በህወሓቶች ዘንድ የተለመዱ ግን ደግሞ ያልተፃፉ አቋራጭ የስልጣን መወጣጫ መሰላሎች አሉ፡፡ብዙዎቹ የሃገራችን ጎምቱ
ጎምቱ ባለስልጣናት እነዚህን መሰላሎች ተጠቅመው ከቀበሌ አስተዳዳሪነት ወደ ሚኒስተርነት ተወንጭፈውባቸዋል፡፡ከሌሎች የተለየ የትምህርት
ደረጃ፣የማስፈፀም ብቃትና የአመራር ችሎታ ስላላቸው ግን አይደለም፡፡የስርዓቱ ቀዳዳዎችና የመሰላሎቹን አቅጣጫዎች ጠንቅቀው በማወቃቸውና
ተግባራዊ በማድረጋቸው ብቻ እንጂ፡፡
መሰላሎቹን የት እንዳሉና እንዴት እንደሚጠቀሙባቸው የማያውቁ ግን ዛሬም ድረስ ‹‹ባለህበት ርገጥ›› እየተባሉ ባዛችው
ቀበሌ ይገኛሉ፡፡የስልጠናም የስልጣንም ዕድል ሳያገኙ ሀል ጊዜ የበላይ አለቃ ትእዛዞችን ለማስፈፀም ሲዋትቱ ይኖራሉ፡፡ንሯቸውም ያው
ነው፤ ልክ እንደኗሪው ህዝብ አፈር ለብሰው ዳዋ ልሰው ይኖራሉ፡፡ይሁን እንጂ ህዝቡም አይወዳቸውም በመንግስት ደረጃም ብዙ ተቀባይነት
የላቸውም፡፡ሰርተው እዳያልፍላቸው ሙሉ ጊዝያቸውን የበላይ አለቃ ትእዛዝ ለማስፈፀም ሲብከነከኑ ያጠፉታል፡፡የአለቃቸው ትእዛዝ
‹‹ከለይ የወረደ መመርያ ነው›› እያሉ በህዝቡ ላይ በግዳጅ ስለሚጭኑበት ደግሞ ህዝቡ አቂሞባቸዋልና ከሁለት ያጣ ሆኖው ይኖራሉ፡፡
የስልጣን ኮርቻ መቆነጣጫ ርካቦቹ ብዙ ናቸው፡፡ለጊዜው ሁለት በጣም የታወቁ መሰላሎችን በናሙናነት አቀርባለሁ፡፡ሃተታየም
በእንዚሁ ፍቱን መሰላሎችን የሚያጠነጥን ይሆናል፤ መልካም ንባብ፡፡
የስጋ ዝምድና
የመጀመርያው መሰላል ድሮም የነበረ፣ ዛሬም ህወሓቶች ከድረው በበለጠ አሳምረው የሚጠቀሙበትና በዚሁ የፖለቲካ አካሄዳችን
ከቀጠልን ደግሞ ምናልባት ለወደፊቱም የሚኖር ነው፡፡ባለፉት ስርዓቶች፣ ዝምድና ሁነኛው የስልጣን መቆናጠጫ መሰላል ነበር፤ ሰሎሞናዊው
ስርወ ንግስነትን ልብ ይሏል፡፡ስልጣን፣ ለተመረጡ ጎሳዎች ከፈጣሪ የተሰጠና ከትውልድ ወደ ትውልድ በዘር የሚተላለፍ እንደነበር በክብረ
ነገስት ሰፍሮ ይገኛል፡፡
የህወሓቶች የስልጣን ምንጭም በጥቅም ትስስር ወይም በስጋ ዝምድና ነው የሚገኘው፡፡ማንኛውም ሰው አንድ ትልቅ የህወሓት
ባለስልጣን ካለው የስልጣን ኮርቻውን ለመቆናጠጥ ሁለት ዓመታት አይፈጁበትም፡፡በቃ ስራ ከያዘ ከሁለት ዓመታት በኋላ የወረዳ፣የዞን
ወይም የአንድ ፌደራል መስርያ ቤት ማናጀር፣ኦፊሰር ወዘተ ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ለህዝብ የሚጠቅም ስራ ግን ሲሰራ አይታይም፤ ሙሉ ጊዜውን
ማለት ይቻላል በስብሰባዎችና ስልጠናዎችን ነው የሚያሳልፈው፡፡
ማንኛውም የውጭ ስልጣናዎች ቁጥር አንድ ተጠቃሚ እሱ ነው፡፡ወደ ቻይናና ሌሎች ሃገሮች የሚያደርገው ጉዞ ከስራ ወደ
መኖርያ ቤቱ ከሚያደርገው መመላለስ አያንስም፡፡በየ መስርያ ቤቱ የሚገኙ ህግና ደምቦች ለነዚህ ሰዎች አይመከቱም፤ ተፈፃሚነትም የላቸውም፡፡የአንድ
መስርያ ቤት ህግና ደምብ ይቅርና የሃገሪቷ ህግ ደምብም አይገዛቸውም፡፡ የፈለጉትን ያህል ሃብትና ንብረት ማካበት ይችላሉ፡፡ ቀልባቸው
የከጀላትን ሴት እሺ ካለች እሰየው፣እምቢ ካለች ግን አስገድደው ይደፍራሉ፡፡ ሌላው ቢቀር ሰው ቢገድሉም የሚጠይቃቸው የለም፡፡በአጠቃላይ
ሁሉ በእጃቸው ሁሉ በደጃቸው ነው፤ስልጣኑም፣ ቁንጣኑም፣ሰይጣኑም ለነዚህ ሰዎች ቅርብ ነው፡፡
እዚ ጋ ለምን ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ህወሓቶች አብዮታውያን ስለሆኑ አይደለም እንዴ መስፍናዊው ስርዓት ለመመለስ
ይታገል ለነበረው ኢድዩን በምዕራብ ትግራይ በተካሄደው ጦርነት የደመሰሱት? ለህዝብ የቆሙ አብዮታውያን ባይሆኑ ንሮ ነብሰ በላው
ደርግን ተፋልመው መገርሰስና ህዝቡ የሚከበርበት ህገ መንግስት ቀርፀው ማጽደቅ ለምን አስፈለጋቸው? ብለው የሚጠይቁ እንደሚኖሩ አልጠራጠርም፡፡አዎ፣
ጥያቄዎቹ ተገቢ ናቸው፡፡
ህወሓቶች ለህዝብ የቆሙ ህዝባዊ ተጋዮች ይመስሉኝ ነበር፡፡አይደሉም፡፡የመስፍናዊው ስርዓት ርዝራዥች ናቸው፡፡ይህን
ያረጋገጥኩት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሴን ከጠየቅኩና በቂ መልስ ለማግኘት ብዙ ከተፍጨረጨርኩ በኋላ ነበር፡፡የህወሓቶች ማንነት ግልፅ
የሆነልኝም ከብዙ የሃሳብ ውጣውረድ ግብግብ ነው፡፡ህወሓቶች ህገ መንግስቱን አርቅቀው ያፀደቁት ለምን ነበር? ለምንስ ተግባራዊ እንዲሆን
አያደርጉም? ለምንድን ነው ሌሎችን ህገ መንግስቱን ጥሷል ብለው ሲያስሩና ሲያንገላቱ የራሳቸው አባላት ግን ህገ መንግስቱን የማያከብሩት?
ከሃፄ ሃይለስላሴ አከዛዝ ጀምሮ ያለው የሃገራችን ታሪክ ብንመረምር ሃገር የመሳፍንት ብቻ ነበረች፡፡ስልጣን የሚይዘው
መስፍንና የመሳፍንት ለጅ ብቻ ነበር፡፡ያሻውን የሚበላውና የሚጠጣው መስፍኑና የመሳፍንት ልጆች ናቸው፡፡የትምህርት ዕድልም ቢሆን
ለመስፍናዊው ስርዓት ባለቤቶች ብቻ የተፈቀደ ነበር፡፡የተራው ህዝብ ለጅ መማር ቀርቶ ወታደር የመሆን ዕድልም አልነበረውም፡፡ከአንዱ
መስፍን ጋር ተለማምጦ ወታደር(ነጭ ለባሽ) የመሆን ዕድል ካጋጠመውም ሁል ጊዜ ተራ ወታደር ሆኖ ነው የሚኖረው፤ ቀድሞ የጥይት እራት
የሚሆነውም እሱ ነው፡፡
የህወሓት የትጥቅ ትግል ጀማሪዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወይም ምሩቆች እንደነበሩ ገድለ ህወሓት በሆኑ
መፅሓፎች ሰፍሮ ይገኛል፡፡በተለይ በወቅቱ በእድሜም በስልጣንም ተወዳዳሪ ያለነበረው ገሰሰው አየለ(ስሑል) የአፄ ሃይለስላሴ የምክርቤት(ፓርላማ)
አባል ነበር፡፡እነ ስብሃት ነገጋ፣መለስ ዘይናዊ፣ ስየ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን ወዘተ እልም ያሉ የመሳፍንት ልጆች ናቸው፡፡
በዛን
ጊዜ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ገብተው የመማር ዕድል የሚገጥማቸው የመሳፍንት ልጆች ብቻ በመሆናቸው የህወሓት የትጥቅ ትግል ጀማሪዎችም
የመስፍናዊው ስርዓት ትርፍ ራፊዎች ናቸው፡፡የትጥቅ ትግል የጀመሩበት መክንያትም ለትግራይ ህዝብ አስበውና ተቆርቁረው ሳይሆን የስልጣን
ጥማቸውን ለማርካት ብቻ ነው፡፡በስልሳዎቹ ተነስቶ እንደ ፊኛ ፈንድቶ የቀረው ህዝባዊ አብዮት የተቀጣጠለውም የከሰመውም በመስፍናዊ
ስርዓት ርዝራዣች በመጠለፉ ነው፡፡የስልሳዎቹ ጦርነቶችም ልክ እንደ በዘመነ መሳፍንት እንደ ተካሄዱት ጦርነቶች በመሳፍንት ልጆች
መካከል የተካሄደ የስልጣን ሽምያና እሽቅድድም ነበር፡፡