Thursday, October 31, 2013

ህወሓትና ሙሴ ፡ ደርግና ሂትለር





በወርሐ ጉንበት 2005 ዓ.ም በአንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብየ ሻይ ቡና በማለት ላይ ነበርኩ፡፡አንድ በ40ዎቹ መጨረሻና በ50ዎቹ መጅርያ የዕድሜ ክልል የሚገኝ ጎልማሳ እኔ በተቀመጥኩበት ጠረጴዛ የነበረው ክፍት ወንበር ሰው ይንሮው አይንሮው ካጣራ በኋላ መጥቶ ተቀመጠ፡፡በካፌው ውስጥ የነበረው ቴሌቪዥን ደርግ የወደቀበት የጉንበት 20 በዓል ዝግጅቶች በማሳየት ላይ ነበር፡፡የቴሌቪዥኑ ዝግጅት ከአጠገቤ ለተቀመጠው ሰውየ የሚመች አልነበረም መሰለኝ ‹‹ጉንበት 20 እኮ የህወሓት ድል እንጂ የኢትዮጵያውያን አይደለም›› እያለ ማጉረምረም ጀመረ፡፡‹‹የሃገራችን አንድነት የተናጋው ደርግ ተሸንፎ ህወሓት ለስልጣን ስለበቃ ነው፤ የህወሓት ዓላማ ስልጣን ብቻ ነበር…›› እያለ ያነበንባል፤ ባልመልስለተም እኔን ማናገሩ ነበር፡፡

እኔ በሐሳብ ማዕበል እንገላታለሁ፤አወርዳለሁ እወጣለሁ፤እየወደቅሁ እነሳለሁ፡፡በሓሳብ መርከብ ተሳፍሬ ሁሉንም ስፍራዎች አዳርሳለሁ፤ቆላውና ደጋው፣ገጠርና ከተማው፣ቅርብና ሩቁ አካልላለሁ… እማልደርስበት የለም፡፡አልፎ አልፎ እንዲህ ያደርገኛል፤አመል ሳይሆንብኝ አልቀረም፡፡አጠገቤ የተቀመጠው ጎልማሳ ብስልና ጥሬውን ይዘባርቃል፤በተመስጦ የምከታተለው ሳይመስለው አልቀረም፡፡ለተወሰነ ጊዜ መልስ ላለመስጠት ሞክሬ ነበር፤የኋላ ኋላ ግን አልቻልኩም፡፡ሰውየው የዋዛ አልነበረምና ኮርኩሮ ኮርኩሮ ሊያናግረኝ ችሏል፡፡የደርግ ሐጥያቶች እንዳለ በህወሓት ላይ መለጠፉን ሲቀጥል፣‹‹ ማስረጃህ ምንድንው?›› ብየ ጠየቅኩት፡፡‹‹እኔ እኮ ያኔ ትልቅ ነበርኩ፤አንተን በብዙ ዓመታት እበልጥሃለሁ፤ እንዳውም ሳልወልድህ አልቀርም፤እንዴት እንዲህ ትላለህ?›› እያለ የተናገረውን ሁሉ አሜን ብየ እንድቀበልለት ወተወተኝ፡፡‹‹አይ፣ በዕደሜ ብትበልጠኝም ብዙ የታሪክ ፅሑፎች ስላሉ በመረጃ አስደግፈን በንናገር ይሻላል ብየ ነው፡፡›› ስለው፣ ‹‹በለ ያዝ እንግዲህ፤ መረጃዎቹን ልዘርዝርልህ›› አለና፡

  1.  ደርግ ወደ ጦርነት የገባው በህወሓትና በሻዕብያ ተገድዶ እንደሆነ 
  2. የሰላምና የአብዮት ጥሪ አልቀበልም ብለው አሻፈረኝ በማለታቸው መሆኑን
  3. ደርግ ስልጣን የተረከበው መስከረም 1967 ዓ.ም ሲሆን ወያኔዎች ደግሞ ከሻዕብያ ጋር ወግነው በየካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም(ደርግ ስልጣን ከያዘ ስድስት ወር እንኳን ሳይሞላው) በኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ላይ ጦርነት በማወጃቸው ደርግ የሃገሩ ሰላምና አንድነት ለማስጠበቅ ወደ ውግያ መግባቱን ወዘተረፈ እያለ ሊያሳምነኝ ሞከረ፡፡ 



እኔም መረጃዎችን እያጣቀስኩ እሱ የሚላቸው ነገሮች በመክንያትና በመረጃ ያልተደገፉ የአስተሳሰብ ህፀፆች መሆናቸውን ላሳምነው ሞክርኩ፡፡ሰውየው ቀድሞውንም ለውይይት ሳይሆን ለወሃ ቀጠነ ክርክር የተዘጋጀ ነበርና ክርክራችን እየጋለ ሂዶ በሁለታችን በኩል መደማመጥ ጠፋ፡፡ከዛም በአነጋገር ዘየየ ትግራዋይነትየን ስላወቀ ነው መሰለኝ ‹‹ ድሮውም ከእናንተ ጋር መነጋገር ትርፉ ይህነው፤ሰው ሲናገር አትሰሙም፤ እናንተ ያለችሁት ግን ያለምንም ማገራገር እንዲሰማላችሁ ትፈልጋላችሁ…›› በማለት ራሱ የጀመረው ዝርጠጣ አርእስቱን ስለቀየረው ሂሳቤን ከፍየ ካፌውን ትቼለት ወጣሁ፡፡
ከላይ ያቀረብኩት ፅሑፍ ዓምና የተከሰተ ነበር፡፡ዛሬም ድረስ ግን ‹‹የደርግ ጭቆናዎች፣የዘር ማጥፋት ወንጀሎች፣ያለ ፍርድ የተፈፀሙ የንፁኃን ጅምላ ግድያዎች፣ቀይሽብር፣ የአውሮፕላን ድብደባዎች ወዘተ በህወሓት ምክንያት የተፈፀሙ ናቸው›› የሚሉ ወገኖች በጣም ብዙ ናቸው፡፡ብዙ ዋልጌዎች፣‹‹ደርግ ቀይ ሽብር ያወጀው ኢህአፓ ነጭ ሽብር በመጀመሩ ነው›› ብለው ይከራከራሉ፡፡ነገር ግን እነዚህ አባባሎች በህፀፆች የታጨቁ ሸውራራ አመለካከት የወለዳቸው ናቸው፡፡ከሰኔ 21 ቀን 1966 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የተከሰቱት መልካአ ምድራዊ፣ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ቀውሶች በደርጋውያን የተፈፀሙ ናቸው፡፡
የዚህ ፅሑፍ መነሻ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ሲሆኑ ዓላማውም ድርግ ሃገር ያላሳደገው፣ተውልድ የገደለውና ሃገራችንን የጦርነት አውድማ ያደረገው ወዶ ሳይሆን ተገድዶ ነው የሚባለው አስተሳሰብ መሰረት የሌለውና የደርግ ጭካኔና ፈላጭቆራጭነት ለማድበስበስ የለመ መሆኑን በማስረጃ በማስደገፍ ፉርሽ ማድረግ ነው፡፡ደርግ ዓለም የመሰከረለት አምባገነን ነበር፤ የቄሳርን ለቄሳር ይሰጥ ዘንድ ግድ ነው፡፡

ህወሓት ለምን የትጥቅ ትግል መረጠ?


በኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የተፃፈው ‹‹ትግላችን›› የተሰኘው መፅሓፍ እንደሚጠቁመው ደርግ የተረገዘው ከሰኔ 19 ቀን 1966 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡በገፅ 153 ላይ ፣‹‹ከሰኔ 19 ቀን 1966 ዓ.ም ጀምሮ በአራተኛ እግረኛ ክፍለጦር ስብሰባ አዳራሽ በአዲስ አበባ ከተማና በአከባቢው የሚገኙ የጦር ክፍል ተወካዮች በተሰበሰቡበት ጊዜ…›› ይላል፡፡
ትንሽ ወረድ ብሎ በገፅ 157 ደግሞ፣‹‹ድርጅታዊ ሥራችንንና ምርጫችንን አከናውነን ሰኔ 21 ቀን 1966 ዓ.ም በቀኑ የሃገሪቱ የዜና ማሰራጫ ሰዓት በራድዮ፣እንዲሁም በምሽቱ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ገፃችንንና የተሰበሰብንበትን ስፍራ የሚያሳይ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ስእላዊ መግለጫ ሳይታከል አጠር ባለ አጃቢ መግለጫ የደርጉን ህልውና ለኢትዮጵያ ህዝብ አበሰርን፡፡›› በማለት ድርግ በይፋ የተመሰረተበትና ዘውዳዊው አገዛዝ ወሽመጡ የተመታበት ቀን ይነግረናል፡፡ከዛች ቀን ጀምሮ የአፃው ስራዓት እየፈራረሰ የደርግ ስልጣን ደግሞ እየጠነከረ ቀጥሏል፡፡በዛች ቀን አምሳለ ሂትለሩ ደርግ በይፋ ተወልዷል፡፡የደርግ ልደት ግን ኮ/ሌ መንግስቱ ‹‹ለኢትዮጵያ ህዝብ አበሰርን›› እንዳለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ብስራት ሳይሆን ታላቅ መርዶ ነበር፡፡
በመቀጠልም ደርግ ሽዋሚና ሻሪ እየሆነ መምጣቱን በገፅ 176 ላይ፣‹‹ጠቅላይ ሚኒስተር እንዳልካቸው መኮንን… ሊያጠፉን ስለሞኮሩ ሓምሌ 15 ቀን 1966 ዓ.ም ከሥልጣናቸው ወረደው ከመሰሎቻቸው… ጋር ተቀላቀሉ፡፡››በማለት ያስረግጥልናል፡፡‹‹ከመሰሎቻቸው ጋር ተቀላቀሉ›› ማለት ከ60ዎቹ ጋር ታሰሩ ማለት ነው፡፡ስለሆነም ሐምሌ 15 ቀን 1966 ዓ.ም ደርግ መሾምና መሻር እንዲሁም እንደፈለገው ማሰር የጀመረበት ቀን መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡ጃንሆይ ግን ‹‹ንጉስ አይከሰስ፣ሰማይ አይታረስ›› የሚባለው ከእርሳቸው ጋር እኩል ያረጀው አባባል ተንተርሰው በማንቀላፋት ላይ ነበሩ፡፡ዳሩ ግን ግዛታቸውም በጥይት ታርሳለች፤እርሳቸውም መከሰስ ብቻም ሳይሆን ግድያም ተፈፅሞባቸዋል፡፡
ፕሮፌሰር ባሕሩ ከላይ በተጠቀሰው መፅሐፋቸው ላይ የ66ቱ አብዮት ጠንሳሾች የደርግ አካሄድ ምን ሊመስል እንደሚችል የታገሩት ትንቢት እንዲህ ፅፈዋል፤‹‹ ንጉሠ ነገሥቱ ከዙፋን ከመውረዱ ከሁለት ቀናት በፊት የወጣው ‹የሠፊው ሕዝብ ድምፅ› በወታደር የሚመራ መንግሥት፣ የፈለገውን ያህል ቅን ልቦና ቢኖረው፣ ዞሮ ዞሮ አገሪቷን ባንድ አምባገነን መሪ መዳፍ ሥር ይጥላታል ሲል ትንቢታዊ ትንተና አቅርቦ ነበር፡፡››(ገፅ 247)
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም ዘውዳዊው ስርዓት ተገርስሶ በወታደራዊው አምባገነን መተካቱን የኢትዮጵያ ህዝብ መርዶ ሰማ፡፡ከዛም የደርግ አዋጆች መጉረፍ ቀጠሉ፡፡መስከረ 4 ቀን 1967 ዓ.ም ከአራት ኪሎ ግቢ የተጀመረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ስልፍ በደርግ ወታደሮች ተቋርጠዋል፡፡የተቃውሞ ሰልፉ ተከትሎም በሰላማዊ ሰልፊ የሚደረግ ተቃውሞ የሚያግድ የአደጋ ጊዜ አዋጅ በደርግ ታወጀ…
የህይወት ተፈራ ‹‹Tower in the sky›› የሚከተለውን ያስነብበናል፡

… On 16 September, 1974 University students organized a demonstration that commenced from Arat Kilo campus. It was going to be the litmus test for the Derg’s patience.
… All of a sudden, we heard shots when we reached Berhanena Selam Printing press in Arat Kilo. There was total chaos…

… A few days after the protest rally, the Derg declared a state of emergency prohibiting protest demonstrations and strikes. It held union leaders and members of the armed forces in custody, accusing them of calling out for Provisional Peoples’ Government, and killed peasants in different provinces for demanding land. In October, it threw teachers and others into jail, on charges of pushing for a Provisional Peoples’ Government. Five members of the armed forces were killed, and several wounded in Harar. A number of people standing in front of the office of the workers’ union looking for a job were mercilessly shot dead.
The Derg’s motto, Ethiopia Tikdem yaleminim dem – Ethiopia first without blookshed – became tainted with blood. (ገፅ 114-116)

ሃይላይ ሓድጉ በ‹‹ፅንዓት›› መፅሐፉ እንዳሰፈረው፣ ደርግ ሕዳር 12 ቀን 1967 ዓ.ም
ማንኛውም ሰው ‹ኢትዮጵያ ትቅደም› የሚለውን ዓላማ ለመፈፀም በመንግስት ወይም በመንግስት በለስልጣን የሚወጡ አዋጆች፣ድንጋጌዎች፣ትእዛዞች እና ደሞቦች እንደይከበሩ፣በንግግር፣በፅሑፍ ወይም በማንኛውም መንገድ በግልፅ ሲያነሳሳና ሲያደፋፈር ከተገኘ ከአንድ እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ከባድ የእስር ቅጣት ይቀጣል፡፡(ገፅ 37)
 የሚል አዋጅ አውጥቶ ማንኛውም ሰላማዊ ተቃውሞ ተቀባይነት እንደሌለው አሳወቀ1፡፡

ዕለተ ቅዳሜ፣ ሕዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም ደግሞ 60ዎቹ የአፄ ኅይለሥላሴ ከፍተኛ አመራሮች ያለምንም ፍርድ በግፍ ተገድሏል8፡፡ቀኑ የደም ቅዳሜ() እየተባለ ይጠራል፡፡
ህይወት ተፈራ ገን በ‹‹Tower in the sky›› ላይ የደም ቅዳሜን ወደ ሕዳር 12 ሳብ አርጋዋለች፤‹‹On November 22, 1974 the Derg’s brutality was officially unleashed. I was home when the radio announced the execitopms pf sixty people, over fifty of whom were ministers and high officials of the former regime,the rest were members the Derg. ›› (ገፅ 117)
እንግዲህ ከላይ ከቀረቡት ማስረጃዎች የምንረዳው ነገር ቢኖር ደርግ ስልጣን እንደ ተቆናጠጠ ሰላማዊ ስልፍ ማገዱን፣ስልጣኑን የጀመረው ሃገራችን በዜጎችዋ ደም በመቀባት ሲሆን ያ መረን የለቀቀ የመግደል ባህሪውም እየቀነሰ ሳይሆን ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት ሄዶ ጨርሶ ነፍሰ በላ መሆኑን ነው፡፡
ታድያ የዚያኛው ዓይነቱ በደም የሰከረ ጭራቅ በነበረበት ወቅት ህወሓቶች ምን ማድረግ ነበረባቸው? መታገል ወይስ እንደ መኢሶኖች ‹‹ሂሳዊ ታቃውሞ›› ባሉት አጉል ስትራቴጂ ከደርግ ጋር በመጠጋት የደርግ ሰለባ መሆን ነበረባቸው? ወታደራዊው የደርግ አገዛዝ እስካለ ድረስ ሰላማዊ ታቃውሞ እንደማይቻል የተረዱ የህወሓት መስራቾች የትጥቅ ትክግል መጀመራቸው ተገቢ ነበር፡፡
የደርግ ፈላጭ ቆራጭነት ብቻ ግን አልነበረም ህወሓት የትጥቅ ትግል እንዲያካሂድ ያስገደደው፡፡ግገሓት፣ኢህአፓና ኢድዩ በትግራይ መሽገው ከደርግ ጋር ጦርነት በመክፈት የህዝቡ ብሔራዊ ጭቆናና ድህነት ከቁብ ሳይቆጥሩ ህዝቡን ያለ አግባብ ይመዘብሩ ስለነበር ለህወሓት ሌላ አሳሳቢ ጉዳይ ነበር፡፡ 

ደርግና ሂትለር


ደርግና ሂትለር በአስተሳሰብና በአሰራራቸው ተመሳሳይ ነበሩ፡፡ሁለቱም መንገዳቸውን የሚገታ ጋሬጣ መስሎ ለሚታያቸው ሰውም ሆነ ድርጅ እንዲሁም ሃገር እንደ መፍትሔ የሚጠቀሙት በማውደም ወይም ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ላይ የጠነጠነ ነበር፡፡‹‹በኢትዮጵያ ትቅደም›› ሃይማኖት አምኖ ያልተጠመቀ ግለሰብ ወይም ድርጅት ፍርዱ ስቅላት ነው፤ ይገለበጣል፣ ይገደላል፡፡ከዛም
‹‹የፍየል ወጠጤ ልቡ ያበጠበት
  ለነብር ብሎ ለነበር ላከበት፡፡
የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች
ልጆችዋም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች፡፡›› (‹‹Tower in the sky›› ገፅ 134)
የሚባለው የዘመኑ ‹‹የስኬት ዘፈን›› በሬድዮና በቴሌቪዥን ያስተጋባል፡፡መንግስቱ የሂትለርና የስታሊን ማንነት የተላበሰ ብቻ ሳይሆን ጠንካራ አምላኪም ነበር፡፡እናም አነሱ ያደረጉት ሁሉም ነገር አድረጓል፡፡ዳሩ ግን የእነሱ አሟሟት አልሞተም፤ከኢትዮጵያ ህዝብ መንጋጋ ዘርፎ በወሰደው ገንዘብና ቀርቅ ዝምባቡዌ እየተዝናና ይገኛል፡፡የአንድ ትውልድ ደም ጠጥቶ የደለበ ዲያብሎስ ዛሬም በኢትዮጵያውያን ላብ በተገኘው ሃብት ዠናጭ ንሮ እየመራ ነው፡፡
ድርግ(መንግስቱ) አሳካቸዋለሁ ብሎ ከተነሳባቸው ዓላማዎች በንፁኃን ላይ የፍፀመው ‹‹ነፃ እርምጃ›› ብቻ ነበር፡፡ልማት፣ስላምና ዴሞክራሲ ግን ከዘውዳዊው አገዛዝ በከፋ መልኩ ነበር ድራሻቸውን ያጠፋቸው፡፡ባስ ብሎ የጦርነት አባዜውም በተጦርነት ለማስቀጠል ሳይችል ቀርቷል፡፡‹‹ኢትዮጵያ ወይም ሞት›› ብሎ እንዳልፎከረ ኢትዮጵያን በመሰዋት በማድረግ ራሱን አድኗል፡፡‹‹ኢትዮጵያ ትቅደም›› መፈክሩን በ‹‹መንግስቱ ይቅደም›› ቀይሮታል፡፡
ያ ፀረ ውይይት፣ መልአከ ሞት
ያ ፀረ ሰላም፣ መንበረ አጋንንት
የቀይ ሽብር ፈላስፋ የጦርነት አባት፡፡
ያ ፀረ ልማት ትውልድ ገዳይ
አምሳለ ይሁዳ የወንዝ ድንጋይ
አቋም የለሽ ወላዋይ
ቃልሉን የበላ ቃል አባይ፡፡
ደብረ ብርሃን ሲተኮስ ከሃገር ሊበር
‹‹አንዲት ጥይትና አንድ ሰው እስኪቀረን ድረስ እንዋጋለን!››
ብሎ ሲፎክር
በሃገር ፍቅር ተቃጥሎ
‹‹ኢትዮጵያ ትቅደምን›› አስከትሎ
ጥሏት የፈረጠጠው እግሬን አውጪኝ ብሎ
ህዝቡን የፈጀው በጠኔና በጦር
ሃገር ያሸበረው በቀይ ሽብር
በሽሽት የሚኖረው እግሮቹ እስኪሰበር
የቃላት ጀግናው ጓድ ሊቀመንበር
‹‹አምሳለ ቴወድሮስ›› የኸው ነበር፡፡
ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ፤ ከ1847 እስከ 1983›› ባሉት መፅሓፋቸው ላይ ደርግን እንዲህ ነበር የገለፁት፡
በብዙ ሰዎች ኅሊና፣ የኢትዮጵያ አበዮትና የመንግሥቱ ስብእና የማይነጣጠሉ ሆነው ቆይቷል፡፡በተለይም ለምዕራቡ ዓለም ከ1966 እስከ 1983 ያሉት የአብዮት ዓመታት አንዳችም ማርከሻ የሌለው ዘመነ ጥፋት ነው፡፡አያሌ ኢትዮጵያውያንም ቢሆኑ፣ሽብርና የርሰ በርስ ጦርነት  ካስከተሉት ደምና ዕንባ ባሻገር፣የአብዮቱን በጎ ገፅታች ለማየት ይቸገራሉ፡፡በሰከነ መንፈስ ሆኔታዎችን ለማጤን ለሚሞክር ተመራማሪም ቢሆን፣ ከሁለት አሠርት ዓመታት ያህል ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች በኋላ ሀገሪቷ ይህን በጎ ነገር አገኘች ብሎ አፍ ሞልቶ ለመናገር ያዳግታል፡፡(ገፅ 238)
አዎ! ደርግ ካፈራው ይልቅ ያወደመው፣ከገነባው ይልቅ ያፈረሰው፣ካለማው ይልቅ ያጠፋው በብዙ ዕጥፍ ያስከነዳል፤ከመወያየት ይልቅ ፍርሐት የወለደው ጭካኔ እንደ ቆራጥነት በመቁጠር፣ ‹‹ነፃ እርምጃ›› እንደ መፍትሔ በመውሰዱ ሃገራችን የጦርነት አውድማ አድጓታል፡፡ካስተማረው ይልቅ ያለፍርድ የገደለውና ያስገደለው ኢትዮጵያዊ ወጣት በእጅጉ ይበልጣል፡፡መንግስቱ ‹‹የአንድ ትውልድ ወጣት›› እንደ እሳት ዶግ አመድ ያደረገ ጭራቅ ስለሆነ አይሁዳውያንን ለመፍጀት ሆለካስትን ከፈለሰፈው ሂትለር ጋር በጣም ይቀራረባሉ፡፡
በሌላ መነፅርም ደርግን እንደ ፎርዖን ማየት ይቻላል፡፡ይህ ማለት ደግሞ የትግራይ ህዝብ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብን ከፎርዖኖች የጭቆና ከንበር የሚያወጣ ህወሓቱ ሙሴ አስፈላጊ ነበር ማለት ነው፡፡እናም በማሓሪ ተክለ(ሙሴ) የሚመራው ህወሓት በጉልበት የህዝብ ስልጣን የነጠቀው ፎርዖንን በሚያውቀው ቋንቋ በማስረዳት ህዝቡን ለመታደግ ወደ ደደቢት በማምራት የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም የሁለተኛው ወያነ መጀመር የበሰረችው ጥይት ተኮሰ፡፡ህወሓት ደደቢት ወርዶ የትጥቅ ትግል ባይ ጀምር ንሮ እንደ ኢህአፓና መኢሶን የቀይ ሽብር ሰለባ ሁኖ ይቀር ነበር፡፡
ስለዚህ የተራዘመ የትጥቅ ትግል እንዲያደርግ የተገደደው ህወሓት እንጂ ደርግ አልነበረም፡፡ድርግን የሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት፣ የወታደራዊና የፖለቲካዊ ስልጣን ባለቤት ስለነበር የፈለገውን ሁሉ የማድረግ ዕድል ነበረው፡፡‹‹ጊዚያዊ ህዝባዊ አስተዳደር አሁን›› እያሉ ለሚቃወሙት ተቃውሟቸው በሰላማዊ መንገድ እንዲቀጥሉ ማግባባት ይችል ነበር፡፡ደርግ የወሰደው ምርጫ ግን ገድሎ መጠየቅ፤ከዛም ‹‹የፍየል ወጠጤ›› እያሉ መዝንን ነበር የመረጠው፡፡


ህወሓትና ሙሴ


ህወሓት(የህወሓት መሪ የነበረው ታጋይ ሙሴ) እና የመፅሐፍ ቅዱሱ ሙሴ ታሪካዊ አሻራዎች ተመሳሳይ ናቸው፡፡ህወሓት የኢትዮጵያ ህዝብን የብሔራዊ ጭቆና ግንባር ቀደም ተጠቂ የነበረውን  ከደርግ መንጋጋ ነፃ አወጣ፡፡የኦሪቱ(የመፅሐፍ ቅዱሱ ወይም አይሁዳዊው) ሙሴም አይሁዳውያንን ከፎርዖኖች አገዛዝ ነፃ በማውጣት ወደ ‹‹የተስፋይቱ ምድር›› አድርሷል፡፡ልዩነታቸው፣ የአይሁዶች መሪው ሙሴ ‹‹በእግዚአብሔር የተመረጠ››፣ ‹‹የእግዚአብሔር ምክርና ድጋፍ ያልተለየው የእስራእየላውያን ነፃ አውጪ›› ሲሆን ህወሓት ግን በራሱ ብቃት፣በራሱ ውሳኔ፣አስከፊ ብሔራዊ ጭቆናና ጭቆናው የወለደው ድህነት አንገሽግሾት የተነሳ የኢትዮጵያውያን ነፃ አውጪ መሆኑን ነው፡፡የህወሓት ጥንካሬ ህዝባዊነቱ ሲሆን የሙሴ ጥንካሬ ግን የሰይጣን ይሁን የመልአክ በውል ያልታወቀ ምትሐት ነበር፡፡
እናም ህወሓት ለአብዛኞቻችን ኢትዮጵያውያን ከአይሁዳዊው ሙሴ በላይ ነው፡፡የህወሓት ታጋዮች ለህዝቦች ነፃነትና እኩልነት ራሳቸው አሳልፈው የሰጡ፣የቆሰሉ፣የተራቡ፣ የታረዙና የተጠሙ ሰማእታት ሲሆኑ አይሁዳዊው ሙሴ ግን በምትሓት እየታገዘ ‹‹በዱላው ባሕሩን እያደረቀ››፣ያለ ምንም ድካም ‹‹ከአለት ውሃ እያፈለቀ፣ ባንዲት አምባሻ ሽዎችን እየመገበ›› ነበር ‹‹እስራኤላውያንን ከፈርዖኖች አገዛዝ መንጭቆ››፣ የሲናይ በረሃዎችን እያቆራረጠ በመምራት፣ ቀይባህርን አሻግሮ ወደ ‹‹የተስፋይቱ ምድር›› ያደረሰው፡፡
ሙሴ አይሁዳውያንን ብቻ ከፎርዖኖች ጭቆና ለማዳን በአይሁዳውያን አምላክ የተላከ ሲሆን ህወሓት ግን ዘራቸው፣ብሔራቸውና እምነታቸው የፈለገው ይሁን መላው ጭቁን ኢትዮጵያወያንን ነፃ ለማውጣት በራሱ ተነሳሽነት(በአምላክም ይሁን በሰይጣን ሳይላክ) እንደ አምላክ ሆኖ የአምላክ ስራ የሰራ ነፃ አውጪ ነው፡፡ህወሓት እንደ ሙሴ የመረጠውን ብቻ(አይሁዳውያን ብቻ) ይዞ ከፎርዖኖች አገዛዝ ለማምለጥ የሸሸ ሳይሆን ፎርዖኑን ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ በፎርዖን የጭቆና ቀንበር ስር የነበሩትን ሁሉ ነፃ ያወጣ ህዝባዊ ድርጅ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ አንድ አንድ ከሃዲዎች በህወሓት ስም ክልክ በላይ የሚባልጉና ህዝብ የሚያንገላቱ ህወሓት መሰል ተኩላ ባለስልጣኖች የደደቢቶቹ ታጋዮችን አይወክሉም፡፡እነዚህ ሙሰኛ በርጫም ባለስልጣናት በማንኛውም መስፈርት ከድሮዎቹ የህወሓት ተጋዮች አይመሳሰሉም፡፡የዛሬዎቹ ከድሮዎቹ በቅርፅ፣በአኗኗር፣በአስተሳስብና በአሰራር የተለዩ ናቸው፡፡የድሮዎቹ(እውነተኛ ህወሓቶች) ታጋዮች የእኔ የሚሉት ነገር አልነበራቸውም፤ዛሬም ድረስ የላቸውም፡፡ውድ ህይወታቸውም ጭምር የህዝብ እንደሆነ ነበር የሚያምኑት፤ዛሬም ይህንን አቋም የሚያራምዱ ታጋዮች አሉ፡፡በመሆነም አንድ አንድ ሙሰኛ የህወሓት ባለስልጣኖችን በመጠቆም ፎርዖኑ ደርግ ከህወሓት ጋር ማወዳደር ተገቢ አይደለም፡፡


ዋቢ መፃሕፍት
[1]. ሃይላይ ሓድጉ፡፡ፅንዓት፡፡መቐለ፤2001፡፡
[2]. መንግሥቱ ኃይለማርያም፡፡ትግላችን፤የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ፤ቅፅ፤ 1፡፡ሎስአንጀለስ፤2004፡፡
[3]. ባሕሩ ዘውዴ፡፡የኢትዮጵያ ታሪክ፤ ከ1847 እስከ 1983፡፡አዲስ አበባ፤2000፡፡
[4]. Hiwot Tefera.(2012). Tower In The Sky. Addis Ababa University Press, Addis Ababa.


ዋቢ ድረገፆች

4 comments:

  1. Thank you Asfaw Gedamu, it is very interesting article. Just a minor comment: You wrote ''በሌላ መነፅርም ደርግን እንደ ፎርዖን ማየት ይቻላል፡፡ይህ ማለት ደግሞ የትግራይ ህዝብ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብን ከፎርዖኖች የጭቆና ከንበር የሚያወጣ ህወሓቱ ሙሴ አስፈላጊ ነበር ማለት ነው፡፡እናም በማሓሪ ተክለ(ሙሴ) የሚመራው ህወሓት በጉልበት የህዝብ ስልጣን የነጠቀው ፎርዖንን በሚያውቀው ቋንቋ በማስረዳት ህዝቡን ለመታደግ ወደ ደደቢት በማምራት የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም የሁለተኛው ወያነ መጀመር የበሰረችው ጥይት ተኮሰ፡፡''

    Musie was not one of the 10/11 Tegadelti who shot the first bullet in Dedebit in Lekatit 11, 1967 Et/C. It is true that Musie had prior contact with TPLF, but he joined them few months later. He led the few Tegadelti who were trained in Eritrea and joined the first group at Hirmi. You can read Biserat Amare's and Hailay Hadgu's books. Thank you and keep it up!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. This comment has been removed by the author.

      Delete
    2. You are right Anonymous! I didn't mean Muse was among the 11 TPLF members who fired the first bullet of straggle.

      Delete
  2. I am really sorry to read a kind of article from you. i thought you are neutral and can be one of the emerging young generations in Tigray but all of the sudden you become a more biased than the man you mention for your article. really shame to compare Musie TPLF to Bible Musie . I am sure even the old drunkard sibat can't accept this analogy . your article is really rash, i wast my precious time reading... It shame you try to hide you jackass identity in sheep by just inserting a simple clause which blames some TPLF leaders and tries to defuse the perception. for sure if TPLF was genuine from the beginning it couldn't be twisted to be a bad corrupt organization of a family like we are seeing it now. I am not saying all TPLF fighters was evil but I can surely say TPLF was in the hands of evil and corrupt mind cadres at least from the time it takes a shape of a party.

    ReplyDelete