Friday, April 22, 2016

የእኛ ሃገር ጉድ አይልቅም!!!


ዛሬ ጥዋት ፋና ብሮድካስቲንግ የዘገበው አስገራሚ ዜና ነው፡፡ሰላም ሐጎስና ሰላም ደሞዜ የተባሉ ታማሚዎች ለህክምና ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ይመጣሉ፡፡ሰላም ሐጎስ የሃሞት ጠጠር ሕመምተኛ ስትሆን የቀዶ ሕክምና ቀጠሮዋ ደርሶ ወደ ሆስፒታሉ ታመራለች፡፡ሰላም ደሞዜም የቀዶ ሕክምና ቀጠሮ ነበራት፣ የእንቅርት እጢ ለማስወጣት፡፡

የሆነው ግን እጅግ የሚያሰደነግጥ ነው፡፡ሰላም ደሞዜ የእንቅርት(የአንገት እጢ) ቀዶ ጥገና ብቻ ሊደረግላት ሲገባ የሃሞቷም ጭምር ተቀደደች፡፡ከኤንስቴዥው ስትነቃ ጨኾች፤ የታመምኩት እንቅርቴ ሆኖ ሳለ ሆዴ ለምን ቀደዳችሁኝ ብላም ጠየቀች፡፡ነርሶቹ ‹‹ችግር የለውም ተረጋጊ፤ እንዳውም ተጨማሪ ቀዶ ጥገና በነፃ አድርገንልሻል›› አሏት፡፡ባትስማማም ሰሚ አላገኘችም፡፡

ሰላም ሐጎስ በበኩሏ እንደጠበቀችው የእንቅርት እጢ ለማስወጣት የሚደረገው ቀዶ ጥገና ሳይሆን የሃሞት ጠጠር ሊወጣላት መሆኑን ተነገራት፡፡አይደረግም አለች፡፡አራጆቹ አልተበገሩም፣ በሐይል ሊቀዷት ተዘጋጁ፡፡ እርይታዋን አቀለጠቸውና ወጣች፡፡

ይህን በተመለከተ የሐኪሞቹ ተቆጣጣሪ ማነጋገር እንደሚፈልጉ ተናገሩ፡፡ አርፋችሁ ተቀመጡ የሚል መልስ ተሰጣቸው፡፡የፋና ጋዜጠኛ እንደዘገበው ከሆነ የዘውዲቱ ሆስፒታል መዲካል ዳይረክተርም ተፈልጎ ሊገኝ አልቻለም፤ ስብሰባ ላይ ናቸው በሚል ሰበብ፡፡

ይህ ወሬ፣ የሙያ ስነምግባርና የአካዳሚክ ብቃት ሳይኖራቸው በፎርጅድ ወረቀት ሰው የሚያርዱ ‹‹ሓኪም›› ተብየዎችን ይባስ እንድፈራቸው አደረገኝ፡፡ኧረ እንዳውም ሐኪም የሚሉት ሁሉ እንድጠራጠር አድርጎኛል፡፡

ለምን ቢባል እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ክስተቶች መደጋገማቸው ስለበዛ፡፡የታመመው እግሩ ሊቆረጥ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ያመራው ታካሚ ጤነኛው እግሩ መቆረጡን አስታውሳለሁ፡፡

Monday, April 18, 2016

ብዙ የተወራላቸው የኢትዮጵያ የሃገር የመከላከያ ሰራዊትና የድህንነት ተቋማት የት ገቡ?



የትግራይ ህዝብ ሲተርት ‹‹ጨጓርያ ከልብስ ኣሎ እናበልኻዮ ይመውት›› ይላል፡፡ፀጉራም ውሻ አለ እያሉት ይሞታል ማለት ነው፡፡ፀጉራም ውሻ መታመሙንና ምንኛ እንደከሳ ማወቁ አዳጋች ነው፤ ለተመልካቹ ሁሌም ገዝፎና ወፍሮ ስለየሚታየው፡፡እናም ሲሞት ድንገት የሞተ ያህል ምን ነካው? ያስብላል፡፡የሃገራችን መከላከያ ሰራዊት በተለያዩ የአፍሪካ ሃገሮች ስኬታማ የሚባሉ የሰላም ማስከበር ስራዎች በማከናወኑ በተደጋጋሚ ሲወደስና ሲሞገስ ይስተዋላል፡፡

በአሁኑ ሰዓት እንኳን ሁለቱም ሱዳኖች ባፋጠጠችው በአብዬ ግዛት ስላም በማስከበር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡በሃገረ ሶማልያም አልሻባብን እየተፋለመ እንደሚገኝ የሚታወስ ነው፡፡በቴክኖሎጂ ዘርፍም ከፍተኛ የሆኑ እምርታዎች በማስመዝገብ ላይ መሆኑን በመንግስት ሚድያዎች ተዘግቧል፡፡ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የሃገር መከላከያው ባዘጋጀው ዓውደ ርእይ ሰው አልባ በራሪ አካላት (ድሮንስ) እስከ ማምረት እንደ ደረሰ ተነግሮን ነበር፡፡

ሌላው የሃገር ድህንነት ተቋሙ በአወቃቀርም ሆነ በቴክኖሎጂ አጠቃቀሙ የተራቀቀ በመሆኑ የሃገራችን ሰላምና መረጋጋት ማረጋገጡን ሲለፈፍ ነበር፡፡ኬንያ የአልሻባብ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ለማስተናገድ ስትገደድ፣ ዩጋንዳና ጁብቲም የጥቃቱ ሰለባ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት ጥቃት ያልደረሰባት የድህንነትና የመከላከያ ሃይላችን አስተማማኝ ስለሆነ ነው የሚሉ ክርክሮች መስማትም አዲስ አይደለም፡፡

በቅርቡ ሙርሌ የተባሉ የደቡብ ሱዳን ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ውስጥ በሚገኙ የኑዌር ተወላጆች ያደረሱት ጥቃትና አፈናን ጨምሮ በሃገራችን የተሰነዘሩት ተደጋጋሚ ጥቃቶች ስንመለከት ግን እውነታው ሌላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡በኤርትራ አዋሳኝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሻዕብያ መንግስትና ኤርትራ በመሸጉ አማፂ ቡድኖች በተደጋጋሚ ይታፈናሉ ይገደላሉ፡፡

በሃገር ውስጥም ግጭት በተከሰተ ቁጥር በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት ማለፉንና ደም መፍሰሱ አልቀረም፡፡ፖሊስ፣ መከላከያና ድህንነት ዘመናዊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት ማክሸፍ፣ ግጭቶቹ ከተከሰቱም የሰው ህይወትና ንብረት ሳይወድም በቀላሉ መቆጣጠር ሲገባቸው በተደጋጋሚ ህይወትና ንብረት ሲወድም ይስተዋላል፡፡እናም እነዚህ ተቋማት የተሸከሙት ክብርና ዝና ከልሏዋቸው አሉ ብለን ስንኩራራ አሸልበው እንዳይሆን ያሰጋል፡፡የስጋቴ ምንጭ የሚከተሉት ናቸውና አንድ በአንድ እንያቸው፡፡

የአየር ክልላችን ክፍተት ያጋለጡ ክስተቶች