![]() |
ኢትዮጵያዊነት በየዓይነት
ነው፤ ዓይነት በተጨመረበት ቁጥር የሚጣፍጥ፡፡
|
ይህ ጥቅስ የእግዚአቢሔር
ቃል እንደሆነ በሚነገርለት መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 13፤ ቁጥር 23 ላይ ተከትቦ ይገኛል፡፡ብዙ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ደጋግመው የሚጠቅሱት
ጥቅስ ነው፤ በተለይም በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችና ሰባኪዎች ተደጋግሞ የሚጠቀስ የፈጣሪ ቅዱስ ቃል ነው፡፡እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝና
ስለሃይማኖት ለመስበክ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትየን ለማስረዳትና አስረገጨ ለመሞገት ምርጫየን አድርጌዋለሁ፡፡በተለይ ደሞ ከሁለት ሳምንታት
በፊት ‹‹“ኢትዮጵያዊነት” ማንነት ሳይሆን ዜጎች በህግ የሚጎናጸፉት ማሊያ ነው!›› ብለው እንደ
ፍካሬ እየሱስ በቀይ ቀለም ለፃፉት ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደገብሪኤል በዚሁ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስና ሌሎች ምክንያቶች ልሞግታቸው እሻለሁ፡፡
ዲያቆን ሙሉጌታን በዚሁ ጥቅስ ልሞግታቸው
የተነሳሁት ስለኢትዮጵያና ስለማንነት በመፃፋቸው ‹‹የኢትዮጵያን ክብር አቃልሏል››፤ በመሆኑም ‹‹ፀረ አንድነት›› ናቸው ብዬ ስለማምን
ሳይሆን ‹‹ማንነትንና ኢትዮጵያዊነትን እተረጉማለሁ›› ከሚል ቅንነት
ቢነሱም የሁለቱም ቃላት ትርጉም አንድም ከእውቀት ማነስ ትርጉማቸውን አበላሽቷቿል፣ሁለትም አንድ አንድ ወገኖች
‹‹በኢትዮጵያዊነት ላይ የአንበሳ ድርሻ ያላቸው ያህል›› ስለኢትዮጵያዊነት ሲፃፍ በፀረ ኢትዮጵያዊነት እየፈረጁ እልህ ውስጥ ስለከተቷቸው
እነሱን ለመበቀል በማሰብ የተሱበት ዓላማ ትተው(ረስተው) በመጠኑ የቆሸሸውን ‹‹ኢትዮጵያዊ መግባባት›› ለማደፍረስ ሞክሯል ብዬ
ስለማምን ብቻ ነው፡፡
