Friday, May 30, 2014

‹‹ችጋራም ጉምበት 20!››



ከአንድ ሳምንት በፊት ‹‹የኢንፎርሜሽንና ኮምኒኬሽን ሚኒስትር የጉንበት 20 ክብረ በዓልን በድንምቀት ለማክበር በአዲስ አበባ የመሰብሰብያ አዳራሽ የውይይት መድርክ አዘጋጅቷልና እንድትገኙ ተጋብዛችኋል›› የሚል የኢሜል መልእክት ደረሰኝ፡፡ትንሽ ወረድ ብሎ ደሞ ‹‹በውይይቱ መገኘት ግዴታ ነው…NB. Attendance is mandatory ›› የሚል በቀይ ቀለም ተፅፏል፡፡በመሆኑም ልክ የዛሬ ሳምንት (12/05/2014) በመሰብሰብያ አደራሹ ተገኘሁ፡፡የስራ ባለደረቦቼም ግዴታቸው ነበርና በስብሰባው ላይ ተገኝቷል፡፡

‹‹የውይይቱ›› ርእስ ‹‹ባለፉት የGTP ዓመታት ያገኘናቸውን ድሎች በማስጠበቅ ሁለንተናዊ አቅማችንን በቀጣይነት በመረባበር( በመረባረብ ለማለት ፈልገው ይመስለኛል) የህዳሴ ጉዟችንን ይበልጥ እናፋጥናለን!›› የሚል ነበር፡፡እኔ ግን የውይይት መድርክ ሳይሆን የዲስኩር መድርክ ነበር ባይ ነኝ፡፡አስገዳጅ ስብሰባና የውይይት መድርክ የሰማይና የምድር ያህል የተራራቁ ናቸው፡፡የውይይት መድርክ ህግና ስርዓት ኣለው፣ የውይይቱርእስና ጊዜ ይገድቡታል፣ በውይይቱ ርእስ(አጀንዳ) ላይ የግል ፍላጎት የሌለው የውይይት መሪ( ሞደሬቶር) ያስፈልጓል፡፡አወያይም ሆነ የሚወያዩ ሰዎች በፍቃደኝነት ብቻ ነው  በውይይት መድርኩ የሚገኙት፡፡ተሰብሳቢዎቹም መቆየት የሚችሉት የውይይቱ ሙቀትና ድምቀት እንዲሁም ርእሰ ጉዳዩ እስከመሰጣቸው ድረስ ብቻ ነው፡፡

Wednesday, May 28, 2014

ተጋሩ ሕበሩ ከይትድፈሩ፡ ህዝቢ ትግራይ ክሳብ መዓዝ እዩ መስሐቒ ጓህማማት ኮይኑ ክነብር?


ንእሽተይ ቆልዓ እናሃለኹ ‹‹ዕትሮ ዝሕከም… ዕትሮ ዝሕከም… ዕትሮ ዝሕገከም ደሎ?›› እናበሉ ዓዲ ንዓዲ ዝዘሩ ተጋሩ ነይሮም፡፡ሓንቲ በዓልተት ክሳደን ቅልቅል ኣቢለን ‹‹ክንደይ?›› ኢለን ይጥይቓ እሞ እቶም ሓካሚ ዕትሮ ድማ ‹‹ከም ነቃዕኹን›› ኢሎም መለሱለን ይብሃል፡፡እዛ ቀልዲ እዚኣ ኩሉ ስለዝፈልጣ ብዙሕ ተስሕቕ እያ ኢለ ኣይኮንኹን ሐዚ ዘልዐልኩዋ፡፡ካሊእ መኽንያት ኣለኒ፡፡

ኣብ አዲስ አበባ ብዙሓት ተጋሩ ከምዘለና ይፍለጥ፡፡አረ ንሕና ተጋሩ ዘይንረከበሉ ክፋል ዓለም ዘሎ ዘይመስሎም ብኹዕ ርእሶም መረሕቲ እውን ሓሊፎም እዮም፡፡ ሓደ ማዓልቲ እዩ ይብሉዋቶ ሓደምሁር ንሃፀይ ሃይለስላሴ ኣብ ክፍሊ ዓለም ኣንታርቲካ ሰብ ከም ዘይነበር ይነግሩዎም፡፡ እቶም ሃፀይ ግን ኣይተወሓጠሎምን ‹‹ሌላስ ይቅር ትግሬዎችም አይኖሩበትም?›› ኢሎም ሓተቱ ይብሃል፡፡ብሓፂሩ ‹‹ትግራዋይ ዘይብሉ ክፋል ዓለም የለን›› ንምባል ደልዮም እዮም፡፡እወ፣ ብኣሻሓት (ሐዚማ ብምልዮናት እውን ንኸውን ንኽእል) ዝንቑፀር ተጋሩ ኣብኩሎም ኩርናዓት ዓለም ናብራ ስደት እናመራሕና ከምእንርከብ ፀሓይ ዝወቕዖ ሓቂ እዩ፡፡

Monday, May 26, 2014

‹‹ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ››


ዛሬ ጥዋት ወደ ስራ ስገባ አንድ ‹‹ትልቅ›› ባለስጣን በመስራቤታችን አጥር ግቢ ኢክስክዩቲቭ መኪናውን አቁሞ በብዙ ነገሮች የታጨቀው ቦርሳውን አንጠልጥሎ ወደ ቢሮ ሲገባ ዘበኞቹ የሚሆኑት ሲያጡ ታዘብኩ፡፡ሁሉንም ዘበኞች ተስፈንጥረው ተነሱና ኮፍያዎቻችውን አውልቀው አንዳንዶቹ ሽበታም ፀጉራቸውን እያሻሹ ሌሎቹ ደሞ መላጣቸውን እያከኩ ጎንበስ ቀና እያሉ ምንም ሳይፈትሹት አሳለፉት፡፡እኔን ግን የማለብ ያህል ከላይ እስከ ታች ምጥጥ አድርገው ከመፈተሻቸውም በተጨማሪ ማስታወቅያየን እንዳሳያቸው ጠይቀውኛል፡፡የመስርያ ቤቱ የጥበቃ ህግ ይሁን ምን ባላውቅም ትላልቅ ባለስልጣናትና የውጭ ሃገር ዜጎች አይፈተሹም፡፡
በመስርያ ቤታችን የቻይናውያን ቁጥር ከኢትዮጵያውያን ጋር ሊመጣጠን ትንሽ ነው የቀረው፡፡ከቻይናውያን በተጨማሪ ግን የተለያዩ የውጭ ሃገር ዜጎችም ወደ መስርያ ቤታችን ይገባሉ ይወጣሉ፡፡ሆኖም ግን ማንም አይፈትሻቸውም፡፡አላስፈላጊ እንግልቶችን ጨምሮ እጅግ የጠበቀ ቁጥጥርና ፍተሻ የሚደረግባቸው የበታች ሰራተኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ናቸው፡፡ነገርየው አዲስ ክስተት ባይሆንም እንደ ዛሬ ግን በሁኔታው ተገርሜ አላውቅም ነበር፡፡ልክ ቢሮ እንደገባሁ በስራ ስለምጠመድ በቀላሉ እረሳዋለሁ ብየ ጠብቄ ነበር፤ አልተሳካልኛም፡፡የፈለገው ያህል ስራ ቢበዛብኝም ስለሁኔታው መብሰልሰሌን አላቆምኩም፡፡

Thursday, May 15, 2014

ኢህአዴግ በምርጫ 2007 በቀይ ካርድ መባረር አለበት



የአዲስ አበባ ንሮ
ግማሽ በልቶ ግማሽ ጦም አድሮ
ግማሽ ጠጥቶ ግማሽ ተጠምቶ
ግማሽ በርቶ ግማሽ ጠፍቶ
ግማሽ ተደስቶ ግማሽ ተማርሮ

ሰሞኑን ውሃ የለም፡፡በተለይም ከቀጨኔ መድሃኒአለም አንስቶ እስከ አራዳው ጊዮርጊስ ደረስ ውሃ ከጠፋ ቆይቷል፡፡ትናንት ደሞ የውሃው ችግር ለገሃር ወደ ሚገኘው መስራቤታችን ተከትሎን መጣና መፀዳጃ ቤቶች በጣም ከመቆሸሻቸው የተነሳ ገምተው ስራ መስራት ከልክለውን ውሏል፡፡

በምግብ ቤቶች ገብቶ ምግብ በልቶ ውሃ ማግኘት እርም ሆኗል፡፡በውሃ መጥፋት አሳብበው በፕላስቲክ የታሸገ ውሃ እንድትገዛ የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ከቀን ወደ ቀን እየተባባሱ በመምጣታቸው በካፌዎችና ሬስትራንቶች ውሃ በነፃ ማግኘት ታሪክ ወደ መሆን እየተቃረበ ነው፡፡
1.   የቤት ክራይ ዋጋ ከልክ በላይ መናር
2.   የትራንስፖርት እጥረት
3.   የውሃ ችግር
4.   የመብራት መቆራረጥ
5.   የንሮ ውድነት ናቸው፡፡

የእነዝያ ችግሮች ዛሬም መፍትሔ አልተበጀላቸውም፡፡ህዝቡ ዛሬም ቤት ወደ ስራ እንዲሁም ከስራ ወደ ቤት ሲመላለስ በየመንገዱ ብያንስ ሩብ ሰዓት ተሰልፎ መቆሙ ግዴታው ሆኗል፡፡በየጊዜው በውሃና በመብራት መቆራረጥ ንሮው እንደተቃወሰ ይገኛል፡፡የቤት ክራይ ንረትም ከቁጥጥራችን ከወጣ ቆይቷል፡፡ስራችን ሰርቶ ለቤት አከራዮች ማስረከብ ሆኗል፡፡የድሮው ርስተ ጉልታዊ ስርዓት መልኩን ቀይሮ እያስገበረን ነው፡፡

ከዚህ የምንረዳው ይህ መንግስት ስራውን መስራት እንዳልቻለ ነው፡፡የህዝብ ችግሮችን ለመፍታት ፍላጎትም ሆነ ቁርጠኝነት እንደሌለው ነው የምንረዳው፡፡በመሆኑም ይህ መንግስት ከስልጣን መባረር አለበት፡፡የኢህአዴግ ቀልዶችና ተረት ተረቶች ለዓመታት ሰምተን ሰልችቶናል፡፡ነገረ ስራው ሁሉ ‹‹አበበ በሶ በላ›› ሆኗል፡፡ወሬው ‹‹አበበ በሶ በላ›› ነው፣ስራውም ‹‹አበበ በሶ በላ›› ነው፡፡እናም ይብቃው፡፡ከዚህ በላይ መታገስ አንችልም፡፡

ኢህአዴግን እንዴት ከስልጣን እናባርረው?

Monday, May 12, 2014

‹‹ኣይሃብኻ፣ ትኩስ ግዓት ኣብኢድኻ››



ኣብ መቐለ እዮም ተፋሊጦም፡፡ ንሱ ኣብ መምህራን ኮለጅ ተማሃራይ እንተሎ ንሳ ድማ ናይ ጥዕና ጣብያ ተማሃሪት ነይራ፣ ደቂ ሓደ ወረዳ ስለዝኾኑ ወርሓዊ ፀበል ሓቢሮም ይሰትዩ ነይሮም፡፡ስልጣነኦም ወዲኦም ምስ ተመረቑ ክልቲኦም ኣብ ወረዳ ራያ ዓዘቦ በቢሞያኦም ስራሕ ተመዲቦም፡፡እቶም ደቂ ዓዶም ዝኾኑ መሓዙቶምን ዓፅመ ስጋ ቤተ ሰቦምን ኣብቶም ክልተ ወራዙት ዝነበረ ንንሕድድኻ ብፍቕሪ ምጥምማትን ምድልላይን ብምዕዛብ ብሓዳር ንክጣመሩ ይደፋፍእዎም ነይሮም፡፡ውሽጦም እናደለየ ብዕንይንይ ተግባራዊ ከይገበሩዎ ፀኒሖም፡፡

መምህር ድያቆን ካሕሳይ ታደለን ‹‹ሲስተር›› ጊደተ ጣሰውን ይብሃሉ፡፡እቲ በብገፆም ዝሓልምዎ ተማሂሮም ናብራኦምን ናብራ ስድራኦምን ምልዋጥ እዩ ነይሩ፡፡ክልቲኦም ናብራ ንምሽናፍ ዘይወረድዎ ቁልቑለት የዘይደየብዎ ዓቐበት የለን፡፡ንምልዋጥ ዝተሃንጠው ሰባት ኩሉሻዕ ብዛዕባ ፅባሕ እምብር ብዛዕባ ትማልን ሎምን ብዙሕ ኣየስተባህሉን፡፡ብስሩ እውን መብዛሕቲኦም ደቂ ሰባት ‹‹ትማሊ ኣብ ምንታይ ኹነታት ነይረ፣ሎሚ ኸ ከመይ ኣለኹ፣ ካብ ትማልን ሎምን ብምብጋስ ንፅባሕ ክህልወኒ ዘለዎ ስብእና እንታይ ክኸውን ኣለዎ?›› ኢሎም ኣይኮኑን ንባዕሎም ዝሓቱ፡፡ ባዕልኻ ንባዕልኻ ምውድዳር ድኣ ዓብዪ ፀጋ እንድዩ፡፡ኩሉሻዕ ንርእሶም ምስ ካልኦት ሰባት የነፃፅሩን የወዳድሩን፡፡ምስ ክንደይ ቢልዮናት ተወዳዲርካ ክዝለቕ? እቲ ኣብ ኢዶም ዘሎ ውህብቶ ካልኦት ኣይተዓደልዎን፤ ይኹን እምበር ብዙሕ ኣይግደስሉን፡፡እቲ ካልኦት ዝተዓደልዎ ድማ ኣብ ኢዶም የለን፤ ንዙይን ወድ ዙይን ንምርኻብ እዮም እምብኣር ድቃስ ስኢኖም ዝሓድሩን ዝንብሩን፡፡

Saturday, May 3, 2014

ነገረ ኢትዮጵያውያን፡ ‹‹…አበበ በሶ በላ…ጫላ ጩቤ ጨበጠ…››


ይህን ፅሑፍ የሚያንብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሶ በልቶ ብያውቅም ባያውቅም፣ ጩቤ ቢጨብጥም ባይጨብጥም ‹‹አበበ በሶ በላ››ና ‹‹ጫላ ጩቤ ጨበጠ››ን መቼም የሚረሳቸው አይመስለኝም…ልክ እንደ እጆቹ ጣት ማንኛውም ነገር ባከናወነ ቁጥር የሚያስታውሳቸው ይመስለኛል፡፡በተለይ ሲበላ እነዚህ አረፍተ ነገሮች ሳያስታውሳቸው አይቀርም…ቁርጥ ሲበላ ጩቤ…ሌላ ነገር ሲመገብ ደሞ በሶ፡፡ምክንያቱ ደሞ አማርኛ የተማረ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ...አእምሮው ምንም እንዳልተፃፈበት ነጭ ወረቀት ንፁሕ እያለ ነበረና የተቀረፁበት፡፡
በአንደኛ ክፍል የአማርኛ ክፍለ ጊዜ ጮሕ ብሎ ‹‹…አበበ…በሶ…በላ…ጫላ…ጩቤ…ጨበጠ…›› እያለ እንዲያስተምር ታዞ የሚያውቅ ካለማ ከስጋና ደሙ ጋር ሳይዋሃዱበት አይቀሩም፡፡ይሆነው ሆኖ ግን ሁላችንም የእነዚህ አረፍተ ነገሮች ዘመን አሽሬ ትውስታዎች አሉን ብቻ ሳይሆን ከእለት ተእለት ንሯችን ጋራ የተሳሰሩ ሆኗል፡፡በእንዱ ጫፍ በሶ በሊታ አበበዎች ለመብላት አሰፍስፈው ይጠባበቃሉ…በሶ ይበላሉ…በሶ በጥብጠው ይጠጣሉ፡፡በሌላኛው ጫፍ ደሞ ጩቤ የጨበጡ ጫላዎች ጩቤ ለመርገጥና ለማስረገጥ ሁሌም በተጠንቀቅ ቆሞው ይኖራሉ፡፡እናም በአጠቃላይ ፊደል ቀመስ ኢትዮጵያውያንን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡

Thursday, May 1, 2014

Historical surgeries: beautify the disfigured and disfigure the others




There has never been a flawless Ethiopian ruler. As a matter of fact, all were formerly outlaws and came to power by forcefully subduing and/or killing their opponents mercilessly. Menelik was among the cruelest ones that no words can express the crimes he committed against Ethiopians. He was known to indiscriminately cut off breasts and limbs of those he succeeded to subdue. Menelik not only amputated helpless Ethiopians but also sold Ethiopia piece by piece to France and Italy. Today’s Djibouti and Eritrea are monumental witnesses of his salesmanship.

Thanks to historical surgeries of his disciples though; the devils incarnate in action is now portrayed as a saintly hero of all time…nicknamed as “Emeye” …an adorable mom. The surgeries were insanely monotonous that went on for centuries and still are underway to this day. They were and still are unnaturally difficult since they had to create a new Menelik that absolutely denies his disfigured personality and demonic history. The fact that he happily handed over and signed Eritrea to Italy and Djibouti to France for few rifles must be awarded to his diplomatic mastery. The fact that he mutilated innocent Ethiopians of all age groups and genders must be amounted to “holy wars” that meant to expand Ethiopia’s territory. His totally reductionist campaigns that meant to rebuild Ethiopia of purely homogeneous ethnicity, history, religion, language and culture must be considered as angelic crusades that meant to unify Ethiopia. To affect these, songs of all genres have been sung, movies and theaters have been done…media outlets of all kinds have been dedicated to praise his newly personified self for centuries now.