Wednesday, February 20, 2013

የኢትዮ ቴሌኮም ቀሽም ማስታወቂያ








ኢትዮ ቴሌኮም አሁንም እንደ ካሮት የቁልቁል እድገቱን ቀጥሎበታል፡፡እንሆ አሁንም ከወዳጅ ዘመዶቻችን ጋር ያለ መቆራረጥና የመስመር መጨናነቅ ሊያገናኘን አልቻለም፡፡ አሁን እማ ጭርሶ ብሶበታል፡፡በመክሲኮ የሚገኘው የደምበኞች የአገልግሎት መስጫ ቢሮው ዘግቶ ቁጭ ብሏል፡፡ይህም የፈረንጆቹ መሪዎቻችን የአመራር ብቃት ማሳያ መሆኑን ነው፤በጣም ያሳዝናል፡፡ኢትዮ ቴሌኮም(የሃራችን ብቸኛው የኮምኒኬሽን ሲስተም ሞነፖል)እንዲህ የሚል ከሆነ ባንኮችና ሌሎች ኮምፒተራይዝድ የሆኑ አግልግሎት ሰጪ ተቋማት ምን ሊሉ ነው?

ደግሞስ ደምበኞች ውድ ጊዜያቸውን ሰውተውና ወጪ አውጥተው ቢሮው ድረስ ከደከሙ በኋላ ‹‹ሲስተም ስለተቋረጠበን ለጊዜው አግልግሎት እየሰጠን ስላልሆነ…፡፡››የሚል መስታወቂያ መለጠፉ ምን ማለት ነው?ችግሩ አንዴ ተፈጠሯል፤ምንም ማድረግ አይቻልም…ከመጠገን ውጪ፡፡ነገር ግን በሌላው ጊዜ በፅሑፍ መልእክት እንደሚያጨናንቀን ሁሉ ችግር ስለመፈጠሩም እንዲሁ በያሉበት ማሳወቅ ነበረበት፡፡

መንግስታችን የቴሌኮምኒኬሽን የጥራትና ተደራሽነት ችግር ፈረንጆች‹‹Domino effect›› ብለው የሚጠሩት እንደ ወረርሽኝ በሽታ ወደ ሌሎች ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቀላሉ እንደሚዛመት አልተረዳም፡፡አዎ! ቴሌ፣መብራት ሃይልና የመንገድ ትራነስፖርት የሃገራችን የደም ስሮች ናቸው፡፡የአንዳቸው መጥፋት ወይም የጥራት መጓደል በሌሎቹ ላይ ተዛመጅ የሆነ ከባድ ጫና አለው፡፡እናም መንግስት በሶስቱም ተቋማት ላይ አፅንኦ ሰጥቶ ሌት ተቀን ሳይል ጠንክሮ መስራት ነበረበት፤አለበትም፡፡የእስካሁን ድረስ የተሰራው ስራ‹‹አበራታች ነው›› እያሉ ሪፖርት ለማሳመር የሚደረገው የቃላት ጨዋታ ስለተነቃበት ቢቆም ይሻላል፡፡የተበላበት ቀሽም አባባል መሆኑን ከተደረሰበት ስንበቷል፡፡

መንግስታችን ሰሙኑን ለሁሉ የሚባል የመብራት፣የውሃና የስልክ ክፍያ በአንድ መስኮት መፈፀም የሚያስችል ‹ሲስተም› ተግባራዊ ማድረጉን አስውቋል፡፡‹ሲስተሙ› በሐሳብ ደረጃ ይበል የሚሰኝ ነው፤ ነገር ግን አሁንም ‹‹የአፈፃፀም ችግሮች›› አሉበት፡፡የህ ‹‹ከ15 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ››የሶስቱም አግልግሎቶች ክፍያ ለማከናወን ያስችላል የተባለለት የአሰራር ስርዓት ከሩብ ሰዓት በነሰ ጊዜ ማስተናገዱን ይቅርና ከሰዓታት እንግልት በኋላም ደምበኞቹን በአግባቡ ሊያስተናግድ አልቻለም፡፡የፈረደባቸው ወገኖቻችን አሁንም አናት በሚበረቅስ ፀሐይ እየተቃጠሉ ከመሰለፍ ሊታደጋቸው አልቻለም፡፡



አረ ወዲህ በሉ ጎበዝ፡፡ምንድነው ነገሩ?የተጀመረው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ላይፈፀም፣የተፈፀመውም የታለመው ዓላማ በአግባቡ ላይከውን ድግምት አለበት እንዴ?


Monday, February 18, 2013

የኢፈዲሪ መከላከያ ሰራዊ ቀን አከባበር እና ሃገራዊ ፋይዳው













ባለፈው ሳምንት(የካቲት አንድ እስከ ሰባት 2005 ዓ.ም) የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቀን በመስቀል አደባባይና በእግዚቢሽን ማዕከል ‹‹ህገ መንግስታዊ ታማኝነታችንና ህዝባዊ ባህሪያችን እንደተጠበቀ ይቀጥላል›› በሚል መፈክር ሲከበር በዓለም የሰው ሂይወትና ንብረት በማውደም የሚታወቁት የተለያዩ ዓይነት የጦር መሳርያዎች ለህዝእይታ ክፍት ሁነው ሲጎበኙ ከርሟል፡፡ ብዙ ወገኖች ከመሳርያዎቹ ጋር ተቃቀፈውና በታንኮቹላይ ወጥተው ፎቶ ሲነሱ ነበር ፡፡እኔ ግን አላደረግኩትም፤ ከነዚያ ነፍሰ በላ መሳርያዎች ጋር ፎቶ መነሳት ይቀርና ድጋሚ ባጠገባቸውን ለማለፍም አልሻም፡፡ 
 




የሆነ ሁኖ ግን የተለያዩ አውዳሚ የጦር መሳርያዎች አፈሙዛቸውን ወደ ቤተ መንግስቱ አቅጣጫ ወድረው ሰንብቷል፡፡የፍልውሃና የአራት ኪሎ መሪዎቻችን ግን የህን ያህል ደፋሮች ናቸው ማለት ነው?የድሮዎቹ የጦር መሳርያዎች አብዛኛወቹ ራሽያ ሰራሽ ሲሆኑ በደቡብ ኮርያና በቻይና የተፈበረኩም የገኙበታል፡፡አሁን ግን እነዚያ መሳርያዎች በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር የሚተዳደረው ጋፋት አርማመንት እንዲስቱሪ እየሰተሩ ይገኛሉ፡፡በመከላከያ የምህንድስና ኮሌጅም ከመለዋወጫ እስከ ቀላልና ከባድ መሳርያዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡አረ እንደውም እውነት ያድርገውና ሰው አልባ የውግያ በራሪ መሳርያዎችም(ደሮን) በነዚህ ተቋማት መሰራታቸውን ተነግሮናል፡፡



የሃገራችን የመከላከያ ሰራዊት በእውቀትና በዘመናዊ ትጥቅ ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን ብዙ ወገኖችን እስደምሟል፤ እስደስቷልም፡፡ለወደፊትም መከላከያችን የሃገራችን ዕድገትና ትራነስፎርሞሽን እንዲፋጠን ድርሻውን እንደሚወጣ ያላቸው እምነት ሲገልፁ ተሰምቷል፡፡አገራችን ኢትዮጵያ መቸም ቢሆን በማያነቀላፉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን የተከበበች መሆኗን አያካድም፡፡እናም ዘርፈ ብዙ በሆነ ዕድገት ወደ ፊት መራመድ ብቻ ሳይሆን ከተቻለ መብረር ብትችልም ደስታውን አንችለውም፡፡

 
ይህ ነገር ግን በተግባር እንጂ በወሬ መሆን የለበትም፡፡እንድያውም ምንም ዓይነት ትዓምር ብንሰራም ይህን ያህል ማራገቡ አስፈላጊ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡በአሁኑ ጊዜ የመከላከያ ሰራዊታችን በጅማሮ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ጅማሮውም ‹‹ የሚያበረታታ ነው›› ማለት እንችላለን( ኢህዴግ አባባል ተውሰን)፡፡ ነገር ግን እንኳንስ በቴክኖሉጂ ‹ሀ…ሁ› ደረጃ ላይ ሁነን ይቅርና በጠፈር ምርምርና በኒኩለር ቴክኖለጂ በከፍተኛው እርከን ላይ ብንደርስም ለማንም መናገር ያለብን አይመስለኝም፡፡ምን ያስፈልጋል? ጊዜው ሲደርስ በንፈፅመው ተግባር እናስመሰክር የለም እንዴ፡፡

እስራኤላውያን በዓለም አለ የሚባል የውግያ ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆናቸውን ይታወቃል፡፡ነገር ግን አንድም ቀን እንኳን ሰላላቸው የጦር መሳርያ ዓይነትና የሰራዊታቸው ብቃት ትንፊሽ በለው አያውቁም፡፡እንሱ ማንነታቸውን የሚያስመሰክሩት በዓውደ ውግያ ብቻ ነው፡፡ባለፈው ጊዜ(ጥቅምት 2005 ዓ.ም) ከሐማስ ታጣቂዎች ጋር ባደረጉት ጦርነት እስራኤላውያን ዓለምን ጉድ ያሰኘ የፀረ ሚሳይል ሚሳይል ባለቤት መሆናቸውን በተግባር አስመስከሯል፡፡‹‹የሚያደርገውን የሚያውቅ ልጅ ለእናቱ አይናገርም›› ማለት ይህ ነው፡፡

እናም የባለፈው ሳምንቱ የመከላከያ ሰራዊታችን በል ሳይሉት ራስን ለጠላት የማጋለጥ ዘመቻ አልተዋጠልኝም፡፡ልክ እንደ እስራኤል የመከላከያ ሰራዊት በተግባር ብቻ ተፈትኖ የስመሰከረ እንዲሆን ለሰራዊታችን እምመኝለት፡፡አሁን ግን የሆነ ጉራ ብጤ የተቀላቀለበት የፈሪዎች አጉል ፉከራ መስሎ ተሰምቶኛል፡፡ ልማታዊነትም ሆነ ወታደራዊ ብቃት በዓውደ ውግያ እንጂ በዓውደ ራኢ ይለካል የሚል እምነት ይለኝም፡፡ጉራ እንድም የፍራቻ ምልክት ነው…ለውድቀት የሚዳርግ፡፡አልያም አጉል ትዕቢት ነው፡፡ፈረንጆች ‹‹Pride comes before a fall…ትዕቢት ውድቀትን ትቀድማለች›› የሚል አባባል አላቸው፡፡ስለሆነም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በአጉል ጉራ ወይም ትዕቢት ተወጥረን ጠላቶቻችንን እኛን ቀደመው እንዲገኙ እየረዳናቸው እንዳይሆን የሚል ሰጋት አድሮብኛል፡፡



ዓለማችን ብዙ ትዕቢተኛ አምባገነኖችን በየጊዜው አስተናግዳለች፡፡ከነዚህ ዓለማችን የፈራቻቸው ነፍሰ በላ ጭራቆች እነ ሂትለር፣ሳዳም ሁሴን፣ጋዳፊና መሶሎኒ ይገኙበታል፡፡የነዚህ ሰዎች ኢሰብኣዊ ግፍ፣ እብሪትና ባዶ ፉከራ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ አሟሟታቸውም እንዲሁ በጣም ይመሳሰላሉ፡፡

አዶልፍ ሂትለር በዓለማችን በጭካኔው ተወዳዳሪ እንደማይገኝለት ይነገራል፡፡ያየሚመካበት ጭራቅ ሰራዊቱ አርካሪውን ተሰባብሮ እንደ ጉም ሲበን ግን የጠላቶቹን ፊት ማይት ስላልደፈረና የእጁን እንዳያገኝ ሰለፈራ ራሱን አጠፋ፡፡በሰላም እጁን ቢሰጥ የሚጠብቀው ያውቅ ነበርና፡፡

ሳደም ሁሴንም እንዲሁ ርህራሄ አልባ ጭራቅ ነበር ይባላል፡፡ምዕራባውያን ሐያላን መጣን መጣን እያሉ ልያስፈራሩት ሲሞክሩ‹‹ኑ! ነገር ግን ኢራቅ ወስጥ ሰምጣችሁ ትቀራላችሁ››እያለ ሲፎክርበትና ሲመካበት የነበረው ጅምላ ጨራሽ መሳርያው ግን እንደ አይጥ ከጉድጓድ ወደ ጉድጓድ ከመሽሎክሎክ አልታደገውም፡፡እድውም ጉድጓድም ምስጢሩን ሊደብቅለት አልፈለገም መሰል ለነዚያ በህልሙና በውኑ እየመጡ የሚያስበረግጉት ምዕራባውያን ጠላቶቹን አሳልፎ ሰጠው፡፡ አሜሪካኖች ከተደበቀበት ጉድጓድ ቆፍረው በማውጣት ሱሙኒ በማታወጣ ገመድ አንጠልጥለው ሲገድሉት የተመለከተው የዓለም ህዝብ የሆሊውድ ፊልም የሚመለከት ነበር የመሰለው፡፡

በደናግላን አጃቢዎቹና ቄንጠኛ አለባበሱ የሚታወቀው የኮለኔል ጋዳፊ እብሪት ከእብሪትም በላይ እንደነበረ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ጋዳፊ የሊቢያ ፈጣሪ፣ባለቤትና ንጉስ መሆኑን ብቻ አልነበረም ራሱን የሚያስበው የአህጉረ አፍሪካ መሪ ጭምር እንደሆነም እንጂ፡፡ከነዳጅ ሽያጭ በሚያገኘው ገቢ ኪሱ ስለደለበ አስተሳሰቡም እንዲሁ እንደ ኪሱ በትዕቢት ተወጥሮ ያስቸግረው ነበር፡፡ የአሜሪካና አጋሮቿ ምት ግን መቋቋ አልቻለም፡፡እንደ የአዲስ አበባ ሌባ ቱቦ ውስጥ ተደብቆ ተገኘና ያለፍርድ በጥይት ተደብድቦ ከዚች ዓለም ተሰናበተ፡፡

በኒቶ ሙሶሎኒም እንዲሁ እንደ ሌሎቹ አምባገነኖች ሲሸሽ ተገኝቶ ከውሽማው ጋር በጥይት ተጨፍጭፎ ነበር የተገደለው፡፡

ወደሃገራችን ስንመለስም የአፄ ቴድሮስና የመንግስቱ ሃይለማርያም ጭካኔና ትዕቢት ከመጠን በላይ ጎልቶ ይታያል፡፡አፄ ቴድሮስ ቆራጥና ሃገራቸውን የዘመናዊ መሳርያ ባለቤት ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም እንደነበራቸው ይተረካል፡፡ነገር ግን ከመጠን በላይ ጨካኝና ትዕቢተኛ(እንደውም ወደ ዕብደት የሚያደላ ራስን የመቆለል አባዜ) ጭምር ነበሩ፡፡ያ ባህሪያቸው ነበር ድያ ራሳቸውን ለማጥፋት ያደረሳቸው፡፡ግዛተቸውን ከቱርኮችና ሱዳኖች ለመታደግ ያስችላቸው ዘንደ የእንግሊዝ ንግስትን የጦር መሳርያ ሚሰሩላቸው በለሞያዎች እንዲልኩላቸው በደብዳቤ ተማፅነው መልስ ሊሰጧቸው ስላልቻሉ ተናደው በእጃቸው የነበሩ ሚሴናውያንን በማሰር አስገድደው መድፍ አሰሯቸው፡፡
ይህን የሰሙ እንግሊዞች የአፄ ቴወድሮስን የእትዕቢት እባጭ ለማስፈንዳት ታጥቀው ወደ መቅደላ ገሰገሱ፡፡አፄ ቴወድሮስ የርሳቸው እጅ በቀላሉ ሊጠመዝዝ የሚችል ሃይል ያለ አይመስላቸውም ነበርና መድፋቸውን ወድረው ጠበቋቸው፡፡ ከዛም መድፉ አንዴ ፈንድቶ አቆመ፤ ወታደሮቻቸው(አጃቢዎቻቸውም ጭምር) በእንግሊዝ ወታደሮች ተገድለው አለቁ፡፡በስተመጨረሻም እርሳቸውም በሽጉጣቸው አናታቸውን አስፈነዱትና የትያትር ቤት ተዋናዮችን ቀልብ በእጅጉ መሳብ ቻሉ፡፡


የመንግስቱ ሃይለማርያም ጭካኔና ትዕቢትም እንዲሁ መላው ዓለም የሚመሰክረውና ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው፡፡መንጌ የስልጣን ጥሙን እስኪያረካ ደርስ ‹‹ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም›› በሚል መፈክር ህዝቡን ሲያጃጅል ከርሞ ሃገራችን ደምበደም አደረጋት፡፡ ከዛም በአፍሪካ አንደኛ እንደ ነበረ የሚነገርለት የመከላከያ ሰራዊት አቋቆመና ማን እንደኔ በሚል ትዕቢት ተወጥሮ ጠላቶቹን ‹‹ትሐህት፣ቅማላም፣ምንትስ›› እያለ ማጣጣሉን ገፋበት፡፡እንዚያ ትሐህት እያለ በወሬ ብቻ ሲያንቋሽሻቸው የነበሩት ታጋዮች ግን ያ አንጀቴ የተባለለት ሰራዊቱን ማባረር ጀመሩ፡፡መንጌም በየቴለቪዥን ጣብያው ያለ የሌለውን መቀባጠር ጀመረ፡፡በመጨረሻም ‹‹አንድ ጥይትና አንድ ሰው አሲኪቀር ድረስ›› እንደሚዋጋ ቃል ገብቶ ሲያበቃ የተኩስ ድምፅ ሳይሰማ መንበረ ስልጣኑን ትቶ ፈረጠጠ፡፡ይህ ነው የሁሉም ፈሪዎችና ትዕቢተኞች መጨረሻ‹‹በለፈለፉት አፍ ይጠፉ›› እንዲሉ፡፡


አሁንም የፈለገው ያህል በቴክኖሎጂ የታገዘ የጦር መሳርያ ባለቤት እንሁን ጉራና ትዕቢቱ የቆይልን ነው እምለው፡፡ትዕቢተኛ ሰው ወይም ሃገረ ገዢ በጣም የተነፋ ፊኛ ምስሎ ይሰማኛል፡፡ ፊኛ ሲነፋ ጠንካራና ሙሉ መስሎ ይታያል… እንዲሁ ሲመለከቱት በቀላሉ እጅ የሚሰጥ አይመስልም፡፡በስለታም ነገር ትንሽ ቢነካ፣ቢረገጥ ወይም በቡጢ ቢመታ ግን ወድያው ይፈነዳል፤ ይተነፍሳል፡፡አንዴ ከፈነዳ ደግሞ የነበረም አይመስልም፡፡እናም የፊኛ እጣ እንዳይ ደርስብን ከመጠን በላይ የተወጥረን መስለን መታየት የለብንም የሚል አቋም አለኝ፡፡


Thursday, February 14, 2013

የፍቅረኞች ቀን (VALENTINE’S DAY?)



የፍቅረኞች ቀን (የቅዱስ ቫለንታይን ቀን) የአዲስ አበባ ወጣቶችና የአፍ.ኤም ጋዘጠኞች አእምሮ ከተቆጣጠረ ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ሰሙኑን በየሬድዮ ጣብያው ሲለፈፍ ከርሞ እንሆ ዛሬ በቀይ ሸሚዝ፣ቀይ ከናቲራ፣ቀይ ቲሸርት፣ቀይ የጀሮ ጌጥ፣ቀይ ቦርሳ፣ቀይ የጥፈር ቀልም፣ቀይ የከንፈር ቀለም(ቻፒስቲክ)፣ቀይ ሱሪ፣ቀይ ጫማ… ቀይ በቀይ እየተከበረ ይገኛል፡፡ለኔ ግን ይህ ቀን ስሜት አይሰጠኝም፡፡ምክንያቱም፡

አንድ

ለምንድነው ቀይ ቀለም የፍቅር መግለጫ የሆነው? የቀለሞች ስነ አእምሮ(color psychology)ቀይ ቀለምን ከፍቅር፣ከአደጋ፣ተመልካችን በቀላሉ ከመሳብ ወዘተ ያይዟል፡፡
እኔ ግነ በተፎጥሮየ ደማቅ ቀይ ቀለም አልወድም፡፡ቀይ በቀይ የለበሱ ሰዎች ስመለከት ጥሩ ስሜት አይሰማኝም… ይሰቀጥጠኛል፡፡የእሳት ቃጠሎ፣አስከፊ አደጋ ደርሶ ደም በደም የሆነ ፍጡር፣ ቀይ ሽብር፣እጅግ አደገኛ የሆነ ነገር ወዘተ ያስታውሰኛል፡፡እኔ ባደግኩበት አከባቢ ቀይ ደሮና ቀይ በግ ዛር ለያዛቸው ሰዎች በጠንቋዮች ለመድሃኒትነት የሚታዘዙ ናቸው፡፡ ቀይ ጥለት ያለበት ነጠላ፣መቀነት ወይም ቀሚስም እዲሁ የሚለብሱት ዛር(ጂኒ) ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ደብዳቤ በቀይ እስኪርቢቶ አይፃፍም ይባላል፡፡

ሁለት

ባህላችን አይደለም፤ የምዕራባውያን መጤ ባህል ነው፡፡ባህል የማንነት መገለጫ ነው፡፡ የክብረ በዓላት አከባበር፣ አለባበስ፣አመጋገብ፣ የሃዘንና ደስታ አግላለፅ የአንድ ማሕበረሰብ የማንነት መገለጫዎች ናቸው፡፡የራስ ባህል ትቶ በሌሎች መሞዳሞድ ግን ማንነት ከመሽጥ አይተናነስም፡፡ቆይ መከተል ያሉብን ምርጥ ምርጥ ባህሎችን እየተውን የማይረቡትን ላይ የምናተኩረው ለምንድ ነው? ለምሳሌ ልዩነታችንን ዲሞክራስያዊ በሆን መንገድ መፍታት ትተን እርሰ በርስ እየተናቆርን ለኛ የማይ ጠቅሙ ነገሮች ላይ ጊዜ ማጥፋቱ አይታየኝም፡፡

ሶስት

ፍቅር እንደ ዓመት መለወጫ በዓመት አንዴ ብቻ የሚከበር ሳይሆን በየሲኮንዱ መታሰብ ያለበት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ፍቅር በአመክንዮ የሚደረት አያደለም… ከልብ ትርታ ጋር አብሮ ትር ትር ይላል፡፡የልብ ትርታ ሲያቆ ያቆማል፡፡ ታላቁ መፅሐፍ ቅዱስ‹‹ እምነት፣ተስፋና ፍቅር ለዘላለም ፀንተው ይኖራሉ፤ ከሁሉም ግን ፍቅር ይብልጣል›› ያለው ለዋዘ አይደለም፡፡እናም ለኔ እያንዳንዱ ቀን የፍቅርና የልደት ቀን ነው፡፡

በመጨረሻም ነጮች የሚያደርጉት ሁሉ በጎ ነው ማለት አያቻልም፡፡ መጥፎ ባህል እንዳለ ሁሉ ጥሩ ባህልም አለ፡፡ ሰለዚህ የሚጠቅመንን ከማይጠቅመን  እየለየን ቢሆን ደግ ነው፡፡ የሆነ ሁኖ ግን የፍቅረኞች ቀን ለምታከብሩ ወገኖቼ መልካም የፍቅር ቀን እመኛለሁ፡፡

Tuesday, February 12, 2013



ይኸው ኢትዮ ተሎኮም ከቤተሰቦቻችን ጋር እንዳንገናኝ አንድም ‹‹ከአግልግሎት መስጫ ክልል ውጪ›› አድርጓቿል፡፡ሁለትም መስመሮቹ ሁሉም ለጊዜው መያዛቸውንና ‹‹ከትንሽ ጊዜ በኋላ›› መደወል እንዳለብን ቅላፄ በሌላት ሰትዮ አማካኝነት እየነገረን ይገኛል፡፡ትንሹ ጊዜ ግን ምንያህል መሆኑን አይታወቅም፡፡ለሰዓታት ጠብቀን ሞክርን አልተሳካም፡፡የሰዓታት ጥበቃ ቀናትን ወለደ፡፡ሳምንታት አለፉ አሁንም አልተሳካም፡፡

ሳምንታትም ወራትን፣ወራትም ዓመታትን ማስቆጠራቸውን አልቀረም…ያው ተስፋ ባለመቁረጥ ምኮራችንን ብንቀጥልም ‹‹ለፍቶ መና›› ሆነናል፡፡‹‹ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የተሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋም›› ከቤተሰቦቻችን ካቆራረጠን ከራርሟል…አሁንም የችግሩን ቁልፍ አልተገኘም፡፡እናም እንደ ድሮው ደብዳቤ በመላላክ ፍቅራችንን ለመግለፅ ወስነናል፡፡እነሆ የመጀመርያው ደብዳቤ፡፡
‹‹ደብዳቤን በፖስታ ልኬልሃለሁ
መልሱን በተሎ እጠብቃለሁ›› በሚለው ተወዳጅ እንጉርጉሮ ወደ ደብዳቤው፡፡





ይድረስ ለደጉ ባላገሩ አብሮ አደጌ ሰላም ይበልጣል!

ውድ ጓደኛየ ሰላም ይበልጣል ሆይ እንደምነህልኝ?መላው አብሮ አደጎቻችን፣ቤተሰብና ወገንዘመዳችን አማን ነው?ደጉና ጀግናው የገጠር ኗሪ ህዝባችንስ እንዴት ነው?ያጭቃ አብኩተን፣ወሃ ተራጭተን፣ተረት ተረት፣ድብብቆሽ፣እሽቅድድምና ሌሎች መቸም የማይረሱ እጅግ በሚያዝናኑ ጨዋታዎች እየተደሰትን ያደግንበት ቀያችንስ?ቸሩ እግዚሔር ይመስገን እኔ ደህና ነኝ… ካንተ ናፍቆት በስተቀር፡፡ያአብረን ያደግንበት ጋራ ሸንተረሩ፣ሜዳና ገደሉ፣ ወንዝና ጫካው እንዴት እንደናፈቀን ልነገርህ አልችልም፡፡ያበሃዘንም ሆነ በደስታ ሃፍትና ደህነት፣ ሰላምና ጦርነት እንዲሁም የሃይማኖት ልዩነት ሳይለው  ያለውን በፍቅር እየተካፋፈለ አብሮ የሚኖረው የደግነት ተምሳሌት ወገናችንሰ በትል ሰላም?

ውድ ሰላም ሆይ! ፍቅር፣መተሳሰብ፣ መረዳዳትና አብሮ መኖር እኮ በኛ አከባቢ ቀረ፡፡እንደምታውቀው በኛ አከባቢ ስትለያይ ዳግም በሰላም ለመገናኘት በጎውን ሁሉ በመመኘት፣እንባ በመራጨት ደናሁን ደናሁኚ እየተባባልክ ነው፡፡ስትገናኝም እንዲሁ ሞቅ ያለ ያአክብሮት ሰላምታ በመለዋወጥ ነው፡፡ በኛ አከባቢ እወቀው አትወቀው በንገድህ ለሚያጋጥምህ ሰው ሁሉ ‹‹እንደምን ዋሉ፣ እንደምን አደሩ፣እንደምን አመሹ፣አረፈዱ›› ካልተባባልክ ‹‹ምነው እንደ እንስሳ ዝምብሎ ያልፋልሳ?›› ትባላለህ፡፡የእገዚሔር ሰላምታ የምታ የምትነፋፈገው በከረረ ጥላቻ ላይ ስትሆን ብቻ ነው፡፡ይህም በሃገር ሽማግሌዎች አማካኝነት በቀላሉ ይፈታል፡፡

እዚሁ አዲስ አባባ ግን ይህ ነገር እንደ ፋራ ያስቆጥርሃል፡፡ባንድ ህንፃ ውስጥ አብረህ እየኖርክ የእገዚሔር ሰላምታ መለዋወጥ እንደ ነውር ይቆጠራል፡፡የአዲሰ አባባ ሰዎች ሲገናኙና ሲለያዩ እምባ የሚራጩት ቦሌ የአውሮፕላን ማረፍያ፣ በፊልምና በሙዚቃ ምስሎች ብቻ ነው፡፡እናም ሰዎች እንደሚነፋፈቁ ለማወቅ ከፈልግ አንድም  ወደ ቦሌ የአውሮፕላን ማረፍያ ጎራ ማለት አለብህ አልያም ፍቅረኛሞች ሲለያዩና ሲገናኙ የሚያሳይ ፊልም ወይም በምስል የታጀበ ሙዚቃ ማየት የግድ ይልሃል፡፡

እንደምታስታውሰው የድሮው የኢትዮጵያ ተሌኮምንኬሽን ኮርፖሬሽን(ነብሱን ይማረውና) አንድ የማይረሳ መፈክር ነበረው፤ ‹‹ኢትዮጵያን ከመጭው ዘመን ጋር መገናኘት›› የሚል፡፡እንኳን ዘመድ ካዝማድና ወገን ከወገን ዘመን ከዘመንም ለማገናኘት ይፎክር ነበር፡፡ አሁን ግን ያነገር ቀርቷል… በመፈክርም በተግባርም፡፡ኢትዮተሌኮም ‹‹የጋራ ስኬት(shared success)›› እያለ ይፎክራል፡፡ ስለየትኛው ስኬት እንደሆነ ግን አልገባኝም…ትርፉ ለግሌ ብስጭቱ ግን ለደምበኞቼ ቢል ያምርበት ነበር፡፡ደብዳቤ መፃፍ እስከዚህም ነኝ፤ ግን ምንታደርጓለህ?ይህ የደምበኞቹን ንጉስ መሆኑን በተግባር የስመሰከረ መስራቤት በስልክና በኢንተርነት እንዳንገናኝ ስለከለከን ናፍቆቴን ለመግለፅ ይችን ደብዳቤ እየፃፍኩልህ ነው፡፡ተሌ በሞባይላችን ያለው የፅሑፍ መልክት መቀበያ ሳጥን እንደ ማስተወቅያ ሰሌዳ ብቻ መጠቀሙን ካቆመና እንድንላላክ ከፈቀደልን ግን  ‹‹መሰጅ›› አድርግልሃለሁ፡፡

በለፈው ሳምንት ስልክ ቁጥርህን በስንት መከራ አፈላልጌ እንዳገኘሁ ልደውልልህ ደጋግሜ ብሞክር ያች የተሌ ውሸታም ሰትዮ‹‹ይቅርታ(የስላቅ ምልክት)የደወልላቸው ደምበኛ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው፡፡እባክዎ ትንሽ ቆይተው ይደውሉ›› እያለች ስታስቸግረኝ ጊዜ ተስፋ ቆርጬ ተውኩት፡፡አይገርምህም!ገንዘብህን ከፍለህ ከናፈቅከው ጓደኛህ ጋር እንዳትገናኝ እየከለከለች ደጋገማ‹‹ይቅርታ›› መለቷ አያናድድም?ይቅርታ ሲባል በፈፀምኩት በደል ተፀፅቼለሁ፣ ተሳስቼ አስቀይሜሃለሁ፣ ከአሁን በኋላ አይለመደኝም፤ ለአሁን ብቻ ማረኝ ይቅር በለኝ ማለት አያደልም እንዴ?በተደጋጋሚ እየጎዱ ደጋግመው የቅርታ መጠየቅ ምፀት ነው፤…ምንያመጣል ከሚል አስተሳሰብ የሚመነጭ የንቀት ምልክት፡፡ለዛም ነው ‹‹ትንሽ ቆይተው ይደውሉ›› ትልህና ከአንድ ሰዓት በኋላ ብትሞክርም አይሳካልህም፡፡

የሚገርመው ደግሞ ደውለህ ለማግኘት ስትሞክር ብቻ አይደለም እንዲህ የምትለው፡፡ ከስንት ጊዜ ምኮራ በኋላ ቀንቶህ የናፈቀከውን ወዳጅና ዘመድ አግኘተህ እጅግ ተመስጠህ እየተነጋገርክ እያለህም ጣልቃ ትገባና‹‹ መስመሮቹ ሁሉም ለጊዜው ተይዟል፡፡እባክዎ ትንሽ ቆይተው ይደውሉ ›› በማለት መስመሩን ትቆርጧለች…ያች የፍቅር ምቀኛ!የመገናኘት፣መጠያየቅ፣ሰላምታ ልውውጥ ፀር!በገኛት በጥርሶቼና ጥፍሮቼ ነበር ቦጭቄ ቦጫጭቄ ወፎችን ለማስበርገግ በእንጨት ላይ የተሰቀል ብትቶ ጨርቅ እማስመስላት፡፡

የምወድህና የማከብርህ ሰላም ይብልጣል ሆይ ባለፈው’ለታ  ወደ አዲስ አበባ መጥተህ መኖር እንደምትፈልግ ከነገርከኝ በኋላ ነበር ስልኩ ድንገት የተቋረጠው፡፡ከመምጣትህ በፊት ግን ስለ አዲስ አበባ አንድ አንድ ነገሮች ልንገርህ፡፡አዲስ በእድገት ግስጋሴ ላይ መሆኗን የሚያመለክቱ የህንፃ ግንባታዎች እዚህም እዛም ይታያሉ፡፡አሁን ደግሞ የባቡር መስመር ግንባታ ተጀምሯል…እየተፋጠነ ነው፡፡ሰፋፊ አስፓልቶቸም በመሰራት ላይ ናቸው፡፡

ነግር ግን ኗሪዎቿ በትራንስፖርት እጥረት፣በውሃና መብራት መቆራረጥ፣በቤት ክራይና በንሮ ውድነት እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡በፈልከው ሰዓት የፈለከው ነገር በጊዜው ማከናወን አትችልም፡፡ይቅርና የኢትዮጵያ ትላልቅ ባለስልጣናት የአፍሪካ ህብረት መሪዎች መቀመጫም እዛው አይደልም እንዴ? ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ፡፡አልተሳሳትክም! እነዚህ ባለስልጣናት እዚህ የሚኖሩት ለችግሮቻችን መፍትሔ ለማፈላለግ ሳይሆን ምኞታቸውን ለመናገር ነው፡፡ምኞት ደግሞ ማንም ያመኛል፡፡ምኞት ከቅዠት በምን ይለያል ጃል?

አዲስ አበባ ስትኖር ብዙ የሚያበሳጩና ግራ የሚያጋቡ ነገሮች ያጋጥሙሃል፡፡ለምሳሌ ያክል የሚከተሉትን ልጥቀስልህና ሐሳቤን በዚሁ ልቋጭ፡፡
1.              እንደኔ ተከራይተህ የምትኖር ከሆነ፣ አምሽተህ ቤት እንዳትገባ ማጅራት መቺዎች(የከተማ ሽፍቶች)ይገድሉሃል፤ በግዚ ከገባህ ደግሞ አከራዮች ያፈጡብሃል፣ የቤት ከራይ ጨምር ወይም ቤቱን ለቀህ ውጣ ወዘተ ሊሉህ ይችላሉ፡፡ ግራ ትጋባለህ፣ ተበሳጫለህም፡፡
2.              የስራ ቅጥረኛ ከሆንክ፣ ካረፈድክ የቅርብ አለቃህ ይቀጣሃል(ከስራ ማባረርም ጭምር)፣ በሰዓቱ ቢሮ እንዳትገኝም ታክሲ አታገኝም፤ ብታገኝም በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ቶሎ አትደርስም፤… ሌላ ብስጭት፣ ሌላ ግራ መጋባት፡፡
3.              በአዲስ አበባ ጎደናዎች በእግርህ ስትጓዝ በሆነ ግምብ ላይ ‹‹እዚህ አከባቢ መሽናት ክልክል ነው›› የሚል ማስታወቅያ ተለጥፎ ስታይ ብዙ ሰዎች ተሰልፈው ሲሸኑና ሲፀዳዱ ትመለከታለህ፡፡አፍንጫን የሚቆርጥ ሽታም ያጋጥምሃል፡፡በአዲሳባኛ አባባል ‹‹የተከለከለ ነው›› ማለት ‹‹ የተፈቀደ ነው፣ይቻላል›› የሚል ትርጉም ያለው ይመስላል፡፡
4.              ‹‹አከባቢያችንን ፅዱና በአረንጓዴ እትክልቶች የተሸፈን እናድርግ›› የሚል መፈክር የተፃፈበት ታፔላ ካስተዋልክ፣ ያአከባቢ በቆሻሻ ክምር፣ በሰዎች ተረጋግጠውና ተቆራርጠው በደረቁ አትክልቶች ወዘተ ምስቅልቅሉን ወጥቶ ነው የምትመለከተው፡፡
5.              በልብስ መሸጫ ስቆች ‹‹በቅናሽ ዋጋ እንሸጣለን›› የሚል በፕላስቲክ የታሸገ የማስታወቅያ ፅሑፍ አንብበህ ወደ ስቁ ጎራ ስትል፣ አንድም ከአስፓልት ዳር ተለቃቅመው የተገዙ ልብሶች(ስልባጆች) ታያለህ አልያም ወጋቸው በእጥፍ መጨመሩን ትገነዘባለህ፡፡በአዲሳባኛ አባባል ‹‹ማይት ማመን አይደለም››፡፡
6.              ልመናና አለማመን ቦታ፣ፆታ፣ቁመናና ዕድሜ አይለይም፡፡አንድ ካንተ በሶስት እጥፍ የሚበልጥ ጎረምሳ ‹‹ነብሴ ሳንቲም ሙላልኝ›› ይልሃል፡፡ ከምን ምንያህል እንደጎደለበት ራሱ ነው የሚያውቀው፡፡ምን የሚያካክሉ ግብዳ ሴቶችም እንዲሁ ይላሉ፡፡ከሁሉም በላይ አንጀት የሚበላው ግን ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ‹‹ ጋሼ ለዳቦ መግዥያ ሳንቲም ስጠን›› እያሉ አፈር ለብሰው በሚያሳዝን ድምፅ ሲማፀኑ መመልከት ነው፡፡ አንድ አንድ የውስጥ አዋቂዎች ግን እነዚህ ህፃናት የሚለምኑት ለራሳቸው አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡‹‹በልጅ አመካኝቶ ይበላል አንግቶ›› ሲባል አልሰማህም?
7.              እጅግ ብዙ ሰዎች የሚበላ አጥተው ከልክ በላይ የከሱና ሆድና ጀርባቸው ተጣብቆ የተሰፋ የሚመስል ቁመና ያላቸው ወገኖች ስትመለከት ቆይተህ ትንሽ እንደተጓዝክ ደግሞ ክልክ በላይ ከመብላታቸው የተነሳ ባምቡላ የሚመስሉ መንቀሳቀስ ያቀተቸው ሮቶዎች ተገኛለህ፡፡ሁለቱም ያሳዝናሉ፤ ከልክ በላይ በሆነ ርሃብና  ክልክ በላይ በመብላት አካለስንኩል ሁኗል…<<The two extremes are always vices>> እንዳለው ግሪካዊው ፈላስፋ አሪስጣጥሊስ፡፡
8.              እንዱ ሰማይ ጠቀስ በሆነ ፎቅ ወይም ቤተ መንግስት በሚመስል ቪላ ሁሉንም ነገር ተማልቶለት ተንደላቆ ሲኖር ሌለው ከፎቁ ስር በሚገኘው አስፓልት ላይ በባዶ ሆዱ እጅና እግር በሚቆራርጥ ብርድና እንደ ቅቤ በሚያቀልጥ ፀሐይ እየተቃጠለ የኖራል፡፡‹‹ዓለም ደሮ ናት፤ ላንዱ እንቁላል፣ለሌላው ኩስ ተጥላለች›› ይሉሃል ይህ ነው፡፡

ውድ አብሮ አደጌ ስላም ይበልጣል እንግዲህ ለዛሬው በዚሁ ይብቃን፡፡በሚቀጥለው ጊዜ በስልክ የልብ ልባችንን እንድናወራ ፈጣሪ ለኢትዮተሌኮም ማስቷሉን የቸረው ዘንድ በትጋት እፀልያለሁ፡፡  ያች በስላቅ‹‹ይቅርታ፣የደወልላቸው ደምበኛ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው፡፡›› እያለች የምታደርቀንና እንዳንገናኝ የምትዋሸው ሰትዮም የበጋ መብረቅ ያድርቃት ብያለሁ፡፡ ፈጣሪ ፆሎቴን ከሰማ በእርግጠኝነት እደውልልሃለሁ፤ አካል ሆነ ግን በሌላ ደብዳቤ እስክንገናኝ ድረስ ሰላም ሁንልኝ፡፡አሜን!

የምንጊዜም ወዳጅህና አክባሪህ
አስፋው ገዳሙ
አዲስ አበባ፡፡





Thursday, February 7, 2013

ዓለማችን ቆሽሻለች: መጥረግያና መወልወያ ይዘን እናፅዳት







ዓለማችን ከልክ በላይ ቆሽሻለች ማለት ብቻም ሳይሆን የቆሻሻ ክምር ሆናለች ቢባል ከእውነት ያራቀ አደለም፡፡በየቤቱ፣በየአከባቢው፣በየሃገሩና አህጉሩ እነዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቆለለው የቆሻሻ መዓት ዓለምን ወደ ገሃንምነት እየቀየራት ነው፡ቆሻሻ በቆሻሻ ላይ እየተደራረበ ዓለምን በመርዛማ ንጥረ ነገሮች ተበክላ ሁሉም ነገር እየነተበና እየሻገተ ይገኛል፡፡ያልተበከለ ነገር ማግኘት ቅዠት እየሆነ ነው፡፡ንፁህ አየር፣ንፁህ ውሃ፣ንፁህ ምግብ ከሁሉም በላይ ደግሞ ንፁህ አስተሳሰብ፣ ንፁህ ህሊናና ቅን አስተሳሰብ እንደ ሞኝነት ይቆጠራል፡፡


የቆሸሸ ነገር ለማፅዳት ቆሻሻ መሆን የግድ ነው ያለው ማን ነው?መንግስት ቆሸሸዋልና ፀረ መንግስት የሆነ አቋም ያለቸው ተቃዋሚዎችም መቆሸሽ አለባቸው እንዴ? እሳትን በእሳት ፈጥፋት እንዴት ይቻላል?እንዴት ነው አሸባሪዎችን በአሸባሪዎች ማስወገድ የሚቻለው?ዓየነ ደረቅ ውሸታም፣አምባገንን፣ ዘረኛ፣ሙሰኛና ጨቋኝ መንግስት ልክ በእርሱ አምሳያ፣ አስተሳሰብና ተግባር የተቃኘ እንደውም በባሰ ሌላ ወሮበላ ለመተካት የህልም ውግያ ማወጅ ፋይዳው ምንድ ነው? የሰው ሂይወትና ንብረት በማውደም ድህነትና ኋላቀርነትን ከማባባስ ወደፊት ፈቀቅ አያደርገንም፡፡በዚህ አካሄድ የትም መድረስ አንችልም…ታሪክ ምስክሬ ነው፡፡ያረጀ ያፈጀውን ነገር በሌላ ዓዲስ ነገር የመተካት ዓላማ ካለን መጀመርያ ራሳችንን ማሳደስ አለብን፡፡ አስተሳሰባችንን ማፅዳት የግድ ይለናል፡፡ግድያን በግድያ ለማስቆም መውተርተር የመገዳደል ሱሰኞች ያደርገናል እንጂ የትም ደያደርሰንም፡፡

በቆሸሸች ሃገር፣ በቆሸሸች ዓለም መኖር ስልችቶናል፣አቅለሽልሾናል፣ እጅ እጅ ብሎናል አይደል? ታድያ እንዚህ ነገሮች አጥፍቶ ለማጥፋት የሚደረጉ የቆሻሻ አስተሳሰብ ወጤቶች ሰለሆኑ በመጥረግያና መወልወያ ድራሻቸውን ማጥፋት አለብን፡፡ ጊዜ ሳናጠፋ አሁንኑ እንጀምር፡፡ እናም መጥረግያ መወልወያ! መጥረግያ መወልወያ! መጥረግያ መወልወያ! እያልን በየቤቱ፣በየስፍራው፣በየመስራቤቱ፣በየሃገሩ በአጠቃላይ ቆሻሻ ባለበት ስፍራ ሁሉ እየዞርን እናፅዳ፡፡ቆሻሻው እኛን ከማፅዳቱ በፊት!ቆሻሻው እኛን ከማቆሸሹ በፊት እንቅደመው፡፡ቆሻሻን ቆሻሻ!በለን በመለየት ሃገራችንን ለማፅዳት በጋራ ካልዘመትን በቀር መፍተሔ አናገኝም፡፡የቆሸሸ ማንነታችን በቆሻሻ ክምር ላይ እያንከባለልን ‹ሻወርን› ማሰብ የአስተሳሰብ ዝቅጠት ነው፡፡

ካሁለት ዓመታት በፊት የዓረብ ሃገሮችን ሲያምስ የነበረው የሰላማዊ ሰልፎች ደግግሞች ‹‹የዓረቦች ትንሳኤ›› የሚል የሽፋን ስም ቢሰጠውም እስካሁን ድረስ ግን የታለመው መፍትሔ አላስገኘም፡፡በእርግጥ ቆሽሸዋል፣ አርጅቷ፣ አምባገነኖች ናቸው ወዘተ የተባሉት ግለሰቦች ለእስርና ለግፋዊ ግድያ ዳርጓል፡፡ሰላማዊ ሰልፎቹ ግን በሰላም ሳይሆን በጦርነት፣ውንብድናና ድህነትን ነው የተተኩት፡፡ግብፅ አሁንም በዜጎቿ ደም እየታጠበች ትገኛልች፡፡ሶርያ መቋረጫ በሌለው ጦርነት እየታመሰችና ወደ ማትወጣበት መድረሻው የማይታወቅ ግሃንማዊ ጉድጓድ በስጠም ላይ ነች፡፡የቀሩትም በእስላማዊ መንግስታት ተተክቷል እየተኩም ነው፡፡

 እናም እነዚያ ከኩረጃ በስተቀር ምንም የማያውቁ ድያስፖራ አክራሪዎች ያን የዓረቦች ብጥብጥ መንትፈው ወደ ሃገራቸን ለማስገባት ‹‹በቃ!›› የሚሉ ባዱ ጭሆቶች በየድረ ገፆችና እንደ ፌስቡክ ባሉ የማህበረሰብ መገናኛ ዘዴዎች(social networks)ማስተጋባት ጀመሩ፡፡በቆሸሸ አፋቸውና አስተሳሰባቸው የነተበ ዘረኛ መርዝ መርጨት ስራየ ብለው ተያያዙት፡፡ቢሄሮች በቢሄሮች ላይእንዲነሱ ለፈፉ፤ እኛም ባናዳምጣቸውም ታዘብናቸው፡፡በቆሻሻ አስተሳሰባቸውና አመለካከታቸውና አልተደነቅንም ከነቆሻሻ ጭሆታቹ ገደል መግባት ትችላላቹህ አልናቸው፡፡እናም ‹‹በቃው›› በዚሁ አበቃ፡፡

የበቃው ዘመቻ መክሸፉ የተገነዘቡት በጥላቻ ታውረው መጮህ የለመዱ ቆሻሻ ዲያስፖራዎች ሱሳቸውን ለማርካት ‹‹የበቃ›› አርበኞቻችን ይፈቱ በማለት የተለመደው የማደንቆር ዳንኪራቸውን ቀጠሉበት፡፡ አሁንም ሰሚ እንጂ የሚያዳምጥ ጀሮና የሚመለከት ዓይን መሳብ አልቻሉም፡፡ነገር ግን በመስማትና ማዳመጥ ያለው ልዩነት መለየት ስለተሳናቸው አሁንም‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› በሚል ሌላ የጭሆት መዓት መመርቀን ቀጠሉ፡፡ ‹‹ሃገር የጋራ ሃይማኖት/እምነት ግን የግል ነው፡፡›› እየተባለ ባለበት ዘመን‹‹አንዲት ሃገር በአንዲት ሃይማኖት!›› የሚል መፈክር አንግቦ ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› እያሉ ማደንቆር ስካር ነው ወይስ ዕብደት? አፍን ዋሻ አስመስሎ የኔ እምነት ከናንተ ይበልጣል፤ በይበልጥም የግድ መከተል አለባችሁ፤ ካልሆነ ግን አንገታቹህ ለገጀራ ስጋቹህም ለአሞራ ይዳረጋል እያሉ ማስፈራራት ጤንነት ሳይሆን የለየለት ዕብደት ነው፡፡

ታድያ ዕብደትን ዕብደት ይወልዷልና የህ የሙጃህዲኖች የቁም ቅዠት ዓለማችን በአራቱም አቅጣጫዎች ሰላሟን እየበጠበጠና እያሸበራት ይገኛል፡፡እነዚያ በምዕራባውያን ሃገሮች የሚገኙ ጅቦችም የስልጣንና የፍቅረ ንዋይ ጥማቸውን ለመቁረጥ ሲሉ ብቻ የጨሆው ሁሉ እየተከተሉ እንደ ውሻ ማላዘናቸውን ቀጥለውበታል፡፡እንዚህ ሰዎች ትናንት ሃገራችን ሲያደሙና የነበረንን ሁሉ ሲያወድሙ የነበሩ ከሃዲዎች በቆሸሸው ማንነታቸው ሌሎችን ከሃዲዎች ብለው ቢፈርጁ አይደንቀኝም፡፡ለነሱ ከነሱ ወድያ አስተዋይ፣ታማኝ፣ ጀግና ታጋይ፣ አርበኛ፣ ለሃገሩና ወገኑ ተቆርቋሪ የለም፡፡በጣም የሚያሳዝነው ግን የነሱ ሳይሆን የነዚያ በጀግኖች ወላጆቻችን፣ወንድሞችና እህቶችን ደምና ሬሳ እየተረማመዱ አሁን ባሉበት ከደረሱ በኃላ የማይረቡ ቆሻሾች መሆናቸውን ነው፡፡እናም ቆሻሻ ቆሻሻን አየሳበ ውዷ ሃገራችን የቆሻሾች መጫወቻ ሁና እንድትዘልቅ በዚህም በዚያም የዲያብሎሶች ጭሆት እያስተጋባ ነው፡፡

ህግን ጥሶ ‹‹ህግ የከበር›› የሚል ዲስኩር ማሰማት ብለጠት ነው ወይስ የአስተሳሰብ ዘቅጠት?ህግን አፍርሶ ምን ዓይነት ህግ ለማቋቋም ነው ይህን ሁሉ የገድል ማሚቶ የሚያስተጋባው? ከአሁን በፊት ስህተት ስለተሰራ እኔም በበኩሌ እንዚያ ስህተቶች በማባባስ ሽግሮችን ለማስወገድ ተነስቻሎሁና ‹‹ድሚፄን ስሙ፣ መንገዴንም ተከተሉ፣ጳጳሱም፣ሸኩም፣ንጉሱም እኔ ነኝ እናም ካለኔ በስተቀር ዓለምና መንግሰተ ስማያትና አትወርሱም›› እያሉ ማስረራራትና የፍጥጫ ስብከት መስበክ ምን የሚሉት እንዝህላልነት ነው?ዓይንህን ጨፍን ልሸውድህ!

በህክምናው ሳይንስና በሳይኮሎጂ ሶስተዮሽ የጨለምተኛ ብህርያት(Dark Triads)የሚባል ሐረግ አለ፡፡ ሶስት ተማሳሳይ የሆኑ የስብእና ችግሮች ያጠቃለለ ሲሆን የዚህ ዓይነት ችግር ያለው ሰው የስነ አእምሮና የስነ ልቦና ህክምና ያስፈልጓል፡፡‹‹ከራስ በላይ ንፋስ›› ለንደዚህ ዓይነት ሰዎች የተመሰል ሳይሆን አይቀርም፡፡እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡
1.              ናርሲሲዝም(Narcissism)፡ ራስን እንደ ተራራ አግዝፎ መመልከት፣ ከኔ ውጪ ሌላ ታማኝ አስተዳዳሪ፣መሪ፣አርበኛ የለም ብሎ መደምደም፣ ከመጠን በላይ ራሰ ወዳድነት፣ ደካማ አሳፋሪ የተጨማለቀ ማንነትን ተወዳዳሪ እንደ ሌለው አድርጎ ማሰብ ነው፡፡
2.              ማኬቨሊያኒዝም(Machiavellianism)፡ የፍልስፍናው አባት ጣልያናዊው ኒኮሎ ማኬቨሊ (1469-1527 ዓ.ም እ.አ.አ.)ነው፡፡ በፖሊቲካው ዓለም በጣም የታወቀ ሲሆን ‹‹ማንኛውም ዓላማ የሚለካው በውጤቱ ብቻ ነው›› የሚል ፍልስፍና ያራምድ ነበር፡፡ አካሄዱ የፈለገው ይሁን የግል ፍላጎትህ ለማሳካት ብቻ የቻልከውን ሁሉ ያለርህራሄ እንደትፈፅም የሚመክር አስተሳሰብ ነው፤ መሸወድ፣ማጭበርበር፣መዋሸት፣መስረቅ እንዲሁም መግደል(እናት፣አባት፣እህት ወንድም፣ሚስትና ባል ጭምር!) ይቻላል በዚህ አስተሳሰብ መሰረት፡፡ ፡፡ እናም በስነ አእምሮ እንደ ጨለምተኝነት ይቆጠራል፡፡
3.              ሳይኮፓዚ(Psychopathy):ሶስተኛው ይስነ አእምሮ ችግር ሲሆን ይህም ከመጠን በላይ ራስን መውደድ፣ ለጊዘያዊ እርካታና የግል ደስታ ሌሎችን ማሰቃየት፤እንዲሁም ሲሰቃዩ በመመልከት በደስታ መቦረቅ፣ለሌሎች ቅንጣት ታህል አለመጨነቅ፣ ስለ ሞራል፣ሰብአዊነትና ህግ አክባሪነት ድንታ አለመኖር፣ስህተትን አለማመንና እንዳውም እያወቁ ማጥፋት፣በጠፋው ጥፋትም አለመፀፀት ወዘተ ያጠቃልላል፡፡

እነዚህ  ባህርያቶች በሃገራችን ፖለቲከኞች በተለይም በአክራሪ ድያስፖራዎች የሚደጋገሙ ተግባራት ናቸው፡፡ ሞት የሰው ልጅ ፍፃሜ መሆኑን እያወቁ በሞተ ሰው ይደሰታሉ፣ይጨፍራሉ፣ እነሱ እንደገደሉ የፉከራና ቀረርቶ ዳንኪራ ይረግጣሉ፡፡ሰዎችን በዘር፣በአከባቢና በእምነት በመከፋፈል አንዱን ባልዋለበትና በላሰበው ይከሳሉ ይወነጅላሉ፡፡ለሌላው ደግሞ የማይገባው የአርበኝነት ካባያለብሳሉ፡፡የህ ታድያ ፍርደ ገምድልነት፣ጨለምተኝነት በአጠቃላይ የአስተሳሰብ መቆሸሽ አይደለም? እኛን ደግፍ፣እኛን እንጂ ሌላ እትስማ፣ እኛ ከምንጠላቸው ሰዎች ጋር ብትቀርብ አብረህ ተወቀጣለህ የሚል ፅንፈኛ እምነት ማራመድ የማንነት መቆሸሽ ያመለክታል፡፡

ይህ የሻገተ አስተሳሰብ ለማፅዳት መጥረጊያ መወልወያ ይዞ በሕብረት መዝመት የግድ ይላል፡፡ያለፈውን አልፏል ከዚህ በኋላ ግን ይበቃል ማለት አለብን፡፡ከዘመነ መሳፍንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣብንና በስልሳዎቹና ሰባዎቹ የተጋጋለው እርሰ በርስ የመበላላት በሽታ መታከም አለበት… ላይመለስ፡፡ ያለፈውን ትውልድ ክፉም ይስራ ደግ ጊዜው ሲያልፍ አልፏል፡፡ ደግነቱ አብሮን እንዳለ ሁሉ ግን ክፋቱም እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ሁላችንም የዓመድ ክምር እያደረግን ስለሆን ተረባርበን እና ጥፋው፡፡እናም በጋራ መጥረግያ መወልወያ! መወልወያ መጥረግያ! መጥረግያ መወልወያ! እያልን የቆሸሸውን ለማፅዳት እንዝመት፡፡



Tuesday, February 5, 2013

ዝርፍያ፡ ድሮና ዘንድሮ




በዚህ ዘመን የማይዘረፍ ነገር የለም፡፡ምሁራን ይህ ያለንበት ክፍለ ዘመን የመረጃ ዘመን የሉታል፡፡ጊዜና መረጃ እኩል የሚሮጡበት ዘመን ነው፡፡ለሰው ልጅ ሂይወት ወሳኝ የሆነ መረጃ እንደተገኘ በጊዜው ጥቅም ላይ ካልዋለ ከትንሽ ጊዜ በኃላ ከትዝታነት የሚያልፍ ፋይዳ አይነረውም፡፡እናም በአሁኑ ዘመን ዓለም እንደ ሸረሪት የተሳሰረች ስለሆነች የንብረት ብቻ ሳይሆን የጊዜ ቀማኞችም እንደ አሸን ፈልቷል፡፡

ልክ ነው አጭበርባሪዎች፣ዘራፊዎችና ኪስ አውላቂዎች የሰው ንብረት ለመዘረፍ ማዘናጋትን እንደ ቀዳሚ ምርጫቸው አድርገው ይጠቀሙበታል… በተለይ የአዲስ አበባ ሌቦች፡፡ ሌብነት በሃይማኖት ሃጥያት፣ በባህላችን ነውር በሕግ ደግሞ ወንጀል ነው ቢባልም አሁንም ከማሕበራዊ ንሯችን ልናስወግደው አልቻልንም፡፡እንደውም ከጊዜ ወደ ጊዜ ድግግሞሹ እየበዛና አፈፃፀሙም እየከፋ ይገኛል፡፡በተለይ ትላልቅ ከተሞች የሽፍቶች መሸሸግያና መናሃርያ ጫካዎች እየሁኑ ነው፡፡ኪስ አውላቂዎችም ከኪስ አውላቂነት ወደ እስትንፋስ አውላቂነት በመሸጋገር ‹‹ማጅራት መቺ›› የሚል መዓርግ ተቀዳጅቷል፡፡  

ነገር ግን ለገንዘብ ሲባል መተክያ የሌለውን የሰው ሂይወት ከሚያጠፉ ማጅራት መቺዎች የኪስ አውላቂዎች አዘራረፍ ይሻል ነበር፡፡እንደውም አንዳነዴ አሰራረቃቸው በመጠኑ ፈገግ ያሰኛል…የጦጣና ቀበሮ ባህሪ ነው ያላቸው፡፡የማጅራት መቺዎች መሳርያ ክንድ ብቻ ሲሆን ኪስ አውላቂዎች ግን እጅግ ውስብስብ የሆኑ የስነ ጥበብ አስተሳሰቦችን በመጠቀም ነው ዓላማቸውን የሚፈፅሙት፡፡ኪስ አውላቂዎች የኪስ መጠን ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ወደ ባዶ ኪስ ዝው ብለው አይገቡም፡፡ ከዝርፍያው ክብደትና ቅለት ተመጣጣኝ የሆነ ጥናት ያካሂዳሉ፤ትርፍና ኪሳራቸውን ይቀምራሉ፡፡እናም ትልቁ መሳርያቸው አእምሮ ነው፡፡አእምሮን ተጠቅሞ የሚከናወን ስራ ደግሞ እንደ ፈረጠመ ክንድ መሰንዘር ቀላል አይደለም፡፡

የማጅራት መቺዎች አሰራር ግን ከአሸባሪነት የማይተናነስ እንስሳዊ ተግባር ነው፡፡መጀመርያ ይገድላሉ ከዛም ኪስ ይፈትሻሉ፤ካገኙ እስየው ካላገኙም ምራቃቸውን እሬሳው ላይ በመትፋት እየተራገሙ ወደ ሌላ ግድያ ያመራሉ፡፡እንዚህ ሰዎች ከጅብ የሚለዩት ቤት ውስጥ ሰለሚኖሩ ብቻ ነው፡፡ልክ እንደ ጅብ ዝርፍያውም ግድያውም የሚያከናውኑት ጨለማን ተግን አድርገው ነው፡፡ህሊናና አእምሯቸው በተለያዩ ስሶች ታውረዋል፡፡የቀቢፀ ተስፋ አኗኗር ነው ሚመሩት፡፡‹‹የሰው ልጅ ሰው የሆነው ሰውን ገድሎ ነው››በሚል የጫካ ሕግ ይመራሉ፡፡ማጅራት መቺዎች በአብዛኛው ጊዜ ግለሰቦች ሳይሆኑ ብዱኖችና ደርጅቶች ናቸው… ‹‹ተደራጅተው ይገድላሉ፣ከዛም ይዘርፋሉ››… በደመ ነፍስ፡፡ይህ ዓይነት የመንግስት መዋቅሮችም ይጨምራል…ሙስናና ኩረጃ!!!

በአንድ ስሙን በውል የማላስታውሰው መፂሔት ያነበብኩት ገጠመኝ እንደ ምሳሌ ላቅርብ፡፡ልጁ ወጠምሻ ነገር ነው አሉ፡፡እናም የሰፈሩ ልጆች አደራጅቶ ማጅራት እየመታና የግዳዮቹን ኪስ እየበረበረ በሚያገኘው ገንዘብ ይጠጣል፣ያጨሳል፣ይጨብሳል ሌላም ሌላም ያደርጋል፡፡አንድ ምሽት ታድያ  እንደልማዱ ለማድረግ ከግብረ አበሮቹ ጋር  ሁኖ በሆነ አሳቻ ቦታ አሽምቆ ይጠብቃል፡፡ከዛም አንድ ሽማግሌ ከዘበኝነት ስራቸው ወደ ቤታቸው ሲያዘግሙ ይመለከታሉ፡፡ያወጠምሻ ጥግ ይዞ ጓደኞቹን በሉት አላቸው…በምልክት፡፡እንዚያ ወመኔዎች ተንደርድረው ሂደው ያሚስኪኑን ሽማግሌ አንገት ቆልምመው ግደሏቸውና ኪሳቸውን በርብረው ያገኟት ሐምሳ ብር ይዘው ሊሄዱ ሲሉ አንዱ ፊታቸውን ትኩር ብሎ ሲመለከት የወጠምሻው አባት መሆናቸው አወቀና ድንገት ራሱን ይዞ‹‹ጋሼ እንትና! ጋሼ! ጋሼ!›› እያለ እየየውን አቀለጠው፡፡ወሮበላው ማጅራት መቺ በፀፀት አንጀቱ አረረ፤ተቃጠለ፣ጨሆ አባቴ አባቴ እያለ አለቀሰ፡፡ነገር ግን በመፀፀትና በማልቀስ ሊመልሳቸው አልቻለም፡፡የእጁን በእጁ አገኛት!!!

ዘራፊዎች ድሮም ነበሩ፤አሉ ለወደፊትም ይኖራሉ፡፡በዕዳዊ አገዛዝ፣ ሽፍትነትና የባርያ ገባያ ድሮ የነበሩ አሁንም ያሉ ሰይጣናዊ የዝርፍያ ዓይነቶች ናቸው፡፡የድሮው ዝርፍያ የግለሰቦች፣ድርጅቶችና የላዓለዊ ሃገሮች ድምበር በመሻገር በጉልበት የሚፈፀም ነበር፡፡አሁን ግን የትም ሳይንቀሳቀሱ ባንኮች፣የግለሰብና የድርጅት ምስጢሮች፣ የሃገር ድሕንነት ወዘተ አደጋ ላይ የሚጥሉ ምስጢራዊ ሰነዶች በርቀት እየተመነተፉ ይገኛሉ፡፡

የሚዘረፍ ምስጢር ካልተገኘም አግልግሎት ማሳጣት(Denial of service)የሚባል የጊዜ ስርቆት አለ፡፡ኮምፒተሮች በተጠቃሚያቸው የታዘዙት ስራ እንዳይ ሰሩ የሚያስተጓጉል መጥፎ ተግባር ነው፡፡
ኢራን እስራኤልን ስትወነጅል እንደነበር በቅርቡ የምናስታውሰው ጉዳይ ነው፡፡የኒኩለር ማበልፀጊያ ቴክኖለጂዋ በቫይረስ ስለተጠቃባት፡፡ጁልያን አሳንጅም አምባገነኗን አሜሪካን ሳይቅር ጉድ አስኝቷት ነበር፡፡ዊኪ ሊክስ ብሎ በሰየመው ድረገፁ ላይ ያጋልጣቸው በነበሩ የአፍጋኒስታንና የኢራቅ ዘግናኝ ግፎች፡፡ አሜሪካ አሁንም ቻይናን ጥብቅ ምስጢሮቼን እየዘረፈችብኝ ነው ስትል እየወቀሰች ነው፡፡ሌባን ሌባ ቢዘርፈው ምኑን ይደንቃል?

እናም ዝርፍያ ከጊዜው ጋር እየዘመነ፣ የአዳዲስ ፈጠራዎች ባለ ቤት በመሆን የዘራፊዎችን ንሮ እያበለፀገ ይገኛል፡፡ዘራፊዎች ሁሌም ዓይናቸውን በሌሎች ንብረትና ምንነት እዳንከራተቱ የኖራሉ፡፡የናጠጠ ቱጃር ሁነውም የሚስኪኑ ወገናቸው ንብረት፣ጉልበትና ጊዜ ከመመንተፍ ዓይናቸውን አያሹም፡፡

Monday, February 4, 2013

ዋዛና ቁም ነገር


1. አገርም ጐረቤትም እየረዳኝ



በአንድ አካባቢ አንድ በስተእርጅና ዘመናቸው ቆንጆ ወጣት ሴት ያገቡ አዛውንት እየሸመገሉ ሔዱና ዕድሜያቸው 105 ሞላ፡፡ በአንጻሩ ሚስት እየቆነጀች፣ እያማረባት መጣ፤ አዛውንቱ ዕድሜያቸው እየገፋ ቢመጣም ሚስት ግን ልጅ መውለድዋን አላቆመችም፡፡

የአካባቢው ሰው ግን ሚስት ጐረቤትዋ ከሆነ አንድ ጐረምሳ ጋር ሥውር ወዳጅነት መፍጠርዋን ከመጠርጠር አልፎ ሁኔታውን በግልጽ ያውቅ ነበር፡፡ አንድ ቀን ከአካባቢው ነዋሪዎች አንዱ አዛውንቱ ዘንድ ሔዶ፡-

‹‹አባት ለመሆኑ ይህን ያህል ዕድሜ ከሆነዎት በኋላ እንዴት ነው የሚወልዱት?›› አላቸው፤ ሽማግሌው የሰውየው ጥያቄ ከምን ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገብቷቸው ኖሮ፡-
‹‹መቼም አገርም ጐረቤትም እየረዳኝ›› ብለው መለሱለት አሉ፡፡
- ካሕሣይ ገ/እግዚአብሔር፣ ‹ኅብረ-ብዕር›› (1998)


2. እሱማ እኔም ነበረኝ

አንድ ደጃዝማችና አንድ ቀኛዝማች ከሌሎች ሹማምንቶች ጋር በመሆን ድግስ ላይ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፡፡ በመካከሉ ቀኛዝማቹ ውኃ ሽንታቸውን ለመክፈል ፈልገው አሽከራቸውን መክፈያ እንዲያመጣላቸው ያዙታል፡፡

አሽከሩም በታዘዘው መሠረት መክፈያውን ይዞ ከተፍ አለ፡፡ ይሁንና ቀኛዝማች ሽንተቸውን ለመሽናት ቢፈልጉም ፈሳቸው አብሮ መጣሁ መጣሁ እያለ አላሸና አላቸው፡፡ ከዚያ አምልጦኝ ሰው ፊት ከምዋረድ ብቆይ ይሻላል በሚል፡-

‹‹በል አንሳ›› ብለው መክፈያውን ወደዛ ገፋ ከማድረጋቸው አጠገባቸው የነበሩ ጓደኛቸው (ደጃዝማቹ)፡-

‹‹አንተ እምቢ ካልህ እኔ ልሞክር›› አሉና ሽንታቸውን መሽናተ ሲጀምሩ አምልጦአቸው አንድ ሁለቴ ቷ…ቷ አደረጉ፡፡ በዚህን ጊዜ ከሚያመልጠኝ ይቅርብኝ ብለው የተቀመጡት ቀኛዘማች፡-

‹‹አዬ ደጃዝማች ሌላ ታመጣለህ ብዬ ነው እንጂ እሱማ እኔም ነበረኝ›› አሉ ይባላል፡፡
- ካሕሣይ ገ/እግዚአብሔር፣ ‹‹ኅብረ-ብዕር›› (1998)




source: http://www.ethiopianreporter.com/index.php/other-sections/2012-12-14-13-20-52/zinnik/item/502-በመቀሌ-ዩኒቨርሲቲ-ዋና-ካምፓስ-ተማሪዎች-የኢትዮጵያንና-የዛምቢያን-እግር-ኳስ-ጨዋታ-ሲመለከቱ

Saturday, February 2, 2013


ወድሰብን ለቖታን፡ ናይባህሪ ምምስሳል



ወድሰብ ተወሊዱ ዓብዩ ካብዛ ዓለም ዚኣ እስካብ ዝሰናበት ደረስ ዘንፀባርቖም ባህርያት ምስ ናይ ለቖታ ባህርያት ብጣዕሚ እዩ ዝመሳሰል፡፡ናይ ጠሊ(ጤል)ቆርበት ብዕንጉለን ሽንቲ ከፍትን ንሰለስተ መዓልትታ ምሰአጀለ አውፂእካ ይንፋሕ እሞ እቲ ፀግሪ ይምለጥ፡፡ቀፂሉ ድማ ብፅሓይ ንክደርቕ ይግበር፡፡እቲ ብፅሓይ ዝደረቐ ቆርበት አንጋረ ይብሃል፡፡አንጋረ ብጣዕሚ ደረቕ እዩ፤ዋላኳ ባዶ እንተኾን ብጣዕሚ ተወጢሩ ክሳብ ዝቕደድ ዝመልአ ይመስል፤እንተነኺእኻዮ ድማ ኮርርፋዕ ፋዕ ዝብል ድምፂ የስምዕ፡፡

አንጋረ ጠሊ ንዝተወሰነ ግዜ ጉድኣት አብ ዘይበፅሖ ቦታ ይቕመጥ (ዓናፁን ካልኦት ባልዓትን ከይቀድኦ ምእንታን)እሞ እንጣጢዕ ተወቒጡ ምስላሓመ ይብፅበፅ፡፡ስዒቡ እት ኣንጋረ ናብቲ ዝተበፅበፀ እንጣጢዕ ዝሓዘ ኣቅሓ ኣእቲውኻ ንሓደ ሰሙን ተዘኽዚኹ ንክቕኒ ይግበር፡፡በኻሊእ ኣባሃህላ መጥለል ኣቲውሎ ማለት እዩ፡፡ድሕሪኡ ድማ ናብ ፅሓይ ኣውፂእኻ ንኻልኣይ ግዜ ንክደርቕ ይግበር፡፡ካብ መጥለል ዝወፀአ ቆርበት ብጣዕሚ ጠምባው እዩ፤ ኣፍንጫ ዝቖርፅ ጨና ኣለዎ፡፡ምስ ደረቐ እቲ እንጣጢዕ ሙሉእ ንሙሉእ ክሳብ ዝረግፍን እቲ ቆርበት ድማ ብጣዕሚ ክሳብ ዝልስለስ ብእግሪ ይርገፅ፤ ብኢድ ከዓ ይሕሰ፡፡እት ተሓስዩ ተሓስዩ ብጣዕሚ ዝለስለሰ ቆርበት ለፊዑ ይብሃል፡፡ዝለፍዐ ቆርበት እዩ እምብኣር ለቖታ ተባሂሉ ዝፅዋዕ፡፡

ሓዲስ ዝለፍዐ ለቖታ ጨናኡ ሙሉእ ንሙሉእ ኣይገድፍን…መጥለል መጥለል እዩ ዝሸትት፤ብዙሕ ጥራይ(እኽሊ) እውን ኣይሕዝን… ቅሩብ ምሰ ኣተዎ ዝመልአ ይመስል፡፡ኮርርፋዕ ፋዕ ዝብል ድምፂ እውን የስምዕ እዩ፡፡ሙሉእ ብሙሉእ ዝለፍዐ ለቖታ ግን አይጨንውን፣ድምፂ ኣየስምዕን ብዙሕ ጥራይ ድማ ይሕዝ፡፡ብዙሕ ጥራይ ኣእቲኻሉስ ዝመልአ ኣይመስልን፡፡ሕቑን ሕቑን እናበልካን እናሓሰኻን ተወሳኺ ጥራይ ይእቱ፡፡

ወድሰብ እውን ከመዚ ዓይነት ብህሪ እዩ ዘለዎ፡፡ኢከለ እኮ ኣታሓሳስባኡ ከም ህፃን እዩ፤ አይበሰለን፣ልቢ ኣይ ገበረን ወዘተ ዝብሉ መግለፂታት ነዘይለፍዐ ሰብ ዘመልክቱ እዮም፡፡ዘይበሰለ ሰብ ልክዕ ከም ዘይለፍዐ ለቖታ ጠራዕራዕ እዩ ዘብዝሕ፤ውሽጡ ባዶ እናሃለወ ይዕስ የዕስ ንክብሃል ጥራሕ ጉራ የብዝሕ፡፡ፈላጥ ንክብሃል ዝፈልጦን ዘይፈልጦን ይዘባርቕ፡፡ ዝዝረብን ዘይዝረብን ፍልዩ ኣይፈልጥን፤በቃ ከምዝመፅአሉ እዩ ዝቕደድ፡፡በፍልጠትን ክእለትን ዝብልፅዎ ሰባት እንተጋጢመሞ ከምፀለእቱ ገይሩ ይቖፅሮም፤ ከርሕቖም ከዓ ይምኩር፡፡ምኽንያቱ ምስ ከምዚኦም ዝበሉ ሰባት ክሕወስ ከሎ ባዶነት ይስመዖ፤ ዓርሰ እምነት ይስእን፡፡ምዓንጣኡ ብቅንኣት ሕርር ኹምትር ይብል፡፡ከምዚ ዓይነት ሰብ ሽግራት ናይ ምፅዋር ብቕዓቱ በጣዕሚ ዘታሓተ እዩ፡፡እዚ ባህሪኡ እንተዘየማሓይሹ ድማ ናይ ጥዕናኡ እናተቃወሰ ይኸይድ፡፡

ዝበሰለ ሰብ ግን ከም ዝለፍዕ ለቖታ ፀባዩን ኣታሓሳስባኡን ልስልስ ዝበለ እዩ፡፡ብዙሕ እናፈለጠ እንትኸይድ ምንም ከይመዘይ ፈልጥ ይርዳእ፤ ሰቁራጠስ ከምዝበሎ ‹‹ኣነ ዝፈልጦ ዘይምፍላጠይ ጥራሕ እዩ››ይብል፡፡ብዝበለፀ ከዓ ንምፍላጥን ክእለቱ ንምምዕባልን ላዕልን ታሕትን ይብል፡፡ካብ ምዝራብ ምድማፅ የቕድም፤ምስ ብዙሓት ምትሕውዋስ ብዙሕ ፍልጠትን ክእለትን ከምዘዕጥቕ ይፈልጥን ዘፈለጦ ነገር ከዓ ኣብ ተግባር ንምውዓል ይፅዕር፡፡ዝፍልጦን ዝኽእሎን ንኻልኦ ካብምክፋል ንድሕሪት ኣይብልን፡፡ዓለም ፅላሎት ምኻና ስለዝርዳእ ንዝሓልፍ ግዜ ዘይሓልፍ በሰላ ከይገድፍ ይጥንቀቕ፡፡ትምክሕትን ዘርኣውነትን ኣጥቢቑ የወግዝ፤ንደቂ ሰባት በእምነት፣ብኣከባቢ፣ብመልክዕ፣ብሃፍቲ፣ብዘርኢ ወዘተ ብምክፍፋል ኣየዳልውን፡፡ልዕሊ ኹሉ ድማ ብጣዕሚ ፅንፈኛ ዝኾኑ ኣታሓሳስባታት ይፀልእን ንምውጋድ ከዓ ይፅዕር፡፡

ከም ዓይነት ሰባት ድማ እዮም ሊቓውንቲ ዝብሃሉ፡፡ሊቓውንቲ ፍልጠቶም ተግባራዊ ንምግባር ብዙሕ ኣይሽገሩን፡፡ገንዘቦምን ፍልጠቶምን ማሕበራዊ ሽግራት ንምቕራፍ ዝጠቕሙ መሳረሕታት እዮም፡፡ንኣድናቖትን ዘብለጭለጩ ነገራትን አይግደሹን፡፡ምስ ከምዚኦ ዝባሉ ሰባት ምውዓል ብዓለም ምሩፃት አብ ዝኾኑ ዩኒቨርሲትታ ኣቲኻ ካብ ምምሃር ኣይድሕርን፡፡