Friday, March 25, 2016

ከምርቃቱ በፊት የማስታወቅያ ስራውን በስኬት ያጠናቀቀው ቤዛ ፊልም


ቢዛ ፊልም
በሬድዮና ቴሌቪዥን ዝግጅቶች የምናውቀው ብርሃነ ንጉሰ ወደ ፊልም ኢንዲስትሪው በይፋ መቀላቀሉን የሚያበስር ወሬ ይዞ ብቅ ብሏል፤ቢዛ ፊልም፡፡በፖስተሩ ላይ ያሉ ተዋናዮች ስመለከት የልጅነት ጀግኖቼን አስታወሱኝ፡፡እነ ሻምበል ሮማን፣ እነ ጓል ዓይነታ፣ እነ ሲሳይ ገበል፣ እነ ጉማ፣ እነ ቀጭ ሕርሙ፣ ሽላ መረብ…

በተላይ ያቺ ሰላም ተስፋይ የሚሏት ልጅ ሳይ በጣም ነው የደነገጥኩት፡፡ያቺ ገና ህፃን እያለሁ ‹‹ማንጅስ፣ ይህ ትግል ከግቡ የምታደርሱት እናንተ ናችሁ፤ ስጋ ብፆት›› የሚል ትንቢት የነገረችኝ ሻምበል ሮማን በአካል ድቅን አለችብኝ፡፡በህይወት ትኑር አትኑር አላውቅም፡፡ምስሏና አነጋገሯ ግን በህይወት እስካለሁ ድረስ ከእኔ ጋር ይኖራል፡፡ይህ እውነታ የእነ እንትና ጭሆት ሊፈቀው አይችልም፡፡በጭራሽ!

እነ ሻምበል ሮማን የታገሉት የደርግ ስርዓት አሁን ባለው ስርዓት ለመተካት እንዳልነበረ በእርግጠኝነት መመስከር እችላለሁ፡፡ለዛም  ነው ‹‹ትግሉን ከግቡ የምታደርሱት እናንተ ናችሁ›› ያለችኝ፡፡በእቅፏ አድርጋ ስስ ፀጉሬን እያሻሸች፣ በራሽን መልክ ተሰጠቻት ዳቦ በሻይ ለእኔ አስረክባ፡፡ይህ መሆኑን ሁለት ጠላቶች እንዳፈራ ግድ ብሎብኛል፡፡ባንድ በኩል ሁሉንም ጠቅልሎ ሲያበቃ፣ ሁሉንም እንድናጣ የደረገን ስርዓት መታገል ይኖርብኛል፡፡በሌላ በኩል ደሞ ይህ ስርዓት ሙሉ በሙሉ የጠቀለለውን ሁሉ በሃይል ለመረከብና ‹‹የጠቅላይ አግላይ›› አዙሪቱን ለማጦዝ የተዘጋጁትን መፋለም እንዳለብኝ ያሳብቃል፡፡

ዳኛታተይ ስውኣት ብፆተይ እዮም (2)


ሰላም፣ ጥዕና ሃበለይ ክቡራት ተኸታተልቲ መርበብ ሓበረይታ ኣራዳ ፎሮም፡፡ኣብ ዝሓለፈ እዋን ምስ ነባር ተጋዳላይ ስዩም ካሳየ ካብ ዝገብርኹዎ ቃለ መጠይቕ ነቲ ቓደማይ ክፋል ኣቕሪበልኹም ምንባረይ ዝዝከር እዩ፡፡ሐዚ ድማ፣ ነቲ ናይ መወዳእታ ኻልኣይ ክፋል ሒዘልኹም ቀሪበ ኣለኹ፡፡ነዚ ቃለ መጠይቕ ኣሰናዲአ ብምቕራብ ንኽተዳምፁለይ ብኽብሪ ዝዕድመኩም ኣስፋው ገዳሙ እየ፤ ሰናይ ፃንሕት፡፡


ኹሉ ግዜ ኲናት ጠላዕ እዩ፤ሰብ ትቐትል ሰብ እዩ ልቓትለልኻ፡፡
ኣድያቦ እነይ ኢለ እየ ልፅውዓ፡፡
ናቕደም፣ ነቲ ድኹም ጎድኒ ትወቅዖ፤ ነቲ ጥንካረ ትዕቅቦ፤ ንሱ እዩ ዘዐወተና፡፡
ናሎሚ ድሃላይ እምበር ሃናፃይ ኣይኾነይ፡፡
ናቕደም ወታደር ተግነያ ቅርሺ ናብ መራሒኡ እዩ ልድርብያ፡፡ሎሚ ወታደር ሃምኡ ዶ ከቕምጥ መስለካ?
ኣብቲ ኣኽባሪ ሰላም ምኸድኹ፣ ምደለኹ ነይረ፤ ግን መንክሰደኒ፡፡

ኣባይ ነብሶ ታይ ድዩ? ታይ ኾይኑ እዩ ለይሕብረና?




Sunday, March 20, 2016

ዳኛታተይ ስውኣት ብፆተይ እዮም (1)


ተጋዳላይ ስዩም ካሳየ (ወዲ ራያ)
ስዩም ካሳየ ይብሃል፡፡ኣብ ዞባ ደቡብ ትግራይ፣ ናይ ቀደም ወረዳ ስለዋ፣ ድርከራ ኣብ ዝተብሃለት ፍሉይቲ ቦታ ብ1956 ዓ.ም ተወሊዱ፡፡ወረዳ ስለዋ ኣብዚ ሐዚ እዋን ኣብ ትሕቲ ወረዳ እምባ ኣላጀ ካብ ዝተጠርነፉ ንኡስ ወረዳታት ሓደ እዩ፡፡ብ1978 ዓ.ም ተጋዲሉ፤ ክሳብ 1985 ዓ.ም ድማ ኣብ ቃልሲ ፀኒሑ፡፡ኣብ እዋን ብረታዊ ቃልሲ፣ ሓደ ዓይኑን ሓደ ኢዱን ስኢኑ እዩ፡፡

ተጋዳላይ ስዩም፣ ኣብዚ ሐዚ እዋን ብሓንቲ ዓይኑ እናጠመተ፣ ብሓንቲ ኢዱ ዕርፊ ጨቢጡ እናሓረሰ ሽዱሽተ ደቁ የዕብይሎ፡፡ይኹን እምበር፣ ምስቲ ኣካላዊ መጉደልትን ዕድመ ምድፋእን ተደማሚሩ ዝተጎሳቆለ ናብራ ይመርሕ ከም ዘሎ የዛረብ፡፡ብምዃኑ ድማ፣ ንዓኡን ከምኡ ንዝበሉ ጉድኣት ኣካልን ውድብ ህወሓት ንክትሕብሮም ይላቦ፡፡

ብዝኾነ ምስ ተጋዳላይ ስዩም ካሳየ ስፍሕ ዝበለ ቃለ መጠይቕ ገይርና ኣለና፡፡እቲ ቃለ መጠይቕ፣ ብኽልተ ክፍሊታት ተሰናድዩ ዝቐረበ እንትኾን ነቲ ቀዳማይ ክፋል ንክተዳምፁላይ ብኽብሪ ይዕድም፤ ሰናይ ፃንሒት፡፡

 




ሓደ ኢደይ ሓደ ዓይነይ ኾይነ ለኹ፤ እዚ ተወቒዐ ኢለ እውን ኣይምበርከኹይ፡፡
ወታደር ይኹን ተጋዳላይ ክርእይ ተለኹ ሰለስተሻዕ ተቀይሮም እዮም፡፡
ልፈልጡኻ ወታደር ለ ለይፈልጡኻ ይመስሉ፡፡
ኣካለይ ምስተጎዳእኹ ድየ ለይሕበር ልብል ቅርሕንቲ ኣለኒ፡፡
ኣንሕና ኻፊእና ተሞይትና እቲ እንሆ ወለዶ ኸ ክወሓጠሉዶ ክኾን?
ኣማዓልኻ ልብሎ የብሉይ እዚ ጉዱእ ኣካል፡፡ልሰፍትኔት እኽሊ ሓገዝ እኳስ ልኻበሮም ብፆት ኣለው፡፡

ኣብፍቲ ቀውጢ ግዜ እነኻይ ውድብኻይ ኣሕሊፍኻ ላብ ልውሃብ ነገር የብሉይ፤ ብግልፂ ማለት እዩ፡፡ግን ልግዜኡ ይሓዝን ኣለኹ፡፡



Monday, March 7, 2016

‹‹ከአሜን ባሻገርን›› አሜን ብዬ የማልቀበልበት ምክንያቶች (II)

ምክኒያታዊነትና ሰብአዊነት

‹‹ከአሜን ባሻገር›› በ246 ገፆች የተሰደሩ 20 መጣጥፎች ይዛለች፡፡የመፅሐፏ ሽፋን ልዩ ምልክት ብስኪሌት(ባይሲክል) ስትሆን የሳይክሏ የፊትጎማ የዳግማዊ ምኒልክ ምስል ያለው ሳንቲም፣ እንዲሁም የኋለኛው ጎማ በ2002 ዓ.ም ታትሞ በማገልገል ላይ ያለው ብረቱ የአንድ ብር ኖት ነው፡፡

የሳይክሏ በዚህ መልኩ መቅረብ የሚጠቁመው ድሮና ዘንድሮ የኢትዮጵያ የማይነጣጠሉ ሁለት ገፅታዎች መሆናቸውን ለመጠቆም ይመስላል፤ ‹‹የኋላው ከሌለ አይኖሩም የፊቱ›› እንዲሉ፡፡ወይም ድሮ ያለዘንድሮ መንቀሳቀስ አይችልም የሚል እሳቤ ለማስረገጥ ነው፡፡አንድ የርቀት ዝላይ ስፖርተኛ ወደፊት መዝለል የሚችለው ርቀት ወደ ኋላ ተንደርድሮ የሮጦው ፍጥነት ወሳኝ የሆነውን ያህል፣ የዛሬው የሃገራችን እርምጃም ትናንት ስትራመደው በነበረው ፍጥነት ይወሰናል፤ አሳማኝ ነው፡፡

ደራሲው ድሮና ዘንድሮ ምንኛ እንደተዋኸዱ ሲገልፅ፣‹‹የዛሬው ዘመን ምን ቢታገል ካለፈው ዘመን ተለይቶ ጎጆ መውጣት አይችልም፡፡ያለፈው ዘመንና የዛሬው ዘመን እንዳይፋቱ ሆነው ተቆራኝተዋል፡፡አንዳንዴ ሳስበው፤ ‹‹ዘንድሮ›› በሚለው ቃል ውስጥ ‹‹ድሮ›› የሚለው ቃል መገኘቱ ባጋጣሚ አይመስለኝም፡፡›› ብሏል በገፅ 9 ላይ፡፡እዚ ጋ፣ አንድ ጥያቄ መነሳት አለበት፤ እሱም፣ ድሮና ዘንድሮ ይህን ያህል የተቆራኙ ከሆኑ ዘንድሮን ከድሮ ነጥለን መተቸት እንችላለን ወይ? የትናንቱ ታሪካችን ያተነፈሰው ጎማ፣ ዛሬ በፈለግነው ፍጥነት ሊያንቀሳቅሰን ካልቻለ ዘንድሮን ነው መኮነን ያለብን? ደራሲው፣ እስከ መቼ ድረስ የነበረውን ታሪካችን ነው ‹‹ድሮ›› እያለ የሚጠራው? ‹‹ዘንድሮ›› የሚለውንስ?

Thursday, March 3, 2016

‹‹ከአሜን ባሻገር››ን አሜን ብዬ የማልቀበልበት ምክንያቶች (I)



ስሜት


በውቀቱ ስዩም ዘመኑ ካፈራቸው ደንቅ የስነ ፅሑፍ ሰዎች አንደኛው ነው፡፡ በቅርቡ ‹‹ከአሜን ባሻገር›› የተሰኘው መፅሐፉን ለሕትመት ማብቃቱን ስሰማ ደስታየ ወደር አልነበረውም፡፡ የእርሱ መፅሐፍ ለማንበብ የነበረኝ ጉጉት የላቀ ስለነበረም የመጀመርያው እትም ገዝቼ ማንበብ ችያለሁ፡፡

የበውቀቱ ሽሙጦች ባነበቡኩኝ ቁጥር እንባየን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ ድረስ በሳቅ እንፈረፈራለሁ፡፡በመሆኑም የሆነ ደባሪ፣ረዥምምምና ጨፍጋጋ ጊዜ መግደል ሲያስፈልገኝ ‹‹መውጣትና መግባት››ና ‹‹እንቅልፍና እድሜ›› የተሰኙ መፃሐፎቹን ደጋግሜ አነባለሁ፡፡ከ‹‹አሜን ባሻገር››ን ሳነበም ሁለት ነገሮች እንደ እብድ ብቻየን እንድስቅ አስገድደውኛል፡፡አንደኛው የበረራ አስተናጋጆች(ወይም በወንበሩ በተገጠሙት ስክሪኖች አማካኝነት የሚታየው መመርያ) በአደጋ ጊዜ እንደህ አድርጉ እንድያ በሉ እያሉ ተጓዦችን የሚያስቡኩበት ክፍለ ጊዜ የገለፀበት ፅሑፍ ላይ፣

‹‹ለመሆኑ በአደጋ ሰዓት ከወንበሬ ስር መንሳፈፍያ ከረጢት መኖር አለመኖሩን ይቅርና፣ ወንበር ላይ ልቀመጥ ጉቶ ላይ እንዴት ትዝ ሊለኝ ይችላል? ሰው አለቅጥ ሲደነግጥ እንዲህ ያለውን የጥንቃቄ ዝርዝር ይቅርና በሽንት ቤት እና በሱሪው መካከል ያለውን ልዩነት እንኳን ይረሳዋል፡፡ለዚህ ነው ብዙ ደንጉጦች በአደጋ ሰዓት ሽንታቸውን ለሱሪያቸው የሚያስረክቡት፡፡›› የሚለውን ሳነብ በጣም ስቄያለሁ፡፡ አሁንም እየሳቅኩኝ ነው የምፅፈው፡፡(ገፅ 41)

ሌላው በጣም ያሳቀኝ ደሞ፣ በቢላደን ምክንያት ፂማም ሰዎች ሁሉ አሸባሪዎች እንደሚመስሉት ይገልጥና፣ ካጠገቡ የተቀመጠው ፂማም ተሳፋሪም አሸባሪ እንዳይሆን ስለጠረጠረ ሰውየው ‹‹ጠብደል ከመሆኑ የተነሳ›› አውሮፕላንዋን አንዳይጠልፋት መስጋቱን ይተርካል፡፡ከዛም፣ ያ አሸባሪ ሊሆን ይችላል ብሎ የገመተው ሰውዬ አውሮፕላንዋን ሳይሆን ሽንት ቤቱን መጥለፉ( ሽንት ቤት ውስጥ በጣም መቆየቱን) ይታዘባል፡፡ያኔ፣ ‹‹ሰውዬው ኑሮውን ነው እንዴ የሚፀዳዳው?›› የሚለውን መስመር ሳነብ በሳቅ ፍርስ ብያለሁ፡፡(ገፅ 43)

የስነ ግጥም ጥበብ መግጠሙ ላይ ብቻ ሳይሆን አነባበቡም የተለየ ተሰጥኦና ክህሎት የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ለዛም ሳይሆን አይቀርም በሃገራችን በገጣሚነታቸው ወደር የለሽና አንቱ የተባሉ ገጣሚዎች የገጠሙት ግጥም ራሴ ሳነበው ያን ያህል ስሜት አይሰጠኝም፡፡በተለይ ግጥሙ በጣም ረዥም ከሆነ፣ያለወትሮየ እንቅልፍ እንቅልፍ ይለኛል፤ አሁንም አሁንም ያፋሽገኛል፡፡እናም ሳልጨርሰው በጅምር ይቀራል፡፡ገጣሚዎቹ ሲያንቆረቁሩት ማዳመጥ ግን የሆነ ለመግለፁ የሚከብደኝ የመንፈስ ልዕልና ይሰማኛል፡፡

የበውቀቱ አጫጭር ግጥሞች ግን ከዚህ የተለዩ ሆኖው አግቻቸዋለሁ፡፡ገጣሚው ሲያነባቸውም ሆነ ራሴ ሳነባቸው፣ ህሊናየን እንደ ምግብ ያጠግቧታል፣ ለነብሴም መድሓኒት ሆኖው ይፈውሷታል፡፡ራሱ የገጠማቸው ግጥሞች ብቻም ሳይሆን የሚፅፋቸው መጣጥፎች ጥልቅ የሆነ መልእክት እንዲያስተላልፉለት የሚመርጣቸው ግጥሞችም አስደናቂ ናቸው፡፡