Friday, November 30, 2012

የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ናፍቆት

                          
አህጉራችን አፍሪካ አሁንም የተመዋላ ሰላም አላት ለማለት ያስቸግራል፡፡ የማሊ ስሜናዊ ግዛት በእስላማዊ ፅንፈኞች ቁጥጥር ስር ከወደቀ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ የዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ሰላምም ከድጡ ወደ ማጡ ሁነዋል፤ ሰሙኑን ጎማ የምትባል የግዛትዋ ከተማ ኤም ሃያ ሶስት ሚባሉ አማፅያን ተቆጣጥረዋታል፡፡የሶማልያ ነገር ሙሉ በሙሉ አልየለትም፡፡ ሶርያ በከባድ ጦርነት እየተናጠች ትገኛለች፡፡ የሰሙኑን የእስራኤልና ፍልስጤም አታካራ የአንድ መቶ አርባ ሰዎች ነፍስ መቅጠፉን ይነገራል፡፡የአፍጋኒስታን፣ ኢራቅና ሊብያ ሰላም አልፎ አልፎ ጉም እየጋረደው ይገኛል፡፡
በስልጣን ላይ ያለው በምርጫም ሆነ በጡጫ እጁ ላይ የገባውን ስልጣን ላለማጣት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡የስልጣን ጥማት ወይም አዙሪት የላባቸው ተቃዋሚዎችም ከተቻለ በምርጫ አሳብበው፣ ከልሆነ በህዝባዊ ዓመፅ፣ ይህን ካልተሳካ ደግሞ በጠብመንጃ አፈሙዝ ስልጣን ለመጨበጥ ይፈጨረጨራሉ፡፡የተቃዋሚዎችም ሆነ የባለ ስልጣኖች ግትርነት ወይም በፖለቲኮኞቹ አባባል አክራሪነት ጦስ ግን የሚተርፈው ለህዝቡ ነው፡፡ሁለቱም በግድም በውድም የመሪነት ህልማቸውን እውን ለማድረግ የማያድርጉት ነገር የለም፡፡ የዋሻሉ፣ነጩን በማጥቆር፣ ጥቁሩን በማንጣት የድጋፊዎችን ቀልብ ለመሳብ ይጣጣራሉ፡፡እኔ እሻላሎህ የሚለውን ጉንጭ አልፋ ዲስኩራቸውን በመደጋገም ያደነቁሩናል፡፡ ይህ ለአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ የሰላም ማጣት አንዱ ምክንያት ነው፡፡በዚማሃል ግን ህዝቡ ይሰቃያል፡፡የመልካም አስተዳደር ችግር ይነግሳል፤ሙስና ይስፋፋል፤ድህነትና መሃይምንት የሃገሮቹ መገለጫ የሆናሉ፡፡ይህ ደግሞ ስደትን ያስከትላል፣ለህገወጥ የሰው ዝውውር መስፋፋት በር ይከፍታል፡፡ለዚህም ነው ብዙ ወገኖቻችን እንደ እቃ በኮንቴነሮችን ውስጥ ታሽገው ለመጓዝ እስከ መወሰንና ለአሰቃቂ እልቂት ራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት እያስገደዳቸው የሚገኘው፡፡
ሰላም የዓለም ብርሃን፣የመፈቃቀርና አብሮ የመኖር ሚስጥር ነው፡፡ሰላም ከሌለ ግን ሁሉም ነገር የለም፡፡ ቢኖርም ሙሉ በሙሉ አይታይም፤ይደበዝዛል፣ይጨልማል፡፡ ምዕራባውያን አምባገነኖች በተለይም አሜሪካ ለዓለማችን የሰላም መስፈን እንቅፋት ናቸው፡፡ ሽብርተኝነት የነሱ እከይ ተግባር ውጤት ነው፡፡እነሱ የፈለጉት ሁሉ እያደረጉ(ንፁሃንን መጨፍጨፍና ለዓላዊ ሀገሮችን መውረርም ጭምር)ሌሎች እጅና እግራቸውን አጣጥፈው ቁጭ እንዲሉላቸው ይፈልጋሉ፡፡በአጠቃላይ ይች ዓለምና ህዝቦችዋ በተለይም አፍሪካውያንና ዓረቦች እነሱን ለማገልገል እንደተፈጠሩ አርገው ያስባሉ፡፡ ያስባሉ ብቻም አይደለም በተግባርም እያሳዩን ይገኛሉ፡፡ ዲስኩራቸው ሌላ ተግባራቸው ሌላ ነው፡፡ስለሰላም እየለፈፉ በላዓላዊ ሃገሮች ላይ ጦርነት ያውጃሉ፡፡  
የሚገርመው ነገር ግን በቅንነት፣በመፈቃቀድና በመፈቃቀር የተመሰረተ ግንኙነት በመፍጠር ዓለምን ገነት ማድረግም ይቻላል፡፡ አዎ! ክፉ መስራት ካላቃተን ጥሩ ነገር ማድረግ አያቅተንም፡፡ለሰው ልጅ ከአየር ቀጥሎ ሰላም ያስፈልገዋል፡፡እስኪ ለዓለማችን ሰላም ድርሻችንን እንወጣ፡፡ ሰላም ለመላው ዓለም እንመኝ ለተግባራዊነቱም እንትጋ፡፡
                                  ሰላም!

ሰውና ሮቦት



የሰው ልጅ “ጥረህ ግረህ ብላ” ተብሎ እስከ ተረገመበት ቀን ጀምሮ ያልወጣው ዳገት ያለወረደው ቁልቁለት የለም፡፡አሻፈረኝ አልታዘዝም በማለቱ ከገነት ወደ መሬት ተሽቀንጥሮ መወርወሩ ይነገራል፡፡ከዛም መሬት ወርዶ ብዙ ተንገላትተዋል፣ወንዝ ተሻግረዋል፣ባሕር አቁዋርጠዋል፣ ሰማይና መሬትን አዳርሶዋል፡፡ባጋጣሚ ግን ትልቅ ዋሻ አገኘ፡፡ እዛውም ተጠልሎ ድንጋይ ለይ እየተኛና እንደመሳርያ እየተጠቀመ መኖር ጀመረ፡፡ ያ ዘመንም ዘመነ ድንጋይ ብሎ ሰየመው፡፡እንዲህ እንዲህ እያለ መሬትን ብቁጥጥር ስሩ ማስገባቱ ካወቀ በሁዋላ እንደገና ደግሞ ወደ ሌሎች ፕላኔቶችን እያመራ ይገኛል፡፡ስራውን ለማቃለልና ንሮውን ለማሻሻል ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልዘየደው ዘዴ አለ ለማለት ያሰቸግራል፡፡ ከዘመነ ድንጋይ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ዓይነት መሳርያዎችን ሰርተዋል እየሰራም ይገኛል፡፡ከነዚህ መሳርያዎች አንዱ ሮቦት ነው፡፡ግን ሰው እንዴት ሮቦት መስራት ቻለ?  
ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡መፅሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር የሰው ልጅን በራሱ አምሳል ሰራው” ይላል፡፡በዚህ መሰረት ለመጀመርያ ጊዜ የኮረጀው እግዚአብሔር ሲሆን ሰውም ይህን የኩረጃ ጥበብ ከፈጣሪውን ተምሮ ሮቦትን በአምሳሉ ሰራው፡፡እግዚአብሔር ሰውን የሰራው እንድያገለግለው ነው ይባላል፡፡ ለምን? መልሱ በትክክል ባላውቀውም ምናልባት ግን መስራት ስለደበረው ሊሆን ይችላል፡፡ምክንያቱም ደግሞ ባይደብረው ንሮ እስካሁን ድረስ መስራት አያቆምም ነበር፡፡ነገር ግን ለሰባት ተከታታይ ቀናት ወጥሮ ከሰራ በሁዋላ “መተካካት” የሚባል ፖሊሲ በማርቀቅ ለሰው ልጅ ተላላኪ አድርጎ ሸመው፡፡የመጨሻው ከፍተኛ ስልጣን ግን ዛሬም ድረስ በእጁ ነው…የፈለገውን ማድረግ ይችላልና፡፡ምርጫ ቢኖርም ባይኖርም አሸናፊው ያው ራሱ ነው፡፡የደበረው ስራ እንጂ ስልጣን አይደለምና፡፡ታድያ እግዚአብሔር መስራት ከደበረው የሰው ልጅ እንዴት አይደብረውም?በቃ ሰውም በተራው መስራት ሰለቸውና ሮቦት ሰርቶ የተላላኪነት ስልጣኑን አሳልፎ ሰጠው፡፡ልክ እነደፈጣሪውም ራሱ የማይችለው ወይም መስራት የማይፈልገው ነገር ሁሉ ቀንና ሌሊት እያሰራው ይገኛል… ያለምንም ዕረፍትና ክፍያ፡፡
እግዚአቢሔር አዳምና ሔዋንን ከፈጠራቸው በሁዋላ “በዚህ ዓለም የፈለጋችሁትን ነገር ሁሉ ማድረግ ትችላለቹህ ፤ነገር ግን ያች ዕፀ በለሴን መብላት ይቅርና መንካት አትችሉም፡፡” የሚል ጥብቅ ትእዛዝ ሰጣቸው፡፡ ይህ ነገር ለአዳምና ሔዋን በቀላሉ ሊዋጥላቸው አልቻለም፡፡እንዴት ባንዲት ዕፀ በለስ ምክንያት ሙሉ ነፃነታችን እናጣለን? የሚል ጥያቄ በህሊናቸው መመላለስ ጀመረ፡፡አምፅ አምፅ ፣ሸልል ሸልል አላቸው፡፡ ባልና ሚስት ብዙ ከተመካከሩ በሁዋላ “ነፃነት ወይም ሞት!” የሚል መፈክር አንግበው ወደ ዕፀ በለሰዋን ሄዱና እንክት አድርገው በሉዋት፡፡ወድያውም ማንኛውም ነገር መክፈትና መዝጋት እንዲሁም በቀላሉ የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ፣ማየት፣ይዘው መግባትና መውጣት ቻሉ (የእግዚአብሔር ሴኩሪቲ ሲስተም ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት)፡፡ነገር ግን እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን የሚያስቡትና የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ያውቅ ስለነበር እጅግ በጣም ተቆጣ፡፡ ተቆጥቶም አልቀገረ “ይች ጥሬ ከደረች …” አለና በዱላ እየዠለጠ ከቀያቸውን አባረራቸው፡፡ ከዛማ ምን ይደረግ ሁሉም ነገር አለቀ ደቀቀ…ሳይቀድሙት ቀደማቸው፡፡ማለቅያ የሌለው ስቃይና መከራ ደረሰባቸው፡፡ተንገላቱ አይቀጡት ተቀጡ፡፡አባታችን አዳም ሳይወድ በግዱ እጁን ሰጠ ወንጀለኛ መሆኑንም አመነ፡፡ ከብዙ ጅንጀና በሁዋላ በአዳምና በጌታው መካከል ዕርቀ ሰላም ወረደና አዳም ወደ ቀደሞ ሰራው ተመለሰ፡፡ ቢሆንም ግን ከዛች ጊዜ በሁዋላ የአዳም ዘር በሙሉ ማብርያና ማጥፍያ ያለው ሮቦት ሁኖዋል፡፡አንዴ ይበራል (switch on) ይደረጋል ከዛም ይሰራል፣ሌት ተቀን ይሰራል፣ ግራና ቀኝ ይወራጫል፣ያን የነሳል ይህን ይጥላል፣ቀስ በቀስ እንደ ሻማ ራሱን እያቀለጠ ያጠፋል፡፡የማይሰራ ሰነፍ ካለም ያው ተሎ ካገልግሎት ወጪ ይሆናል፡፡በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ ይጠፋል(switch off) ይደረጋል፡፡ሰው የሰራቸው ምግቦች ካገልግሎት ውጪ እንደሚሆኑ ሁሉ እሱ ራሱም ካገልግሎት ውጪ ይሆናል…ኤክስፓየርድ ያደርጋል፡፡
ፈጣሪ ለመጀመርያ ጊዜ ራሱን ኮፒ አድርጎ ሰውን ፈጠረ፡፡ያገልጋይነት(የበርነት ግዴታ)ስልጣንም ሰጠው፡፡ሰውም በተራው ከፈጣሪውን ኩረጃ ተማረና ሮቦትን በራሱ አምሳል ፈጠረ፡፡ ነገር ግን ሮቦት ማንነቱን እንደማያውቀው ሁሉ ሰውም ማንነቱን አያውቀም፡፡ ሌላ ሰው ካልነገረው በስተቀር መቸ እንደተወለደ አያውቅም፡፡ መቸ እንደሚሞትም እንዲሁ፡፡

Ethiopian Hospitality




I always hear to people saying we Ethiopians are hospitable, respectful, have warm heart.... all superlatives are used to paint Ethiopian behavior/culture colorfully. Unfortunately, I don't believe that our culture of handling customers is wise. We neither live in the traditional Ethiopian hospitality nor in a westernized customer handling technique. It’s a pain, headache, heartache...an agony to wait standing in long line to pay mobile bill, a bill for electric consumption, to withdraw or deposit money in Ethiopian banks etc. For any social services it seems a must to wait for hours, days even months and years. Even worse, especially, to get legal service years are not enough to wait. Almost always citizens don't get justices after waiting for moths/years.
The other day I had to get my blanket washed. I went to a laundry carrying the blanket in a plastic bag. The clerk was a middle aged lady. I asked her how much it costs to wash a blanket. She said it was 80 birr. I gave her the cash and the blanket. To my surprise the lady took the blanket out of the plastic bag and threw it on to the dirty ground. I felt so sorry. I gave her to get a laundry service, but she, the hospitable Ethiopian, dump it to the ground like a trash. What a misfortune to live among such a society I murmured. I asked her when to come back to fetch my blanket. She said after two weeks (15 days)!
I went back after 15 days to fetch my blanket contemplating how neat it might be washed. No! It was even dirtier than before, I could feel the dust, and it looked as if a pile of ash were all over it. You see, that was a service I got for 80 birr.  So where is our so called hospitality? Where is our respectful culture? For me these all seems fake…An empty boast.


ይህች ዓለም የአምባገነኖች መነሃርያ ነች




ፍልስጤማውያን በእስራኤል አውሮፕላኖች የቦምብ ናዳ እየወረደባቸው ነው፡፡ ይሐው ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸው ሲሆን እስካሁን ድረስ የሐማስ ከፍተኛ የጦር አዛዥ ጨምሮ 80 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከእስራኤል በኩል ግን ሦሰት ሰዎች ብቻ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ 27 ፍልስጤሞች ለ 1 እስራኤላዊ  ማለት ነው ሒሳቡ፡፡
ባራክ ኦባማ አሁንም ለእስራኤል ድጋፋቸውን አረጋግጠውላታል፡፡ እስራኤል ራስዋን የመከላክል ሙሉ መብት እንዳላትም አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ የሐማስ አቅምን ያላገናዘበ መፍጨርጨርና አልሞት ባይ ተጋዳይነት የእስራኤል የደም ጥማት ከማርካት ውጪ እስካሁን ድረስ የፈየደው ነገር የለም፡፡ ለኔ ከድንጋይ ጋር እንደ መላትም ነው የሆነብኝ ነገሩ፡፡ እስራኤል እስከ አፍንጫዋ ድረስ የታጠቀች አገር(የጸረ ሚሳኤልም ጭምር) መሆንዋን እያወቁ ሐማሶች ድንጋይ የመወርወር ያህል አጉል ሮኬቶችን ያንጣጣሉ፡፡
ጥርስ አልባው( የስግብግብ ምዕራባውያን ስራስፈጻሚው)ባንኪ ሙን እስራኤል የልብዋን እስክትፈጽም ፀጥ ብለው ከርመው አሁን ለይምሰል መተንፈስ ጀምረዋል፡፡ ይህ ተግባር ግን እጅግ አሳዛኝና የዓለም ኢ-ፍተሃዊነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ትልቅ ዱላ ያለው በፈለገው ጊዜ በፈለገው ሰው ላይ ማሳረፍ ይችላል፡፡ እስኪደክመው ድረስም ደጋግሞ መነረት ይችላል፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ግን አንዱ ሌላውን የአምባገነንት መዓርግ ሲሸልመው ስትሰማ ነው፡፡ ሁሉም እኮ አምባገነኖች ናቸው፡፡ ልይነቱ የአቅም ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ታላቁ ዱላ የተሸው የአምባገነኖቹን አምባገነን ይሆናል፡፡ ልክ እንደ አመሪካ፡፡
አዎ! አመሪካ(የዓለም ታላቁ ዱላ ባለቤት) ከሆንክ በዓለም ለመጀመርያ ጊዜ በጃፓኖች ላይ የአቶሚክ ቦምብ ማዝነብ ትችላለህ፡፡ የሽንፈት ካባ እስክትከናነብ ደረስ ቬትናም ላይ ጦርነት ታውጃለህ፡፡ ቀጥለህ ኢራቅን ትወርና ሳዳምን ባስር ሳንቲም ገመድ ማንጠልጠል ነው፡፡ አፍጋኒስታን የጦር መለማመጃህ ትሆናለች፡፡ ልብያ ላይ የበረራ ማዕቀብ ትጥልና ኔቶን ልከህ ዶግ አመድ ማድረግ፡፡ ከዛም ደምህ ያፈላው ጋዳፊን ጨፈላልቀህ በደም ታጥበውና አስፓልት ላይ ዘርግተህ ይሐው ማለት ነው፡፡ ምን ይሳንሃል ጃል!በመላው ዓለም የጦር ስፈራ አለሃ፡፡
ምን ቀረህ? ኢራን! ቆይ ለስዋም መላ አይጠፋም፡፡ በኢኮነሚ ማዕቀብ ታሻትና ከተዳከመች በህዋላ እስራኤልን ልከህ እንዳልነበረች ታደርጋታለህ፡፡