Saturday, December 14, 2013

አፄ ምንሊክ የጥቂቶች እምዬ የብዙዎች የእንጀራ እናት


ምንሊክ ለእናንተ እምዬ ሊሆኑ ይችላሉ ለሌሎች ደግሞ ጂኒ የሚጋልባቸው የእንጀራ እናት ነበሩ፡፡ የእንጀራ እናት ክፋት የሚያውቀውን ነው የሚያውቀው፤ እናንተ ግን በእናትነቷን ብቻ ነው ምታውቋትና የምታፈቅሯት፡፡ምክንያቱም ማንኛውም የእንጀራ እናት እንደ ምታደርገው ለልጆችዋ ያው እናት ነች፡፡ይህን ካልኩ ዘንዳ አጼ ምንሊክ የሰሯቸው ታሪካዊ ስሕተቶች ነገር ግን በታሪክ ሆን ተብሎ የሚዘለሉትን ላቅርብ፡፡

1.    ኤርትራን በንጉሰ ነገስት ፊርማቸው በማስረገጥ ለጣልያን ሸጧታል፡፡የዓድዋ ድልም ለግል ክብራቸው ብቻ አውለውታል፡፡ይህ ደግሞ የሁለቱ መረቦች ወንድማማቾችን ለመለያየት  የተሸረበ ሴራ ነበር፡፡የሁለቱ  የመረብ ህዝቦች መለያየት ከመረብ ወዲህ የነበሩትን ህዝቦች በአመራር፣በትጥቅና በኢኮኖሚ እንዲንኮታኮቱ አድርገዋቿል፡፡ለዛም ነበር ከ40 አመታት በኋላ ጣልያን ተመልሶ ሲመጣ ከትግራይ ውጪ እዚህ ግባ የሚባል ጦርነት ያላጋጠመው፡፡ከኤርትራ እስከ ማጨው ለመድረስ 6 ወራት ፈጅቶበታል፤ ከማይጨው እስከ አዲስ አበባ ግን በአንድ ወር ደረሰ፡፡

2.    ጁብቲን በአሮጌ ቆርቆሮ(ባቡር) ለፈረንሳይ አሳልፈው ሰጥተዋታል፡፡

3.    በጣልያን አስገዳጅነት የጣልያን ወታደሮች እንዲሆኑ የተደረጉት የኤርትራ ተወላጆች በዓድዋ ጦርነት እንደተማረኩ እጅና እግሮቻቸው እንዲ ቆረጥ ተደርጓል፤ ጣልያናውያኑ ምርከኞች ግን ማንም አልነካቸውም፡፡ ‹‹ጥቁር ሰው ›› ጥቁሮችን ከሞት በላይ በሚከፋ(አካል መጉደል) ቅጣት ሲቀጣ ነጮቹን ግን በእልፍኙ አስቀመጣቸው፡፡ከዛን ጊዜ ጀምሮ ነበር ኤርትራውያን ወንድሞቻችን ኢትዮጵያ ሃገራቸው ስለመሆኗን መጠራጠር የጀመሩት፡፡የምንልክ ስልጣን የተረከቡት ተከታታይ ገዢዎችም ቢሆን ያን ታሪካዊ ቁርሾ ከማለዘብ ይልቅ በእጅጉ ስላባባሱት ኢትዮጵያን እንደ ቀኝ ገዢያቸው ይመለከቷት ያዙ፡፡እነዚህ ነበሩ የመገንጠል ምክንያቶቻቸው፡፡

4.    በኦሮሞዎችና በደቡቦች የደረሰው ኢሰብአዊ ግፍ እንደ ጀብድ ሲቆጠር ያሳዝናል፤ ያስተዛዝባል፡፡የዘር ማጥፋት ዘመቻው እኮ የግዛት ማስፋፋት ብቻ አልነበረም፡፡የታሪክ ፀሓፊዎቻችን የማይመቻቸውን እየቆረጡ በመተው በአማርኛ ስላልዘገቡት ነው እንጂ አፄ ምንሊክ እኮ በኢትዮጵያ ታሪክ ቁጥር አንድ ‹‹የባርያ›› ነጋዴ ነበሩ፡፡ለመሆኑ ንጉሰ ነገስት ከመሆናቸው በፊት መዓርጋቸው ምን እንደ ነበር ታውቃላችሁ? ለኦሮሞ ወንድሞቻችን ያለ ስማቸው ስም የሰጣቸው ማን ነው?

5.    ከላይ የተጠቀሱት አንኳር አንኳር ታሪካዊ ስህተቶች ዛሬም ድረስ የሃገራችን ፖለቲካዊ፣መልከዓ ምድራዊና ኢኮነሚያዊ ራስ ምታቶች ናቸው፤ በተለይ ደግሞ የፖለቲካ ነቀርሳነታቸው ዛሬም ደረስ ማርከሻ ያለው ሁኖ አይታየኝም፡፡

6.    ጥቁሮች ነጮችን ማሸነፍ እንደሚችሉ ያሳየው አሉላ አባ ነጋ ነበር፤ በሳሓጢ፣በጉንዳ ጉንዶ፣በዶግዓሊ እንዲሁም በዓድዋ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል፡፡በአዲሰ አበባ(በኢትዮጵያ ታሪክ) ግን ስሙ አይነሳም፣ ሃወልቱ የለም፡፡በአጠቃላይ ለሌሎች ብሄሮች ጀግኖች ስማቸውና ታረካቸው እንዲነሳ የማይፈለገው ለምንድነው?

                                 መፍትሔው፡

የኢትዮጵያ ታሪክ በእውነት ከተፃፈ የድህነት፣ የህዝቦች ጭቆና፣የእርሰ በርስ መጠላለፍ፣የክህደት ወዘተ ሁኖ ነው የምናገኘው፡፡‹‹ኢትዮጵያ ሃገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ
                                          የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ›› የኢትዮጵያ ታሪክ ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡የዚች በለ ሁለት መስመር ግጥም የቋጠረ ሰው የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመርያው እስከ መጨረሻው(ካለ) እንደ ፊልም በዓይኑ የተመለከተ ነው የሚመስለው፡፡ዝምብሎ የተገጠመና የተዘፈነ አይደለም፡፡

ታሪካችን የተገላቢጦሽ ነው፡፡ ታሪካችን አናጢው ግንበኛ!...ሞደሻ፣ማጭድ፣ማረሻ፣ገጀራ፣ብረት ድስት ወዘተ ሰሪው ቀጥቃጭ(ቡዳ)!... ጋቢ፣ነጠላ፣ቀሚስ፣መቀነት ወዘተ የሚሰራውን ሸማኔ(ክር በጣሽ)! … ነግዶ አትራፊውን መጫኛ ነካሽ!...አርሶ አደፋርሶ ጎተራ(ሆድ) የሚሞላውን አፈር ገፊ!... ለአገሩ ዘብ የሚቆመውና ህይወቱን የሚገብረውን ነፍጠኛ!  በአጠቃላይ ለሃገሩ የሚኖረውን ሁሉ ይኮንናል፡፡

በገባሩ ጫንቃ የሚኖሩትን የሃገርና የወገን ሸክሞችን ደግሞ ያሞግሳል፤ለእነሱ የማይገባ የመዓርግ ስም ይሰጣል - ይሸልማል፡፡ ሞካንንት፣ተወለጄ፣ባላባት፣መሳፍንት፣ምርጥ ዘር(ጭዋ) ወዘተ… ምንም ሳይሰሩና የትም ሳይንቀሳቀሱ(በዘር ብቻ) ደግሞ ቀኝና ግራ አዝማች! ፊተ አውራሪ አፍተራሪ፣ቢትወደድ ወዘተ እያለ ያሞካሻል፡፡ይህ ነገር ዛሬም ድረስ ጨርሶ አልጠፋም፡፡ በሙስና፣በክራይ ሰብሳቢነትና በቤተሰባዊ መድሎ መልኩ ቀጥሏል፡፡


ይሁን እንጂ ያለፈውን ታሪክ ወደኋላ ተመልሰን ማስተካከል አንችልም፤ ብንችልም ፋይዳ የለውም፡፡ስለዚህ ደግም ይሁን መጥፎ(ለእኔ መጥፎ ነበር) ያለፈውን አልፏል፤ እንርሳውና እንደ አዲስ እንጀምር፤የዛሬዎቹን የጋራ ችግሮቻች አብረን መፍትሔ እናበጅላቸው፡፡ሌሎችን በፈጠራ ታረክ እያጣጣልንና ስማቸውን እያጠፋን የእንትና ጦርነት ‹‹ቅዱስ ጦርነት ነበር›› ማለቱን እናቁም፡፡ የትናንቱን ቁርሾ እያነሱ መሸለል፣ቡራ ከረዩ ማለት፣ ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ማስቸገር ለሁላችንም አይጠቅምም፡፡

No comments:

Post a Comment