ከሑዋኔ በአባዱላ ተሳፍሬ ወደ ዓዲ ሽሁ በመጓዝ ላይ ነኝ፡፡ ታክሲዋ መተንፈሻ የላትም…ጥቅ
ጥቅ ብላ ሞልታለች፡፡እኔ የተቀመጥኩት ምናልባት በኢትዮጵያ ብቻ ሰው የሚቀመጥባት፣ ከመዝግያው አጠገብ፣ ከጋቢና ወምበሮች በስተጀርባ
ካለቸው ትንሽ ክፍተት ነው፡፡ በጣም ትሞቃለች…ቂጥ ትለበልባለች ሞተሩ ያለው እዛው ሳይሆን አይቀርም፡፡
ከሹፌሩ ጀርባ ያሉ ሁለት ወምበሮች እንድ ዘመናይ ሴትዮ አምስት ዓመት ከሚሆናት ልጇ ጋር በቀኝ ግዛት ይዘዋቸዋል፡፡
ሴትዮዋ ልጇን አቅፋ ስታበቃ እግሮቿ እኔ ላይ ደርጋቸዋለች፡፡ህፃንዋ ሲረግጡት የሚያፏጭ ድምፅና ብልጭ ድርግ የሚል መብራት የሚያበራ
አሻንጉሊት ጫማ ተጨምታለች፡፡ በእነዝያ ጫማዎች ነው እኔን እየረገጠችኝ ያለቸው፡፡ሌሎቹ ወምበሮች ግን በሶስትና አራት ሰዎች ታጭቋል፡፡ለዛም
ነው ሴትዮዋን ዘመናይ ያልኳት…አንድም የናጠጠች በለሃበት አልያም በለስልጣን መሆን አለባት ብየ ስላሰብኩ፡፡