ጊንጥና እንቁራሪት አፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ ከሚገማሸር ውንዝ ዳር ተገናኙ፡፡ጊንጥ ወደ እንቁራሪት ጠጋ ብላ በጀረቧን አዝላ ወንዙን እንድታሻግራት በትህትና ጠየቀቻት፡፡የጊንጦች አመል ጠንቅቃ የምታውቀው እንቁራሪት ‹‹ወንዙን ባሻግርሽ ደስ ባለኝ፤ ግን ትነድፊኛለሽ›› ስትል መለሰችላት፡፡
ጊንጥ ‹‹በጭራሽ አላድርገውም፤ አልነድፍሽም፤ እባክሽን ወንዙን አሻግሪኝ›› በማለት እንቁራሪቷን
ጊንጥ ‹‹በጭራሽ አላድርገውም፤ አልነድፍሽም፤ እባክሽን ወንዙን አሻግሪኝ›› በማለት እንቁራሪቷን
ተመፀነቻት፡፡
‹‹አይ፣ አይሆንም፤ እንደማትነድፊኝ እርግጠኛ የምሆንበት መንገድ የለም››መለሰች እንቁራሪት፡፡
‹‹አይ፣ አይሆንም፤ እንደማትነድፊኝ እርግጠኛ የምሆንበት መንገድ የለም››መለሰች እንቁራሪት፡፡
‹‹ሙች! አልነድፍሽም፤ የግድ መሻገር ስላለብኝ እባክሽን ተባበሪኝ›› ጊንጥ ተማፀነች፡፡በመቀጠልም ‹‹እስኪ አስቢው፤ ከነደፍኩሽ እኮ ትሰምጪያለሽ፤ እናም እኔም እብሬሽ እሰምጣለሁ ማለት ነው፡፡የምፈልገው ግን ወንዙን በሰላም መሻገር እንጂ ሰምጬ መሞት አይደም፡፡ዓላማየ እንደሱ ቢሆንማ አንችን ለምን አስቸግርሻለሁ? ቢሳካልኝም ባይሳካልኝም፣ ወደ ጎርፉ ዘልዬ አልገባም?›› በማለት እንቁራሪትዋን ለማሰመን አበክራ መጎተቻት፡፡
እንቁራሪት የማትሰማማበት አሳማኝ ምክንያት አልነራትምና ጊንጥዋን አመነቻት፡፡ጊንጢ በእንቁራሪትዋ ጀርባ ተፈናጠጠችና ተዛዝለው ወደ ጎርፉ ገቡ፡፡በወንዙ መሃል እንደደረሱ፣ ጊንጥ ሆዬእንቁራሪትዋን ነደፈቻትና ተያይዘው መስመጥ ጀመሩ፡፡እንቁራሪቷ ለመሞት እያጣጣረች እያለች ‹‹ለምን?›› ስትል ጊንጥዋን ጠየቀቻት፡፡የጊንጧ
መልስ ‹‹ጊንጥ እኮ ነኝ፤ ከጊጥ ሌላ ጠብቀሽ ነበር?
በቃ፣ ተፈጥሮዬ ስለሆነ ነደፍኩሽ›› የሚል ነበር፡፡
ይህ አስገራሚ ተረት ተረት የኤሶፕ እንደሆነ ይነገራል፡፡የሃገራችን ታሪካዊና ነባራዊ ሁኔታዎችን ጥርት አድርጎ የሚያሳይ ሆኖ ስላገኘት እንደ መንደርደርያ
ልጠቀምበት ወደድኩ፡፡እንቁራሪትዋ የኢትዮጵያ
ህዝብ ነች፡፡ጊንጥዋ ደሞ ድሮና
ዘንድሮ በኢትዮጵያ የነገሱ
አምባገነኖችና ሹመኞቻቸውን ትወክላለች፡፡
ሲጀመር መሪዎች መሪ መሆን ያለባቸው የሚመሩት ህዝብ ይሁንታ ሲሰጣቸው ብቻ ነው፡፡የህዝብ
ይሁንታ ሊያገኙ የሚችሉት ድሞ ህዝቡን እየመሩ የህይወት ወንዝን ሊያሻግሩት እንደሚችሉ ሲታመንባቸው ነው፡፡ለተወሰኑ ዓመታት ተፈትነው
ህዝቡን የህይወት ወንዝን ሊያሻግሩት የማይችሉ መሆናቸውን ሲረጋገጥም በሌሎች መተካት አለባቸው፡፡በአጭሩ መሪዎች ህዝብን ለማገልገል
በህዝቡ ፍቃድ የሚሸሙ እንጂ በጉልበታቸው በህዝቡ ጫንቃ የሚፈናጠጡ ጊንጦች መሆን አልነረባቸውም፡፡
በሃገራችን የነበረውና ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግን የዚሁ ግልባጭ ነው፡፡መሪዎቹ ህዝቡን
መርተው ወንዙን ማሻገር ሲገባቸው ህዝቡ መሪዎቹን ተሸክሞ ኢንዲያሻግራቸው ያስገድዱታል፡፡የጊንጥዋን ያህል እንኳን ለጊዜው አሳማኝ
ምክንያቶች ማቅረብ አይችሉም፡፡ህዝቡ የግድ እንዲሸከማቸው ያስገድዱታል፡፡ተሸከሞ የህይወት ወንዙን ሊያሻግራቸው ከጎሩፉ በሚታገልበት
ወቅት ግን ጀርባውን ይነድፉታል፡፡ከዛም ህዝቡም መሪዎቹም አብረው ይሰምጡና ጎርፍ ይወስዳቸዋል፡፡ለምን ቢባል፣ የመሪዎቹ ተፈጥሮ
እንደዛ ሰለሆነ፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ የሚታወሱ ነገስታት እንዳለ ከዚህ የተለየ መንገድ አልተከተሉም፡፡የኢትዮጵያ
ህዝብ አፄ ኃይለሥላሴን ለ40 ዓመታት ተሸክሟቸዋል፡፡በነዝያ ዓመታት ግን የህዝቡን ጀርባ ሲነድፉ ነው የኖሩት፤ በመጨረሻም ከህዝቡ
ጋራ ጎርፍ ወሰዳቸው…የአብዮት ጎርፍ፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ የደርግ ስርዓትንም ለ17 ዓመታት በጀርባው ተሸክሞ የኑሮ ወንዙን ለመሻገር
የቻለውን ሁሉ አድርጓል፡፡መክፈል የነበረበት መስዋእት ሁሉ ከፍሏል፡፡
ደርግ ግን የህዝቡን ጫንቃ ነደፈውና አብረው ሰጠሙ፤ የኑሮ ጎርፍም ወሰዳቸው፡፡አሁን
ያለው ስርዓትም ለ24 ዓመታት ተሸክመን የችጋር ወንዙን ለመሻገር በመጣጣር ላይ እንገኛለን፡፡በጎርፉ መሃል እያለን በተደጋጋሚ ጀርባችንን
ነድፎናል፡፡ሆኖም ግን ሰውነታችን ለንድፍያዎች አዲስ ባለመሆኑና ያለፉት ስርዓቶች ከተውብን ጠባሳዎች ጋራ በመላመዱ ብቻ ተዝለፍልፈን
ልንወድቅ አልቻልንም፡፡ለወደፊት ግን ይህ ነገር ቀጣይነት የሚኖረው አይመስለኝም፡፡አንድም ተናዳፊ መሪዎቹን ከችጋር ወንዙ ውሰጥ
ጥሎ ወደ ብልፅግና ጎዳና ይሻገራል አልያም እንደ ድሮው አብረው ይሰምጣሉ፡፡
እንደኔ እምነት ከሆነ፣ ህዝቡ ከታሪክ መማር አለበት፡፡ከነገስታት አክሱም፣ላሊበላ፣ጎንደር፣ትግራይና
ሽዋ ጋር አብሮ በጎርፍ በመወሰዱ ከዓለም የብልፅግና ቁንጮነት ተንከባልሎ ወርዶ ወርዶ ወርዶ… ዛሬ ላለበት የድህነትና የኋላ ቀረነት
ተምሳሌትነት ደርሰዋል፡፡ከዚህ በታች ግን መውረድም መዋረድም አይችልም…መሞትና ጨርሶ ከምድረ ገፅ መጥፋት እንጂ፡፡ይህ እንዳይሆን
የኢትዮጵያ ህዝብ ጊንጦችን አምኖ መሸከም የለበትም፡፡በየዋህነቱ ተታልሎም ይሁን ተገድዶ የተሸከማቸው ጊንጦችም ተባብሮ ከጫንቃው
አሽቀንጥሮ ሊወረውራቸው ይገባል፡፡ጊንጦችን ተሸክሞ ያደገው ጉዞ ስኬት አልባ ነበር፡፡ጊንጦችን በጊንጦች መቀያየርም ከንድፍያ አልታደገውም፡፡
ከአሁን ወድያ ግን በቃኝ ማለት አለበት…አሁን ያለውን የምርጫ ጭላንጭል ተጠቅሞ ከዘመኑ
ጋራ አብረው መራመድ የሚችሉ መሪዎቹን መምረጥ አለበት፡፡የፈለገው ቢመጣም ጦረኛ ጊንጦችን ማመን የለበትም፡፡በጠብ መንጃ አፈሙዝ
ዙፋን የተቆናጠጡ ሁሉ ጊንጦች እንደሚሆኑ ከታሪክ ተምረናል፡፡ስለሆነም፣ ነፍጥ አንግበው ህዝቡን ከጭቆና ቀንበር አላቅቀን፤ የነፃነት፣የሉዓላዊነትና
የዲሞክራሲ ባለቤት እናደርጋለን የሚሉ ሁሉ ግባቸው የስልጣን ኮርቻን መቆናጠጥ ብቻ መሆኑን ልንስተው አይገባም፡፡ጦረኛ ነፃ አውጪ
ሊኖር አይችልም፡፡
ጦርነት የነበረውን ያወድማል እንጂ የሚጨምረው ነገር እንደማይኖር ከታሪክ ተምረናል፡፡በጦርነት ዘመናዊ የስልጣን
ሽግግር ሊኖር አይችልም፡፡በታሪካችን የተከሰቱት የስልጣን ሽግግሮች ዘመናዊ ስላልነበሩ አሁን ለለንበት የድህነትና የኋላ ቀርነት
ተምሳሌትነት ተዳርገናል፡፡ከአሁን በኋላ ግን ይብቃው፤ እባቦችና ጊንጦች በእርግቦች ይተኩ፡፡
No comments:
Post a Comment