Tuesday, July 1, 2014

የአንዳርጋቸው ፅጌ በየመን ድህንነቶች መታገትና የጉንበት ሰባት ባዶ ሽለላ


ጉንበት ሰባት ጉራ አያልቅበትም፡፡ አባለቱም ሆነ አመራሮቹ በሄዱበት ሁሉ አቧራ ያስነሳሉ፤ ይፎክራሉ፣ ያቅራራሉ፡፡ በኢህአዴግና በኢትዮጵያ ላይ የእነርሱን ያህል የዛተ ባይኖርም እስካሁን ድረስ ግን ዝምብም አባርረው እንደማያውቁ ተግባራቸው ይናገራል፡፡አፋቸው እንደሚቆላ ተልባ ነው፤ ከመጠን በላይ ይንጣጣሉ፡፡ተልባ የሚንጣጣው እየተቆላ መሆኑን ያህል ግን ጉንበት ሰባቶችም እያረሩ ነው የሚንጣጡት ‹‹በቆሉ እያረረ…›› እንዲሉ እያረሩ ይሸልላሉ፣ይንጣጣሉ፡፡የውስጣቸው እሳት ግን ከራሳቸው አልፎ ማንንም ሲጎዳ አይታይም፤ ቁጥር አንድ ጠላታቸው ‹‹ወያኔም›› ጭምር፡፡የእነዚህ ሰዎች ባዶ ጭኾት ከአይመች ጋር ተመሳስሎብኛል፡፡


አዝብጤና አይመች የሚባሉ ጎረቤታሞች ነበሩ፡፡አይመች ሲበዛ አጭርና ቀጫጫ ሲሆን በምግባረ ብልሹነቱ የታወቀ፣ ከማንም ጋር የማይስማማ ነግራም ነበር፤ ልክ እንደ ስሙ አይመች፡፡የአስብጤ ስብእና ግን የአይመች ተቃራኒ ነበር፡፡በቁመትና በውፍረት ወደር የለሽ ሲሆን ማንም ታግሎ የማይጥለው ግድንግድ ነበር፡፡ታድያ ለማንም የማይተናኮል ቅን አሳቢና ትእግስቱ የማያልቅ አስተዋይ ስለነበር ሰዎች እንደፈሪ ይቀጥሩታል፡፡በተለይ አይመች ሁሌም እንደ ተፈታተነው ነብር፡፡ሁሌም ይሰድበዋል፣ሊመታው ይሞክራል ግን በምን ቁመቱና ጉልበቱ ይደርስበታል? አይመች ይሳደባል፣ይሸልላል፣ለመማታት ይፍጨረጨራል፡፡አዝብጤ ግን አጠገቡ እስካል ደረሰ ድረስ ከቁብ አይቆጥረውም፤ ዝም ብሎ በስራው ላይ ይተጋል፡፡

አንድ ቀን ታድያ አይመች በፉከራና ስድብ አልተገታም፡፡ አዝብጤን ለመደብደብ ተንደርድሮ ሄዶ በሽመል ሰነዘረበት፡፡ አዝብጤ ሽመሉን በመመከት አናቱ ከመፈንከት አዳነና አይመችን ምንም ላይንቀሳቀስ ግጥም አድርጎ ያዘው፡፡አይመች እራሱን ለማስለቀቅ በለው በሌለው ጉልበቱ ተጠቅሞ ይጣጣራል፡፡ አዝብጤ ከያዘ አይለቅም፤ በጣም ጉልበተኛ ነው፡፡አይመች ተፍጨርጭሮ ተፍጨርጭሮ ራሱን ሊስለቅቅ አልቻልም፡፡በጣም ተዳክሞ ማለክ ለክ ጀመረ፡፡ ሆኖም ግን መሸነፉን ከሚያምን ሞት የሚመርጠው አይመች ‹‹በቃ ተሸንፍያሉ ልቀቀኝ›› ማለቱን ትቶ ‹‹ አዝብጤ ልቀቀኝ! እገድልሃለሁ ልቀቀኝ! ልቀቀኝ ብየሃለሁ ኋላ ጉድ እንዳትሆን…›› እያለ ማስፈራራት ጀመረ፡፡ አዝብጤ ፈርቶ ሳይሆን ‹‹ይሄ ቁንጫ ይታባቱ ይደርሳል›› ብሎ አይመችን ይለቀዋል፡፡

ልክ እንደለቀቀው ግን እንደፎከረው ለመማታት ተንደረደረ፡፡ አዝብጤ አይመችን ይዞ በአየር ላይ ሶስቴ አሽከርክሮ እመሬት ላይ ፈጠፈጠው፡፡ አይመች አሁንም ተስፋ አልቆረጠም በወደቀበት ሆኖ ጩቤ መዝዞ አዝብጤን ለመውጋት ተፍጨረጨረ፡፡ አዝብጤ የአይመች እጅ ጠምዝዞ ጩቤውን ነጠቀውና ግዙፍ ሰውነቱ በአይመች ላይ ተከመረበት፡፡አይመች አሁንም ማስፈራራቱን ይጀምራል ‹‹ አዝብጤ ልቀቀኝ! እገድልሃለሁ ልቀቀኝ! ልቀቀኝ ብየሃለሁ ኋላ ብነሳ ጉድ እንዳትሆን…›› አዝብጤ ብድግ ይላል፤ በእጁ እንዳያርፍበት ስለሰጋ፡፡ አይመች ግን ለመማታት መፍጨርጨሩ አይተውም፤ በጣም ተዳክሞ መላወስ 
እስኪያቅተው ድረስ፡፡

የጉንበት ሰባት የጉራ ተራራ አይመችን አስታውሶኛል፡፡ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከቃልቲ እስር ቤት ‹‹በይቅርታ›› እንደ ተለቀቁ አሜሪካ ገብተው ‹‹ኢህአዴግን በማንኛውም መንገድና ስልት ተጠቅሜ በስድስት ወራት ውስጥ ከአራት ኪሎ ቤተ መንግስት አባርረዋለሁ›› ብለው ዛቱ፡፡ ብር የማያልቅበት ድያስፖራ ደሞ ሽለላቸው ከማመኑም ባሻገር ለትጥቅና ስንቅ ይሆናቸው ዘንድ በዶላር መዓት አምበሸበሻቸው፡፡ዶክተር ብርሃኑ ግን ኢህአዴግን በስድስት ወራት ውስጥ ከአራት ኪሎ ሊያባርሩት ቀርቶ ከስድስት ዓመታት በኋላም ከኢሳት የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ቴሌቪዥን ውጪ ያመጡት ነገር የለም፡፡በኤርትራና ግብፅ የሚሰለጥኑና የሚደጎሙ ወታደሮቻቸው በኤርትራ መመሸጋቸው ከተናገሩትም ዘመን የላቸውም፡፡ ሆኖም ግን አንዲት ጥይትም ተኩሰው አያውቁም፡፡

አሁን ደሞ የባሰውን ነገር ተከስቷል፡፡የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ ሆኖው ሲሰሩ የኖሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን የፀጥታሐይሎች መታሰራቸውን ይፋ ሆኗል፡፡ይህን ተከትሎ ታድያ ጉንበት ሰባት ልክ እንደ አይመች ወድቆ ሳለ ‹‹ተው ልቀቀኝ! ከተነሳሁ አይማረኝ አልምርህም›› አይነት ማስፈራርያ በድረገፁ አስነብቦናል፡፡የጉንበት ሰባቱ ወናፈ እንዲህ ሲል ነበር በየመን ላይ የዛተው፣
‹‹የየመን መንግሥት የየመንን የወደፊት የረዥም ጊዜ ጥቅም እንዲያሰላና ያገተብንን መሪ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንመክራለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በመሪያችን ላይ ጉዳት ቢደርስ ወይም ለወያኔ አሳልፎ ቢሰጥ የመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የማይሽር ቂም ውስጥ የምትገባ መሆኑን የየመን መንግሥት አውቆ በጥብቅ እንዲያስብበት እናስጠነቅቃለን።›› 

ይህ ፉከራ ጉንበት ሰባት በቅዠት ዓለም የሚኖር መሆኑን ከማጉላት ውጪ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡፡፡በዘመናዊው ዲፕሎማሲ ቢሞክሩ ይሻላቸው ነበር፡፡ እንደ አይመች በትዕቢት እንደፊኛ ያበጠው ማንነታቸው ትክክለኛውን መንገድ ከመከተል ይልቅ ራሳቸው የነገዋ ኢትዮጵያ መሪዎች አድርገው በመቁጠር የቁም ቅዠታቸውን ይቀበዥራሉ፡፡የከፈው መስጠንቀቅያ ግን የሚከተለው ነው፡፡



እውነት ግን ጉንበት ሰባት ወኔውንና ብቃቱን ቢኖረው ንሮ ልክ እንደ መንግስቱ ሁሉንም የኢህአዴግ(እነርሱ እነደሚሉት የወያኔ) ባለስልጣናት በአንድ ሌሊት የጥይት እራት አያደርጋቸውም ነብር? ‹‹በማንኛውም መንገድ ወያኔዎችን ከሚኒሊክ ቤተ መንግስት አባርራቸዋለሁ›› ብሎ የፎከረው ለማን ሆነና ነው እንዲሁ ጭዋ ለመምሰል የሚሞክረው? መላ ቅጡ የጠፋቸው ምስኪኖች! አሁን ይህ ማስፈራርያ ‹‹ወድቆ መምፈራገጥ ለመመላለጥ›› እንደሚባለው ካልሆነ በስተቀር ምን ሊፈይድ ነው? የጉንበት ሰባት ተግባር ፀሐይ የሞቀው ዓለም ያወቀው ነው፡፡ ‹‹እንኳንስ ዘምበብሽ ድሮውም ጤዛ ነሽ›› የተባለው እንደነ ጉንበት ሰባት ላሉ የጉራ ቱልቱላዎች ይሆን እንዴ?





No comments:

Post a Comment