Sunday, February 9, 2014

‹‹ኢህአዴግ በዚህ ኣካሄዱ በቀጣዩ ምርጫ በዝረራ ይሸነፋል››ቢንያም ከበደ




ብንያም ከበደ(ቤን) የኢትዮጵያፈረስት ድረገፅ ባለቤትና ብሎገር ነው፡፡በሃገራቻንም በድምፅና በተንቀሳቃሽ ምስል የተቀነባበሩ ዝግጅቶች በማቅረብ ብቸኛውና ቀዳሚው በግሉ የሚሰራ ጋዜጠኛ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ሰሞኑን ታድያ ‹‹ኢህአዴግ ክብደቱ ካልቀነሰ ለህይወቱያሰጋዋል›› በሚል አርእስ ያዘጋጀው የድምፅ ሓተታ ያልተለመደና የኢህአዴግ ውድቀት አሁን የተገለጠለት ነብዪ አስመስሎታል፡፡

የኢህአዴግ ውድቀት እያፋጠነው ያለው ራሱ ኢህአዴግ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ አብጠርጥሮ የሚያውቅ ቢሆንም ለቤን ግን ገና አሁን ነው የተገለጠለት፡፡አንድ ሃገሬን ካለፉት ስርዓቶም በበለጠ እያስተዳደርኩ ነው የሚል መንግስት ‹‹የህዝብ ሮሮ አታሰሙኝ፤ሮሮ የሚያሰሙት የህዝብና የመንግስት ጠላቶች ናቸው፣የእኔ መልካም ምግባሮች ብቻ በብዙ እጥፍ እያባዛችሁ ንገሩልኝ፣ችግሮች የተፈጠሩት በጥቅቲ ስግብግብ ነጋዴዎች ነው…ምንትስ ነው››ማለት ከጀመረ መንግስትነቱን አብቅቶለታል ማለት ነው፡፡እስካሁን በስልጣን ላይ የቆየውም በተቃዋሚዎች ድክመት ነው ቢባልም ማጋነን አይሆንም፡፡

‹‹እውነቱን እንነጋገር ካልን ኢህአዴግ ቦርጫም ሁኖዋል›› የሚለው ቤን፣በማከለም፣ ‹‹ደሞ ለጤናው በጣም አደገኛ የሆነ ቦርጭ፡፡›› ይለናል፡፡የቤን አንጋገር እውነትም ነብዪንት የተለበሰ ያስመስልበታል፣‹‹እውነት እውነት እላችሁዋለሁ ብዙ ኪሎ መቀነስ አለበት፡፡አለዛያ የተሸከመው ኮሌስትሮል እንዳይገድለው ያሰጋል…›› ታድያ ሞት ብርቅ ነው እንዴ?የኢህአዴግ ስብስብ ይቅርና የስንት ሰማእቶችም ታሪክ ሁኗል፡፡ይልቅ የሚያሰጋው ኢህዴግን የሚተካው ፓርቲ ከኢህአዴግ የተሸለ ይሆናል ወይ የሚለውን ነው፡፡እንጂ ኢህአዴግ እማ ስልጣን የሰለቸው ነው የሚመስለው፤ እጅ እጅ ካለው ቆይተዋል፡፡

 እንደ ቤን እይታ ኢህአዴግ በሁለት ይከፈላል፤የድሮና የዘንድሮ፡፡

‹‹የድሮዎቹ ኢህአዴጎች ለህዝብ ማንኛውም መስዋእት ለመክፈል የማያመነቱ ነበሩ… ምርጦች ነበሩና…ግለኝነት የማያጠቃቸው ነበሩና…››እንደ ቤን ገለፃ ከሆነ የድሮዎቹ ኢህአዴጎች ‹‹ህዝብ ለማገልገል የተፈጠሩ …ልዩ ትውልድ የሚመስሉ…›› ናቸው … እያለ የድሮ ገድላቸው የዘረዝር እና እነ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣መለስ ዜናዊና ጌታቸው አሰፋን በምሳሌነት ይጠቅስልናል፡፡

‹‹አቶ መለስ በዚህ ስንት መስራት በሚችልበት እድሜው ለዘልአለሙ ያንቀላፋው  የውስጥ ህመሙን መመልከቱን ትቶ ሃገራዊ ህመም ላይ በማትኮሩ ነበር፡፡ለራሱ ጊዜ አይሰጥም ነበር…››

‹‹ስዩም መስፍን የውጭ ጉዳይ ምኒስተርነቱን አንዲት ጥይት ተኩሶ ላማያውቀው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አስረክቦ በአምባሳደርነት ወደ ቻና የደዋል..››
‹‹አባይ ፀሃየም ከጠቅላይ ምኒስተር አማካሪነት የስኳር ፋብሪካ አስተዳዳሪ ለመሆን አላንገራገረም…›› እያለ እንደ መላእክት ካወደሳቸው በኋላ እንድያ የሆኑበት ምክንያት ሲገልፅ ደግሞ የድሮ አባላት ብዙ ተጠንተውና ‹‹በመንፊት ተንጎባልለው›› የአባልነት ካርድ ስለሚያገኙ ነው፡፡

  የዘንድሮዎችን ደግሞ እንደሚከተለው ይገልፃቸዋል፡፡


‹‹የዝንድሮዎቹ ኢህአዴጎችን ግን ህዝቡን ለማገልገል ሳይሆን በህዝቡ ለመገልገል  የተቀመጡ እሚመስሉ…የዚህ ድሀ ህዝብ እሮሮና እምባ የማይታያቸው… በቃላት ጋጋታ ብቻ የተሞሉ…እውነቱን እንነጋገር ካልን ግለኞች…የመልካም አስተዳደር እንቅፋቶች…የቀድሞዎቹ የሰሩትን ሁሉ ለማፍረስ ቆርጦው የተነሱ የሚመስሉ ስብስቦች…››

እንዲህ በመሆናቸውም ‹‹መልካም አስተዳደር ድራሹ ጠፍተዋል…›› እነዚህ‹‹ክፉ የጭቃ ሽሞች…››የሚናገሩት ሌላ የሚሰሩት ሌላ ነው፡፡አፋቸው‹‹ ሙሰኝነትንና ኪራይ ሰብሳቢነት ሰለመዋጋት ›› ይለፍፋል ስራቸው ግን እነዚህ ነገሮችን ይበልጥ እንዲስፋፉ ማድረግ ሆኗል ነው የሚለን ጋዜጠኛ ብንያም ከበደ፡፡እንዳውም ‹‹በካድሬዎቹ የተሳሳተ ሪፖርተ የተሳሳተ ውሳኔ እንዲያስተላለፍ እያደረጉት ነው…››

የአሁኖቹ ኢህአዴጎች ‹‹ውሃና መብራት›› በሃገሪትዋ ምንያህል እንደተስፋፉ እና ህዝቡም ተጠቃሚ እንደሆነ ጥዋትና ማታ ይደሰኩራሉ፡፡ህዝቡ ግን ‹‹ጄሪካን ይዞ ውሃ ልምና ከቤት ወደ ቤት፣ከሰፈር ሰፈር ይዞራል›› አብየት ቢልም ሰሚ አላገኝም፡፡‹‹አሁን አሁን እማ›› ይላል ቤን፣ምርር ብሎ ‹‹ ኢህአዴግ የሚሰበስበው ትያትረኛውን ነው የሚመስለው…››ኢህአዴጎች እውነትም ተዋንያን ናቸው፡፡

‹‹መብራት 30 ጊዜ ይጠፋል… እንደ ናይት ክለብ ብልጭ ድርግም ብልጭ ድርግም ይላል…›› አሁንም አሁንም የሚጠፋው መብራት አዲስ አበባን ለማሳመር እስኪ መስል ድረስ፡፡ ቀጠል አድርጎም ‹‹እዚ ላይ የስልክ ነገር ተውት…መንግስት ያለ አይመስልም…›› ብሎ ይደመድማል፡፡እስካሁን ድረስ የህን እንዳልታየው ግን አልገባኝም፡፡

ቤን በትክክል የህዝቡን እሮሮ አዳምጧል፤‹‹ባአንዱ ክፍለ ከተማ ህዝብን ያስለቀሰ ባለስልጣን ካንዱ ቦታ ተነስቶ በሌላ ቦታ ይሾማል…ለምን? ብሎ የሚጠይቅ ካለ ‹ተውት ሂሱን ውጠዋል› ይባላል…›› በማለት ለዓመታት ሲያስገርመን ንሮ አሁን ግን ተስፋ ያስቆረጠን የድርጅቱ አሰራር አፍረጥርጦታል፡፡ወደ ትግራይ አከባቢ ብቅ ቢል ደግሞ ከዚህ የባሱ ዘግናኝ አሰራሮች ማየት ይችል ነበር፡፡

በትግራይ ክልል የቀበሌ ህዝቦችን ደም ያስለቀሰ አምባገነን ከወረዳ እስከ ከልል ያለው ከፍተኛ ስልጣን ይሰጠዋል፡፡ከፍ ሲልም በፌደራል መስራ ቤቶም የምኒስተርነት መዓርግ ይሸለማል፡፡ይህ አሰራር ማንኛውም ሰው የሚያውቀውና ብዙ ዓመታት ያስቆጠረ እውነታ ነው፡፡

የዘድሮዎቹ ኢህአዴጎች ከላይ እንደ ተገለፀው የሆኑበት ምክንያት ይላል ቤን፤‹‹የኢህአዴግ የአባልነት ካርድ ሻሞ እየተባለ ስለሚበተን ነው…›› በመሆኑም ኢህአዴግ ከተኛበት ይንቃና እነዝያ ‹‹ሻሞ ተብሎ የተሰበሰቡት አባላት ሁሉ አንጎባልሎ ሊተፋቸው ይገባል…››
ቤን፣ ሃሳቡን ሲያጠቃልል፤‹‹ህዝቡ ተማርሮዋል…ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ…››
ይህ ካልሆነ ግን‹‹የዚህ የህዝብ እሮሮ እንደ ምርጫ 97ቱ በአፍጢሙ ይደፋዋል…››

‹‹እንደ እኔ፣ እንደ ቤን ከሆነ ግን ኢህአዴግ በዚህ ኣካሄዱ አትሊስ በመዲናዋ አዲሳባ በቀጣዩ ምርጫ የሚሸነፍ ይመስለኛል፤ እውንት እውነት እላችሀለሁ በዝረራ›› በማለት ከልብ የመነጨ የሚመስል ምክሩን ልግሷቸዋል፡፡

ቤን የተናገረው ሁሉ፣ ዘገየ ካላልን በስተቀር፣ የሚጣል የለውም፡፡ኢህአዴግም የቤን ምክር ተቀብሎ ፀሐይ ከመጥለቅዋ በፊት የቤት ስራውን ቢሰራ ይሻለዋል፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ከአሁን በኋላ ይቅር የሚለው አይመስለኝም፤ከልክ በላይ ታግሶታልና፡፡በመሆኑም የብን እይታ ከማጣጣልና አቃቂሮችን ከመፍጠር ይልቅ የህዝቡን እሮሮ ለማዳመጥ ቢሞክር የተሸለ ነው፡፡





2 comments:

  1. ‹‹አቶ መለስ በዚህ ስንት መስራት በሚችልበት እድሜው ለዘልአለሙ ያንቀላፋው የውስጥ ህመሙን መመልከቱን ትቶ ሃገራዊ ህመም ላይ በማትኮሩ ነበር፡፡ለራሱ ጊዜ አይሰጥም ነበር…››

    ተው እንጂ ይልቁንስ መለስ በዚህ እድሜው የሞተው ስልጣንን ከመጠን በላይ በመውደዱ ብሄርን ከብሄር በማጋጨቱ ኢት/ያ የምታክል ሀገር ወደብ አልባ ማድረጉ በቀን ሶስት ጊዜ ትበላላቹ ብሎ በመዋሸቱ ከ70ሺህ በላይ ኢት/ውያን ያለቁበትን ባድምን ይግባኝ በሌለው ፈርድ ማሰጠቱ ብዙ በምርጫ ስም 1997 እና ከዛም በኃላ ቡዛዎችን በማስገደሉና በማሳሰሩ ንጹኀንን በማሽገደሉ እ/ር ቀሰፈው እንጂ ለዝች ሀገር ካመጣላት ይልቅ ያመጣባት ይብሳል ድሮስ ባንዳ ባንዳ ነው…

    ReplyDelete
  2. why you need approval.who r u to approve.if you are approved why don,t you proof this‹‹አቶ መለስ በዚህ ስንት መስራት በሚችልበት እድሜው ለዘልአለሙ ያንቀላፋው የውስጥ ህመሙን መመልከቱን ትቶ ሃገራዊ ህመም ላይ በማትኮሩ ነበር፡፡ለራሱ ጊዜ አይሰጥም ነበር…››

    ReplyDelete