| እቴጌጣይቱ ሆቴል |
ሆቴሉ በማሐል ፕያሳ(አራዳ) የሚገኝና በእቴጌ ጣይቱ እንደተመሰተ የሚነገርለት በኢትዮጵያ ቀዳሚው ሆቴል
ነው፡፡
የተለያዩ ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶችን በማቆያነት እንዲያገለግል ተስቦ የቋቋመው፣ የሃገራችን
አንጋፋና ታሪካዊ ሆቴል ከጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን አጠገብ ከሚገኘው የእሳት አደጋ ድርጅት ድንጋይ ወርውሮ ሊደርስበት በሚችል ርቀት
የሚገኝ ቢሆንም በጊዜ ደርሶ ከቃጠሎው ሊታደገው አልቻለም፡፡
ድርጅቱ የእሳት ቃጠሎው እንደተነሳ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ቢደወልለትም ከአንድ ሰዓት በኋላ
ደርሶ ሆቴሉ ብዙ ውድመት ከደረሰበት በኋላ ‹‹በቁጥጥር ስር›› እንዳዋለው ገልፀዋል፡፡
ይሁን እንጂ፣ድርጅቱ በደቂቃዎች ሳይሆን በሳዓቶች
እየዘገየ የሚደርስ በመሆኑ የአዲስ አበባ ኗሪዎች ሁሌም እንደ ተማረሩበት ነው፡፡
አዲስ አበባ በየዓመቱ የሰው ህይወትና በሚሊዮን የሚቆጠር ንብረት በእሳት አደጋ የሚወድምባት ከተማ ነች፡፡
ባለፈው
ዓመት(ታሕሳስ ወር 2006 ዓ.ም) መርካቶ አከባቢ በተለምዶ ጆንያ ተራ እየተባለ በሚጠራው ሰፈር የደረሰው የእሳት አደጋ በ32 ሰዎች ላይ
አደጋ እንዳደረሰ፤ 40 ሱቆች ሙሉ በሙሉ እንዳወመና አምስት መጋዝኖች ዶግ አመድ እንዳደረገ የሚታወስ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment