Sunday, June 30, 2013
Heavy rain pouring down in Addis Ababa
Friday, June 28, 2013
ደደቢት
የካቲት 1966 ዓ.ም የአፄ ሃይለስላሴ ዘውዳዊው ስርዓት ከስሩ ምሶ የሚያፈራርስ የህዝብ ተቃውሞ አጋጥሞታል፡፡ሊወልቅ እንደ ተቃረበ ጥርስ መነቃነቅ ጀሯል፡፡የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
‹‹መሬት ላራሹ አትሽሹ››፣
‹‹ ወዝ አደር ወዝ አደር
ወዝ አደር ገበሬ
በርታ ለአነት ሆኗል
ጥገትና በሬ፡፡››
የሚሉና ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄዎች የሚያስተጋቡ መፈክሮችን አንግበው የአዲስ አበባ ጎደናዎችን
እያጨናነቁ ነው፡፡የታክሲ ሹፌሮች፣አስተማሪዎችና የመንግስት ሰራተኞችም ስራ የማቆም አድማ በማድረግ የአፄው ንጉሳዊ አገዛዝ ከስረ መሰረቱ
ለማናጋት ቆርጠው ተነስቷል፡፡የአፄው አገዛዝ ግን ቀጥተኛ መልስ ከመስጠት ይልቅ ‹‹የእንዳልካቸው ካቢኔ›› ምናምን እያለ የስልጣን
እድሜውን ለማራዘም ‹‹መሟዘዙን›› የሙጢኝ አለው፡፡
የዝያኔው ሞላጫ ወታደሮች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የደሞዝ ጭማሪ ይደረግልን በሚል ሰበብ ተጋግሎ በመቀጣጠል የነበረው
ህዝባዊ አመፅ የስልጣን ጥማቸውን ማርክያ አደረጉት፡፡ሰኔ 21 ቀን 1966 ዓ.ም የወታደራዊው አምባገነን ደርግ ምስረታ እውን ሆነ፡፡ቀጥሎም
የአምባገነንነቱን አመላካች የሆኑ አዋጆችን ማወጅ ጀመረ፡፡
ደርግ ‹‹ዴሞክራሲያዊ አስተደደር ለጭቁኖች አሁን››፣‹‹ኢትዮጵያ ወይም ሞት››፣‹‹ከምንም በላይ አብዮቱ››፣‹‹ኢትዮጵያ
ትቅደም›› ወዘተ የመሳሰሉ የውሸት መፈክሮች አንግቦ ማስተጋባት ሲጀምር እነኢህአፓ ደግሞ ‹‹ገዜያዊ ህዝባዊ አስተደደር አሁን››፣‹‹እናቸንፋልን››ወዘተ
በማለት የመልስ ምት ማስተጋባቱን ተያያዙት፡፡
የደርግ አዋጆች በቢሮከራሲዎች፣በአህአፓና በሜኢሶን ተቃውሞ ገጠመው፡፡የዘውዳዊው ስርዓት ርዝራዦችም ቢሆን ሙሉ በሙሉ
አልከሰሙም ነበር፡፡መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም ዘውዳዊው ስርዓት ተገርስሶ በወታደራዊው አምባገነን መተካቱን የኢትዮጵያ ህዝብ
መርዶ ሰማ፡፡ከዛም የደርግ አዋጆች መጉረፍ ቀጠሉ፡፡
ደርግ ሕዳር 12፣ 1967 ዓ.ም ‹‹ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን ዓላማ ለመፈፀም በመንግስት ወይም በመንግስት
በለስልጣን የሚወጡ አዋጆች፣ድንጋጌዎች፣ትእዛዞች እና ደሞቦች እንደይከበሩ፣በንግግር፣በፅሑፍ ወይም በማንኛውም መንገድ በግልፅ ሲያነሳሳና
ሲያደፋፈር ከተገኘ ከአንድ እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ከባድ የእስር ቅጣት ይቀጣል›› የሚል አዋጅ አውጥቶ ማንኛውም ሰላማዊ ተቃውሞ
ተቀባይነት እንደሌለው አሳወቀ፡፡ወደዳችሁም ጠላችሁም የኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ እኔ ነኝ አለ፤በድፍረት፡፡
ሰላማዊው የህዝብ ተቃውሞ ወደ ለየለት የእርሰ በርስ ደም መፋሰስ ተሸጋገረ፡፡ኢህአፓዎች ማንኛውም የነሱ ዓላማ ተቃዋሚ
መስሎ የታያቸውን ሁሉ ጭጭ ለማድረግ የከተማው ነጭ ሽብር አቀጣጠሉት፡፡ ደርግ ነጭ ሽብሩን በቀይ ሽብር መታው፡፡ኢትዮጵያ ደም አነባች፤በልጆቿ
ደም ታጠበች፡፡ሃገር የደም ሃይቅ ሆነች፤የደርግ ጀሌዎች የወንደሞቻቸው ደም በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አድርገው ከልክ በላይ ሰከሩ፤
ሰክረውም የዲያብሎስ ጭሆት ጨሁ… ኢትዮጵያ ትቅደም! እያሉ እማማ ኢትዮጵያን ለሞት አሳልፈው ሰጧት፡፡
ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ በጋራ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የብሄረ ትግራይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማሕበር ወደ ማገብት ተቀየረ፡፡ማገብት(ማሕበር
ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ…የብሄረ ትግራይ ተራማጆች ማሕበር) የከተማው ሰላማዊ ትግል እንደማያዋጣ ስለተገነዘበች ሌላ መንገድ መፈላለግ
ጀመረች፡፡ስብሰባዎች በድብቅ መካሄዳቸው ቀጠለ፤‹‹የከተማው ትግል አያዋጣም፤ረዥምና መራራ የትጥቅ ትግል›› ለማካሄድ ተስማሙ፡፡በዚህም
መሰረት ማገብት በሶስት ብዱኖች ተከፋፈለች፡፡
አንደኛው ብዱን የከተማው ስምሪት ለማጠናከር በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ተሰማራ፡፡ሁለተኛው ወደ አስመራ በማቅናት
እዛው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በትጥቅ ትግሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማግባባትና ከሻዕብያ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ወታደራዊ ስልጠና
ለመውሰድ ያለመ የቤት ስራ ተስጥቶታል፡፡ሶስተኛው ግን ወደ ደደቢት አመራ፤በምድረ ትግራይ የነፃነት ትግል በይፋ መጀመሩን ለማብሰር፤የነፃነት
ጅቦ ለማቀጣጠል፡፡
በአፄው ጊዜ የፓርላማ አባል የነበረው አየለ ገሰሰ(ስሑል) ለትጥ ትግል አመቺ የሆነ ቦታ እንዲያጠና በተሰጠው የስራ ድርሻ መሰረት በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በምዕራብ ትግራይ
በአድያቦና አስገደ ፅምብላ አከባቢ የምትገኘው ደደቢት ተመራጭ መሆኗን ለትግል ጓዶቹን አበሰረ፡፡ደደቢት በሱዳን ደምበር ትገኛለች፤
ጠላት ገፍቶ ቢመጣ ወደ ሱዳን ለማፈግፈግ፣ከነፍሰ በሎቹ የደርግ ሚጎች ለመሸሸግ፣ውሃና ምግብ በቀላሉ ለማግኘትና ህዝቡን ለማስታጠቅ
አቻ የማይገኝላት ስፍራ በመሆን ተመረጠች… ደደቢት፡፡
በጥናቱ መሰረት 11 የማገበት አባላት በየካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም አንድ ጓንዴ፣አንድ ካርባይን፣ አንድ ቶምሶን፣አንድ
ሳንጃ አልቢን እና አንድ ሽጉጥ(በአጠቃላይ አምስት ኋላ ቀር መሳርያዎች) ይዘው ደደቢት ደረሱ፡፡የትግል ችቦው ለኮሱ፤የነፃነት ትግሉ
በይፋ ተበሰረ፡፡ዳግባይ ወያነ ትግራይ እውን ሆነ፡፡የትግራይ ህዝብ እና መሬት እንደልማዳቸው ‹‹ለፋሽስቶች አልገዛም! በጭራሽ!››
ብለው ለነፃነታቸው ለመፋለም ተነሱ፡፡ትግራይ ዳግም አነባች… በሃዘን፣በችግር፣በግፍ ጭቆና፣በድርቅ፣በጦርነት እንደገና… እንደገና
የገሃንም ደጆች ተከፍተው በማይጠፋ እሳት ነደደች፣እንደበረዶ ድንገይ የበሚያደርግ ቅዝቃዜ ተቃጠለች፣በማያንቀላፋ… በቃኝ በማያውቅ
ዲያብሎስ ልጆቿን አጣች፡፡የትግራይ ሰማይ ይህን አይቶ ደነገጠ፤ክው አለ፡፡ ወደ ሰባተኛው ሰማይ ሸሸ…ቢጠብቁት ቢጠብቁት…ሳይመለስ
ለዘመናት እዛው ደርቆ፣ተንጠልጥሎ ቀረ፡፡ትግራይ በርሃብ ተመታች! ይህን አልበቃ ብሏት በምድር እሳት…በሰማይ እሳት … እንደ ቡርክታ
በእሳት ባህር ተጠበሰች፡፡
‹‹እንዳያሉፍት የለም…ያሁሉ ታለፈ
ታጋይ ህዝብ ልጅ…በደሙ በላቡ ደማቅ ታሪክ ፃፈ…››
ኢትዮጵያዊነትኢትዮጵያዊነት
እውነቱ በእውነተኞች ሲፈርጥ
የዋሾዎች፣የምስጦች ድብቅ ሴራ
ሲጋለጥ
ከንቱነታቸው ዓይኖቹን ሲያፈጥ፣ጥርሶቹን
ሲያገጥ
የወገን ልብ ቅቤ ሲጠጣ፣በደስታ
ጩቤ ሲረግጥ
ያኔ! ያኔ ነው መዝለል፣ያኔ
ነው መደሰት
በልዩነት ተከባብሮ መኖር፤ለሃገራዊ አንድነት
በዋሾዎች፣በምስጦች፣በትዕቢተኞች፣በጨቋኞች፣በአስመሳዮች
ላይ
በድህነት፣በኋላ ቀርነት፣በሙስና፣በመልካም
አስተዳደር እጦት ላይ
ቆፎው እንደተነካበት ንብ
ሆ! ብሎ በአንድነት መዝመት
ይህ ነው ያገር ፍቅር! ይህ
ነው ኢትዮጵያዊነት፡፡
ይህ ነው ታሪካችን
የኢትዮጵያዊነት መለያችን፡፡
እችን ግጥም መሳይ ለመቋጥ ያነሳሳህኝ ወገኔ መሳፍንትዘ ጎንደር ከታላቅ አክብሮት ጋር መስጋናየ ይድረስህ፡፡
Monday, June 24, 2013
Ethiotelecom assigns Andualem Admassie as Acting Chief Executive Officer (CEO)
Andualem
Admassie, formerly Chief Human
Resources Officer of the company, has received a letter that informs his assignment as an
acting Chief Executive Officer from Ethio telecom board chairman Deriba Kuma on
June 18, 2013.
The
contract between Ethio telecom and former CEO, Bruno Duthoit, has ended. The
French man, Bruno Duthoit …from France Telecom/Sofrecom, has served
Ethio telecom for 10 months now.
Bruno
said in his outlook email to all employees,” As I am ending my assignment in Ethio telecom, I want to thank all of you for the work done during last months
in order to support telecom development in the country, giving more
accessibility to people and better services.”
Bruno
added,” When I arrived in September 2012, I discovered a company on the path of
change. I was very happy to see - thanks to you - progresses in many domains,
happy to work with colleagues passionate by what they are doing, accepting
difficult challenges and committed to projects delivery.”
Directors,
Officers and Chief Officers have emotionally responded to his farewell email, thanking and praising him
for his diligence, brilliance, commitment and charismatic leadership as CEO of
Ethio telecom. To be frank, Bruno was humble, considerate and communicative with
all Ethio telecom employees which make him unique from the greedy wolves of the
old pensioners.
Ethio telecom
has been under the tutelage of France Telecom/Sofrecom for over three years
now. It is to be recalled that France Telecom overtook the managerial role of
the company for two and a half years contract amassing over 30 million Euros.
The white guys pledged that they would build “A World Class Operator” within
the given period. Though the outcomes show “A World Class Operator” has not yet
materialized.
***************************************************************
Ps:
Acting
(such as acting manager, acting officer, acting chief officer etc.) is a temporary
but a sure fire assignment at Ethiotelecom that serve as a stepping stone to the
next level.
Saturday, June 22, 2013
የጉዞ ማስታወሻ (ክፍል ሁለት)
የጉዞየ አቅጣጫ ከሕዋኔ ወደ ዓዲ ሽሁ የሚያመራ ስለነበር ሕዋኔ ወርጄ የደጃዝማች ወልደኪዳን አሸብር ህንፃን ፎቶ አንስቼ ፣በሕንጻው ላይ የተፃፉ ሁለት መፈክሮችም ዘግቤ ነበር… በክፍል አንድ የጉዞ
ማስታወሻየ፡፡መፈክሮቹን ለማስታወስ ያህል አንደኛው፣‹‹ትግራይን በጥፈራችን እንገነባታለን!!!›› የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደሞ ‹‹ዴሞክራሲያዊ
ሕገ መንግስት የገዢዎች ማነቆ ነው›› ይላል፡፡የባለፈው ጥያቄ እነዚህ መፈክሮች መቼ ተፃፉ፣ማን ፃፋቸው፣ ለምን? በማለት ትንሽ እንሻሽለው እና እንቀጥል፡፡
እነዚህ መፈክሮች የተፃፉት
ነፍሰ በላው የደርግ አገዛዝ ከ17 መራራ የትግል ዓመታት በኋላ ከምድረ ትግራይ ተጠራርጎ እንደተባረረ ነበር… በ1980ዎቹ፡፡የደርግ
አገዛዝ የተገረሰሰበት ማግስት ትግራይ ብሎም መላው ኢትዮጵያ በማሕበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋበሮች የፈርስራሽ ካቦች
ክምር ሆኖው ነበር፡፡ያች የፈራረሰች ብሔርና ሃገር መልሶ ለመገንባት ነበር ታድያ ‹‹ትግራይን በጥፈራችን እንገነባታለን!!!››፣‹‹ዴሞክራሲያዊ
ሕገ መንግስት የገዢዎች ማነቆ ነው›› እና ሌሎች መፈክሮች በመላው ትግራይ ያስተጋቡ የነበረው፡፡
እነዚያ መፈክሮች ከተፃፉ
ብያንስ 20 ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ለዛም ነው ቀለማቸው ደብዝዞ የተፃፉበት ህንፃም ሊፈርስ ተቃርቦ የሚታየው፡፡ግን የትግራይ ችግሮች
ተፈቷል? ህዝቡ ከአሳፋሪው የድህነት ማቅ ተላቋል?ያበሞቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የምርጥ ልጆቹን ህይወት ገብሮ በትግሉ ያገኘው ድልስ ዴሞክራስያዊ
መብቶቹን አንዲከበሩለት እስችሎታል?ወይስ በድሉ ማግስት ከአፅናፍ አፅናፍ ያስተጋቡ የነበሩ መፈክሮች ቀለማቸው ደብዝዞ ከነመኖራቸው
እንደተረሳው ሁሉ የህዝቡ ዴሞክራስያዊ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችም ተረስተው ይሆን?የሃገራችን መጣኔሃብታዊ እድገት ታድያ
ማን ይሆን አያጣጣማቸው የሚገኘው?ጉዟች ን ይቀጥላል፤ትእዝብታችንም
እንዲሁ እየቀጠለ ነው እና የጥያቄዎቹ መልስ ወደፊት የምናገኘው ይሆናል፡፡
ከሕዋኔ ወደ ዓድ ሽሁ
የተሳፈርንባት አባዱላ መኪና በተሳፋሪዎች ብዛት ከልክ በላይ ተጨናንቃለች፡፡ሰው በሰው ላይ ተጭኗል፡፡ትርፍ መቀመጫ ቀርቶ ተሳፋሪዎች
ንፁኅ አየር የሚተነፍሱበት ክፍተትም አልነበራትም፡፡ከመጠን በላይ ተጠጋግተው የተቀመጡ ተሳፋሪዎች ሳይወዱ በግድ ትንፋሽ ለትንፋሽ
እየተለዋወጡ ለብዙ ዓመታት በጦርነት ታርሰው ተምሰው ጥርሶቻቸው ገጠው፣ፀጉራቸው ተመላልጦ የተቀረውም ሸብቶ በሚታዩት ተራሮች እየተጠማዘዙ
ይወርዳሉ ይወጣሉ፡፡ከቤትመራ ጀምሮ፣አሁን ፈራርሳ እንዳልነበረች በሆነቸው ዓዲጉራ አልፎ፣እምባ አላጀን ወደ ምዕራብ ትቶ ዓድሽሁ
የሚያደርሰው ጠመዝማዛና ተዳፋት መንገድ መጫን ካለባት በላይ በተጫነች አባዱላ መጓዝ ቀርቶ በእግርም ቢሆን በጣም ያስፈራል፡፡በወረዳ
እምባ አላጀ ከተማ ዓድሽኁ ለስም ብቻ ፖሊሶች አሉ… ተራፊክ ፖሊሶች ጭምር፡፡ነገር ግን መኪኖች ያን ያህል ከልክ በላይ ተሳፋሪዎ
ቢጭኑም ሃይ የሚላቸው አልነበረም፡፡ፖሊሶቹ የተቀጠሩት ደሞዝ ለመቀበል እንጂ ህዝብ ለማገልገል መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች በፍፁም
አይታዩም፡፡ከከተማ ውጭ ያለው አደገኛ የአስፓልትና የጠጠር መንገድ ማንም ተቆጣጣሪ የለውም፡፡አሽከርካሪዎች እንዳሻቸው ይጭናሉ፤
እንዳሻቸው ሒሳብ ያስከፍላሉ፡፡
በስንት ፀሎትና ስለት
ዓድሽሆ ደርሰናል፡፡ህሊና ቢስ፣ጥርስ አልባ ፖሊሶች በከተማዋ ውስጥ ሲርመሰመሱ ነበር፡፡ያሁላ ስራ ፈት፣ያሁላ ከርሳም ሙሰኛ የተከበረውን
የፀጥታ አስከባሪዎች መለዮ ለብሰው፣ ቦርጮቻቸውን ታቅፈው በኩራት ይንጎማለላሉ፡፡ከዓድሽሁ ተወልጄ ወዳደግኩባት ደላ(ስለዋ) ለመጓዝ ሚኒ ባስ ተሳርኩኝ፡፡ሚኒ ባሷ በተሳፋሪዎች ብዛት ተጨናንቀው በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እንደሚርመሰመሱ የከተማ አውቶብሶች ጢቅ ብላ ሞልታለች፡፡ህፃናት የዘሉ እናቶች፣አቅመ ደካማ ሽማግሌዎችና በሽተኞች ሳይቀር ለመተንፈስ ሲጣጣሩ ማየት አንጀት የሚበላ ነበር፡፡አንድ ትራፊክ ፖሊስ ሚኒ ባሷን አይቶ እንዳላየ፣ አንዲት ቃል ሳይተነፍስ ተቷት ሄደ… የተሳፋሪዎች ድህንነት ለማረጋገጥ ሳይሆን ሚኒ ባሷ ለባለቤቶቿ ትርፍ ማግበስበስ እንድትችል ለመቆጣጠር የተቀጠረ ይመስላል፡፡
በቲኬታችን የተፃፈው
የገንዘብ መጠን 13 ብር ቢሆንም እንደንከፍል የታዘዝነው ግን 20 ብር ነበር፡፡እኔ ለምን ብዬ በመከራከር መብቴን ለማስከበር ብሞክርም
ከሚኒ ባሷ እንድወርድ ነበር የተነገረኝ፡፡ወደ ወረዳው ፖሊስ ጣብያ ለማመልከት በዝግጅት ላይ እያለሁ አንድ አንድ ወገኖች ‹‹ምንም
ለውጥ ለማታመጣበት ጉዳይ ጊዜህን በከንቱ አታጥፋ፡፡አሁን በፊት ብዙ ጊዜ ሞክረን ሊሳካልን ስላልቻለ ነው ሰንወድ በግዳችን አሜን
ብለን ለመቀበል የተገደድነው፡፡በዚህ ወረዳ ገንዘብ እንጂ ሰው ተናግሮ ማሳመን አይችልም፡፡›› የሚል ምክር ሰጡኝ እኔም 20 ብር
ለመክፈል ተገደድኩኝና ጉዞ ተጀመረ፡፡እማይደረስ ነገር የለምና መኪናዋ ዳገት መውጣት ሲያቅታት በእግራችን እየተጓዝን፣በሜዳዎችና
ቁልቁለቶች ደግሞ በፍርሃት ትንፋሻችን ይዘን ፈጣሪያችንን እየለመንን ደላ ደረስን፡፡
ደላ የድሮ ወረዳ ስለዋ
ፅሕፈት ቤት የነበረች የገጠር ከተማ ነች፡፡አብዛኛው የትግራይ ክፍል በደርግ አገዛዝ ስር በነበረበት ጊዜ ስለዋ ከቀደምት የህወሓቶች
ነፃ ግዛት አንዷ ነበረች፡፡የስለዋ ጋራ ሸንተረሮች እንደ ኮብራ መርዝ በሚረጩና ለነፃነታቸው ለመሰየፍ ወደ ኋላ በማይሉ ማሊሻዎች
ይጠበቁ ነበር፡፡ይህን የሚያውቁ ህወሓቶች በስለዋ ተራሮች የስልክ መገናኛ ምሽጎች ነበሯቸው፡፡ይህን የተገነዘቡ 20 የሚሆኑ የታጠቁ
የድርግ ወታደሮች ህጉጦ በሚባል ተራራ ላይ የነበረው የስልክ መገናኛ ለማውደም አሪ የሚባል አከባቢ ሲደርሱ የአከባቢው ማልሻዎችና
አርሶ አደሮች ተሰባስበው በመክበብ ብረት ያለው በብረት፣ብረት የሌለው ደግሞ በድንጋይ፣በገጀራና በዱላ ተረባርበው ለወሬ ነጋሪ ሳያተርፉ
ሁሉንም ገደሏቸው፡፡በዚህ የተነሳ አንድ ዛሬም የማይረሳ ዘፈን ይዘፈን ነበር በመላው ሰለዋታይ፡-
አታሪእሐኹም ዶ አሪ
ዝተገበረ
ንካላሽን ጎጀሞ ስዓረ
ይባል ነበር፡፡
አያችሁ ወይ አሪ የተደረገው
ለክላሽን ገጀራ ያሸነፈው…
ለማለት ነው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)


