Wednesday, August 24, 2016

ወልቃይት እንኳን ህዝቡ መሬቱም ትግራዋይ ነው




1.    መግብያ


የኢትዮጵያ ክልሎች አወቃቀር ሁሉንም ኢትዮጵያውያን አብረውና ተከባብረው እንዲኖሩ የሚያስችል ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡በተለያዩ ወቅቶች ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ ገዢዎች ለህዝቡ ምቾት ሳይሆን ለራሳቸው በሚመች መልኩ ሃገሪቱን ሲስተዳድሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡የአሁን መንግስትም ለራሱ በሚመቸው መልኩ እያስተዳደራት ይገኛል፡፡ሆኖም ግን ብዙ ሰዎች፣ በተለይም የጎንደር ተወላጆች በደርግና በአጼ ሃይለስላሴ ወደ ነበረው አከላለል ካልተመለስን እያሉ ይገኛሉ፡፡ይህ ጥያቅያቸው እንደ ድሮው ቋንቋው አማርኛ፣ ሰንደቅ ዓላማው ልሙጡ አረንጓዴ፣ ብጫ ቀይ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ግን ወልቃይትና ፀገዴም ወደ ጎንደር ካልተካለሉ እያሉ ይገኛሉ፡፡ጥያቄው የተነሳበት ቦታ፣ታሪካዊና ነባራዊ ሁኔታ ግን አሁን ካለው አከላለል አንፃር ወደ መግባባት ሳይሆን ወደ ንትርክ የሚያመራ ነው፡፡ወልቃይት በአማራ ክልል ስር ስለነበር ወደ አማራ ክልል ይመለስ የሚሉት ጥያቄ ቢዘሁ የሚያበቃ አይመስለኝም፡፡ ቤንሻንጉል ጉሙዝም ወደ አማራ ካልተካለለ ሊባል ይችላል፡፡ ሲጀመርም የጌቶች ትእዛዝ እንጂ የህዝብ ጥያቄ ነው ለማለት ይከብዳል፡፡

ሁለት እረኞች ራቅ ብሎ በሚገኘው አንድ ትልቅ ቋጥኝ ላይ የሆነ እንስሳ አሻግረው ያያሉ፡፡
አንዱ ፡-እዛጋ ያለው እንስሳ ምንድነው?