Thursday, July 3, 2014

አልቃሻው ጃፓናዊ ፖለቲከኛ፡Ryutaro Nonomura

  


በኛ ሃገርስ መቼ ይሆን ጋዜጠኞች አጭበርባሪ ፖለቲከኞችን እንዲሁ በበሳል ጥያቄዎችን አፋጥጠው በህዝብ ፊት ማስለቀስ የሚችሉት?

Ryutaro Nonomura
በኛ ሃገር ጋዜጠኞች ፖለቲከኞች ፀሐይ እንዳይመታቸው ዣንጥላ ይዘው ወደ ሄዱበት ወድያ ወዲህ ሲሉ ነው የሚታወቁት፡፡ ይህ አስገራሚ ጃፓናዊ ፖለቲከኛ የህዝብ ገንዘብ በምን መልኩ እንዳጠፋው በጋዜጠኞች ተጠይቆ መልስ መስጠት ሲያቅተው በፕረስ ኮንፈረስ ላይ የተሌቪዥን ካሚራዎች ወደ እርሱ አነጣጥረውበት ሳለ እንዲህ እንደ ህፃን ልጅ ስቅስቅ ብሎ በማልቀስ ዓልም ጉድ አሰኝቷል፡፡

የጃፓን ጋዜጠኞች እንዲ ዓይነቶቹ ልክስክስ ፖለቲከኞችን የህዝብ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ይንቀጠቅጣሉ፣ ያደፋንቃሉ፡፡ የኛ ሃገር ፖለቲከኞች ግን በግልባጩ ጋዜጠኞችን በጥያቄ ሲያፋጥጡ፣ ሲያንቀጠቅጡ፣ሲያስለቅሱ ይስተዋላል፡፡ ዓንዶም ገብረየሱስ የሃገራችን ጋዜጠኝነት በደምብ ገልፆታል፤ እንደሚከተለው፡፡


ፖለቲከኛ እንዲህ ሲነፋረቅ ማየት እንዴት ያስደስታል? ‹‹ለሁሉም ጊዜ አለው›› ነው ያለው መፅሐፉ? ለካ ህዝብ ሲያስለቅስ ለኖረው ፖለቲከኛም እንዲህ የሚያለቅስበት ጊዜ አለ? እስኪ ሊንኩን በመጫን ፎቶውን ተመልከቱና እናንተም እንደኔው ተገረሙ፡፡

No comments:

Post a Comment