Tuesday, December 24, 2013

የክላሽንኮቭ( AK-47) ፈጣሪው ምኻይል ክላሽንኮቭ በ94 ዓመታቸው አረፉ




Lieutenant General Kalashnikov  With his Ak-47
ምኻይል ክላሽንኮቭ ራሽያዊ ሲሆኑ ለዓለም ህዝብ ስርተው በበረከቱት ገዳይ መሳርያ ይታወቃሉ፡፡ያገዳይ መሳርያ ለስማቸው መታሰብያ ይሆን ዘንድ በስማቸው ይጠራል…ክላሽንኮቭ ( AK-47)፡፡ የክላሽንኮቭ በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዛት ከተሸጡ ገዳይ መሳርያዎች በአንደኝነት ይመራል፡፡መሳርያው በሃገራችንም ሆነ በዓለም ደረጃ ብዙ ሰዎች ተገድሎበታል፤ በጦርነት፣ በእርሰ በርስ ግጭት፣ በአምባገነኖች ቅጣት ወዘተ፡፡


የ60ዎቹ የሃገሬ ወጣቶች ደርግን ለመጣል እስከ አፍንጫቸው ከታጠቋቸው እሳት የሚተፉ መሳርያዎች የክላሽንኮቭ( AK-47) ቀዳሚው ነበር፡፡የደርግ ወታደሮችም በትግራይ ተራሮች በእረኝነት የተሰማሩ ወጣቶች ሳይቀር ዓልሞ ተኳሽነታቸውን ለማስመስከር በዚሁ መሳርያ ይገድልዋቸው እንደነበር የቅርብ ተውስታ ነው፡፡የብዙ ህፃናትና ወጣቶች ለጋ ዕድሜ ቀጭታለች…የክላሽንኮቭ( AK-47) ፡፡ የዚች አውዳሚ መሳርያ ፈጣሪ ግን ለ94 ዓመታት በዚች ዓለም ኖሮ ከሶስት ቀናት በፊት ማረፉቸው ያስደምማል፤ ዓለም ፍርደ ገምድል ነች ያሰኛል፡፡ደግሞ ማንም ተኩሶ አልገደላቸውም… አርጅተው ጃጅተው ነው የሞቱት፡፡


AK-47
ሌፍትናንት ጀነራል ምኻይል ክላሽንኮቭን በኣካል የሚያውቋቸው በጣም ጥቂተ ናቸው፤ ምናልባትም ጥቂት ራሽያውያን፡ለመጀመርያ ጊዜ ንድፍ ሃሳብ አውጥተው የፈጠሯትና የሚልዮኖች ፍጡራን ህይወት የቀጠፈችው ክላሽንኮቭ ግን ብዙ ታጋዮች ያውቋታል፡፡የብዙዎቹን ስጋና ጅማት በጣጥሳለች፣ የብዙዎችን አጥንት ድቄት አድርጋለች… አሁንም ድረስ አረሯን በሰውነታቸው ተሸከመው የሚንቀሳቀሱ፣ መርዛማ ስቀይዋን በየሰከንዱ፣በየደቂቃውና በቀኑ ተቋቁሞው የሚኖሩም ብዙ ናቸው፡፡


በዓለማችን አራቱም ማአዘኖች ራሳቸውንና ሃገራቸውን ከወራሪዎች ነፃ ለማውጣት ወይም ለመከላከል ወይም በሃይል ለመውረር ከተጠቀሙባቸው የጦር መሳርያዎች ሁሉ በብዛት ክላስንኮቭን የሚያስከነዳ የለም፡፡


ክላሽንኮቭ በራሽያዊው ለፍተናንት ጀነራል ተስርታ ለገበያ ብቅ ካለችበት ጊዜ ጀምሮ ከ70 እስከ 100 ሚሊዮን በለይ መሸጧን ይነገራል፡፡ምን ያህል የሰው ህይወት እንደቀጠፈች ግን በውል አይታወቅም፡፡የሚያሳዝነው ደግሞ ይህች መሳርያ ዛሬም ድረስ ብዙ ሰዎች እየተገደሉባት ነው፤ ለወደፊትም መግደልዋ የሚቀር አይመስለኝም፡፡





No comments:

Post a Comment