ድሮ ሴቶችን እማውቃቸው በአይነ ዓፈርነታቸው ነበር። አብሮኝ ያደገው የክፍለ ሃገር ውቦች መሽኮርመም
ከህሊናየ መቸም አይጠፋም። ትኩር ብለህ ብታያቸው ፊታቸው ወደ ሌላ አቅጣጫ ይመልሳሉ፣ አንገታቸውን ሰበር ያደርጋሉ።እንኳንስ ልጃገረዶች
እናቶቻችንም አይነ ዓፋሮች ናቸው። ባላቸውን በስሙ ለመጥራት አይደፍሩም፤
ከጠሩም አንቱ በማለት ነው።
ምክንያቱ ይላል አንድ ህፃን እያሎህ የሰማሁት ተረት ተረት፡ ድሮ የዓለም መሪዎች ሴቶች ነበሩ።መቼ?
የሰው ልጅ እርሻ ከመጀመሩ በፊት… እንደ ወፈ ሰማይ ሳይዘራ ያጭድ በነበረበት ዘመን።ያኔ ጫካው፣ሜዳው፣ ዳገቱና ቁልቁለቱ ሁሉ በሴቶች
ግዛት ነበር።ምክንያቱም፣ ያኔ የእናቶች እናትነት እንጂ የወንዶች የአባትነት እውቅና አልተሰጠም ነበር። እናም አባቶችም ሆነ ልጆች
የእናቶቻቸው ተገዢ ወይም ታዛዥ ነበሩ፤ ልክ እንደ ነገስታት ሰራዊት(ወንዶች የሴቶች ሎሌ ነበሩ)።
እናም የሰው ልጅ በዚህ ዓይነት ስርዓት ይተዳደር በነበረበት ዘመን ሶስት ሴቶች ሁነው አንድ ምስኪን
መንገደኛ ያገኙና አስገድደው ይደፍሩታል። ተራበተራ እያሉ አደከሙት ሶስቱም ስሜታቸው እስኪረካ ድረስ። ይባስ ብሎ ግን እየተመላለሱ
ዱቄት ካደረጉት በኋላም ለሚቀጥለው ቀን እንዲጠቅማቸው በማሰብ ከአንዱ ዛፍ ጋር አጣብቀው ሁሉት እጆቹን ኋሊት ጠፍረው ያስሩታል።
ፀሓይ ጠለቀች፤ መሬት የጨለማ ብርድልብሷን ለበሰች። የአውሬዎች ክፍለ ጊዜ ታወጀ፤ ከያሉበት በመጠራራት
ተሰባሰቡና ጉዞ ጀመሩ። ሲጓዙ አምሽተው ያ የፈረደበት ምስኪን መንገደኛ ተስሮ አገኙትና የመስቀል ቅርጫ ያደርጉታል። ይህን ግፍ
ሲመለከት የነበረው የእግዚሔር መልአክም በሴቶቹ ተግባር በጣም ይናደዳል። እናም የሶስቱም ፊት በጥፊ ለመምታት እጆቹን ሲወረውር
ፊቶቻቸውን መለስ፣ ዓይኖቻቸውን ሰበር ያደርጋሉ።ያኔ ነበር ታድያ እህቶቻችን አይነ ዓርነትና በወንዶች መመራት የተጀመረው።
አሁን ግን የከተማ እህቶቻችን ያ የድሮው ስልጣናቸው ለመመልስ በመታገል ላይ ያሉ ይመስላል። ድፍረታቸው
ጉድ ያሰኛል … አይናውጣ ሁኗል። ገላቸውን አራቁተው መታየቱን እንደ ፋሽን ይቆጥሩታል። የነሱ ራቆትነት ታድያ የወንዶች አንገት
እያስደፋ ይገኛል። ብዙ አይነ ዓፈራ ወንዶች እሚገቡበት ሲያጡ ይታያል፤ በተለይ ታክሲ ውስጥ። እንሱ በሚያስተዳድሮት ቤት ተከራይተው
የሚኖሩ ወንዶች ወየውላቸው። በተለይ፣ በተለይ ሽንት ቤትና ሻወር የጋራ ከሆነ።
ከላይ የሚታየው ፎቶ የተነሳው በአንድ የጋራ ሻወር ውስጥ ነው። ምናልባት ሰሙኑን ውሃና መብራት በተደጋጋሚ
ይጠፋ ስለነበር ፓንታቸውን የሚያጥቡበት ውሃ አጥተው ይሆናል። ቢሆንም ግን ግፍ ነው፤ ጡር ነው እህቶች። ድሮ ወንዶች ነበሩ በጫማ
ሽታና በሰውነት ንፅህና ጉድለት የሚታሙት አሁን ግን እንጃ። ሴቶች በሚገዙት ቦታ ሁሉ እንዲህ ይሆን?የአዲስ አበባ ጭዋ ልጆች ምን
ትላላችሁ? እንደ እኔ በገጠር ተወልደው የደጉ እህቶቼ እንኳን በጣም እንደሚገረሙ አልጠራጠርም።


Thank Paulo Gonçalves. Greetings from Addis Ababa, Ethiopia, too. I visited your blog...
ReplyDeletehttp://viajaredescobrir.blogspot.com Really amazing photos, you must be a photographer, right?