትራክሽን ሥራ የተሰማራውን ‹‹የአፍሪካ ቪዝነሪስ ዴቨሎፕመንት ካምፓኒ›› መስራችና ባለ ቤት ነው፡፡
ü ‹‹ኮፊ ላንድ ኮፊ›› የተሠኘ የወጪና ገቢ ንግድ ድርጅቱ የኢትዮጵያን ቡና ወደ ውጭ ይልካል፡፡
ü ከሌሎች አጋሮች ጋር በኢቴቪ “ባለ ራዕይ” የሚል ቶክሾው ነበረው፡፡
ü የሚዲያና የሞቲቬሽን ሥራዎች እንሠራል፣ የአስጐብኚ ድርጅት አለው፡፡
ü
ከሕንድ ኩባንያ ጋር በጆይንት ቬንቸር ጣና ሐይቅ ላይ የሪዞርት ሥራ ጀሯል፤ በሀዋሳ ሐይቅ ላይም ሪዞርት ለመሥራት ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር የቦታ ጥናት እያደረገ ነው፡፡
ü የሳሙኤል ዴቨሎፕመንት ኢንስቲቲዩት ‹‹ፍርሃታችንን እንዴት እንገራለን? የሚለው ከማኔጅመንት ሥልጠናዎች›› ይሰጣል፡፡
ü በአጠቃላይም ሰኬታማ ምሁርና የብዙ ፈጠራዎች ባለቤትና ኢንተር
ፕረነር፡፡
አዲስ አድማስ፡ከዩኒቨርሲቲ እንደተመረቅህ የት ነበር ሥራ የጀመርከው?
ፎርጅድ ዶክተር ኢንጅነር፡ በጥሩ ውጤት ስለተመረቅሁ የመጀመሪያው ሥራዬ በዩኒቨርሲቲው ቀርቼ ማስተማር ነበር፡፡ ሁለተኛ ሥራዬ በአዲስ አበባ መስተዳድር የመሬትና ግንባታ ጉዳዮችን ማማከር ነበር፡፡
አዲስ አድማስ፡ከመንግሥት ሥራ የለቀከው ለምንድነው?
ፎርጅድ ዶክተር ኢንጅነር፡ የመንግሥት ሥራ የለቀኩት በ1998 ዓ.ም ነበር፡፡ ምክንያቴ ደግሞ ሰነፍ ሆኜ ወይም በሌላ ምክንያት ሳይሆን የራሴን ሥራ ለመጀመር ነው፡፡
አዲስ አድማስ፡ያኔ ደሞዝህ ስንት ነበር? የጀመርከውስ ሥራ ምን ነበር?
ፎርጅድ ዶክተር ኢንጅነር፡ ከቅጥር ስወጣ ደሞዜ 22ሺ ብር ነበር፡፡ ሥራ የለቀኩት፣ ደሞዝ አነሰኝ ብዬ ሳይሆን፣ በቀሰምኩት እውቀት የራሴን ሥራ ለመጀመር አስቤ ነው፡፡
አፍሪካን ቪዥነሪስ ዴቨሎፕመት ኩባንያን ከጓደኛዬ ጋር በአንድ ሚሊዮን ብር ካፒታል አቋቋምን፡፡ ለሁለት እናቋቁም እንጂ ገንዘቡ የእኔ ነበር፡፡ ይህንን ኩባንያ የመሠረትኩት፣ ራሴን እንደ አፍሪካዊ ባለራዕይ ስለምቆጥር፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ እኔ ካለፍኩ በኋላ የማይቆም (የማይቋረጥ) ኩባንያ እንዲሆን ስለፈለግሁ ነው፡፡ ብዙ ድርጅቶች ባለቤቱ ሲሞት ሕልውናቸው ያቆማል፡፡ የእኔ እንደዚያ እንዲሆን አልፈለግሁም፡፡
/*********************************************************************************
ህዳግ፡
እላይ
በጠቀስኩት ቀን ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ሳነብ በብቃቱ በጣም ተደንቄ ነበር፡፡ከአዲስ አበባ መስተዳደር
ጋር የነበረው ይቅጥር ውል ሲያፈርስ ደሞዙ 22ሺ እንደነበር የገለፀው ግን ለማመን አልቻልኩም ነበር፡፡ምክንያቱም በሃገራችን ለዛውም
ከአስር ዓመት በፊት ገደማ ያህን ያክል ደሞዝ የሚከፈል አልነበረምና፡፡ እኔ በዚሁ ሰውየ የማታለል ፈጠራ ከመገረምም በላይ ተደንቄያለሁ፡፡
እርሶስ ምንተሰማዎት? አስተያየትዎን ያካፍሉኝ፡፡ከቻሉም ፅሑፉን ወይም ጦማሩን ከጓደኞችዎ ጋር ያጋሩልኝ፡፡ ‹‹እንዲህም
አለ ለካ?›› ብለው መማር አለባቸው፤ ለወደፊት እንዳይታለሉ፡፡
Ethiopians are usually accepting words uttered by people. Since Ethiopians are highly believers in God, they assume that people will not lie in such 180 degrees way behind the truth. That is why many Diasporas telling us many false things. Personally I was saying that a person will not lie like saying the white as black or vise verse. Probably only minor lie. But I have seen many Diasporas telling us absolutely non existent and totally false things about them. I think this must be a curse. But they gave me a lesson that I should not always believe what people are saying, particularly if they are Diasporas.
ReplyDeleteይድረስ ለጦፎኛ ሬዲዮ ፋና መባል ካቆመ እኮ ቆየ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሚል ይስተካከል
ReplyDelete@Anonymous well said!!
ReplyDelete@Anonymous well said!!!
ReplyDeleteThe person who wrote the upper comment is taking no where but fabricated doctor& engineer is know how to lie and how to organize.
ReplyDeleteI worked with Sami three years ago and the only thing I remember is that he was not picking our phone calls after we paid him in Advance. Shame on you Sami and Addis Admas!
ReplyDeleteበነካ እጃችሁ የአገር መሪዎችንም ጨምሩ። እስቲ አንዴ እንኳ ድፈሩ። በተል እኮ አገኘን የሚሉት ከየትኛው ዩንቨርሲቲ በምን ያህል ጊዜ አገኙ? ቅርብ ጊዜ አይጋ ፎረም አርከበ እቁባይ በ እንግሊዞች ዩኒቨርሲቲ ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ በማይታወቅ ፍጥነትና ከፍተኛ ውጤት ዶክተርነቱን አገኘ ብሎን ነበር። ዩኒቨርሲቲው ሲጠየቅ ሌላ ቦታ ሊሆን ይችላል እንጂ እኛስ ጋ አይደለም ብሎ መልስ ሰጥቷል። አትፍሩ። በተለይ በጦር ሠራዊት አመራር ላይ ያሉትን አትርሱ። እንዴት ይህን የመሰለ ድግሪ ይዘው እንግሊዝኛ ቋንቋ በቅጡ መጻፍና መናገር አልቻሉም እያልኩ ይቆጨኝ ነበር። ለካንስ ትልቁ ዳቦ ሊጥ ኖሯል።
ReplyDelete