Saturday, August 31, 2013

‹‹ለምን ተለያየን? ብሄር መሰረት ያደረገ ፖለቲካ ተከተልን›› አብርሃ ደስታ



እወይ ፖለቲከኛ !!! እወይ ክህደታችሁ!!! እወይ አሌነታችሁ!!! ‹‹ኢትዮጵያ ወይም ሞት!››፣‹‹ኢትዮጵያ ትቅደም››፣ ‹‹ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም›› ወዘተ የሚሉ መፈክሮች ግን እንድንስማማ አስችለውናል፤ አይደል?‹‹የግል መብት እንጂ የብዱን መብት አያስፈልግም›› እያልከን ነው ወንድማችን? እሺ በናንተ(ኢትዮጵያ ግለሰቦች በውድም በግድም የሚታጨቁባት ትልቅ ጎተራ ነች ለምትሉ) አስተሳሰብ (አክራሪ አመለካከት) ኢህአዴግ ስልጣን ከመያዙ በፊትና ‹‹ብሄር መሰረት ያደረገ ፖለቲካ›› ከማቋቋሙ በፊት በኢትዮጵያ አለመግባባ ተፈጥሮም ተሰምቶም አያውቅም አይደል? ‹‹ነጭ ሽብር››ና ‹‹ቀይ ሽብር›› ኢትዮጵያችን የምሁራንና የወጣቶች ደሃ ያደረግዋት መቸ ነበር ወዳጄ?
ኢትዮጵያችን የጠርነት አውድማ፣ የደም ጅረት፣ የእርሰበርስ መጠላለፍና መጠፋፋት የነበረችው በኢህአዴግ ጊዜ ነው ያለህ ማን ነው?መስፍን ነጋሽ?ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም?ፕሮፌስር አል ማርያም?ዶክተር መራራ ጉዲና?እነዚህ ሰዎች መኢሶንና ኢህአፓ በሚገዳደሉበት ጊዜ፣ መኢሶኖች የደርግ ሰላዮች ሆነው ኢህአፓዎችን ሲያስጨፈጭፉ ምን ይሰሩ ነበር? ስለሰላም፣ስለአንድነት፣ ስለ  የአስተሳሰብ ብዙኋነት ይሰብኩ ነበር እንዳትለኝ፡፡ወንድም አብርሃ ስላሞካሹህና የፃፍከውን ሁሉ ስላስተጋቡልህ(share ስላደረጉልህ) ብቻ እውነትን አትስቀላት፡፡እነዚህ ሰዎች እነሱን ደግፈህ ሌሎችን በጭፍን ነቅፈህ ስትፅፍ ብቻ እንጂ ህሊናህን ያዘዘህ ስታደርግ ፊታቸው እንደሚያዞሩብህ የኢቲቪ ዜና አንባቢው ተመስገን ዘገየ መደብደቡ ትክክል አለመሆኑን ስትፅፍ ምን አሉህ? ስንቶቹ ይህን የግል አስተያየትህ ተቀበሉት፤ ለሌሎች አካፈሉልህ?ለምን?


ለመሆኑ በአፍ መፍቻ ቋንቋህ የማትፅፈው ለምንድንው?‹‹የናት ቋንቋህ ለመሰዳደብ ብቻ የሚጠቅም የወፍ ቋንቋ ነው›› ብለው የሰበኩህን አምነህ ስለተቀበልከው ነው፡፡በነሱ ባህልና ቋንቋ ተፈብርከህ ከላደክ በስተቀር ያንተ ማንነት እንደማይቀበሉት ታውቃለህና የፈለጉትን ለማድረግ ትገደዳለህ፡፡እነሱ እኮ በባህልህና በቋንቋህ እንድትኮራ አይፈልጉም፡፡እንዳውም በእነሱ የአፍ መፍቻ ቋንቋ መናገር ብቻ አይደለም የሚጠበቅብህ፤ ዘዬውና ለዛው ከበላሸኅባቸው መቀለጃና መሳለቂያ አሻንጉሊት እንደሚያደርጉህም በደምብ ታውቃለህ፡፡ያደክበት ማንነት እርግፍ አድርገህ በመተው እነሱን ለመምሰል የምትፍጨረጨረውም ለዛው ነው፡፡እስኪ በአፍ መፍቻ ቋንቋህን ፅፈህ ፌስቡክ ላይ የለጠፍካቸው ፅሑፎች መለስ ብለህ ተመልከታቸው፡፡የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዳንተው ካልሆነ በስተቀር ማንም አያይልህም፡፡

‹‹ቋንቋ መግባብያ ነው፤ስለዚህ እኔና እነርሱ በምንግባባበት ቋንቋ ብፅፍ ምን ችግር አለው?››ለትል ትችላለህ፡፡መግባባት ወይም መረዳዳት ሊኖር የሚችለው አንተም እነሱም ለመግባባት ፍቃደኞች ስትሆኑ ብቻ ነው፡፡ይህ የሚሆነው ደግሞ አንተ የነሱ ቋንቋ ማወቅ ስትችል ብቻ ነው፡፡እናም ግዴታው ባንተ ጫንቃ ብቻ እንዲኖር ነው የሚፈለገው፡፡ለምን?በዓል አሸንዳ በድምቀት በመከበሩ ሲያለቃቅሱ የከረሙት ለምን ይመስልሃል?ያንተ ባህል፣ቋንቋና እሴት ቀጣይነት እንዲኖረው ሰለማይፈልጉ ነው፡፡ለዚህም ነው ቋንቋን መሰረት ያደረገ የብዱን መብት እንዲሻር መቃወማቸውን እየገፉበት ያለው፡፡አንተም የነሱ ተቆርቋሪ ሁነህ አረፍከውና ‹‹ለምን ተለያየን?ብሄር መሰረት ያደረገ ፖለቲካ ስለተከተልን›› የሚለው ጭሆታቸውን እንደ ገደል ማሚቶ ታስተጋባለህ፡፡

ኢትዮጵያ ያለ ብሄር ብሄረሰቦችዋ ምንድነች?የትኞቹ ብሄሮች ጠፍተው በየትኛው ብሄር መጠራት አለባት ነው ይምትለው አብርሃ ደስታ?የትኞቹ ቋንቋዎች ጠፍተው በየትኛው ቋንቋ እንድንግባባ ነው የምትፈልገው? ተው እንጂ ወንድማችን፤ወዳጅ መስለህ ጠላት አትሁንብን፡፡አዲስ አበባ ውስጥ ከአስር በላይ መፂሔቶች እየታተሙ ለንባብ ይቀርባሉ፡፡ከነዚህ ውስጥ አንድ ብቻ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተም ሲሆን ሌሎቹ እንዳለ በአማርኛ ቋንቋ የሚታተሙ ናቸው፡፡ጋዜጦቹም ቢሆን ከእንግሊዘኛና አማርኛ ቋንቋዎች ውጪ እንዳይታተሙ የተከለከለ ይመስላል፡፡በአፋን ኦሮሞ ዜሮ፤በትግርኛ ዜሮ፤በሱማልኛ ዜሮ፤በአፋርኛ ዜሮ… በሌሎቹም ምንም!!!ለምን?‹‹የአንዲት ሃይማኖት፣አንዲት ቋንቋና አንዲት ኢትዮጵያ›› ውጤት ነው፡፡ብሄር ወይም ቋንቋ መሰርት ያደረገ ፖለቲካ እንዳኖር መቃወምህ ታድያ ከላይ የተጠቀሰው ነገር ለማስቀጠል መታገልህ መሆኑን እመን፡፡ደግሞ አታፍርም ‹‹I am not for sale›› ትላለህ፤ ከዚህ በላይ ምን ልትሆን ፈልገህ ነው አብርሽ?ባህልና ቋንቋውን ተገፎ ራቆቱን የቀረ ሰው ማንነት አለኝ ማለት አይችልም፡፡
 
አየህ ወንድም አብረሃ፤ኢህአዴግ ፍፁም ህዝባዊ ስለሆነ ሊነቀፍ አይገባውም እያልኩኝ አይደለም፤ የህዝቡን አደራ የበላ ከሃዲ ነው፡፡ ቃል መግባት እንጂ የተናገረውን ተግባራዊ የሚያደርግ መንግስት አለመሆኑን አውቃለሁ፡፡ እቅዶቹና መርሃ ግብሮቹ ወረቀት ከማድመቅ የዘለሉት ቢኖር ኢምንት ነው፡፡ባጭሩ ኢህአዴግን ከንተ በላይ ልሰድበውና ልቃወመው አልችልም፤አንተም ታውቃለህ፡፡የኢህአዴግ ችግሮች ከማንም በላይ እናንተ ታውቃላችሁ፡፡
ነገር ግን ኢህአዴግ ‹‹የብሄር ብሄረ ሰቦች መብት(እስከ መገንጠል) የከበር›› ማለቱ ነው እርሰበር እንዳንግባባ ያደረገን፤ ተለያይተን እንድናድግ ያስገደደን፤የተለያዩ ቋንቋዎች እንደንናገርና የተለያዩ ግን ተመሳሳይ አስተሳሰቦች እንድናራምድ ምክንያት የሆነን መለትህ አልቀበለውም፡፡‹‹በአንዲት ኢትዮጵያ ከአንድ ሃይማኖትና ከአንድ ቋንቋ በላይ አይፈቀድም›› ማለት እኮ አክራሪነት ነው፡፡ እኔ የምናገረው ቋንቋ ካልተናገርክ፤በኔ አምላክ ካላመንክና የኔ ትእዛዝ ካላከበር በስተቀር ኢትዮጵያዊ አይደለህም ማለት ምን ማለት ነው?
አንተም ‹‹የያ ትውልድ ነውጠኝነት›› ተጋባብህ ልበል? በጎውን ሁሉ አጥቁረህ፤ እውነታውን ሁሉ ሽምጥጥ አድርገህ መካዱን ካስተማሩህ በላይ የተካንክ ትመስላለህ፡፡አካፋን አካፋ ማለቱን ብትደፍር ምን አለበት? ተቃዋሚዎች ገዢ ፓርቲውን ሽምጥጥ አድርጋችሁ ስትክዱትና በጭፍን ስትቃወሙት እናንተን ለማጥፋት ከመትጋት ውጭ ምን ይሰራል ብላችሁ ታስባላችሁ? ‹‹ የሚያድርጉት አያውቁምና ይቅር በላቸው›› ብሎ እንዲፀልይላችሁ ነው ይምትፈልጉት?



Tuesday, August 27, 2013

ሁሉም 12ኛ ክፍል የላይበርያ ተማሪዎች የዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ መግበያ ፈተና ወደቁ


አጠቃላይ በዛታቸው 25,000 የሚጠጋ የላይበርያ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባው ፈተና አንዳቸውም ሳያልፉ መቀርታቸውን የቢቢሲ ድረገ ገፅ ዘግበዋል።
 ተማሪዎቹ የትምህርት ፍላጎት እንደሚያንሳቸውና የእንግሊዝኛ ቋንቋ መስርታዊ እውቀት እንደሌላቸው አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር ተናግረዋል።

  የላይበርያ ትምህርት ሚኒስተርዋ ወይዘሮ ዴቪድ ታርፓ አንድ ተፈታኝ እንኳን የዩኒቨርሲቲ መግበያ ፈተናውን ማለፍ አለመቻሉን ለማመን መቸገራቸውን አስታውቀዋል። << የተምህርት ተቋሞች ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው አውቃለሁ፤ይሁን እንጂ ፈተናውን የወሰዱ ሁሉም ተማሪዎች ወድቀዋል ሲባል ግን ያጠራጥራል።ዘር ለማጥፋት ይሚደረግ ጅምላ ጭፍጨፋ ሊባል ይችላል>> በማለት ነው ሁኔታውን የገለፀት።ስለሆነም የተማሪዎቹ የፈተና ውጤት ማየት እንደሚፈልጉም አስታውቀዋል፤ወይዘሮ ዴቪድ።

ሞሞዱ ጌትዋህ የተባሉ የዩኒቨርሲቲ ቃለ አቀባይ በቦኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በውሳኔው እንደሚፀናና ስሜታዊነት ውሳንያችው እንደማያስቀይራችው ተናግረዋል።

**************************************************************************************
<<ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም>> አሉ አበው።አሁን ጉዱን ሰምተናል፤መስከረም ሆይ ተሎ ነይ።

Saturday, August 24, 2013

የፎቶ ትንተና: ዶክተር ብርሃኑ ምን እየሰሩ ነው?




አንድ                                             

ዶክተሩ ቀላል ሰው አይደሉም፡፡ሃይለኛ ኢህአፓ ነበሩ ይባላል፤ምናልባትም የነጭ ሽብሩ ጠንሳሽ፡፡በከተሞች የተሰማሩ ኢህአፓዎች በቀይሽብር ተመትተውና እርሰበርሳቸው ተገዳድለው ድራሻቸው ሲጠፋ የአሲምባዎቹ ኢህአሠዎች ደግሞ በተዋጉበት ግንባር ሁሉ አሳፋሪ ሽንፈቶች ሲከናነቡ ቆይተው የመጨረሻ ዕጣ ፈንታቸው መበታተን ሆነ፡፡የነደክተር የስልጣን ጥማት ቅዠት ሁኖ ቀረ፡፡

ሁለት

ብሬ አሜሪካ ሄደው ደክትረው መጡና ከአሲምባ ያባረራቸው ኢህአዴግን በ97ቱ ሃገራዊ ምርጫ ለማሸነፍ ከቅንጅቶች ጋር ያለ አቻ ጋብቻ ተጋቡ፡፡የ‹‹ወደነበሩበት እንመልሳቸዋለን›› ፉከራ ከሽፎ በክብር ቃልቲ ወረዱ፡፡ኋላ በይቅርታም ይሁን በማስጠንቀቅያ ከእስርቤት ሲለቀቁ ወደ አሜሪካ አመለጡና ‹‹በተገኘው አጋጣሚና ስልት›› ተጠቅመው ኢህአዴግን ከስልጣኑ ለማባረር ጉንበት ሰባት የሚባል አክራሪ ቡድን አደራጅተው በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ሶስት

አሁን በምስሉ ላይ የሚታዩ ዶክተር ብርሃኑንን በደጋፊና ተቃዋሚ ምልከታ እንቃኛቸው፡፡

ደጋፊዎቻቸው፤

ዶክተር ብርሃኑ  ሊቅ ወይም ‹‹ጂኔስ›› ናቸው፡፡ኢህአዴግን ከበትረ ስልጣን አባርረው የአራት ኪሎው ቤተ መንግስት ለመቆጣጠር እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ ፅንሰ ሐሳቦችን በመተንተን ላይ ናቸው፡፡በላፕቶፓቸው ላይ አፍጥጠው በትኩረት እያነበቡና እስክርቢቶና ወረቅ ይዘው ማስታወሻ እየወሰዱ ነው፡፡የጭንቅላተቸው ሐሳቦችን የመተንተን ብቃት ከሮኬት ይፈጥናል፡፡ የማስታወስ ብቃታቸው ከ‹‹ሃረድ ዲስክ›› የሚበልጥ ሲሆን ‹‹በትሪልዬን ቴራ ባይቶች›› የሚለካ ነው፡፡አሁን ታድያ ይህን ሁሉ የመረጃ ክምር በከፍተኛ የሒሳብ ቀመር(ሃየር ማትማቲክስ) ተጠቅመው በማስላት ላይ ናቸው፡፡የኢሳት ጋዜጠኞች ኢቲቪን በቅርቡ ይቆጣጠራሉ፡፡የፌስቡክ ግንባር አዋጊዎችና ተዋጊዎች የወደፊትዋ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ይሆናሉ፡፡ያኔ ኢትዮጵያ ግሃንም መሆኗ ታሪክ ሁኖ ወደ ገነትነት ትቀየራለች፡፡

ተቃዋሚዎቻቸው፤

ዶክተር ብርሃኑ ምን ያህል ቢበላና ቢጠጣ ነው ይህን ያከለው?አሁን እኮ ለማያውቀው ተመልካች በላፕቶፑ የሚያነብ ይመስለዋል፤ጉረኛ፡፡እውነታው ግን ሌላ ነው፤ ዶክተሩ የወሲብ ፊልም በመመልከት ላይ ናቸው፡፡አራቱ ብርጭቆዎች ለምን ደረደራቸው?ላሜ ቦራውን አታልሎ በሰበሰበው ዶላር የተለያዩ ዓይነት ውድ መጠጦች እየተጎነጨባቸው ይሆናል፡፡አናናሱ በጥርሱ ሊቦጫጭቀው ነው እንዴ! ይህ ሰውየ ከመብላትና(ማባላት) ከመጠጣት(ማስጠጣት) ውጪ ሌላ አያውቅም ማለት ነው?ሆዳም! ሁለት መነፅሮች ምን ሊፈይዱለት ሰበሰባቸው?አንዱ ፊልም ሊያይበት፤ሌላኛው ማንነቱን ሊሸፍንበት፡፡መላጣው ያብረቀርቃል፤እንደመስታውት ፊት ያሳያል፡፡መላጣው ሲያልበው የሚያብስበት ጨርቅ ያኸውና፤ከማሃለኛው ብርጭቆ አጠገብ፡፡

ማስጠጣት


ማባላት

ዶክተር ብርሃኑ ከወሲብ ፊልም ሌላ ምን ሊመለከት ይችላል?የዓረቡ ፀደይ በኢትዮጵያም ተግባራዊ የሚሆንበት መንገድ ያሰላስላል፡፡ኢትዮጵያውያንም ልክ እንደ ግብፃውያን ጎራ ለይተው ሲጨፋጨፉ የሚያሳይ ፊልም የመላጣው ‹‹ስክሪን›› ከሳትላይቶች እየተቀበለ ያስተላልፍለታል፡፡ይህ አስደሳች ዜና በኢሳት ሲተላለፍ በቁሙ እየቃዠ ይመለከተዋል፡፡በዶክተሩ አስተሳሰብ በአሁኑ ጊዜ እርሰ በርሳቸው በመገዳደል ላይ ያሉ ግብፃውያን ሳይሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡
‹‹ግብፃውያን የኢትዮጵያውያን መከፋፈል ተጠቅመው የገንዘብ ፈሰስ በማድረግ የጉንበት ሰባት እቅዶችን ከግብ ለማድረስ ሌት ተቀን እየለፉ ነው›› ብሎ ይቃዣል፤ ዶክተር ብርሃኑ፡፡
ዶክተሩ ይቀጥላል፤ከራሱ ጋር አታካራ ይገጥማል፡፡‹‹በቃ ኢህአዴግ በህዝባዊ አመፅ ከስልጣን ተወግዶ ዶክተር ብርሃኑ የሚኒሊክ ቤተ መንግስት ይቆጣጠር እንጂ የህዳሴው ግድብ ጥንቅር ብሎ ይቀራል፡፡መለስ ያስጀመረው ግድብና የዕድገት ጎዳና ቢቻል ወደኋላ መቀልበስ እንጂ ስንዝር እንኳን ወደፊት ፈቀቅ ማለት የለበትም፡፡ይህ ከሆነማ የመለስ ስም ለዘልዓለም ሲወሳ ሊኖር ነው፡፡

ስለዚህ የህዳሴ ግድብና የኢትዮጵያ እድገት ግቡን መምታት የለበትም፤በጭራሽ!›› እያለ በተመስጦ ይብሰለሰላል፡፡እውነታው እሱ በሚያስበው መንገድ እየሄደ አለመሆኑን ሲገነዘብ ፊቱ የተጠበሰ ስጋ ይመስላል፡፡አንጀቱ እርር ኩምትር ይላል፤ለንዴቱ ማርከሻም ይጠጣል፤እየደጋገመ፡፡