ዛሬ ጥዋት ፋና ብሮድካስቲንግ የዘገበው አስገራሚ ዜና ነው፡፡ሰላም ሐጎስና ሰላም ደሞዜ የተባሉ ታማሚዎች ለህክምና ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ይመጣሉ፡፡ሰላም ሐጎስ የሃሞት ጠጠር ሕመምተኛ ስትሆን የቀዶ ሕክምና ቀጠሮዋ ደርሶ ወደ ሆስፒታሉ ታመራለች፡፡ሰላም ደሞዜም የቀዶ ሕክምና ቀጠሮ ነበራት፣ የእንቅርት እጢ ለማስወጣት፡፡የሆነው ግን እጅግ የሚያሰደነግጥ ነው፡፡ሰላም ደሞዜ የእንቅርት(የአንገት እጢ) ቀዶ ጥገና ብቻ ሊደረግላት ሲገባ የሃሞቷም ጭምር ተቀደደች፡፡ከኤንስቴዥው ስትነቃ ጨኾች፤ የታመምኩት እንቅርቴ ሆኖ ሳለ ሆዴ ለምን ቀደዳችሁኝ ብላም ጠየቀች፡፡ነርሶቹ ‹‹ችግር የለውም ተረጋጊ፤ እንዳውም ተጨማሪ ቀዶ ጥገና በነፃ አድርገንልሻል›› አሏት፡፡ባትስማማም ሰሚ አላገኘችም፡፡
ሰላም ሐጎስ በበኩሏ እንደጠበቀችው የእንቅርት እጢ ለማስወጣት የሚደረገው ቀዶ ጥገና ሳይሆን የሃሞት ጠጠር ሊወጣላት መሆኑን ተነገራት፡፡አይደረግም አለች፡፡አራጆቹ አልተበገሩም፣ በሐይል ሊቀዷት ተዘጋጁ፡፡ እርይታዋን አቀለጠቸውና ወጣች፡፡
ይህን በተመለከተ የሐኪሞቹ ተቆጣጣሪ ማነጋገር እንደሚፈልጉ ተናገሩ፡፡ አርፋችሁ ተቀመጡ የሚል መልስ ተሰጣቸው፡፡የፋና ጋዜጠኛ እንደዘገበው ከሆነ የዘውዲቱ ሆስፒታል መዲካል ዳይረክተርም ተፈልጎ ሊገኝ አልቻለም፤ ስብሰባ ላይ ናቸው በሚል ሰበብ፡፡
ይህ ወሬ፣ የሙያ ስነምግባርና የአካዳሚክ ብቃት ሳይኖራቸው በፎርጅድ ወረቀት ሰው የሚያርዱ ‹‹ሓኪም›› ተብየዎችን ይባስ እንድፈራቸው አደረገኝ፡፡ኧረ እንዳውም ሐኪም የሚሉት ሁሉ እንድጠራጠር አድርጎኛል፡፡
ለምን ቢባል እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ክስተቶች መደጋገማቸው ስለበዛ፡፡የታመመው እግሩ ሊቆረጥ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ያመራው ታካሚ ጤነኛው እግሩ መቆረጡን አስታውሳለሁ፡፡
No comments:
Post a Comment