![]() |
| Boycott Bedele Beer |
ደምና ምግል ባመረቀዘው ቁስላችን ላይ ስንጥር የሚጨምሩ ወገኖች ደም የተጠሙ ናቸው፡፡የተድሮስ
ካሳሁን ‹‹የፍቅር ጉዞ›› የሰው ልጅ ፍቅር ሳይሆን የደም ፍቅር ነው፡፡ከ100 ዓመት በፊት የፈሰሰው ደም ዛሬም በበደሌ ቢራ ስም
ማጣጣም አሰኝቶታል፡፡በኢትዮጵያውያን ሬሳ፣ በኢትዮጵያውያን ደም፣በኢትዮጵያውያን የተቆራረጡ የእናቶች ጡቶች፣እግሮች፣እጆች…በኢትዮጵያውያን
የተሰለቡ የተለያዩ የሰውነት አካሎች እየተረማመደ ዳንኪራ መርገጥ አሰኝቶታል፤ እስፖንሰሩም በደሌ ቢራ ነው፡፡
በደሌ ቢራ የተድሮስ ካሳሁንና መሰሎቹ የደም ጥማት ለማርካት ቆርጦ ተነሰቷል፡፡ይህ ጉዞ ለእነሱ
የፍቅር ጉዞ ነው፤ የደም አምሮታቸውን የሚወጡበት፡፡በተከበረው(እነሱ ገን ባረከሱት) የሰው ልጅ ደም ስም በደሌ ቢራን እየተጎነጩ
የደም ሱሳቸውን የሚያስታግሱበት ነው፡፡ምስኪን ወገኖቻችንን ገድለው የሚፎክሩበት፡፡የእናቶችና የህፃናት ጡቶች፣እጅና እግሮች ቆርጠው
የሚሸልሉበት፡፡የበደሌ ቢራ ባለቤቶች እነዚህ ድሮ በተጠጣው ደም የሰከሩ ወገኖች ‹‹የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም›› በሚሉት ፈሊጥ ብዙ
ለማትረፍ ጓጉቷ፡፡
ከ100 ዓመት በፊት ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ሰፍረው የነበሩ ወገኖቻችን
ስጋቸው ተቆራርጦ፣ አጥንታቸው ተፈጭቶ፣የፈሰሰው ደማቸው ከበደሌ ቢራ ጋር ተደበላልቆ ‹‹ለእምዬ ምኒሊክ›› የ100ኛ ዓመት የሙት
መታሰብያ መስዋእት ሊሆን ተፈርዶበታል፡፡
ወገኖቼ ያደም ደማችን ነው፡፡እንዝያ ጡቶቻቸውን የተቆረጡ እናቶች እናቶቻችን ናቸው፡፡ እንዝያ
ውድ ህይወታቸው፣ ተፈጥሮ ሙሉ አድርጋ የለገሰቻቸው እጅና እግራቸው በምኒሊክ ጭካኔ ተቆርጦባቸው የተሰነከሉ ወገኖች ዛሬም ድረስ
ነፍሳቸው ትጮኸለች፡፡የእነሱ ነፍስ ነፍሳችን ናት፡፡የእነሱ ጭኸት ጭኸታችን ነው፡፡የእንሱ ስቃይ ስቃያችን ነው፡፡የእንሱ ቁስል ቁስላችን
ነው፡፡
በመሆኑም ሙሉ በሙሉ ያልዳነውን ቁስላችን ‹‹በጥቁር ሰው›› ስም ሲረገጥ፣ስንጥር ሲጨመርበት፣ድጋሚ ሲደማና ከበደሌ
ቢራ ጋር ተቀላቅሎ እንዲጠጣ ሲፈረድብን እምቢ ማለት አለብን፡፡ያ ያለፈው ክፉ ጠባሳ ዳግም ለማንሰራራት ‹‹በፍቅር ጉዞ›› ስም
ዳንኪራው ሊረገጥ ነውና ማስቆም አለብን፡፡በበደሌ ቢራና በቴዲ አፍሮ መካከል በታሰረው የዳንኪራ ውል ያለን ተቃውሞ ለማሳውቅ የበደሌ
ቢራ ምርቶችን በጋራ እናውግዝ፡፡
የአንዲት የእንጀራ እናት ደግነት መለካት ያለበት ‹‹እምዬ› እያሉ በሚያቆላሙጧት የስጋ ልጆቿ ብቻ ሳይሆን በእንጀራ
ልጆቿም ጭምር መሆን አለበት፡፡የስጋ ልጆቿ እማ የእንጀራ ልጆቿ ድረሻም ጭምር ሳላስታቀፈቻቸው ይወዷታል እንጂ ያ ተግባሯ እንደ
ክፋት አይቆጥሩትም፡፡እናም ‹‹ ‹እምዬ› ቅድስት ነችና የእንጀራ እናታችሁ ብትሆንም ስንሰግድላት አብራችሁን ስገዱ፤ስሟን እየጠራን
ስንጨፍርም አብራችሁን ጨፍሩ፤ ካልሆነም እውነተኛ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁም›› እያሉ የሚያላዝኑትን አድገው እውነታውን እስኪረዱት
ድረስ እንደማይሆን ልንነግራቸው ይገባል፡፡
ለእኔ ማንም ጨፍጫፊ ጭራቅ ከሌላኛው ጭራቅ በመለየት ‹‹ቅዱስ ቅዱስ›› እያሉ መካብ ያቅለሸልሸኛል፤ ያመኛል፡፡ሁሉም
ጭራቆች እኩል ናቸው፡፡ያጭራቅ ተግባራቸው እኩል እናውግዘው፤ መልካም ምግባራቸውም(ካለ) እኩል እናወድሰው፡፡ከሁሉም በላይ ግን የልበ
ወለድ ጀግኖችን ማምለክ ጣኦት ከመምለክ የማይሻል አምልኮተ ጣኦት ነው፡፡
ስለሆነም ከ100 ዓመታት በፊት የተሰወርከው ምኒሊክ ሆይ በሰማያዊ ፓርቲ የምትኖር፣ ስምህ ቴዲ አፍሮ ይጥራው፣ ትናንት
የወገኖቻችን ሰላምና የእለት እንጀራ እንዳሳጣኸው ዛሬም ልታሳጣን አትሞክር፤ አይሳካልህምና፡፡ሳንበድልህ ለበደልከን በደል ይቅር
ብንለህም በደልክን አልረሳነውምና ዳግም አትምጣብን፤ አያዋጣህምና፡፡ ቤተ ምንግስትህ በሃይለማርያም ተይዟልና ብትመጣስ የት ትኖራልህ?
…
እያልን እውነቱን እንንገረው፡፡እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ የሌሎች ኢትዮጵያውያን ስቃይ የኔም ስቃይ ነው፡፡ትናንትም ሆነ
ዛሬ በማንኛውም ንፁኅ ኢትዮጵያዊ ላይ የደረሰው(እየደረስም ያለው) በደል እቃወማለሁ፡፡ ከአፄ ቴድሮስ እስከ አፄ ዮሃንስ 4ኛ፣
ከአፄ ምኒሊክ 2ኛ እስከ አፄ ሃይለስላሴ እንዲሁም ከደርግ እስከ ኢህአዴግ ስቃዩ፣እሮሮው፣ ጭፍጨፋው በማንም የፈፀም በማንም አበክሬ
አወግዛለሁ፡፡

I thought you were reasonable blogger. But seems non professional and lacks fairness for all opinion that you are giving. Will not see you any more. Adieu !!!
ReplyDeletecontrary to you,i found Asfaw more reasonable and professional always forwarding fair opinion free from nationalistic bias.
Deletecontrary to anonymuous i see this post rational.liked this gay.
Delete