Monday, September 30, 2013

‹‹መልኩን ይቀይር እንጂ አሁን ህወሓት ሌላ ደርግ ነው የሆነብን›› አብርሃ ደስታ






በቅርቡ የዓረና ከፍተኛ አመራር ሁኖ የተሸመው(እንደ እራሱ አባባል ዓረናን ለራሱ የተሰጠው) አብርሃ ደስታ ከፌስቡክ አልፎ የጋዜጦችና የመፂሔትች አጀንዳ መሆን ጀምሯል፡፡ከሎሚ መፂሔት ጋር ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ “የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ቢጠላም በሌሎች ፓርቲዎች ላይ ጥርጣሬ አለው” ብሎ እንደ ነበር የሚታወስ ነው፡፡‹‹ለውጥ የምናመጣው ስልጣን ስንይዝ ነው›› ብሎ የሚያምነው አብርሃ ከህወሓት ውጪ ያሉ ፓርቲዎች ከሙሴ ጋር ያስተካክላቸዋል፤ የኢትዮጵያ ህዝብን በመምራት ወደ ‹‹ተስፋይቱ›› ምድር ያደርሳሉ ብሎ ያምናል፡፡ይህ አባባሉ አብርሃና የአብርሃ ፓርቲ የሆነው ዓረናም ህዝቡ በጥርጣሬ እንዲመለከታቸው እያደረገ ነው፡፡
በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ደግሞ ‘‘እኔ ከህወሓት ገንዘብና ስልጣን ሳይሆን ነፃነትን ነው የምፈልገው’’ ብለዋል፡፡ አብርሃ ደስታ ዓረና ለራሱ ባይሰጠው ንሮ እንዲህ አይልም ነበር፤ የዓረና ከፍተኛ ባለስልጣን ከመሆኑ በፊትም እንዲህ ብሎ አያውቅም፡፡ አሁን ግን ተስፋ የቆረጠ ይመስላል፤ ከዓረናዎች ጋር ተጋብቶ ሲያበቃ ራሱን እንዲያስተዳድረ ዓረና ተሰጥቶታልና፡፡እናም ከአሁን በኋላ ከህወሓተ ገንዘብና ስልጣን አይፈልግም፤ እኛም እናውቃለን፡፡
የአብርሃ ፍላጎት ከነአንድነት ጋር መዋሃድ ነው፡፡ይህን የሚያረጋግጥልን ደግሞ ‹‹የአረና አደረጃጀት ክልላዊ ቢሆንም ለሉአላዊነትና የወደብ ጥያቄዎችን ያነሳል። በዚህም ፓርቲው ሀገራዊ መልክ በመያዝና ክልላዊ ወካይነት ለመያዝ እየዋለለ ይመስላል። አንዱን ለምን አትመርጡም?›› የሚለው የሰንደቅ ጥያቄ ሲመልስ ‹‹ተዋህዶ መቀጠሉ ሚዛን እየደፋ ነው። እኔ ከገባሁ በኋላ ባደረግነው ውይይትም የደረስንበት ውህደት መፍጠር አለብን የሚል ነው። ውህደት ሲፈጠር ደግሞ አረና የሚለውን ስም እስከ መቀየር የሚደርስ ነው። ስለዚህ ውህደት ፈጥሮ ሀገራዊ ቅርፅ መያዙ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መሆኑ አይቀርም። አሁን ያለውን የመድረክ ግንባር ወደ ውህደት ከፍ ማለት አለበት የሚል እምነት አለን።›› በማለት ነበር የመለሰው፡፡
እዚ ጋ ሊሰመርበት የሚገባው አረፍተ ነገር አለ፤‹‹ውህደት ሲፈጠር ደግሞ አረና የሚለውን ስም እስከ መቀየር የሚደርስ ነው›› ዓረና ከመድርክ(አንድነት  እንደ ፈለገው የሚዘውረውና ሲያሻው የሚቆልፈው ሲያሻው ደግሞ የሚከፍተው) ጋር ስትወሃድ ስሟ ብቻም ሳይሆን ፖሊሲዋም ጭምር ይቀየራል፡፡ምክንያቱም የአብርሃ የፖለቲካ አነጋገር እንዲህ ይላል እንጂ እውነታው ‹‹ዓረና ከመድርክ ጋር ያለአቻ ጋብቻ ትፈፅማለች›› ነው፡፡አንዴ ከመድርክ ጋር ተጋባች መለት ደግሞ እንደ ፈረንጅ የቤት እመቤት በባልዋ ስም ብቻ ትጠራለች ማለት ነው(በፈረንጆች የጋብቻ ስርዓት ሚስ ጁልያ ከሚስተር ሮበርት ጋር ከተጋባች ስሟ እንዳለ ይቀየርና ሚርስ ሮበርት ትባላለች)፡፡
ዓረና ከመድርክ ጋር ከተዋሃደች በኋላ ማንነትዋን የምታጣበት ምክንያት እንደነ አብነት ያሉ ፓርቲዎች እኛ ያልነው ካልሆነ በስተቀር ልንወሃድ አንችልም የሚል አቋም ስላላቸው ነው፡፡አብዛኞቹ የአንድነት ስብስቦች(መድርክም ጭምር) የኋላ ታሪካቸው ሲመዘዝ የያ ትውልድ ትርፍራፊነታቸው አይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጥጦ ፊትለፊታችን ይገተራል፡፡አንድነቶች የብዱን መብት አይቀበሉም፤ የብሔር፣የቋንቋ መብት አይሰጡም፡፡አብዛኞቹም አንድ ብሄር፣አንድ ሃይማኖትና አንድ ቋንቋ ለመመስረት የሚታገሉ ናቸው፡፡አብርሃ ደስታም የግል መብት እንጂ የብዱን መብት አይደግፍም፡፡ ለዛም ነው የዓረና ሃገራዊና ክልላዊ አጀንዳ ብቻ ሳይሆን ስም እስከመቀየር ድረስ ያስከትላል እያለ ያለው፡፡
አብርሃ ደስታ የሽዋ ልሂቃን ደጋፊ ብቻ ሳይሆን አምላኪም ጭምር ነው፡፡የፌስቡክ ፅሑፎቹን ልብ ብላችሁ አንብቧቸው፤ምንጫቸው አይታወቅም፡፡ምንጭ ያለመጥቀሱ የሚሰጠው ምክንያት ጋዜጠኞች ስለሌሉ የጋዜጠኞች ስራም ጠቅልሌ እየሰራሁ ነው ይለናል፤ምንጭ የማሳወቅ ግዴታ ጋዜጠኞችን ብቻ የሚያስገድድ ህግ ያለ ያህል ፡፡እውነታው ግን ሌላ ነው፤ ውዥምብር ለመፍጠር፤ ውሸቱን ካባ በማስለበስ እውነት ለማስመስል፤ለማጭበርበር፡፡ እቺ ስልት ከተመስገን ደሳለኝና ከተስፋየ ገብርአብ የተወሰደች ነች፡፡‹‹ታማኝ ምንጮቼ ነገሩኝ፤እንትና ሲናገር ሰማሁ …›› በቃ፣ በማንኛውም ስብሰባ የነበሩ አስመስለው ይፅፋሉ፡፡የፈለጉት ይስበኩ፤ የፈለጉት ያህል ለማስመሰል በጥሩም ዓላማቸው የድሮው አገዛዝ ማስመለስ ነው፡፡ወይም ‹‹የትም ፍጭው ስልጣኑን አምጭው›› ነው ዋናው ዓላማቸው፡፡
ተመስገን ደሳለኝም ልክ እንደ አብርሃ ደስታ የመድርክ አምላኪ ነው፡፡ለነገሩ እሱ ማንኛውም የኢህአዴግ ተቃዋሚን ይደግፋል፡፡እስካሁን ድረስ ማስረጃው ያለኝ ግን ከመድርክ ጋር ለመታገልና ስልጣን ለመጨበት መዘጋጀቱን ነው፡፡የመድርክ የ2005 ‹‹ማኒፌስቶ›› እንዲህ ይላል፡-
‹‹ይህንን ፀረ-ህዝብና ፀረ-ሀገር የሆነውን ኢህአዴጋዊ ስርዓት በሰላማዊ አግባብ በምታደርገው ብርቱ ትግልህ መለወጥ እንደምትችል ካለፈው የትግል ተሞክሮህ ሆነ የአለም ህዝቦች ለነፃነት፣ ለዕኩልነትና ለፍትህ ብሎም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን መሆን ከሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችና ከሚያስመዘግቧቸውም ድሎች ትገነዘባለህ፡፡ ስለሆነም መድረክ ይህንን ክቡር ትግልህን በመምራት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝለስልጣን ባለቤትነት እንድትበቃ በፅናትህ ከጎንህ ሆኖ ለመታገለ መወሰኑን ተገንዝበህ ከምንጊዜም በላይ ሁለንተናዊ ድጋፍህን እንድትሰጥ ጥሪያችንን በከፍተኛ አክብሮትና በአንተም ላይ ባለን ሙሉ እምነት እናስተላልፋለን፡፡››
ተመስገን ደሳለኝ ደግሞ ‹‹ከለውጡ በኋላ›› በሚል ርእስ በፋክት መፅሔት ላይ እንዳለ ደግሞታል፡፡‹‹እናንተን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ እየታገልኩላችሁ ነውና እወቁልኝ›› ማለቱን ነው፡፡የመድርክ ስብስቦች ግን ልክ እንደ ቅንጅት ስልጣን ከያዙ በኋላ ለመደራደር በሚል ተልካሻ ሰበብ የእሳትና ጭድ ዓይነት ልዩነታቸው ሲሸፋፍኑት ይታያል፡፡
ኢህአዴግ(እንደ ተቃዋሚዎች አባባል ህወሓት) ከደርግ ጋር የሚያወዳድሩት ምን ማስረጃ ይዘው ነው?እውን ከደርግ ጋር የሚወዳደር ስርዓት በኢትዮጵያ ኖሮ ያውቃል? እነሱ በሚፅፉት እነአብርሃ እንደ ዳዊት በሚያነበንቡት የታሪክ መፅሐፍ መሰረት አዎ! ነው፡፡ይህን የሚቃወሙ የትግራይ ምሁራን ካሉም ‹‹የህወሓት ካድሬ›› ተብለው ይፈረጃሉ፡፡
አብርሃ ደስታ ታሪክ እንዲፃፍ አይፈልግም፡፡ በተለይ የትግራይ ምሁራን ታሪክ እንዲፅፉና ስለሃገራቸው እንዲመራመሩ፤የሽዋ ታሪክ ፀሓፊዎች የፃፉት ከፋፋይና ወገንተኛ ታሪክ ለምን አድላዊ ሆነ ብለው ሲጠይቁ ጅኒ እንደያዘው ያጓራዋል፡፡ለዛም ነው የታሪክ ተማራማሪውና ፀሐፊው ገብረኪዳን ደስታን እደ ጠላት የሚፈርጃቸው፡፡
የሽዋ ልሂቃን ተብየዎቹ የታሪክ ፀሐፊዎች እውነታ በማዛባት ይታወቃሉ፡፡ለምሳሌ የምኒሊክ አንቀፅ ሶስትን በታሪክ ስርዓተ ትምህርት አይተናት አናውቅም፡፡ምንሊክ ከማህዲስቶች፣ከግብፆች፣ከጣልያኖችና ከእንግሊዞች ጋር የተፃፃፋቸው ‹‹ሃፀይ ዮሃንስን ተባብረን እናጥፋው›› መልእክቶች ተደብቀው ኖሯል፡፡ነብሰ በላው ደርግ በቀይ ሽብር ከ500 000 በላይ ወጣቶችን መጨፍጨፉን ይታወቃል(የአምነስቲ ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት)፡፡የሽዋ ፕሮፌሰሮች ግን ቁጥሩ አከራካሪ ነው ሲሉ ነው የሚሰማው፡፡አብርሃ ደስታም እነሱ የተፉትን አጎንብሶ ሲልስ ይታያል፡፡
የህም ቁጥሩን በማሳነስ ወይም በመካድ ደርግን ከህወሓት ጋር ለማስተካከል የሚደረግ ጥረት ነው፡፡
አንዲት ዛፍ የምትቆመው ግንድና ስሯ ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡ታሪክም የአንዲት ሃገር መሰረት ነው፡፡መንደርደርያ ነው፡፡አውሮፕላን ለመብረር መንደርደርያ ያስፈልጋታል፤ ሃገርም ወደፊት መወንጨፍ መንደርደርያ ያስፈልጋታል፤ድሮ ምን ነበረች(የት ነበረች)? አሁን የትነች? ለወደፊቱስ የት መድረስ አለባት? እነዚህ ጥያቄዎች የሚመለሱት የታሪክ መዛግብት በማገላበጥ ብቻ ነው፡፡ታሪኩ ወሸት ከሆነ፣ታሪኩ የተጣመመ ከሆነ ግን ወዳልተፈለገው አቅጣጫ እንደናመራ ያደርገናል፡፡






5 comments:

  1. guys, when I look Abrha Desta in two ways.Abraha desta as an activist and Abraha desta as politician.as an activist, for the Voiceless people of tigray , with all his faults I can accept Abrha Desta as good initiative and good sign. you know my hypothesis is based , not from the believe that Abraha Desta is honest or speaking all the truth. rather for me I take Abraha desta as activist who shouts, raises and speaks the problems what ever the people are facing, he gets an attention and creates pressure on the opposite camp (TPLF). if we look Abraha Desta in this way, he is pretty successful and he has also have the support a significant tigrean youth/scholars including me. because he raises lots of issues , he is a voice for the voiceless, which the main task of an activist, that is great. the problem is, if we see Abraha Desta as politicians, I am not surprised he hates TPLF, as rival party , the main Problem is he has not strategy to remove the problems that the Tigray people is now facing, he is not even have the strategy to sustain his Political power among the politicians, I think he lives in submission, he is already submitted to shewan Elites. I even surprised why ARENA elect him as executive,his believes contradicts the Program of ARENA. anyways he will be the path to conspire ARENA by shewan Politicians, not bother as ARENA is worthy of worrying for us. I don't think he has any Political strategy or vision of how he sustain himself, but what he is expecting a a hand out from shewan for his service. really shame to most of us. so if we see Abraha Desta as politician he is really disgrace.

    ReplyDelete
    Replies
    1. I really agree with this article!!
      Thanks!!

      Delete
  2. Anonymous! Thank you for your insightful analysis, indeed. Abraha Desta is no more an activist; he's a full time politician. I hope you have not missed the news of the new your 2006 in which Abraha Desta was elected as ARENA's both Central Committee and Executive Committee member. Once he officially became a member of any political organization, there is no ground for him to claim as an activist. And what is worst? He is working hard to rename ARENA as mrs.UDJ like that of a foreigner wife.

    ReplyDelete
  3. Anonymous! here is a link in case you have missed the news of Abraha Desta's election as ARENA's highest polity bureau:

    http://asfawgedamu.blogspot.com/2013/09/blog-post_11.html

    ReplyDelete