Wednesday, August 21, 2013

‹‹መለስ መሞቱን ስሰማ በጣም ደስ ብሎኛል››ተመስገን ደሳለኝ

‹‹መለስ መሞቱን ስሰማ በጣም ደስ ብሎኛል››ተመስገን ደሳለኝ

ባለፈው ዓመት አንድ በጣም ታዋቂ ወጣት ጋዜጠኛ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አቡነ ጴጥሮስ ግቢ የክብር እንግዳ ሁኖ እንደሚመጣ የሚገልፅ ማስታወቅያ አንበብኩኝ። የክብር እንግዳው በቀጠሮው ቀን ከች አለና ቃለ መጠይቁ ተጀመረ።የጋዜጠኝነትና ኮምኒኬሽን ተማሪው ይጠይቃል ተመስገን ደሳለኝ ትክክለኛውን ሳይሆን እንደመጣለት ይመልሳል።የጋዜጠኝነትና ኮምኒኬሽን ተማሪዎች ድጋፋቸውን ሞቅ ባለ ጭብጨባ እየገለፁለት ቃለ መጠይቁ ቀጠለ።

ተማሪው ‹‹የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት ስትሰማ ምን ተሰማህ?››
ተመስገን‹‹ምንም››
ተማሪው‹‹ምነው፤ፋራህ እንዴ?››
ተመስገን‹‹እኔ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም፤እንደውም እውነቱን ልንገርህ፤መለስ መሞቱን ስሰማ በጣም ደስ ብሎኛል››

ዛሬ የቀድሞው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በሞት ከተለዩን ድፍን ዓመት ሞላን።በጣም የሚወዱትና የሚያከብሩት መሪያቸው በሞት ያጡ ኢትዮጵያውያን ዓመት ሁኖቸዋል።መለስ ፖለቲከኛ ብቻ አልነበረም፤የሃገር መሪ ብቻ አልነበረም፤በኢህአዴግነቱ ወይም በህወሓትነቱ ብቻ መፍረጅ አልነበረበትም።የሶስት ልጆች አባት፣ብዙ የስጋ እህቶችና ወንድሞች ያሉት፣ሰው በመሆኑ ብቻ ሞቱን ያሳዘናቸው ብዙ ወገኖች አሉ።እነዚህ ወገኖች ለተመስገንም ወገኖቹ ናቸው።ተመስገን ወገኖቹ አዝነው ሲያለቅሱ አይቶ ተደስተዋል፤እነሱ ሲያለቅሱ እሱ ይስቅ ነበር፤ ደነሰዋል፤ጭፍረዋል ።ይህ ነበር በጣም ታዋቂ ወጣት ጋዜጠኛ ያሰኘው።

እነ ተመስገ ከተደሰቱ ዓመት ሁኖቸዋል።ወገኖች ሲያለቅሱ በአውጫጭኝ ተገድደው እንዳለቀሱ አድርገው ነው የሚፅፍፉት፤የሚናገሩት።
ተመስገን ደሳለኝ በጭፍን ጥላቻ የተመረዘ ፍፁም ጨለምተኛ ነው፡፡ጨለምተኝነቱ ተቋምና ግለሰብ፣ግለሰብና የግለሰቡ አሰተሳሰብ ለይቶ እንዳያውቅ ጋርዶታል፡፡ተመስገን ማንም የኢህአዴግ አባልን በጠላትነት ይፈርጃል፡፡ማንም ሰው ከተመስገን ጋር በሃሳብ አልተግባባም ማለት ጠላቱ ሆኗል ማለት ነው፡፡ለዛም ነው ‹‹በመለስ ሞት በጣም ተደሲቻለሁ›› ያለው፤መለስ ጠላቱ ነውና በሞመቱ ተደሰቷል፡፡ ጨለምተኞች ከተደሰቱ ዓመት አልፏል፡፡ግን እነዚህ ጨለምተኞች መለስን (እንደ ግለሰብ) ለምን ይህን ያህል በጥርሳቸው ውስጥ አስገቡት?
 
ምክንያቱም መለስ ጥርት ያለ ራኢ ያለው መሪ ስለነበረ ነው፤የመለስ ራኢዮች የቀን ቅዠቶች አይደሉም፡፡መለስ እንደ ጨለምተኞቹ ሲተኛ የሚቃዥ አልነበረም፤እንደ ጨለምተኞቹ ጉንጮቹን በጫት ወጥቆ አልነበረም የሚቃዠው፡፡መለስ ሙሉ ትኩረቱን ሰብስቦ ነበር የሚያልመው፡፡የቲ.ኢ ላውረንስ የሚከተለው አባባል መለስን በይበልጥ ይገልፀዋል፡፡
 ‹‹ሁሉንም ሰዎች ያልማሉ፤ነገር ግን እኩል አያልሙም፡፡ አቧራ በረጋበት አእምሯቸውን ሌሊት የሚያልሙ ሰዎች ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ቅዠት ሁኖ ያገኙታል፤ቀን የሚያልሙ ሰዎች ግን እጅግ በጣም አደገኞች ናቸው፤ምክንያቱም ህልማቸውን እውን ለማድረግ በትኩረት እርምጃ ሊወስዱ ስለሚችሉ ነው፡፡››
የጨለምተኞች ስራ የበለራኢዮች ሃሳብና ስራ መተቸት፣በጭፍን መቃወምና ማብጠልጠል ነው፡፡የተቃውሞቸውና የትችታቸው መንስኤ ግን በመረጃና በአመክንዮ የተደገፈ ሳይሆን እንዲሁ ከጭፍን ጥላቻ የተነሳ ነው፡፡የጨለምተኞችና አጉል ተጠራጣሪዎች አስተሳሰብ ‹‹You can win…ማሸነፍ ይቻላል›› በሚባለው የሼቭ ኬራ መፅሐፍ በገፅ 13 ላይ በግርድፉ እንደሚከተለው ሰፍሮ ይገኛል፡፡
ሮበርት ፉልተን የተባለ አሜሪካዊ ኢንጂኔር በእንፋሎት የምትሰራ ጀልባ ሰርቶ አዲስ ግኝቱን ለተመልካቾች ለማሳየት ሃድሰን ወደ ሚባል ወንዘ ያመራል፡፡ከተመልካቾቹ መሃል ጨለምተኞችና አጉል ተጠራጣሪዎችም አብረው ነበሩና ‹‹ጀልባዋ በፍፁም አትነሳም፤ አትንቀሳቀስምም›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጡ፡፡ፉልተን ግን ጀልባዋን አስነሳት፡፡የፉልተን ጀልባ ወንዙን እየቀደደች ሰትቀዝፍ የተመለከቱ ጨለምተኞች ‹‹በፍፁም አትነሳም›› ሲሉ እንዳልነበር በ180 ድግሪ ይታጠፉና ‹‹በቃ! ከንግዲህ ወደያ ጀልባዋ መቆም አትችም!›› እያሉ ጨሁ፡፡ይሁን እንጂ ፉልተን በአጉል ተጠራጣሪዎቹ አስተያየት አልተበገረም፤ከተመልካቾቹ እይታ በጣም ሳይረቅ የፈጣሪነት ክህሎቱን ያስመሰከረባት ጀልባውን እየነዳ ቅድም ወደ ነበረችበት ቦታ መለሶ አስቆማት፡፡

መለስን እንደ ፖለቲከኛ ሳይሆን እንደ ግለሰብ በጭፍን እየተቃወሙ ያሉ ጨለምተኞች እንዲህ ናቸው፡፡የኢትዮጵያ ህዳሴን በጭፍን ተቃውመዋል፤የህዳሴ ግድብ እቅድን በጥብቅ ተቃውመዋል…እንደውም እነ ጉምበት ሰባት እማ ሃገራቸውን ለሽያጭ በማቅረብ ከግብፅ አክራሪዎች እስከ መከራከርም ደረሷል፡፡ዓለም አቀፍ መጋናኛ ብዙሐን ‹‹ኢትዮጵያ እያደገች ነው›› ብለው ሲዘግቡ የኛው ጨለምተኞች ‹‹ኢትዮጵያ እየደኸየች ነው፤አንደነቷ አደጋ ላይ ወድቋል…›› እያሉ ነው የሚደሰኩሩብን፡፡ምክንያቱም ለእነሱ የሚታያቸው ጥፋት እንጂ ልማት አይደለምና ነው፡፡ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ ለመቁጠር የሚያታክቱ ግልፅ ችግሮች አሏቸው፤የተቃዋሚዎች ትኩረት ግን በነዚህ እንከኖች ላይ ሳይሆን በግለሰቦች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው፡፡ይህ ግን ለሃገር ከሚያበረክተው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፤መክንያታዊነትና የመቻቻል ባህልን ስለሚያቀጭጭ፡፡



11 comments:

  1. I was so sad by the death of the late PM. But this guy has the right to be happy. People were happy when Gadhaffi was dead or people were happy when Sadam Hussein was dead. I won't be surprised if those who tasted the strong fist of his dictatorship celebrated. Despite his vision to build the country, Meles was a dictator. He committed massacre in more than one occasion in his 21 year of power and the one we saw before our own eyes being the post 97 election massacre in Addis Ababa!! So, don't expect no one to celebrate his death...

    ReplyDelete
    Replies
    1. Teddy, don't like. why not say I was happy in short instead of being soft spoken at start and talking loads of shit.

      Delete
    2. Okaaaaaayyyy, you are from Spain,ah. I wonder why you Diasporas, Keras or Elforas, whatever your title suddenly become all knowing and try to seem like rational once you lay your leg out of the country.I am not affiliated to any political party or have the slightest interest in politics but the reflection of people like you makes me sick!!!!! please visit your post you are contradicting with yourself. Don't pretend to be what you are not.Please know what you are writing before reaching the comp. Thank you for your understanding

      Delete
  2. ይድርስ ለደደቦች ደደብ የደንቆረዎች ሊቀ መንበር ለእኩይ ቱጉሃን ዘ መንበረ ጨለምተኝነት ሊቀ ሊቃነ እርኩሳን ወእጨጌ ዘካሃድያን የዘረኞችና የትምክህተኞች ታሪክ የለሽ መልእክት ኣመላላሽ ፈረሰኛ አቶ ተመስገን ደሳለኝ ባሉበት
    መለስ መሞቱ ደስ ብሎኛል ነው ያልከው.ለመሆኑ መለስ የሞተው ለእንዳንተ ኣይነት ገልቱ ደደብ ኣስተሳሰብ ያለቸው ጭምር ነው ነፃ ለማውጣት እንደ እየሱስ ራሱን መስዋእት የሆነው.ደንቆሮ ስለሆንክ ነው እንጂ በኣደባባይ በነፃነት እንድትለፈልፍ እድል እንድታገኝ ያደረገህ የሱና መሰለቹ ብርቅየ የህዝብ ልጆች የተሰዉበት ስጦታ ነው.ኣነተ ካሃዲ በማንና ለምን እንደምትኖር የማተውቅ የበላበት ድስት የሚሰብር ባለጌ ስለሆንክ እንጂ በዚህ ንግግርህ በኣባቶችህ ዘመን ቢሆን ንሮ ያሰቅልህ ነበር.በጥላው ላይ ሁኖ ጥላው የሚረግም ጥላቢስ ከሃዲ ነህ. ያም ሆነ ይህ መለስ ግን ህያው ነው. ኣንተ ግን በካሃዲነትህ እድሜ ልክህ እያፈርክና እየባነንክ ትኖራለህ
    ከ ሃ ዲ!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. Lemen bomb atwewrim? Be denb abyotawi demcracy tetmeqhal
      "ደደቦች ደደብ የደንቆረዎች ሊቀ መንበር ለእኩይ ቱጉሃን ዘ መንበረ ጨለምተኝነት ሊቀ ሊቃነ እርኩሳን ወእጨጌ ዘካሃድያን የዘረኞችና የትምክህተኞች ታሪክ የለሽ መልእክት"
      At least respect other people thoughts.

      Melesen yemtlat mebet alen period. Endate tebab eyalu mesadeb lik aydelm. Yemiasazinew tigre silhonk bicha melese mamlek yelbihm.
      Melesen yemitla hulu tigren ayteram

      Delete
  3. ይድርስ ለደደቦች ደደብ የደንቆረዎች ሊቀ መንበር ለእኩይ ቱጉሃን ዘ መንበረ ጨለምተኝነት ሊቀ ሊቃነ እርኩሳን ወእጨጌ ዘካሃድያን የዘረኞችና የትምክህተኞች ታሪክ የለሽ መልእክት ኣመላላሽ ፈረሰኛ አቶ ተመስገን ደሳለኝ ባሉበት
    መለስ መሞቱ ደስ ብሎኛል ነው ያልከው.ለመሆኑ መለስ የሞተው ለእንዳንተ ኣይነት ገልቱ ደደብ ኣስተሳሰብ ያለቸው ጭምር ነው ነፃ ለማውጣት እንደ እየሱስ ራሱን መስዋእት የሆነው.ደንቆሮ ስለሆንክ ነው እንጂ በኣደባባይ በነፃነት እንድትለፈልፍ እድል እንድታገኝ ያደረገህ የሱና መሰለቹ ብርቅየ የህዝብ ልጆች የተሰዉበት ስጦታ ነው.ኣነተ ካሃዲ በማንና ለምን እንደምትኖር የማተውቅ የበላበት ድስት የሚሰብር ባለጌ ስለሆንክ እንጂ በዚህ ንግግርህ በኣባቶችህ ዘመን ቢሆን ንሮ ያሰቅልህ ነበር.በጥላው ላይ ሁኖ ጥላው የሚረግም ጥላቢስ ከሃዲ ነህ. ያም ሆነ ይህ መለስ ግን ህያው ነው. ኣንተ ግን በካሃዲነትህ እድሜ ልክህ እያፈርክና እየባነንክ ትኖራለህ
    ከ ሃ ዲ!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  4. እኔ የሚገርመኝ መለስ ማን ነው ብለኻቸው ማንነቱን ሊነግሩህ ወይም ሊያውቁ የማይቹ ሰዎች ስለ መለስ መጥፎነት ሲናገሩ ነው፡፡ ለኔ እነዚህ ሰዎች ጨለምተኞችም አይደሉም ራሳቸው ጨለማዎች ናቸው ምክንያቱም እንደነ ተመስገን ያሉ ግለሰቦች ራዕይ የላቸውም አያዩምም ይህንን ያስባለኝ ዋና ምክንያት መለስ ሞተ በተባለ ጊዜ የመለስ ደጋፊም ይሁን ተቃዋሚ አዝኗል ተገዶ አይደለም ያዘነው ይሁን እንደነ ተመስገን አስተሳሰብ ኢ/ያዊው ተገዶ አዘነ እንበልና በዲሞክራሲ ጫፍ የደረሱ እንደነ አሜሪካ የመሳሰሉ የሃገር መሪዎች የመለስን ሞት ከአንዴም ብዙ ጊዜ እንዳሳዘናቸው የተናገሩት ተገደው ነው እንደማትሉኝ እገምታለሁ ግን አይታወቅም ይህን ለመናገር ወደ ኋላ እንደማትሉም ስለማውቅ አትተዉም ብየ ልለፈው፡፡ ያም ሆኖ ይህ ስለ መለስ መናገር የሚችለው የሚያይ ፣ ምክንያታዊ የሆነ ፣ የሰዎች ሳይሆን የራሱ አቋም ያለው ሰው ብቻ ነው፡፡ ተመስገን ገና ብዙ መማር ያስፈልገዋል አለማወቁ አንድ ቀን ያወቀ እለት ይባንናል፡፡
    አሁን የመለስ ራዕይ ይሳካል!

    ReplyDelete
  5. በዚች ምድር ላይ ኣንድ ዘረኛ ሰው ቢኖር መለስ ብቻ ነው
    በመሞቱ ብዙ የተደሰቱ መኖራቸው ለምን ያስደነግጠናል።
    ስንቱን ገሎ አኮ ነው የሀደው

    ReplyDelete
  6. what stupid thinking is this
    i think Ethiopian Stone is better than this stupid guy
    what ever PM Melese was a human being
    hadush Tesfahuney tanx for your idea
    any who know temesgens addres pls post here iam gonna give my shit

    ReplyDelete
  7. ተመስገን እኮ ትልቅ አይደለም በጣም ትንሽ ልጅ ነገር በአእምሮ ያልበሰለ በወሬ የተማረ በ25 ቀበሌ ማለት ሸራተን አከባቢ ቡሌ እየለቀመ ያደገ የእማማ ፋናዪ ልጅ ነው፡፡ በጠም እምገርመው በ 21 ክ/ዘመን ቆጥ ላይ የሚተኛ ጋዜጠኛ ብኖር ተመስገን ነው፡፡ ግን በተመስገን ሳይሆን የማዝነው የመንግስት አካላት ነው ይህ ሰው እኮ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ሰዘረጥጥ ፤ ስለፈልፍ ሰዎች በመንግስት አመፅ እንድያነሱ ቀን ከሌልት አየሰራ ይገኛል፡፤ ሰው ሰረቀ ተብሎ ስንት ስባልለት ዋሸ ተብሎ ግን የተቀጣ ሰው አልሰማሁም ግን ዉሸት እኮ አገር ያፈርሳል፡፡

    ReplyDelete
  8. በዚች ምድር ላይ ኣንድ ዘረኛ ሰው ቢኖር መለስ ብቻ ነው
    በመሞቱ ብዙ የተደሰቱ መኖራቸው ለምን ያስደነግጠናል።
    ስንቱን ገሎ አኮ ነው የሀደው

    ReplyDelete