Tuesday, January 7, 2014

‹‹በመቐለና መቀሌ ስሞች የትርጉም ልዩነት የለም›› አብርሃ ደስታ





ወንድማችን አብራሃ ደስታ ለጌቶቹ ሲል ማንነቱን ከሸጠ ቀይቷል፡፡ማንነቱን የሸጣት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይሆን አይቀርም፤ ምናልባትም ለማርክ ሊሆን ይችላል፡፡ ሳስበው ሳስበው ‹‹የምሁራን ሰርትፊኬት›› ለማግኘት ማንነቱን መሸጥ ነበረበት መሰለኝ የሚፅፈው፣የሚናገረው፣የሚቃወመውና የሚደግፈው ሁሉ የጌቶቹን ፍላጎት በማጤን ነው፡፡እንዳውም ሲያስተምርም እነሱን እያሰበ ሳይሆን አይቀርም፡፡እኔ በህይወቴ እንዲህ ዓይነቱ ታዛዥ ሰው ይቅርና ለማዳ እንስሳም አይቼ አላውቅም፡፡እንስሳ የፈለገው ያህል ለማዳ ቢሆንም የማይመቸው ነገር ሲያጋጥመው መምፈራገጡ አይቀርም፡፡


የአብርሃ ታዛዥነት በመፅሐፍ ቅዱስ ከምናውቀው የአብርሃም ብቸኛው ልጅ ከይስሐቅ ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡ምክንያቱም (ምስጢራዊ ትርጉም ግምት ውስጥ ሳናስገባ) ሁለቱም የሚጨነቁት ስለሌሎች እንጂ ስለራሳቸው አይደለምና፡፡ይሁን እንጂ የይስሐቅ ታዛዥነት ለሰማያዊ ፅድቅ ሲሆን የወንድማችን አብርሃ ግን ምድራዊ ነው( ምናልባት የአብርሃ ጌቶችም ራስህን ሽጠህ እኛን ለስልጣን ካበቃህን የአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ብቻ ሳይሆን ሰማያዊው ቤተ መንግስትም ትወርሳለህ ብለው ቃል በመግባት ካላሳመኑት በስተቀር)፡፡

አብርሃ ደስታ ምድራዊና ሰማያዊ ቤተ መንግስት ትወርሳለህ ብለው ካላሳመኑት በስተቀር ‹‹በመቐለና መቀሌ ስሞች የትርጉም ልዩነት የለም›› ይላል ብየ አላምንም፤በጭራሽ፡፡ለምን ቢባል፤ መቐለ የትግርኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ደግሞ ለሁለት ወይም ከሁለት በላይ ከፈለ ማለት ነው፡፡መቀሌ ግን በትግርኛ ቀርቶ በማንኛውም ቋንቋ ትርጉም የለውም፤ በአማርኛም ጭምር፡፡ህሊናው ለሳተ፣ጤናው ለተቃወሰ፣ማንነቱን ለሸጠ ሰው ግን ልዩነት ላይኖራቸው ይችላል፡፡ማገናዘብ ለተሳነው ሰው ልዩነት ብሎ ነገር የለማ፡፡ለነገሩ ማገናዘብ ቢችል ንሮ ማንነቱን አይሸጥም ነበር፡፡የአብርሃ ችግር ደግሞ ማገናዘብ እንደተሳነው አለማወቁን ነው፡፡

በመሆኑም የህን ፅሑፍ የምፅፈው አብርሃ ደስታ መሳሳቱን ላስረዳው ፈልጌ ሳይሆን ሌሎች ወገኖቼ እርሱ የፈፀመው ስህተት ትክክል መስሏቸው እንዳይሳሳቱ ለማስገንዘብ ነው፡፡ባለማወቁ የሚሳሳት ሰው ምንጊዜም ቢሆን ለመታረም ዝግጁ ነው፡፡ከእውቀት ማነስ ለሚሳሳቱ ሰዎች የሚያውቁ ሰዎች እንዲያስተካክሉ ሊነገሯቸው ይገባል፡፡ምክንያቱም እንዚህ ሰዎች እየተሳሳቱ ያሉት ሆን ብለው አይደለም፤ ስለማያውቁ ነው፡፡እናም ማሳወቅ በቅንነት ለሚሳሳቱ ሰዎች ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡

እያወቁ የሚሳሳቱ፣ ሆን ብለው የሚያበላሹ ሰዎች ግን ዓላማ አላቸው፡፡ለማወቅም አይፈልጉም፣ አስተካክለው ለመናገርና ለመፃፍም ደንታ አይኖራቸውም፡፡ተናጋሪው ማህበረሰብ ማንነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል አይፈልጉማ፡፡ይህ ደግሞ በተናጋሪው ማሕበረሰብ ያላቸው ንቀት ያሳያል፡፡ከምንም ተነስቶ አንድን ማሕበረሰብ መናቅ ደግሞ ባዶነትን ያሳያል፡፡ባዶ የሆነ ሰው ደግሞ  ለሌሎች ይቅርና ለራሱም ደንታ የለውም፡፡እኛም ማስተካከያ እየጠየቅን ያለነው ባለማወቃቸው ለተሳሳቱ ሰዎች እንጂ እያወቁ ለሚያበላሹ ሰዎች አይደለም፡፡እኔም ይህን ፅሑፍ እየፃፍኩ ያለሁት ሆን ብሎ ለማበላሸት ለተነሳው ድንጋይ ራስ አለመሆኑን ይታወቅልኝ፡፡

አብርሃ ‹‹‘መቐለከማለትመቀሌየሚል ስም የመረጥኩበት ምክንያት እየፃኩ ያለሁት ባማርኛ ስለሆነ ነው።›› ይለናል፡፡ቋንቋ መሰረትና ስርዓት ያለው መግባብያ ነው፡፡ ቋንቋ መሰረት አለው፤ተናጋሪ ከሌለው ሊኖር አይችልምና፡፡ቋንቋ ስርዓት አለው፤ ከስርዓት ውጪ ከተጠቀምንበት ትርጉም  አይሰጥምና፡፡ትርጉም የማይሰጥ ከሆነ ደግሞ ዓላማው ይስታል ማለት ነው፤ መግባብያነቱ ይቀራል፡፡መሰረቱና ስርዓቱ የሚመነጨው ከተናጋሪው ማሕበረሰብ ነው፡፡መቐለ መሰረቱ ትግርኛ ስለሆነ ትርጉም ሊሰጥ የሚችለው የቃሉ አጠቃቀም እንዴት እንደሆነና ምን ማለት መሆኑን ለሚያውቁ  የትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ ነው፡፡

የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች የመቐለ ትርጉምና የአጠቃቀም ስርዓት ለማወቅ ከፈለጉ ለሚያውቁ ሰዎች መጠየቅ ይችላሉ፡፡መጠየቅ የበታችነት ምልክት ሳይሆን የብልህነት ምልክት ነው፡፡ብልህ ሰዎች ለራሳቸው ክብር ይሰጣሉ፤ ክብራቸው ሊጠበቅ የሚችለው የሌሎች ክብር ሲጠበቅ መሆኑን ስለሚያውቁም ከመሬት ተነስተው የሌሎች ክብር አይነኩም፡፡በመሆኑም ስለሌላው ማሕበረሰብ ባህል፣ ቋንቋ፣ ልምድ፣ እምነትና ስርዓት ወዘተ ክብር አላቸው፡፡

ስለዚህ መቐለ ትግርኛ ስለሆነ የአማርኛና የሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎችም በፈለጉት መንገድ ሊፅፉት አይችሉም፡፡ለትግርኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ክብር አላቸዋ፡፡ከትግርኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ጋር ተከባብረውና ተግባብተው መኖር ይፈልጋሏ፡፡አብርሃ ግን ለራሱም ለትግርኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብም ደንታ የለውም፡፡በመሆኑም መቐለ ብሎ ከመፃፍ ይልቅ መቀሌ ብሎ ይፅፋል፡፡ በትግርኛ ሲፅፍ መቐለ ብሎ ይፅፋል፤ በአማርኛ ሲፅፍ ደግሞ መቀሌ እያለ ይፅፋል፡፡

እዚጋ ልብ እንበል፡፡ አብርሃ ሆን ብሎ እያበላሸ ያለው የትግርኛ ቋንቋ የአጠቃቀም ስርዓት ብቻ ሳይሆን የአማርኛም ጭምር ነው፡፡የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የአማርኛ አጠቃቀም በየትኛም ቦታና ጊዜ እንዲበላሽባቸው አይፈልጉም፡፡የሌሎች ቋንቋ አጠቃቀምም እንዲበላሽ አይፈልጉም፡፡ሌላ ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች ጋር ተከባብረውና ተግባብተው ለመኖር እስከፈለጉ ድረስ፡፡እናም የትግርኛ ቋንቋ የአጠቃቀም ስርዓት እንዲሽሩና ሆን ብለው እንዲያበለሹ በማድረግ የአማርኛ አጠቃቀምም እንዲሻር እያደረገ ነው፡፡
 
እርሱ ራሱ ያበላሸው እንደምሳሌ ልጠቀም፤አብርሃ ‹‹በትግርኛአምሓርኛእንላለን።አምሐርኛማለትአማርኛማለት ነው።››ብሎ ፅፈዋል፡፡ አማርኛ ቋንቋ በትክክል ሲፃፍ አምሓርኛ አለመሆኑን የማያውቁ ትግርኛ ተናጋሪዎች ‹‹አምሐርኛማለትአማርኛማለት›› ሊመስላቸው ይችላል፡፡ነገር ግን ስለመሰላቸው ትክክል ናቸው ማለት አይቻልም፡፡አማርኛ በትግርናም ይፃፍ በአማርኛም ይፃፍ ያው ነው፤ አማርኛ፡፡ከዚህ ውጪ የሚፃፍ ካለ ስህተት ነው፤ መታረም አለበት፡፡ የቋንቋው ስርዓት አይፈቅደምና፡፡አማርኛን ምሓርኛ ተብሎ ከተፃፈ ትርጉም አይሰጥም፡፡ትርጉም ካልሰጠ ደግሞ አያግባባም፡፡
 
በሌላ ምሳሌ ደግሞ ‹‹መቐለለሚለው የትግርኛ ቃልና ድምፅ መቀሌ በሚል ቃልና ድምፅ መተካቱ ካናደደንበእንግሊዝኛምመቐለተብሎ አይፃፍም። በእንግሊዝኛ ‘Mekelle’ (‘መከለ’) ይሉታል።መቐለመከለ’ (Mekelle) እኩል ነው እንዴ? አይደለም።››በማለት ሌሎች ለማሞኘት ሞክሯል፡፡ሲጀምር መናገርና መፃፍ ሁለት የተለያዩ የቋንቋ ችሎታዎች ናቸው፡፡መቐለን በትክክል ማድመጥና መፃፍ የሰማይና የምድር ልዩነት አላቸው፡፡
 
‹‹ቐ›› በአማርኛ ወይም በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚተካው ፊደል ከሌለ ከዚሁ ፊደል ጋር በድምፅ የሚመሳሰል ሊተካው ይችላል፡፡በመሆኑም መቐለ በእንግሊዘኛ Mekelle ተብሎ ሊፃፍ ይችላል፤ Mekelye ግን አይባልም፡፡ፈረንጆች ‹‹ቐ››ን ማድመጥ ካልቻሉም ‹‹መከለ›› ብለው ሊያነቡት/ሊያደምጡት  ይችላሉ፡፡ አሁንም ግን ስህተቱ በትክክል ተቀርፈዋል ማለት አይቻልም፡፡ብያንስ ብያንስ ግን መቐለ በመከሌ አልተተካም፡፡ ነገር ግን መፃፍና መናገር(ማድመጥ) በልምምድ ልናዳብራቸው እንችላለንና ‹‹ስላልቻልን ነው›› እያሉ በተደጋጋሚ ጥፋት  መስራት ተገቢ አይደለም፡፡
 
‹‹በመቀሌና መቐለስሞች መሰረታዊ የሆነ ልዩነት የለም።››ይላል፤ ለትግራይ ህዝብ ነፃነት እየታገልኩኝ ነው ባዩ አብርሃ ደስታ፡፡መሰረታዊ ልዩነታቸው ከላይ ፅፌዋለሁ፡፡አሁን ደግሞ ራሱ ባመነበት ልሞግተው፤‹‹ትግሬና ትግራይ የተለያየ ትርጉም አላቸው።››ካልን በመቀሌና በመቐለም በጣም ሰፊ ልዩነት አለ፡፡መቐለ ትርጉም አለው ‹‹ከፈለ›› ማለት ነው፤ በተጨማሪም የከተማ ስም ነው፡፡መቀሌ ግን ትርጉም የለውም፡፡እናም ሁለት የተለያዩ ቋንቋዎች የሚወክሉ ስሞች የተለያዩ ናቸው እያልን፣ ትርጉም  ያለው ቃልና ትርጉም የለሹ በምን ሂሳብ ነው ‹‹መሰረታዊ  የሆነ ልዩነት የለም›› የምንለው???
 
‹‹‘የትግራይ ከተማ ስም ምንድነው?’ ቢባል መልሱመቀሌ’ (ባማርኛ ስትናገር ወይ ስትፅፍ) ነው።›› መምህር አብርሃ፣ ይህ በጣም ትልቅ ኤክስ ነው፡፡የትግራይ ዋና ከተማ ስም በትግርኛም ተፃፈ በአማርኛ ያው ነው፤ ወደድክም ጠላህም መቐለ ትለዋለህ። ጌቶችህም ቢፈልጉ አፍንጫቸውን ይልሳሉ እንጂ ሰማይና ምድር ቢገለባበጡም መቐለ  መ…ቐ…ለ  ነች፡፡ይህን የማታውቅ ከሆነ ወደ አፀደ ህፃናት ሂደህ ተማር፤ ሀ..ሁ...ሂ…
 
‹‹መርከቧ የፌደራል መንግስት (የሀገር) ንብረት ከሆነች በአማርኛ ቢፃፍ ችግር ያለው አይመስለኝም።›› በአማርኛ ቢፃፍ ችግር ከሌለው በትግርኛ መፃፉስ በምን ስሌት ነው ችግር የሚኖረው???በትግራይ ዋና ከተማ ‹‹መቐለ›› የምትጠራ መርከብ የፌደራል መንግስት በመሆንዋ ‹‹መቀሌ›› ከተባለች በአማራ ዋና ከተማ ‹‹ባህር ዳር›› የምትጠራ ሌላኛዋ የፌደራል መንግስት መርከብ ‹‹ባሕሪ ወሰን›› ብትባልስ???    
‹‹ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች የመርከቧ ስም ማወቅና ማንበብ መቻል አለባቸው።›› እኛም እንዲያውቁ ነው እየሰራን ያለነው፤ ገሼ አብርሃ፡፡ማወቅ የለባቸውም ያለ ሰው የለም፤ ሊኖርም አይችልም፡፡ስናሳውቃቸው ግን (ደረታችን ነፍተን) የመርከቧ ስም  መቀሌም ተባለ መቐለ ያነው ብለን ሳይሆን መቀሌ ትርጉም የለውም መቐለ ግን የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሚወክል ሲሆን ትርጉሙ ደግሞ ከፈለ ማለት ነው፤ እያለን ነው፡፡ከዛ በኋላም ‹‹የመርከቧ ስም አንብቦ ማወቅ የሚችል ሰው ትግርኛ ቋንቋ የሚችል ብቻ›› ሳይሆን የፈለገው ቋንቋ የሚናገር ሁሉ በደንብ አንብቦ ማወቅ ይችላል፡፡ ከማስተማራችን በፊት‹‹ የመርከቧን ስም ንገረን ወይ ፃፍልን ብንለው›› ግን እርሶ እንዳሉት ‹‹ አይችለውም። ››
በመጨረሻ በአቶ አብርሃ ‹ስለዚሆች› ሃሳቤን ልቋጭ፤ ለጊዜው ሁለቱም እጠቅሳለሁ…ብዙ ስለዚሆች ስላሉ፡፡
‹‹ ስለዚህስማችን መቐለ ነው፤ መቀሌ ብላቹ እንዳትጠሩን!’ ብለን ከተከራከርንጭራሽ ስማችን እንዳትጠሩንእንደማለት ነው።›› ማን አለ??? ‹‹ስማችን መቐለ ነው፤ መቀሌ ትርጉም የለሽ ቃል ስለሆነ እኛን ለመጥራት ስትፈልጉ መቐለ ብላችሁ ጥሩን፤ ከአሁን በፊት መቀሌ ተብሎ የተፃፈ ካለም መቐለ ብላችሁ እንደገና በመፃፍ አስተካክሉት›› ማለት ክርክር ሳይሆን እርማት ነው፡፡‹‹ጭራሽ ስማችን እንዳትጠሩን›› ማለትም አይደለም፡፡
‹‹ስለዚህተሳስተሃልያልከው ስለተሳሳተ ሳይሆን ትግርኛ ስላላወቀ ነው።›› የተሳሳተው ትግርኛ ባለማወቁ  ከሆነ እንዳይሳሳት ከፈለገ ትግርኛ ይወቅ፡፡ ‹‹ትግርኛ የማወቅ ግዴታ ደግሞ የለውም።›› ከተባለም  የትግርኛ ቋንቋ ስርዓት የመሻር መብትምስ ማንሰጠው??? ማለታችን አይቀርም፡፡አይ ‹‹ትግርኛ የማወቅ ግዴታ የለኝም፤ የተሳሳትኩትም ትግርኛ ባለማወቄን ነው›› ብሎ ሙጭጭ የሚል ካለም ‹‹ኻልቢ መን አግበአኪ(ኣእተወኪ) አብፅግኢ›› እንለዋለን፡፡


በመጨረሻ የፍሬው ሃይሉ ‹‹ዓደይየ ዓደይየ መቐለዓደይየ›› ዘመን ተሻጋሪ ዘፈን እንሆ ለቅምሻ፡፡

3 comments:

  1. I don't like Abreha Desta but on the issue of Mekelle he had given us brilliant explanation that we can't even oppose. Guys don't be stiff necked, Abreha can't be all the time wrong and you can't be all the time right. When Abreha writes truth you have to surrender and when he is wrong oppose him. It's so.

    ReplyDelete
  2. እኛ ኢትዮጵያውያን እንዲህ ቃላት እየሰነጠቅን ከምንውል ድህነትን ምናቸንፍበት ፣ ወጣት ለስደት ወጥቶ ከሚረግፍበት ኣስተሳሰብን የሚቀይር ወይም ሙሰኞችን ወደ ልቦናቸው የሚመልስ ትምህርት ኣዘል ነገሮችን ብንወያይ ምን ኣለበት መቐለ ይበል መቀሌ ወይም መከለ በከተማዋ የእድገት፣ የባህል ኣልያም የመዋቅሯ የሚያመጣው ለውጥ ኣለ? ይልቁንስ ኣገራችን ከሚያናጋ ከተማዋን ከሚበዘብዝ ህዝቧ ከሚያናቁር ሰርጎ ገብና ሙሰኞች ኣስመልክተህ ኣንዲት ኣረፍተ ነገር በፃፍክ። 'ትበላው የላት ትከናነበው ኣማራት' ኣሉ ኣበው ። ከተማዋን እንዲህ ባለ መንገድ እቆረቆርላታለሁ የምትል ከሆነ ተሳስተሃል ኣላፊ ኣግዳሚውን ከሚያዳልጥ ወይም ያቆሻታል ብለህኣ ስበህ የሙዝ ልጣጭ ከኣስፓልት ኣንስተህላት ታውቃለህ ? ወገኛ ነህ

    ReplyDelete
  3. @ asfaw gedamu..ስለ መቀሌ እና መቐለ ያለው ልዩነት ጥራት ባለው መልኩ አስፍረኋል.ይሁንና በትግሬ እና በትግራይ ያለው ልዩነትስ...

    ReplyDelete