Tuesday, September 1, 2015

አእምሮ የሌለው ሕዝብ…( ነጋድራሰ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ፣ ስራዎች)




የባለ ምጥቁ አእምሮአርቆ አሳቢእጅግ ታላቅ ሰው...የገብረ ሕይወት ባይዳኝ ስራዎችን እስካሁን ባለማንበቤ ምንኛ ቆጨኝ መሰላችሁ፡፡እስኪ፣ እርሳቸው ከፃፏቸው ያስገረሙኝን ቃል በቃል ላካፍላችሁእንደኔ ያላነበባችሁ ጓደኞቼ በእርግጠኝነት ትገረማላችሁ፡፡ እርሳቸው ይህን ከፃፉት አንድ መቶ ዓመታት( አንድ ክፍለ ዘመን) እንደ ጉድ እብስ ብሏል፡፡ያም ሆኖ ግን፣ የእርሳቸው ወርቃማ ምክሮች ዛሬም ድረስ ተግባራዊ ሆኗል ብየ ለመናገር ያስቸግረኛል፡፡
‹‹ምነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንቅልፍህ መቸ ትነሳለህ? በዓለም ላይ የሚደረገውን ነገር ለማየትስ ዓይንሀን መቸ ትከፍታለህ?
አእምሮ በአእምሮ ካልሆነ በቀር በሌላ አትታገድም፡፡ስለዚህ ወዮለጽ በድንቁርና ለሚቀመጥ ሕዝብ ውሎ አድሮ ይደመሰሳልና፡፡››(ገፅ 22)
መንግስታችንም እንድትቀና የሚከተሉት አስር ነገሮች በቶሎ ቢፈፀሙ ማለፍያ ነበር፡፡
1.
ለመንግስት የሚሆን ገንዘብና ለንጉሱ የሚሆነውን ገንዘብ በስርዓት ይለይ
2.
ሕዝቡ ለመንግስት የሚከፍለው ግብር እንደየሀብቱ መጠን ቁጥር ሁኖ ይታወቅለት
3.
ሕዝቡም የሚከፍለው ግብር በብር እንጂ በእህል፣ በማርም በፍሪዳም አይሁን፡፡የመንግስት ስራ ሁሉም በባላገር አይሰራ፤ በባለ ደሞዝ እንጂ፡፡
4.
የአማርኛ ቋንቋ ገና ስዋስው አልተበጀለትም፡፡ ስለዚህ መንግስታችን ከያገሩ ስዋስው የሚያውቁትን ሊቃውንት ሰብስቦ ያማርኛን ቋንቋ ስዋስው ቢያስወጣ ደግ ነው፡፡
5.
ፍትሐ ነገስታችን ከዛሬው ያደባባይ ስርዓት ጋር አይስማማም፡፡ስለዚህ መንግስት የስርዓት አዋቂዎችን ሰብስቦ ከኤሮጳ ስርዓት ጋር የተስማማ ፍትሐ ነገስት ያውጣ፡፡የተፃፈ ስርዓት የሌለው መንግስት ብዙ ዕድሜ የለውም፡፡
6.
ያገራችን ሰራዊት ስርዓት የለውም፡፡ ስለዚህ የኤሮጳን መኳንንት አምጥተው ሰልፍን ቢማር ማለፍያ ነበር፡፡
7.
የዛሬው የመንግስታችን ብር የተበላሸ ና፡፡ ስርዓት ውል የለውም፡፡ባንዱም አውራጃ በጨው በሌላው በጥይት የሰፈራል፡፡
8.
ላገራችን ነጋዴ ስርዓት እስኪወጣለት ድረስ መንግስታችን አይቀናም፡፡
9.
ሕዝቡ ባንድ መንግስት ውስጥ መሆኑን አጥብቆ እንዲያውቀው አገሩን የሚዞሩ ተቆጣጣሪዎች ይሸሙበት፡፡
10.
የሃይማኖት አርነት ይታወጅ፡፡የሃይማኖት አርነት ጥቅም መሆኑን የማያውቅ ብዙ ሰው ይኖራል፡፡ያገራችን ሰው የተዋህዶ ሃይማኖት ከሁሉ ሃይማኖት ይበልጣል ብሎ ያምናል፡፡ በልጦ ግን ምን ረባን? ማንስ አወቀው? …ደግሞም ባገራችን አንድ የድንቁርና ነገር አለ፡፡ ሃይማኖቱ ተዋህዶ ያልሆነ ሰው አንደ ርኩስ ይቆጠራል፡፡ይህም እጅግ ያስቃል፡፡ አእምሮ የሌለው ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ሳያውቅ የእግዚአብሔር ጠበቃ ሊሆን ይወዳል፡፡
ሃይማኖት የልብ ነገር ነው፡፡ስለዚህ ሰማያዊው ንጉስ እንጂ የዚህ ዓለም ንጉስ አይቆጣጠረውም፡፡(ገፅ 23-28)
በአጠቃላይ፣ አእመሮ የሌለው ሕዝብ የሚከተሉትን ወሳኝ ነገሮች አይኖሩትም፡፡