![]() |
| google pitures |
የታጋይ ገብሩ አስራት መፅሐፍ(ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ) አነበብኩት፡፡ይህ መፅሐፍ
አንብቤ እንደጨረስኩ በአሁኑ ሰዓት ህወሓት የሚባል ድርጅት አለመኖሩን ተገንዝብያለሁ፡፡የህወሓት ታሪክ ያከተመው በ1993 ዓ.ም
ነበር፡፡
ለዚሁ ድምዳሜ ያደረሱኝ ብዙ ምክንያቶች መደርደር እችላለሁ፡፡ለጊዜው ግን ሁለቱን ብቻ ለስቀምጥ፡፡
አንደኛው ምክንያት፣ የህወሓት ህገ ደምብ በ93 ዓ.ም ተሽሯል፡፡ተሻሽለዋል አላልኩም፤ ሙሉ በሙሉ ተሽሯል! ማን አፈረሰው? ቢባል፣ አሁን በስልጣን
ያለው ቡድን፡፡በስምምነት ሳይሆን በወታደራዊ እርምጃ!
‹‹የህወሓት ህገ ደምብ ውስብስብ ሁኔታውችንን በሚገባ ስለማያገናዝብ ቆሻሻ መጠራቀምያ ውስጥ
መጣል አለበት፤ ሠገራ ነው››(መለስ ዜናዊ ገፅ፡298)
‹‹ድርጅቱ ለአደጋ በተጋለጠበት ወቅት ሕገ ደምብ ብሎ ነገር የለም፤በእንዲህ ያለ የድርጅት
ቀውስ ወቅት አሳሳቢ የሚሆነው የድርጅቱ ህልውና እንጂ የሕገ ደምቡ መከበር አይደለም››(ስዩም መስፍን ገፅ፡308)
እነዚህ ሰዎች እያሉን ያሉት ‹‹በመፈንቅለ መንግስት(ኩዴታ) ስልጣን ለብቻችን ተቆጣጥረናል››
ነው፡፡ህገ ደምብ ከሌለ ድርጅት ብሎ ነገር የለም፡፡ምክንያቱም ምትግባበትም ሆነ የምትለያይበት መርሕ አይታወቅም፡፡እንደ ድርጅት
የምትመራበት ደምብ ከሌለ ማንኛውም ስልት ብትጠቀም ትክክል ነው፡፡ይህ ደሞ ማፍያ(ሽፍታ) እንጂ ድርጅት አይደለም፡፡አሁኑ ቡድን
የኸው ነው፡፡
ሁለተኛው ምክንያት፣ ህወሓት የታገለው ቤተ መንግስቱን የሚቆጣጠሩት ሰዎች ለመለወጥ ሳይሆን
ወታደራዊ ስርዓቱን በህዝባዊ ስርዓት ለመቀየር ነበር፡፡ነበር ባይሰበር፡፡ዛሬ ህዝባዊ የሚለው ቃል በተግባር የለም፤ በቃል ደረጃ
እማ ደርግም ይጠቀምበት ነበር፡፡
የአሁኑ ቡድን መነሻና መድረሻው ስልጣንና ስልጣን ብቻ ነው፡፡ስለ ህዝብ ቅንጣት ታህል ስሜት
የለውም፤ ስለ ሃገር የሚያገባው ነገር የለም…ስልጣንና ገንዘብ እስካተረፈባት ድረስ ኢትዮጵያ እንደለ ከመሸጥ ወደ ኋላ እንደማይል
በተግባር አስመስከሯል፡፡ዴሞክራሲ ብሎ ቀልድ አያውቅም፡፡ስለሃገርና ህዝቦቿ ደንታ የሌለው ቡድን በማንኛውም መለክያ ህወሓትን ሊወክል
አይችልም፡፡
ህወሓትን በመፈንቅለ መንግስት የደመሰሰው ቡድን የድህንነት፣የፖሊስና የወታደር መዋቅር ተጠቅሞ
ስልጣኑን አስጠብቋል፡፡ የእነ ተወልድ-ስዬ ቡድን ግን ህገ ደምቡን ብቻ ተከትለው የሃገር ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ለማስከበር ታግሏል፡፡የድርጅቱ
ህዝባዊነት እንዲቀጥል በነበራቸው አቋም ወታደራዊ እርምጃ እንደ አማራጭ ከመጠቀም ተቆጥበዋል፡፡
ገብሩ ይህን ያደረጉበት ምክንያት እንደሚከተለው አስቀምጦታል፡
‹‹ይህ አኪያሄዳችን የፖለቲካ ሥልጣንን ለመቆጣጠር
በማንኛውም መንገድ የኃይል የሚዛኑ ማስጠበቅ ያስፈልጋል የሚለውን የማኪያቬሊያዊ አስተሳሰብ ለሚከተሉ ወገኖች ገራ ገርና ተላላ ሊመስል
ይችላል፤ ሆኖም በኛ አመለካከት ሥልጣን ብናጣ እንኳን፣ ምርጫው በማያወላዳ ሁኔታ በዴሞክራሲና በአምባገነንነት መኻል ነበር፡፡››(ገፅ፡273)
ህወሓትን
አጥፍቶ ሲያበቃ የህወሓት 40ኛው የምሰረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ጋዜጠኞችና አርቲስቶችን ጋራ ወደ ደደቢት
ያመራው አሁን በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ኃይለ ቃል የተላበሱ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አስተናግዷል፡፡
ጋዜጠኛ
ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ ‹‹ያለተሰማ ጭኾትና ትግራይ ሄደን ትግራዮች ሳናይ መጣን›› የመሳሰሉ ፅሑፎቹን አካፍሎናል፡፡የህዝቡ ችጋርና
መከራ በምስል በማስደግፍ አስቃኝቶናል፡፡
ጋዜጠኛ
ጌጡ ተመስገን ደሞ ‹‹የገጠሩ ድህነት አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ኦ ትግራይ አሸናፊው መንግስት የት ሄደ? ያስብላል፡፡›› በማለት የትግራይ ህዝብ ያለበት ሁኔታ በአፅንኦት ገልፆታል፡፡
‹‹የታጋዮች ዓላማ የሚያረክስ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ እናንተን የማይመስሉ ባለሥልጣናት ሾማችሁብናል፡፡ ሕዝቡን ከታች እስከ ላይ እያማረሩ ነው፡፡ ትናንት የደማችሁለት ቅዱስ ዓላማ ዛሬ እየተበላሸና እየረከሰ ነው፡፡ አርሟቸው፡፡ እኛም ጦር ይዘን ከጎናችሁ እንቆማለን፤›› ያለው ደሞ
ደራሲ ጌታቸው በለጠ ነው፡፡
| ሠዓሊ እሸቱ ጥሩነህ ከተናገረው ( በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ) |
የጋዜጠኞቹና
አርቲስቶቹ አስተያየቶች ማጠንጠኛ ‹‹ህዝቡ ከመጠን በላይ ተጎድተዋል፤የገዢዎች ለውጥ እንጂ የስርዓት ለውጥ አገኘም፤እንደ ድሮው
በጭቆና ቀምበር ነው ያለው›› የሚል ነው፡፡እንግዲህ ከዚሁ አጭር ጉብኝት ይህን ያህል የከረሩ አሰተያየቶች ከተስተናገዱ የህወሓት
ለምድ ያደረገ ቡድን እንጂ ህወሓት የሚባል ድርጅት አለመኖሩን ያመለክታል፡፡
ለመግብያ
ያህል ይህ ካልኩ ዘንዳ ፀሐፊውን በጣም አክብሬ የመፅሐፉን ስነ መጎት አሜን ብዬ እንድቀበለው ያደረጉኝ ነጥቦችን ጠቅሼ ሐሳቤን
ልቋጭ፡፡
- ለዘመና እየተመላለሱ ሲያስጨንቁኝ የነሩ ጥያቄዎች መልሶልኛል፡፡የታጋዮች አደራ ለምን ተረሳ? የህዝቡ ውለታ ይህ ነበር ወይ፤ለምን አመድ አፋሽ ሆኖ ቀረ? የመልካም አስተዳደር እጦት፣የሙስና ቅቡልና ልማዳዊ አስራር መሆነ፣የሕግ የበላይነት ቀርቶ በግለ ሰቦች የበላይነት መተካት ወዘተ. ምንጫቸው ምን እንደሆነ ተረድቻለሁ፡፡
- ፀሐፊው ሌሎች ፖለቲከኞች እንደሚያደርጉት ራሱን እየካበ የተቀናቃኞቹን ስም በማጥፋት አልተጠመደም፡፡ድርጅቱ ከፈፀማቸው ታሪካዊ ስሕተቶች አምኖ ሳያቅማማ ድርሻውን ወስዷል፡፡‹‹እኛ አጥፍተናል›› እያለ ራሱንም ጭምር የሚተችና ከሰሕተቶቹ የተማረ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ሳይሆን አይቀርም፡፡
- 3. በጥልቅ ሙያዊ ትንተናውና በርትዓዊ ስነ አመክንዮው በጣም ተማርክያለሁ፡፡ዒላማቸውን ያልመቱ ምክንያቶች አላጋጠሙኝም ብል ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ይህን የመሰለ መፅሐፍ በማንበቤ ራሴን እንደ ዕድለኛ እቆጥረዋለሁ፡፡
4. ‹‹ደርግ
በ1980 ዓ.ም በሓውዜን የፈፀመው ደብዳብ መካድ ናዚዎች በአይሁዶች ላይ የፈፀሙት ዘግናኝ ጭፍጨፋ እንደ መካድ ይቆጠራል›› ማለቱ
የፀሐፊው ህዝባዊነት የበልጥ እንዲጎላ አድርጎታል፡፡የፈለገው ዓይነት ሰበብ ቢደረደር የሓውዜን ድብደባ ለማድበስበስም መሞከር ከጥቅሙ
ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ደርግ አንድ ጊዜ ብቻ አልነበረም የትግራይ ህዝብን በጄቶችና ሄሊኮፕረሮችን የደበደበው…ሳምረ…የጭላ…ቴምቤን…
5. ‹‹በ1977
ዓ.ም ባንድ ኤይድና ሌሎች ለጋሾች ለትግራይ ህዝብ የሰጠው እርዳታ ለጦርነተ መግዣ አውሎታል›› የሚለው የቢቢሲ ወሬ ውድቅ ያደረገበት
ስነ ሞጎት በተራ ቁጥር አራት ካለው ስነ አመክንዮ ጋራ በማቀናጀት ስመዝነው መፅሐፉ የተፃፈው ቅንጣት ታህል ፕሮፓጋንዳ ለማካሄድ
ያለመ አለመሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡የተቀናቃኞቹ ስም ለማጉደፍ ያለመ ቢሆን ኑሮ እንዚህ ሁለት ነጥቦችና ሌሎች ምስጢሮችን አጋንኖ ለማቅረብ
ይሞክር ነበር፡፡
6. በማጣቀሻዎች የተገነባ መፅሐፍ በመሆኑ ፀሐፊው ከምሩ ተዘጋጅቶና ሙሉ ጊዜውን
መስዋእት አድርጎ እንዳዘጋጀው ተገንዝብያለሁ፡፡አንድኛና ሁለተኛ የመረጃ ምንጮችን ተጠቅሞ ነው የፃፈውና ለዶክትሬት ድግሪ መመረቅያ
ያዘጋጀው ይመስላል፡፡
7. በተለይ
ግን በማጠቃለያው ላይ ስድስት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጡ ዋና ግቡ የሃገራችን ፈርጀ ብዙ ችግራች ከስረ መሰረታቸው ተቀርፈው
ማየት መሆኑን ተገንዝብያለሁ፡፡ዓላማው ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ተከብሮ፣በዴሞክራሲ የምትመራ የበለፀገች ሃገር እንድትሆን ድርሻውን
መወጣጥ ነውና ችግሮቹን በመዝርዘር ብቻ ሳይገታ በእርሱ እይታ መፍትሔ ይሆናሉ ያላቸውን ነጥቦችም ሳይጦቅም አላለፈም፡፡
እናም የእነዝያ ቅን የህዝብ ልጆች በፀሐፊው መንፈስ መኖራቸውን ታዝብያለሁ፡፡በሂስና ግለ ሂስ ታንፆ ለዚሁ የበቃ
እውነተኛ ህዝባዊ ታጋይ በመሆኑ ያለውን እንደለ ቁጭ አድርጎታል፡፡ከሌሎችም ይህን መሳይ መፃሕፍት እጠብቃለሁ…ከተወልደ፣አውዓሎም፣አረጋሽ፣አለም
ሰገድ፣ ቢተው…

No comments:
Post a Comment