እውቁ አትሌት ኃይለ ገብረስላሴ ‹‹ለፍሪካውያን በጣም ወሳኙ ነገር ዲሞክራሲ ሳይሆን ጥሩ ገዢ
ነው፤ እንዲህ ሲሆን ነው አህጉሪቱ ልትለወጥ የምትችለው፡፡ካልሆነ ግን በፍፁም ልትለወጥ አትችልም›› ያለው ለቢቢሲ በሰጠው ቃለ
መጠይቅ ላይ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት 1,700 ሰራተኞች እንዳሉትና በሪልስቴት ጀምሮ በስፖርት ማዘውተርያ፣ ስኒማ
ቤት፣ መኪና ድለላ፣ሆቴል፣ ሪዞርት፣ የቡና እርሻ እያለ በወርቅ ቁፋሮ እስከ መሰማራት እንደደረሰ የሚገልፀው አትሌቱ፣ ጋዜጠኛው
የዓለም ባንክ ያወጣው ሪፕርትን ጠቅሶ ‹‹በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ማድረግ ከባድ ነው፤ችግሮች ያጋጥሙሃል?›› ብሎ
ሲጠይቀው፤
ይህን የሚያደርገው ብዙ ሰዎች እንደሚሉት በውጭ ሃገራት መዋዕለ ንዋዩን ለማፍሰስ ዕድል እንዳለው
ነገር ግን ‹‹ይህ ሃገሬ ነው፤ እችው ነች እናቴ…በሃገሬ ኢንቨስት በማድረግ ቅድምያውን በመውሰድ ለሌሎች አርአያ መሆን እፈልጋለሁ››
ብሏል፡፡ በመቀጠልም ‹‹እናትህ መጥፎ ብትሆን አናቴ አይደለሽም ማለት ትችላለህ?›› በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መልሶለታል፡፡
‹‹ብዙ ሰዎች ዲሞክራሲ ያስፈልገናል ይላሉ፤ አንተ ለምን ዲሞክራሲ አያስፈልግም ትላለህ?››
የሚለው ጥያቄ ሲመልስ ‹‹እንዲህ በማለቴ አዝናለሁ፡፡በእርግጥ፣ ዲሞክራሲ ያስፈልገናል፤ነገር ግን፣ መቅደም ያለበት የትኛው ነው?
ሁሌም ዲሞክራሲ ዲሞክራሲ እንላለን…ግን ዲሞክራሲ በመጠኑም ቢሆን ቀንጦት ነው›› ብሏል፡፡
በ2010 ዓ.ም በሚካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ሊወዳደር እንደሚችል ፍንጭ የሰጠው አትሌት ሃይለ
ለ25 ዓመታት ዓለምን ዞሮ ያካበተው ልምድ ቀላል እንዳልሆነና ይህንን ልምዱን ለሃገሩ በሚጠቅም መልኩ የሚያካፍለው በፕረዚዳንትነት፣
በጠቅላይ ሚኒስተርነት ይሁን በሚኒስተርነት ግን ወደፊት የሚታይ ይሆናል ብሏል፡፡
ተወዳጁ አትሌት ሃይለ ገብረስላሴ ‹‹ዲሞክራሲ ለአፍሪካውያን ቅንጦት ነው›› በማለቱ ብዙ ፌስቡክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን
ሳይበሳጩበት አልቀሩም፡፡የአንዳንዶቹን አስተያየትና ግብረመልስ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ እርሶስ ምን ይላሉ? መልካም ንባብ፡፡