Sunday, December 21, 2014

‹‹ቤኒሻንጉል ጉምዝ ከኢትዮጵያ ብትገነጠል የህዳሴው ግድብ ለማን ይሆናል?››


GERD

ከሁለት ሳምንታት በፊት፣ በመስርያ ቤታችን ውስጥ በሚገኘው ክበብ ምሳ ለመብላት ከጓደኞቼ(የስራ ባለደረቦቼ) ጋር ተሰይሜያለሁ፡፡በመሐል አንዱ ጓደኛችን ‹‹ቤኒሻንጉል ጉምዝ ከኢትዮጵያ ብትገነጠል የህዳሴው ግድብ ለማን ይሆናል?›› የሚል ድንገተኛ ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ይህን መሳይ ጥያቄ እጠየቃለሁ የሚል ግምት ኖሮኝ አያውቅም፤ ጭራሽም አላሰብኩበትምና አግራሞትና ድንጋጤ ፈጥሮብኛል፡፡

በመጀመርያ፣ የህዳሴው ግድብ ያረፈበት ቦታ የአማራ ክልል ግዛት ነው ብለን ለራሳችን እናስቀረዋለን፤ የሚል መልስ ሰጠኋቸው፡፡ይህ መልስ ሊያሳምናቸው ስላልቻለ ግን ‹‹ቤኒሻንጉል ጉምዝ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል አንፈቅድላትም››  ለማለት አሰበኩኝና በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 39 ቁጥር አንድ፣ የሰፈረው ‹‹የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት ያለቅድመ ሁኔታ እስከ መገንጠል ድረስ›› የሚፈቅድ መሆኑን ትዝ ስላለኝ ይህን ትቼ የሚከተለውን መልስ ሰጠኋቸው፡፡

‹‹ሲጀመር ከአሁን በኋላ ከኢትዮጵያ የሚገነጠል ክልል የሚኖር አይመስለኝም፡፡የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የግድ ነፃነቴን ይሻለኛል ካለች ግን፣ አንድም ህዳሴው ግድብ ላረፈበት ቦታ በሊዝ መልክ ለኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ማከራየት ይጠበቅባታል፤ አልያም ግን የግድቡን የአዋጪነት ጥናት፣ለዲዛይን፣ ለግምባት የወጣበት ወጪ እንዲሁም ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ ለዘመናት የሚያመነጨውን የኤልክትሪክ ሐይል ዋጋ መክፈል ይጠበቅባታል›› አልኳቸው፡፡ሆኖም ግን፣ አሁንም መልሱ አጥጋቢ አልነበረም፤ ለእኔም ለነርሱም፡፡ምክንያቱም፣ የህዳሴው ግድብ ከምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳው ይለቅ ሃገራዊ ቅርስነቱና የኢትዮጵያውያን አርማነቱ በእጅጉ የሚልቅ ነውና፡፡

ዞሮ ዞሮ ግን፣ የምሳ ሰዓት እረፍቱ አልቆ ወደ ስራ መመለስ ስለነበረብን ጥያቄው በእንጥልጥል ቀረ፡፡ከዛ በኋላም፣ ለአንድ ሳምንት ያህል ትዝ አላለኝም ነበር፡፡ባለፈው ሳምንት የገብሩ አስራት መፅሐፍ(ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ) ገዝቼ ማንበብ ከጀመርኩ ወዲህ ግን ጥያቄው በህሊናየ እየተመላለሰ እረፍት ነሳኝ፡፡ገዢው መደብ ኢህአዴግ፣ በስልጣን ለመቆየት የሚያስችለው እስከሆነ ድረስ ይቅርና ለቤኒሻንጉል ጉምዝ(እንዲሁም ህዳሴው ግድብ) ኢትዮጵያም እንደ ሃገር አስይዞ ቁማር አለመጫወቱም ማረጋገጫ ያለን አይመስለኝም፡፡በተለይ የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ሲነሳማ ጨርሶ ያልጠገገው ጠባሳችን እያመረቀዘ ውስጥ ውስጡን የሚለበልብ የእግር እሳት ሆኖብናልና በሃገራችን ሉዓላዊነት ለመተማመን እጅግ አዳጋች ነው፡፡

ኤርትራ ከኢትዮጵያ የተገነጠለችበት ዋናው ምክንያት ጣልያንና የዓረብ ሃገሮች ኢትዮጵያን በማዳከም በቁጥጥራቸው አስገብተው ለመግዛት ከነበራቸው ከፍተኛ ፍላጎት ቢሆንም ሻዕብያና ህወሓት ውጥኑ በማስፈፀሙ በኩል ወደር የለሽ ሚና ተጫውቷል፡፡ህወሓት፣ በሻዕብያ አስራፂነት ‹‹የኤርትራ ጥያቄ የቀኝ ግዛት ጥያቄ ነው፤ መፍትሔውም ነፃነት ነው›› የሚል አቋም ወስዶና በድርጅቱ የአቋም መግለጫ አስፍሮ ለተግባራዊነቱም ‹‹የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረ ሰቦችና ህዝቦች መብት ያለቅድመ ሁኔታ እስከ መገንጠል ድረስ የሚያጠቃልል ነው›› ብሎ ሲያውጅ በሻዕብያ በኩል የቀረበለት ኢትዮጵያን የመከፋፈልና የማዳከም ሚና መጫወቱን ነበር፡፡

ሁለቱም የቀድሞ አማፅያን ድርጅቶች ተቀናቃኞቻቸውን በጦርነት በማምበርከክ ለመንበረ ንግስና ሲበቁምና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትገነጠል ዓሰብና ቀይ ባሕር ወደቦቻችንን ጠቅልላ ስትሄድ ያለ ባሕር በር መቅረታችን ይታወሳል፡፡

የኤርትራና ኤርትራውያን ጉዳይ ከእንግዲህ ወዲህ ያለቀለት ይመስላል፡፡የህወሓት መሪዎች ዛሬም ‹‹ኤትራውያንን እንጂ የኤርትራን መሬት እንደማይፈልጉ›› ይናገራሉ፡፡ይህ አቋማቸው አደገኛ የሚሆነው ግን ‹‹እኛ የምንፈልገው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ህዝብ እንጂ የቤኒሻንጉል መሬት አንፈልግም›› ያሉ እንደሆነ ነው፡፡ምክንያቱም፣ ህዳሴው ግድባችን በቤኒሻንጉል መሬት ነውና የሚገኘው፡፡

ራሱን የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ (ቤሕነን) የተባለው ዓማፂ ቡድን ደሞ ቤኒሳንጉል ጉምዝን የማስገንጠል ዓላማ አንግቦ የትጥቅ ትግል ከጀመረ 18 ዓመት ገደማ ሆኖታል፡፡ሆኖም ግን አልፎ አልፎ ከሚያደርሳቸው የሽምቅ ጥቃቶች ውጪ ጠንካራ እንቅስቃሴ አከናውኖ አያውቅም፡፡እንዳውም ከሁለት ዓመታት በፊት ይኸው ዓማጺ ቡድን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር አርቀሰላም አውርዶ ትጥቁን ፈትተዋል የሚል አስደሳች ዜና አንብቤ ነበር፡፡አሁን አሁን ግን፣ የህዳሴው ግድብ እየተፋጠነ ባለበት ወቅት ይህን ዓማጺ ቡድን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ብዙ አስጊ ክስተቶች ብቅ ብቅ እያሉ ይገኛሉ፡፡

የመጀመርያው አስጊ ሁኔታ የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች መከፋፈል ነው፡፡እንደሚታወቀው፣ ዶክተር ሪክ ማቻርና ፕረዚደንት ሳልቫ ኪር ጎሳ ለይተው ጦር ከተማዘዙ ዓመታት አስቆጥረዋል፡፡ኤርትራ፣ዩጓንዳና ግብፅ የሳልቫ ኪር ደጋፊዎች ናቸው ይባላል፡፡በተለይ ዩጓንዳ የሳልቫ ኪርን አገዛዝ በሪክ ማቻር ይደርስበት ከነበረው ሽንፈት በመታደግ የማይተካ ሚና ተጫውታለች፡፡ወታደሮችዋን በመላክ ሪክ ማቻርን ታድጋቸዋለች፡፡

ሪፖርተ ጋዜጣ ደሞ ‹‹ከግብፅ ጋር አንዳንድ ወታደራዊ ስምምነት ሲያደርጉ የሚስተዋሉት ፕሬዚዳንት ሳል ቫኪር ኢትዮጵያ / ማቻርን ውስጥ ለውስጥ ትደገፋለች የሚል ሥጋት ያላቸው ይመስላል፡፡ ቀደም ሲል የመንግሥታቸው ማስታወቂያ ሚኒስትር ለዓለም አቀፍ ሚዲያ ይህንን በግላጭ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡›› በማለት ግብፅ ሳልቫ ኪርን እንደምትደግፍ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡በተጨማሪ ግን የደቡብ ሱዳኑ ቀውስ የኤርትራ መንግስት እጅም ሳይኖርበት አይቀርም፡፡
የኤርትራ መንግስት በደቡብ ሱዳን ቀውስ ላይ ቤንዚን ከማርከፍከፍ አልፎ የቤሕነን ታጣቂዎችን በማሰልጠንና በማስታጠቅም ገፍቶበታል፡፡ሪፖርተር ‹‹በኤርትራ መንግሥት ድጋፍ ኤርትራ ውስጥ የተለያዩ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሥልጠናዎችን በመውሰድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማቀድና በመዘጋጀት፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ለመገንጠል የሽብርተኝነት ድርጊት ፈጽመዋል በሚል በተጠረጠሩ አሥር የክልሉ ነዋሪዎች ላይ ታኅሳስ 7 ቀን 2007 .. ክስ ተመሠረተ፡፡›› በማለት እንደዘገበው ከሆነ ሻዕብያ የህዳሴው ግድብ ግንባታን ለማደናቀፍ የቻለውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል፡፡

በተጨማሪ ግን ኢትዮጵያና ግብፅ በህዳሴው ግድብ ላይ ሲያድርጉት የነበረው ውይይትስምምነት ላይ ሳይደርሱ ማቋረጣቸውን ወርልድ ቡሉተን የተባለ ድረ ገፅ በቅርቡ ይፋ አድርጓል፡፡ይህ ማለት ደሞ፣ ግብፅ በሻዕብያ አማካኝነት ቤሕነን ታጣቂዎችን ማሰልጠንና ማስታጠቋ አይቀሬ ነው ማለት ነው፡፡በተለይ ግን በቀድሞው የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር(የአሁኑ አምባሳደር) ስዩም መስፍን  አደራዳሪነት ለአንድ ዓመት ሙሉ ሲካሄድ የነበረው ፕረዚደንት ሳልቫ ኪርና ዶክተር ሪክ ማቻርን የማስታረቁ ጥረት ውጤት አልባ መሆኑን ሲታይ ሁኔታው ውስብስብ ያደርጓል፡፡

ሪፖርተር የአምባሳደር ስዩም ተስፋ እንደሚከተለው ዘግቦታል ‹‹አምባሳደር ሥዩም ሐዘን በተሞላበት አኳኋን፣ ‹‹የተደረጉ ጥረቶች የሉም ማለት አይደለም፡ የፈለግነውን ያህል ለመሮጥ ብንሞክርም መሬት ላይ ያለው ሀቅ ምን ይመስላል ብሎ መጠየቅ ግን ያስፈልጋል፤›› ይላሉ፡፡ ጥረታቸው መና እንደቀረ በሚያሳይ ሁኔታ፡፡›› እንግዲህ ድርድሩ ፍሬ አልባ ከሆነ፣ ፕረዚደንት ሳልቫ ኪር ከግብፅና ኤርትራ ጋር በመወገን ኢትዮጵያን ለመፈታተን ጥረት ማደረጋቸው አይቀሬ ይሆናል ማለት ነው፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞም የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ(ቤሕነንን) የማጠናከር ጉልህ ሚና ይኖሮዋል፡፡ በመሆኑም፣ ቤሕነን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልን ለማስገንጠል የሚያስችል ጫና ለመፍጠር ዕድል ይኖረዋል ማለት ነው፡፡

ለመሆኑ ውድ አንባቢስ ‹‹ቤኒሻንጉል ጉምዝ ከኢትዮጵያ ብትገነጠል የህዳሴው ግድብ ለማን ይሆናል?›› የሚል ጥያቄ በቀርብሎ እንዴት ይመልሱታል?





Sunday, December 14, 2014

ኢትዮጵያ የበይነ መረብ ነፃነትን በማፈን ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ መሆኗን በጥናት ተረጋገጠ



ምንጭhttp://mgafrica.com/
መቀመጫው አሜሪካ የሆነው ፍሪደም ሃውስ የተባለ ኢ-መንግስታዊ ገባሪ ሰናይ ተቋም ያካሄደው ጥናት እነደጠቆመው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ አፋኝ ስትሆን በዓለም ደሞ የአምስተኛ ደረጃ ተቆናጥጣለች፤ኢራን፣ሶርያ፣ቻይናና ኲባን በመከተል፡፡

ያለበይነ መረብ ነፃነት የፕረሰ ነፃነት አይታሰብም የሚለው ሲፒጀይ በበኩሉ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ቀጥላ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን ለእስርና ለስደት በመዳረግ ከአፍሪካ ቀዳሚውን ይዛ እንደምትገኝ መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡

የመረጃ ድህንነት አጄንሲው ኢንሳ በጣም የተወሳሰቡ የኢንተረነት(በይነ መረብ) መቆጣጠርያ ሶፍተዌሮችን ተጠቅሞ የዜጎች የመረጃ ልውውጥ ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠረና ከፍተኛ ስለያ እያካሄደ ይገኛል፡፡ባለፈው 2006 ዓ.ም የወጣው አዋጅ ፌስቡክና ትዊተርን ጨምሮ ማንኛውም የማሕበረሰበ ግንኙነት መረቦችን እንዲሰልል ሙሉ ስልጣን እንደሰጠው የሚታወ ነው፡፡

በአንፃሩ ደሞ፣ ኢትዮጵያ በበይነ መረብ ሽፋን 2 ከመቶ ብቻ በማስመዝገብ ከዓለምም ሆነ ከአፍሪካ የሚጨረሻው ደረጃ ይዛለች፤አፍሪካ ሜል አንደ ጋርድያን የተባለ ድረገፅ ፍሪደም ሃውስን ጠቅሶ እንደዘገበው፡፡ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኘው የተሌኮም አገልግሎት የመሰረተ ልማት ግንባታውን ለማስፋፋት ቢሞክርም ዘመኑ የሚዋጀውን ስኬት አልተቀዳጀም፡፡

ጋምብያ፣ ሱዳንና ዚምብባዌ በቅደም ተከተል የበይነ መረብ ነፃነትን በማፈን ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ደቡብ አፍሪካ፣ ከንያ፣ዩጋንዳና ማላዊ ደሞ በበይነ መረብ ነፃነት አፍሪካን እየመሩ ይገኛሉ፡፡


ፍሪደም ሃውስ መቀመጫው አሜሪካ ሲሆን ለዲሞክራሲ፣ለፖለቲካ ነፃነትና ለሰብአዊ መብቶች ጥብቅና በመቆም የሚታወቅ ግብረ ሰናይ ተቋም ነው፡፡

Monday, December 8, 2014

አሳዛኝ ዜና፡ 70 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በቀይባሕር ሰምጠው ሞቱ



ሙሾና ጭፈራ

በብዛት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሳፍራ በቀይባሕር በኩል ወደ የመን በመሻገር ላይ ነበረች ጀልባ በሃይለኛ ንፋስ ተንጣ በመስመጧ 70 ሰዎች መሞታቸውን ቢቢሲ የየመን ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘገበ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ተጠሪ ደሞ ባለፈው ጥቅምት ብቻ 200 ሰዎች ቀይባሕርን አቋርጠው የመን ለመድርስ በመጓዝ ላይ እያሉ ህይወታቸውን እንዳጡ አሳውቋል።

ብዙ አፍሪካውያን ስደተኞች ሜዲትራንያንና ቀባሕርን አቋርጠው ወደ አውሮፓና ዓረብ ሃገሮች በጀልባ ለመሻገር ሲሞክሩ በተደጋጋሚ ህይወታቸውን እንደሚያጡ የሚታወቅ ነው፡፡

በለፈውዓመት ወርሃ መስከረም 2006 ዓ.ም በብዛት ኤርትራውያን ስደተኞችን ጭና ከልብያ ወደ ጣልያን በመሻገር ላይ ነበረች ጀልባ ሰጥማ ከ360 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ የሚታወስ ነው፡፡

ብዙዎቹ ደሞ በጎዞ ላይ እያሉ አስገድዶ መደፈርን ጨምሮ ኢሰብኣዊ ድብደባዎችእንደሚደርስባቸው የሚታወቅ ነው፡፡ህገ ወጥ ሰዎችን ሚያዘዋውሩ ዴዊኖች ስደተኞቹን ታስረው በማሰቃየት ውጪ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በሽዎች የሚቆጠር ዶላር ልከው እንዲያስፈቷቸው እንደሚያስገደዱ ይታወቃል፡፡

ክልሆነ ግን ሆዳቸውን በመቅደድ ኩላሊቶቻቸው አውጥተው እንደሚሸጡት የዓለም መገናኛ ብዙሓን በተደጋጋሚ የሚዘግቡት ቢሆንም የህገ ወጥ ዝውውሩ አሁንም አልቆመም፡፡ 

ሙሾና ጭፈራ የተቀላቀለበት ቀን

በሌላ ዘይና ደሞ በዛሬው ዕለት( ህዳር 29 ቀን 2007 .) 9ኛው የብሔሮችብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንበቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በአሶሳ ‹‹በድምቀት ሲከበር›› ኢቢሲ የቀጥታ ስርጭት እያስተላለፈ ይገኛል፡፡ የባዓሉ መሪ ቃል ‹‹በህገ-መንግስታችን የደመቀው ኢትዮጵያዊነታችን ለህዳሴያችን›› የሚል ሲሆን  የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በዓሉ ‹‹የብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትን መረጋገጥ መሰረት የጣለ ታላቅ ገፀ በረከት ነው›› ሲሉ አሞካሽተውታል 

የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን በበኩላቸው  ህገመንግስቱ የሁሉንም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ማድረጉን ገልፃዋል፡፡

------------------------------------------------------------------------


‹‹ዓለም ደሮ ናት ላንዱ እንቁላል ሌላው ኩስ ትጥላለች›› እንደሚባለው በዛሬው ዕለት የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከአባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ጋር ‹‹እሰይ እሰይ እናምራለን…›› እያሉ በመጨፈር ላይ ሲሆኑ በሃገራቸው ስረተው ለመኖር የከበዳቸው ወገኖቻችን ደሞ አደገኛው የባሕር መንገድ ለማቋረጥ ሲሞክሩ ህይወታቸውን አጥቷል፡፡እንግዲህ በጭፈራ ላይ የሚገኙ ወገኖች ወደ ህሊናቸው ይመልሳቸው ዘንድ ስንፀልይ ህይወታቸውን ላጡ ወገኞች ደሞ መንግስተ ሰማያት ያዋርሳቸው እንላለን፡፡

Thursday, December 4, 2014

ኣፈሙዝ ፕሮፓጋንዳ ህወሓት ንምንታይ ናብ ገብሩ ኣነፃፂሩ?



ገብሩ ኣስራት ንውድብ ህወሓት እናመርሑ ካብ በረኻ ደደቢት ናብ ቤተ መንግስቲ ኣራት ኪሎ ካብ ዘብፀሑዋ ጀጋኑ ደቂ ትግራይ ቅድሚት ዝስራዕ ተባዕ ወዲ ህዝቢ እዩ፡፡ትብዓቱ ግን ወታደራዊ ጥራይ ኣይነበረን፤ብህዝባዊ ምምሕዳር እውን እንተኾነ ክሳብ ሐዚ መዳርግቲ ኣይተረኸቦን፡፡ኣብ ትግራይ ዝተሰርሓ ዓበይቲ ትካላት ሓወልቲ ህዝባዊነቱን ተባዕነቱን እየን፡፡

መብዛሕቲኦም መቃልስቱ ብስልጣንን ሃፍትን ልቦም ተደፊኑ ሞሳ ህዝቢ ትግራይን ሕድሪ ብፆቶምን ረሲዖም ናብ ውልቀ ረብሓኦም እንተጓይዩ ንሱ ግን ሐዚ እውን ኣብ መትከሉ ይርከብ፡፡ንውልቀ ረብሓኡ ኣይተቓለሰን እሞ ውልቀ ረብሓኡ ራሕሪሑ ንረብሓ ህዝቡን ሃገሩን ኣብ ምቅላስ ይርከብ፡፡ቅደም ነቲ ሽዓኡ ንሃገርና ከዊልዋ ዝነበረ ፀልማት ቀትሪ ከም ሽምዓ ነዲዱ ብርሃን ንኽውልዕ ብረት ኣልዒሉ ተቓሊሱ፡፡ሐዚ ድማ እቲ ብሂወት ደቂ ህዝቢ ዝተወለዐ ብርሃን ብካሕዳማት ከይቅህም ብሰላማዊ መንገዲ እናተቓለሰ ይርከብ፡፡

Friday, November 21, 2014

ከድሮ ጀምሮ ‹‹ትግሬ›› ስንላችሁ ነበርና አሁንም እንቀጥልበታልን ማለት ድሮ ‹‹ጋላ›› ስንላችሁ ስለነበረ አሁንም ‹‹ጋላ!›› እንላችኋለን ማለት ነው



ድሮ የሰው ልጅ ‹‹ባርያ›› ተብሎ እንደ እቃ ይሸጥ ይለወጥ ስለነበረ ዛሬም መሸጥ መለወጥ አለበት ብሎ የሚከራከር ሰው ምን ትለዋለሀ? ድሮ ‹‹ወላሞ›› እንላችሁ ነበርና አሁንም ‹‹ወላሞ!›› ስንላችሁ ቅር ሊላችሁ አይገባም ብለው የሚከራከሩ ፍጡራን ባሉበት ሃገር ከቶ እንዴት መግባባት ይቻላል?ድሮ ሽፍቶ እንዳሻው እየዘረፈ፣ በጉልበቱ እየመዘበረ፣ሴቶችን አስገድዶ እየደፈረ ይኖር የነበረው ሁሉ አሁንም እንደድሮ ይኑር ብሎ ሙግት ምን ይባላል?

አዲሱ ቸኮል የሚባል የፌስቡክ ጓደኛየ ‹‹በከተሞች ፎረም ያወዛገበውትግሬ”›› ሚለው መጣጥፉ እንዲፅፍ ከነሳሱት ነገሮች አንዱ እንደሚከተለው አስቀምጦታል፤‹‹ ‹ድሬዳዋ ከየት ወደየትበሚል ርዕስ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲናድሬዳዋ አስተዳደር ትብብር የተዘጋጀ ጥናታዊ ፅሑፍ ውስጥ በአስተዳደሩ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችን የሚዘረዝርበት ክፍል ላይ ትግሬ የሚል ቃል መኖሩ ሁለት የትግራይ ክልል ተወላጆች ቃሉን ተቃዉመው አስተያየት እንዲሰጡ ያስገደደ ነበር፡፡›› ይልና በመቀጠልም ‹‹የተቃዉሟቸው መነሻ ደግሞ ብሔሩ ትግራይ እንጂ ትግሬ አይባልም የሚል ነበር፡፡ህገ መንግስቱን ሁሉ ዋቢ ያቀረቡ አሉ(ምንም እንኳ በህገ መንግስቱ የተቀመጠው የክልሉ ስም እንጂ የብሔሩ ስም ባይሆንም)፡፡›› በማለት የሁለቱ የትግራይ ተወላጆች የተቃውሞ አስተያየት ውድቅ ለማድረግ ይሞክራል፡፡
አዲሱ በዚሁ አላበቃም ‹‹እነኚህ ሰዎች በአማርኛም፣ በኦሮምኛም ሆነ በሶማሊኛ፣ . . . .ትግራይ የሚባለው ክልሉ እንደሆነና የክልሉ ተወላጆች ግን ትግሬ እንደሚባሉ ሳያውቁ ቀርተው ነው እንደዚህ የሚከራከሩት እንዴ?›› በማለት ራሱን እንዲጠይቅ መገደዱን ጠቅሶ ሲያበቃ ቀጥሎም ‹‹ትግሬ የሚል ቃልትምክህተኞች ለትግራይ ህዝብ ያወጡለት የስድብ ስም ነውእያሉ አንዳንዶች በፌስቡክ ላይ የሚያደርጉት ክርክር ነበር ትዝ ያለኝ፡፡ እነኚህ ከክልሉ ከተሞች የተወከሉ አመራሮች/ባለሙያዎችም እንደዚያ ነው የሚያስቡት ማለት ነው?››› በማለት ይጠይቃል፡፡
አዲሱ መጣጥፉን የደመደመው እንደሚከተለው ነበር፡ ‹‹ትግሬ የሚለውን ቃል ስልጣን ወደትግራይ ከመሔዱ፣ ከትግራይም ወደሸዋ ከመሻገሩ በፊት፣ ሁሉም ጠቅላይ ግዛቶች ተመሳሳይ በነበሩበት የአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ሁሉ ጥቅም ላይ ይውል እንደነበር በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን የተገጠሙ ግጥሞች ማስረጃ ናቸው፡፡››
ይህ ድምዳሜ ‹‹ትግሬ››የሚባለው አጠራር ከድሮ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ መሆኑን ለማስረገጥ የቀረበ ታሪካዊ ማስረጀ መሆኑን ነው፡፡መቼም፣ በማለት ይቀጥላል ወንድማችን፣ ‹‹መቼም በዛ ዘመን የአሁን ፖለቲከኞቻችን የሚያወሩት መናናቅ/መሰዳደብ አለ የሚሉ አይመስለኝም፡፡ እናም ቃሉ ስድብ አለመሆኑን መግባባት ይቻላል፡፡›› ይልና የማመዛዘንና የስነ መጎት ድህነቱን ቅልብጭ አድርጎ ያሳየናል፡፡ቀጥሎ የፃፈው እንተፍንቶም በጥቁር አሜሪካኖች ላይ የሚደርሰው ዘረኝነት ጥቁሮቹ ስለተቃወሙት ነው እየቀጠለ ያለው የሚል ብያኔ ያለው ነውና እሱን ትተን በእኛ ሃገር ስላለው ሁኔታ እንመልከት፡፡