በወርሐ ጉንበት 2005 ዓ.ም በአንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብየ ሻይ ቡና በማለት ላይ ነበርኩ፡፡አንድ
በ40ዎቹ መጨረሻና በ50ዎቹ መጅርያ የዕድሜ ክልል የሚገኝ ጎልማሳ እኔ በተቀመጥኩበት ጠረጴዛ የነበረው ክፍት ወንበር ሰው ይንሮው
አይንሮው ካጣራ በኋላ መጥቶ ተቀመጠ፡፡በካፌው ውስጥ የነበረው ቴሌቪዥን ደርግ የወደቀበት የጉንበት 20 በዓል ዝግጅቶች በማሳየት
ላይ ነበር፡፡የቴሌቪዥኑ ዝግጅት ከአጠገቤ ለተቀመጠው ሰውየ የሚመች አልነበረም መሰለኝ ‹‹ጉንበት 20 እኮ የህወሓት ድል እንጂ
የኢትዮጵያውያን አይደለም›› እያለ ማጉረምረም ጀመረ፡፡‹‹የሃገራችን አንድነት የተናጋው ደርግ ተሸንፎ ህወሓት ለስልጣን ስለበቃ
ነው፤ የህወሓት ዓላማ ስልጣን ብቻ ነበር…›› እያለ ያነበንባል፤ ባልመልስለተም እኔን ማናገሩ ነበር፡፡
እኔ በሐሳብ ማዕበል እንገላታለሁ፤አወርዳለሁ እወጣለሁ፤እየወደቅሁ እነሳለሁ፡፡በሓሳብ መርከብ ተሳፍሬ ሁሉንም ስፍራዎች
አዳርሳለሁ፤ቆላውና ደጋው፣ገጠርና ከተማው፣ቅርብና ሩቁ አካልላለሁ… እማልደርስበት የለም፡፡አልፎ አልፎ እንዲህ ያደርገኛል፤አመል
ሳይሆንብኝ አልቀረም፡፡አጠገቤ የተቀመጠው ጎልማሳ ብስልና ጥሬውን ይዘባርቃል፤በተመስጦ የምከታተለው ሳይመስለው አልቀረም፡፡ለተወሰነ
ጊዜ መልስ ላለመስጠት ሞክሬ ነበር፤የኋላ ኋላ ግን አልቻልኩም፡፡ሰውየው የዋዛ አልነበረምና ኮርኩሮ ኮርኩሮ ሊያናግረኝ ችሏል፡፡የደርግ
ሐጥያቶች እንዳለ በህወሓት ላይ መለጠፉን ሲቀጥል፣‹‹ ማስረጃህ ምንድንው?›› ብየ ጠየቅኩት፡፡‹‹እኔ እኮ ያኔ ትልቅ ነበርኩ፤አንተን
በብዙ ዓመታት እበልጥሃለሁ፤ እንዳውም ሳልወልድህ አልቀርም፤እንዴት እንዲህ ትላለህ?›› እያለ የተናገረውን ሁሉ አሜን ብየ እንድቀበልለት
ወተወተኝ፡፡‹‹አይ፣ በዕደሜ ብትበልጠኝም ብዙ የታሪክ ፅሑፎች ስላሉ በመረጃ አስደግፈን በንናገር ይሻላል ብየ ነው፡፡›› ስለው፣
‹‹በለ ያዝ እንግዲህ፤ መረጃዎቹን ልዘርዝርልህ›› አለና፡
- ደርግ ወደ ጦርነት የገባው በህወሓትና በሻዕብያ ተገድዶ እንደሆነ
- የሰላምና የአብዮት ጥሪ አልቀበልም ብለው አሻፈረኝ በማለታቸው መሆኑን
- ደርግ ስልጣን የተረከበው መስከረም 1967 ዓ.ም ሲሆን ወያኔዎች ደግሞ ከሻዕብያ ጋር ወግነው በየካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም(ደርግ ስልጣን ከያዘ ስድስት ወር እንኳን ሳይሞላው) በኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ላይ ጦርነት በማወጃቸው ደርግ የሃገሩ ሰላምና አንድነት ለማስጠበቅ ወደ ውግያ መግባቱን ወዘተረፈ እያለ ሊያሳምነኝ ሞከረ፡፡
እኔም መረጃዎችን እያጣቀስኩ እሱ የሚላቸው ነገሮች በመክንያትና በመረጃ ያልተደገፉ የአስተሳሰብ ህፀፆች መሆናቸውን
ላሳምነው ሞክርኩ፡፡ሰውየው ቀድሞውንም ለውይይት ሳይሆን ለወሃ ቀጠነ ክርክር የተዘጋጀ ነበርና ክርክራችን እየጋለ ሂዶ በሁለታችን
በኩል መደማመጥ ጠፋ፡፡ከዛም በአነጋገር ዘየየ ትግራዋይነትየን ስላወቀ ነው መሰለኝ ‹‹ ድሮውም ከእናንተ ጋር መነጋገር ትርፉ ይህነው፤ሰው
ሲናገር አትሰሙም፤ እናንተ ያለችሁት ግን ያለምንም ማገራገር እንዲሰማላችሁ ትፈልጋላችሁ…›› በማለት ራሱ የጀመረው ዝርጠጣ አርእስቱን
ስለቀየረው ሂሳቤን ከፍየ ካፌውን ትቼለት ወጣሁ፡፡
ከላይ ያቀረብኩት ፅሑፍ ዓምና የተከሰተ ነበር፡፡ዛሬም ድረስ ግን ‹‹የደርግ ጭቆናዎች፣የዘር ማጥፋት ወንጀሎች፣ያለ
ፍርድ የተፈፀሙ የንፁኃን ጅምላ ግድያዎች፣ቀይሽብር፣ የአውሮፕላን ድብደባዎች ወዘተ በህወሓት ምክንያት የተፈፀሙ ናቸው›› የሚሉ
ወገኖች በጣም ብዙ ናቸው፡፡ብዙ ዋልጌዎች፣‹‹ደርግ ቀይ ሽብር ያወጀው ኢህአፓ ነጭ ሽብር በመጀመሩ ነው›› ብለው ይከራከራሉ፡፡ነገር
ግን እነዚህ አባባሎች በህፀፆች የታጨቁ ሸውራራ አመለካከት የወለዳቸው ናቸው፡፡ከሰኔ 21 ቀን 1966 ዓ.ም ጀምሮ እስከ
1983 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የተከሰቱት መልካአ ምድራዊ፣ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ቀውሶች በደርጋውያን የተፈፀሙ ናቸው፡፡
የዚህ ፅሑፍ መነሻ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ሲሆኑ ዓላማውም ድርግ ሃገር ያላሳደገው፣ተውልድ የገደለውና ሃገራችንን
የጦርነት አውድማ ያደረገው ወዶ ሳይሆን ተገድዶ ነው የሚባለው አስተሳሰብ መሰረት የሌለውና የደርግ ጭካኔና ፈላጭቆራጭነት ለማድበስበስ
የለመ መሆኑን በማስረጃ በማስደገፍ ፉርሽ ማድረግ ነው፡፡ደርግ ዓለም የመሰከረለት አምባገነን ነበር፤ የቄሳርን ለቄሳር ይሰጥ ዘንድ
ግድ ነው፡፡
ህወሓት ለምን የትጥቅ ትግል መረጠ?
በኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የተፃፈው ‹‹ትግላችን›› የተሰኘው መፅሓፍ እንደሚጠቁመው
ደርግ የተረገዘው ከሰኔ 19 ቀን 1966 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡በገፅ 153 ላይ ፣‹‹ከሰኔ 19 ቀን 1966 ዓ.ም ጀምሮ በአራተኛ
እግረኛ ክፍለጦር ስብሰባ አዳራሽ በአዲስ አበባ ከተማና በአከባቢው የሚገኙ የጦር ክፍል ተወካዮች በተሰበሰቡበት ጊዜ…›› ይላል፡፡
ትንሽ ወረድ ብሎ በገፅ 157 ደግሞ፣‹‹ድርጅታዊ ሥራችንንና ምርጫችንን አከናውነን ሰኔ 21 ቀን
1966 ዓ.ም በቀኑ የሃገሪቱ የዜና ማሰራጫ ሰዓት በራድዮ፣እንዲሁም በምሽቱ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ገፃችንንና የተሰበሰብንበትን ስፍራ
የሚያሳይ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ስእላዊ መግለጫ ሳይታከል አጠር ባለ አጃቢ መግለጫ የደርጉን ህልውና ለኢትዮጵያ ህዝብ አበሰርን፡፡››
በማለት ድርግ በይፋ የተመሰረተበትና ዘውዳዊው አገዛዝ ወሽመጡ የተመታበት ቀን ይነግረናል፡፡ከዛች ቀን ጀምሮ የአፃው ስራዓት እየፈራረሰ
የደርግ ስልጣን ደግሞ እየጠነከረ ቀጥሏል፡፡በዛች ቀን አምሳለ ሂትለሩ ደርግ በይፋ ተወልዷል፡፡የደርግ ልደት ግን ኮ/ሌ መንግስቱ
‹‹ለኢትዮጵያ ህዝብ አበሰርን›› እንዳለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ብስራት ሳይሆን ታላቅ መርዶ ነበር፡፡
በመቀጠልም ደርግ ሽዋሚና ሻሪ እየሆነ መምጣቱን በገፅ 176 ላይ፣‹‹ጠቅላይ ሚኒስተር እንዳልካቸው መኮንን… ሊያጠፉን
ስለሞኮሩ ሓምሌ 15 ቀን 1966 ዓ.ም ከሥልጣናቸው ወረደው ከመሰሎቻቸው… ጋር ተቀላቀሉ፡፡››በማለት ያስረግጥልናል፡፡‹‹ከመሰሎቻቸው
ጋር ተቀላቀሉ›› ማለት ከ60ዎቹ ጋር ታሰሩ ማለት ነው፡፡ስለሆነም ሐምሌ 15 ቀን 1966 ዓ.ም ደርግ መሾምና መሻር እንዲሁም
እንደፈለገው ማሰር የጀመረበት ቀን መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡ጃንሆይ ግን ‹‹ንጉስ አይከሰስ፣ሰማይ አይታረስ›› የሚባለው ከእርሳቸው
ጋር እኩል ያረጀው አባባል ተንተርሰው በማንቀላፋት ላይ ነበሩ፡፡ዳሩ ግን ግዛታቸውም በጥይት ታርሳለች፤እርሳቸውም መከሰስ ብቻም
ሳይሆን ግድያም ተፈፅሞባቸዋል፡፡
ፕሮፌሰር ባሕሩ ከላይ በተጠቀሰው መፅሐፋቸው ላይ የ66ቱ አብዮት ጠንሳሾች የደርግ አካሄድ ምን ሊመስል እንደሚችል
የታገሩት ትንቢት እንዲህ ፅፈዋል፤‹‹ ንጉሠ ነገሥቱ ከዙፋን ከመውረዱ ከሁለት ቀናት በፊት የወጣው ‹የሠፊው ሕዝብ ድምፅ› በወታደር
የሚመራ መንግሥት፣ የፈለገውን ያህል ቅን ልቦና ቢኖረው፣ ዞሮ ዞሮ አገሪቷን ባንድ አምባገነን መሪ መዳፍ ሥር ይጥላታል ሲል ትንቢታዊ
ትንተና አቅርቦ ነበር፡፡››(ገፅ 247)
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም
ዘውዳዊው ስርዓት ተገርስሶ በወታደራዊው አምባገነን መተካቱን የኢትዮጵያ ህዝብ መርዶ ሰማ፡፡ከዛም የደርግ አዋጆች መጉረፍ ቀጠሉ፡፡መስከረ
4 ቀን 1967 ዓ.ም ከአራት ኪሎ ግቢ የተጀመረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ስልፍ በደርግ ወታደሮች ተቋርጠዋል፡፡የተቃውሞ
ሰልፉ ተከትሎም በሰላማዊ ሰልፊ የሚደረግ ተቃውሞ የሚያግድ የአደጋ ጊዜ አዋጅ በደርግ ታወጀ…
የህይወት ተፈራ ‹‹Tower
in the sky›› የሚከተለውን ያስነብበናል፡
… On 16 September, 1974 University
students organized a demonstration that commenced from Arat Kilo campus. It was
going to be the litmus test for the Derg’s patience.
… All of a sudden, we heard shots when we
reached Berhanena Selam Printing press in Arat Kilo. There was total chaos…
… A few days after the protest rally, the
Derg declared a state of emergency prohibiting protest demonstrations and
strikes. It held union leaders and members of the armed forces in custody,
accusing them of calling out for Provisional Peoples’ Government, and killed
peasants in different provinces for demanding land. In October, it threw
teachers and others into jail, on charges of pushing for a Provisional Peoples’
Government. Five members of the armed forces were killed, and several wounded
in Harar. A number of people standing in front of the office of the workers’
union looking for a job were mercilessly shot dead.
The Derg’s motto, Ethiopia Tikdem
yaleminim dem – Ethiopia first without blookshed – became tainted with blood. (ገፅ
114-116)
ሃይላይ ሓድጉ በ‹‹ፅንዓት››
መፅሐፉ እንዳሰፈረው፣ ደርግ ሕዳር 12 ቀን 1967 ዓ.ም
ማንኛውም ሰው ‹ኢትዮጵያ ትቅደም› የሚለውን ዓላማ ለመፈፀም በመንግስት
ወይም በመንግስት በለስልጣን የሚወጡ አዋጆች፣ድንጋጌዎች፣ትእዛዞች እና ደሞቦች እንደይከበሩ፣በንግግር፣በፅሑፍ ወይም በማንኛውም መንገድ
በግልፅ ሲያነሳሳና ሲያደፋፈር ከተገኘ ከአንድ እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ከባድ የእስር ቅጣት ይቀጣል፡፡(ገፅ 37)
የሚል አዋጅ አውጥቶ ማንኛውም ሰላማዊ ተቃውሞ ተቀባይነት እንደሌለው አሳወቀ1፡፡
