Thursday, April 25, 2013

ትርፍ ሰዎች


                               



የአዲስ አበባ የትራንስፖርት እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት ይገኛል።በታክሶች መነሻና መድረሻ ቦታዎች ቆሞ የሚጠብቀው ህዝብ ብዛቱ ለጉድ ነው። እንደው በተራ አስከባሪዎች ምክንያት ጋብ አለ እንጂ ታክሲ ለመያዝ ይደረግ የነበረው ግፍያና ሩጫ ለህይወትና ለንበረት በጣም አስጊ ነበር። አብዛኛው ተጓዥ ብዙ ከጠበቀ በኋላ በምትመጣው ታክሲ ተሳፍሮ ካሰበበት ቦታ በጊዜ ለመድረስ ሲጋፋ ሞባይሉ በኪስ አቂዎች የተዘረፈው ብዙ ነው።

ታክሲዎች ትራፊክ ፖሊሶች በሚያዘወትሩበት አከባቢ ትርፍ አይጭኑም፤ ጭነው ከተገኙም የቀጣሉ።ስለሆነም ከብዙ ልፍያና ግፍያ የገባው ተሳፋሪ «ትርፍ ነሽ ወይም ነህ ውረድ/ጂ» ይባላል፤ የተለመደ ነው ።ትራፊከ ፖሊሶች በማይኖሩበት ቦታ ግን ሰው በሰው ላይ ይጫናል፤ ታክሲው በሰው ይታጨቃል።

የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ግን ትርፍ ቢጭኑም ባይጭኑም ስለማይቀጡ ችግር የለባቸውም።ገብቶ መቆም የቻለ ሁሉ ትርፍ አይባልም፤ ጉዞው ይቀጥላል።ከእግር እስከራሱ እየተሻሽ፣እየተፋተገ ትንፋሽ ለትንፋሽ እየተለዋወጠ።

ይህች ዓለምም በታክሲዎችና በአውቶብሶች ልንመስላት እንችላልን።አብዛኛው ጊዜ በሰው ይታጨቃሉ።አውቶብሶችና ሀይገሮች ቻይ ነገር ይመስሉኛል፤ እስከቻሉት ድረስ ብዙ ሰው ይጭናሉ።ታክሲዎች ግን ሲያሻቸው ይጭናሉ ከልተመቻቸውም ትርፍ ነህና ውረድ በማለት ያስወርዳሉ።

ዓለማችንም እንዲሁ ነች።ሲያሻት በሰዎች ትክሻ ታዝለን እንድንኖር ጭምር ትፈቅድልናለች።ሲያሻት ደሞ ቦታ እያለም ትርፍ ነህና ውረድ ትለናለች።ወያለው ከታክሲው አስገድዶ እንደሚያስወርደን ሁሉ ዓለምም ከጀርባዋ አሽቀንጥራ ትወረውረናለች።እኛ ገና ነን፣ ጊዜና ቦታ አለን ብለን ተንደርደረን ለመግባት ስንሞክር በድንገት «ትርፍ አልጭንምና ውረድ» እንባላለን።

እስኪ አስቡት፣ ስንት ሰዎች ናቸው «ትርፍ» ተብለው ከዚች ዓለም የተንሰናበቱት? ለመቁጥረ ይከብዳል። እንደው የቅርቡን እናንሳ ብንል በጣም የምንወዳቸው ብዙ የጥበብ ሰዎች አጥተናል። ዓለም ያንቀጠቀጡ፣በእንብርክክ ያስኬዱ፣ትርፍ ነህ ትረፍ ነሽ በማለት ከዚች ምድር በጉልበት ያሰናበቱ አንጋፋ የሃገር መሪዎችም ጊዜው ሲደር ትርፍ ተብለው ከሚስገበገቡለት ስልጣናቸውና በዙዎችን እንደ ጥሬ ፈጭተው እንደ በረት አቅልጠው ከገዙባት ሃገር ተሰናብተዋል። ወደው ሳይሆን ተገደው «ትርፍ» ተብለው።

«ትርፍ» መባል ብንሮ ደረጃ፣በዘር፣በሃይማኖት፣በስልጣን፣በመልክ፣በቁመት ወዘተ. አይወሰንም።ሁሉም ሰው በጊዜው ትርፍ ይሆናል።ለጊዜው ግን በሌሎች ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ያላቸውን ሁሉ እየመጠጠ በህይወት መርከብ ወድያ ወዲህ ይላል።ነገር ግን የመርከብዋ ጉዞ ሁሌም ሰላማዊ አይሆንም።«ለሁሉም ጊዜ አለው» ተብለዋልና በሰላም ስትቀዝፍ የኖረችው መርከብ በወጀብ ስትናወጥ ብዙዎችን «ትርፍ» በማለት ወደ ውቅያኖሱ ትወረውራለች።

የአሁኑ የፌስቡክ ወሬ ስለየቀድሞው የኢትዮጵያ ወታደራዊ አምባገነን ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም ሁነዋል።አንዴ ሞቱ ተቀበሩ ይላሉ፣ መልሰው ደግሞ «የወያኔ ወሬ ነው» አልሞቱም በማለት ነገር ያምታታሉ። ምንግስቱ የተለየ ሰው አይደም፤ የተለይ ታሪክ የለውም። ማመዛዘን የማይችል፣ እንደ እንስሳ በደመነፍስ የሚንቀሳቀስ ሬሳ ነበር። የፌስቡክ ወረኞች ጊዜዊ ወናፈም አይግደለውም ከሞትም አያድነውም።ሬሳ ነበር ሬሳ ይሆናል፤ በእርግጠኝነት።

የፕሮፖጋንዳ ወናፈ ከየትም በላይ በፌስ ቡክ ይልቃል።ግን ለውጥ አይኖረውም፤ «ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ» ብቻ።ለሃገራዊ ለውጥ የሚደረገው ትግል የሚያቀጭጭ፣ ለጊዜው በተጫኑ «ትረፍ» ሰዎች የሚነፋ፣ የጆሮ ታምቡር የሚቀድ ሻጋታ ወሬ ነው።የቆሻሻ ፖለቲከኞች የዜሮ ድምር ጨዋታ።ልክ «እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል» አለች አህያ እንደሚባለው።

እነዚህ ትርፍ ሰዎች ያልተባለ፣ያልታየና የሌለ ነገር አለ፤ በዓይኔ አየሁት፣በጆሮየ ሰማሁት በማለት ይጮሃሉ። ጭሆቱን መልሰው በማስተጋባትም ውሸቱን እውነት ለማስመሰል ስራየ ብለው ይተጋሉ። ለትርፍ ሰዎች ትርፍ ነገር ማውራት የተለመደ ነውና። 



No comments:

Post a Comment