በዚህች ዓለም ስኖር ሶስት ዓይነት ሰዎች አጋጥመውኛል፡፡የመጀርያዎቹ ለከፍተኛ አደጋ ዳርገውኛል…የመኖርና ያለመኖር
የህይወት ጥያቄዎችን እንዳስተናግድ አስገድደውኛል፡፡የመኖር ፈተና ከብዶኝ ለመውደቅ ስንገዳገድ ወደማልወጣው አዘቅት ገፍትረውኛል፡፡ክፉ
ስለሆንኩኝ ግን አልነበረም፡፡ብቻ፣ እንደ ሰው መኖሬን ያበገናቸው፣ ስያዩኝ ደም ደም የሚሸታቸው ነበሩ፡፡ሁለተኛዎቹ የመጀመርያዎቹ
ከደቀኑበኝ የመኖርና ያለመኖር አደጋ የታደጉኝ የህይወቴ መድህን ናቸው፡፡በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እስከዛሬ ድረስ እንድኖር ረድተውኛል፡፡ጥላ
ከለላ ሆኖውኛል፣ ሳዝን አፅናንተውኛል፣ ተስፋ ስቆርጥ አበረታተውኛል፣ ተዳክሜ ለመውደቅ ስንገዳገድ ደግፈውኛል…ቁሜ እንድራመድ ረድተውኛል፡፡ሶስተኛዎቹ
አልፎ ሂያጆች ናቸው…አልጎዱኝም፤ አልጠቀሙኝምም፡፡ምናልባት ግን፣ በተዘዋዋሪ ጠቅመውኝም ጎድተውኝም ሊሆን ይችላል፡፡
በህይወቴ አለኝ የምለው፣ ምንጊዜም የሚያስደስተኝ፣ ሳዝን የሚያፅናናኝ፣ ቀን ሲጎድልብኝና የተስፋ ወገቤን ሲያጎብጠኝ
ተስፋ የሚያሰንቀኝ፣ ፍረድሪክ ኒች ‹‹That doesn’t kill you makes you stronger››(የማይገድሉ ፈታኝ አጋጣሚዎች
ይበልጥ ያጠነክሩሃል) እንዳለው የመኖር ዕዳና ሸክም ካቅሜ በላይ ሆኖ ከሚሰብረኝ ይልቅ ይበልጥ እንዲያጠነክረኝ የረዳኝ ብቸኛው
ስጦታየ የንባብ ችሎታየ ነው፡፡ለማንበብ ያለኝ ፍቅርና ጉጉት ወደር የለውም፡፡ሱስ የለው፣ ጭስ የለው፣ ድካምና ጭንቀት የለው፣ ፀፀትና
ቁጭት የለው…ደስታ ብቻ፡፡ብዙ አሳዛኝ ልበ ወለዶችና እውነተኛ ታሪኮች አንበቤያለሁ፡፡ሆኖም ግን፣ ለካ እንዲህም አለ? ብየ ከመገረምና
ከመደነቅ አልፌ በማንበቤ የተቆጨሁበት ቀን የለም፡፡ይልቅኑስ፣ የሚነበብ ፍለጋ እሰማራለሁ፡፡በጣም የጠቀሙኝ ሰዎች እንግዲህ ማንበብ
እንድችልና የሚነበብ እንዳላጣ የረዱኝ፣ በተአምረኛ የአፃፃፍ ችሎታቸው ቀልቤን ስበው አድናቄያቸው እንድሆን ያደረጉኝና እያደረጉኝ
ያሉት ናቸው፡፡
‹‹ዋው! ኧረ እንኳን ተወደልድኩ…ኧረ በስሜት ተገፋፍቼ እንኳን እራሴን አላጠፋሁ›› ካስባሉኝ ምክንያቶች አንዱ በአካል
ሳይሆን በንባብ የተዋወቅኳቸውና የዚህች ዓለም ብርሃን እንዳላይ የጋረደኝ የአመለካከት ግርዶሽ ያለ ምንም ስቃይና ጠባሳ በቀዶ ጥገና
ያስወገዱልኝ የተለያዩ ዓይነት ደራሲዎች ናቸው፡፡በተለይ እማ ስለህይወትና ስለሰው የሚፅፉ የጥበብ ዕንቆች፡፡
‹‹በዚች ዓለም አንተን የሚመስል ሰው የለም፤
ልዩ ነህ፡፡ልዩ በመሆንህ እንኳን ደስ ያለህ››( Enjoy your life and your jobe) ከሚለው የዴል ካርኒጄው ድንቅ
የስነ ልቦና መፅሓፍ፣ ማንንም ባላሸንፍም ‹‹You can win…ማሸነፍ
ትችላለህ›› ከሚለው የሼቭ ኬራ መፅሓፍ፣ ‹‹ሰባቱ የውጤታማ ሰዎች ባህሪያት…The seven habits of highly
effective people›› ከሚለው የዶክተር ስቴፈን ኮቨይ የመሳሰሉት ድንቅ መፃሕፍት አንብቤያለሁ፡፡ስለ ራሴና ስለ ህይወት
ያለኝ አመለካከትና የአኗኗር ዜቤየን ሙሉ ለሙሉ እንድቀይር የደረጉኝ መፃሕፍት ግን ‹‹The last lecture›› የተሰኘው የፕሮፌር
ራንዲ ፓውሽ(Randy Pausch) ፣‹‹Tuesdays with Morrie›› የሚባለው የሚች ኤልቦም(Mitch Albom) የመሳሰሉ መፃሕፍትና ስቲቭ ጆብስ
‹‹How to live before you die›› በሚል ርእስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2005 ለስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ
ተማሪዎች ያደረገው ድንቅ ንግግር ናቸው፡፡
ሞዎሪ ቹዋርትስ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ነበር፡፡መላው አካሉ በስብሶ እንደ ቅጠል እንዲረግፍ በሚያደርግ ካንሰር ክፉኛ
ታሟልና የአልጋ ቁራኛ ሆኖ የሚሞትበትን ቀን በመጠባበቅ እንደሚገኝ ያትታል፣ የመፅሐፉ ትርክት፡፡የመፅሓፉ ደራሲ፣ ሚች ኤልቦም፣
ደሞ በገፍ የተሸጡ መፃሕፍት ደራሲ፣የስፖርትና የቀጥታ ስርጭት ጋዜጠኛና ሙዚቀኛ ነው፡፡በመሆኑም ጊዜ የለውም…ሁሌም ጥድፍያ ነው፡፡ሁሌም
ወከባ ነው…መፃፍ፣ ማንበብ፣ መዘገብ...የተለያዩ የሬድዮና የጋዜጣ ዝግጅቶች ማዘጋጀት፣ አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተሉ እንደ ጭልፊት
ቀድሞ መሞጭለፍ…የጥድፍያ ኑሮ ይኖራል፡፡ከእለታት ባንዱ ቀን…የቴሌቪዥን ዝግጅቶች እየተከታተለ እያለ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪው
የነበረው ሞዎሪ ቹዋርትስ የዝግጅቱ ታዳሚ ሆኖ ሲቀርብ ይመለከታል፡፡በቅርቡ እንደሚሞትም ይረዳል፡፡ያኔ፣ የተደራረቡ የስራ ድርሻዎቹን
ጠንጥኖ የቀድሞ ፕሮፌሰሩ ወደ ሚኖርበት ቤት በረረ፡፡ከዛም፣ በየማክሰኘው እየተገናኙ የሚማማሩበትና ‹‹Tuesdays with
Morrie›› የተሰኘ የ14 ማክሰኞዎች የህይወት አስተምህሮ(life lecture) የሆነ ድንቅ መፅሐፍ ለመፃፍ እንደበቃ ይናገራል፡፡በእውነተኛ
ታሪክ የተመሰረተና ወደ በፊልም ተሰርቶ ብዙ ተመልካች ያተረፈና ላቅ ያለ አድናቆት የተቸረው መፅሐፍ ነው፡፡
‹‹ልብህን የፈቀደውን አድርግ፡፡እንዲያ ስታደርግ፣ ደስታ የራቀው ነጭናጫና ምቀኛ አትሆንም፤ ሌሎች በያዙት ነገርም
አትቀናም፡፡ይልቅስ፣ እንዲህ በማድረገህ በምታተርፈው በረከት ትጥለቀለቃለህ፡፡›› ይላል እንደ ሞዎሪ ሆኖ የሚያወራው የመፅሐፉ ዋና
ገፀ ባህሪ፡፡ በመቀጠልም፣‹‹. . . the big things—how we think, what we
value—those you must choose yourself. You can’t let anyone--or any
society—determine those for you.›› (p. 155) እያለ ይቀጥላል፡፡በተለይ ግን፣ የሚቀጥሉት ጥቅሶች እጅጉን
ለውጠውኛል፡፡ ‹‹What if today were my last day on earth?›› (p. 64) ‹‹Once you learn
how to die, you learn how to live.If you accept you are going to die at any
time, then you might not be as ambitious as you are.›› (p. 82-83) ጤናህ ተማልቶ መኖር የመሰለ
ታላቅ ስኬትና ምርጥ ስጦታ ምን አለ?
ከላይ የጠቀስኳቸው መፃሕፍት ከነበብኩኝ በኋላ ሌላ ሰው ሆኛለሁ፡፡አለባበሴ፣ አስተሳሰቤ፣ አነጋገሬ…በአጠቃላይ
ውስጣዊ እኔነቴ ተቀይሯል፡፡
ይህን ያልተለመደና በራስ መተማመን የታጀበ አለባበስ ያስተዋለ አንድ ባለደባየ፣ ‹‹ኧረ ሽክ
ማለት! ‹ኢንተርቪው› ነበረህ እንዴ?›› አለኝ፡፡ስለብሰው በጣም የሚስማማኝ ሙሉ ልብስ( ሱፍ) ለብሼ ስላየኝ ነበር፡፡ከዛ በፊት፣
ለመጀመርያ ጊዜ ሱፍ የለበስኩት በ1999 ዓ.ም ነበር፤ ለዛውም አብሮውኝ ከተማሩት ጉዋደኞቼ ጋራ ፎቶ ለመነሳት የአንዱ ተማሪ ተውሼ፡፡
‹‹አዎ ‹ኢንተርቪው› ነበረኝ›› መለስኩለት፡፡በውስጤ ‹‹ቆይ ግን የሰው ልጅ ምን ነካው?››
እያልኩ እብሰለሰላለሁ፡፡
‹‹የምን ‹ኢንተርቪው› ?ለ ‹ሱፐር ቫይዘር› ወይስ ለ‹ማናጀርነት›?››
አከታትሎ ጠየቀኝ፡፡እኔ የራሴ የሆነ፣ የግሌ የምለው የአኗኗር ዘይቤ መከተል አልችልም? ለቃለ መጠይቅ፣ ለሰርግ፣ ለበዓል ወዘተ.
ካልሆነ በቀር አምሮብኝ መልበስ የለብኝም?
መፅሐፉ‹‹…management
should be the process of getting people to become self-directed›› (The First
Time Manager) ይል የለም እንዴ?
‹‹አይ፣ ለሁለቱም ነው›› መለስኩለት፤ የውስጤን በውስጤ ይዤ፡፡
‹‹እህህም፣ እኛ በአንዱም ሳንጠራ እናንተ በሁሉም ‹ኢንተርቪው› ትጠራላችሁ? ጊዜው ነው››
እንዲህ ሲናገር እንደ ቀልድ አስመስሎ ነበር፤ የገረጣ ፈገግታ እያሳየኝ፡፡የሰው ነገር አሁንም ግርም እንዳለኝ ነው፡፡
በሌላ ቀን ደሞ አንዱ፣‹‹አንተ ልጅ ግን ‹ኦፊስር› ልትሆን ነው እንዴ?›› ሲል ጠየቀኝ፤ሹፈት
በተላበሰ ቃና፡፡በእርሱ ቤት፣ ኦፊሰር ካልሆንኩ በስተቀር ያማረኛ መልበስ የለብኝም፡፡
‹‹አላወቅክም እንዴ? ‹ኦፊስር› ከሆነ እኮ ቆይተዋል›› ሌላው መለሰ፡፡
አንዱ ደሞ ‹‹ፐፐፐ…አምባሳደር መስለሃል›› ይላል፡፡
እነዚህ ሰዎች እኔ ያሳለፍኩት ኑሮ ኖረው ቢሆን ኖሮ እንዲህ አይሉም ነበር፡፡የእኔ ተሞክሮ
መቸውም ሊደርሱበት አይችሉም፡፡እኔ የእነርሱ መኖር እንደማይሆንልኝ ሁሉ፡፡
‹‹ላንተ ካንተና ላንቺ ከእናንተ ወድያ ማንም የለውም፡፡ለእኔም እንዲሁ ነው፡፡››
አንዱ ሳነብ ያገኘሁትና ምንጩ የጠፋብኝ ጥቅስ እንዲህ ይላል፤‹‹If you are the
only person in your team and you are against yourself, how can you expect to
beat the world?›› ይህን ጥቅስ ከነበቡኩኝ በኋላ ሆን ብየ ራሴን የተቀየምኩበትና የቀጣሁበት ጊዜ የለም፡፡ለምን?
‹‹በህይወት የምትኖርበት ጊዜ በጣም የተገደበ ስለሆነ የሌሎች ኑሮ ለመኮረጅ
በመሞከር አታባክነው፡፡የሌሎች አስተሳሰብ ውጤት በሆነው ዶግማ ራስህን አትሰረው፡፡የሌሎች ጭኾትና አስተያየት የውስጥ ስሜትህን አፍኖት
እንዲቀር አትፍቀድ፡፡ከሁሉም በላይ ግን ልብህን የፈቀደውና መንፈስህን የወደደውን ለማድረግ ብርታቱን ይኑርህ››
የሚለው የአፕል ካምፓኒ መስራቹ ስቲቭ ጆብስ ‹‹በህይወቴ ካጋጠመኝ ወሳኙ
መሳርያ በቅርቡ እንደምሞት ማስታወስኔን ነው፤እጅግ የላቁ ውሳኔዎች እንደወስን አስችሎኛልና፡፡በሞት መነፅር ሲቃኝ ሁለም ነገር እንደ
ጤዛ ተኖ ይጠፋል…ይሉኝታ፣ ክብር(ኩራት)፣ ወድቀትን መፍራት፣ አግኝቶ ማጣት ወዘተ. እንደ ጉም ሲበኑ የህይወት ወሳኙ ነገር ይቀራል…እርሱም
ልብህን ያሻውን መኖር ነው፡፡›› እያለ ይቀጥላል፡፡በፓንከሪያቲክ ካንሰር መያዙንና በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚሞት በዶክተሮች ከተነገሮው
በኋላ ያደረገው ንግግር ነበር፡፡ (ጊዜ ሰጥታችሁ አንብቡት ይጠቅማችሁ ይሆናል http://news.stanford.edu/news/2005/june15/jobs-061505.html
ፈጣን ኢንተርኔት ባለው አከባቢ የምትኖሩት ጓደኞቼ ቪድዮውን መመልከት ትችላላችሁ https://www.ted.com/talks/steve_jobs_how_to_live_before_you_die
)
በመሆኑም
‹‹live each day as if it were your last and someday you’ll be right.›› ሲል ደምደሟል፡፡እኔም፣ እናንዳንዷን ቀን የመጨረሻየ እንደሆነች አድርጌ ነው የምኖረው፡፡ብዙ
አታካችና አስቀያሚ የህይወት ገጠመኞች ቢያጋጥሙኝም እንሆ እነዚህን ሰንቄ በማዝገም ላይ እገኛለሁ፡፡እናም ለዛሬው የልደት ቀኔን
ደርሻለሁ፤ እንኳንም አደረሰኝ፡፡
ተከራይቼ በምኖርበት ግቢ ውስጥ የአንዱ ህፃን የአንደኛ ዓመት ድል ባለ ድግስ ተከብሯል፡፡የድግሱ ታዳሚ ስለነበርኩ
ለመጀመርያ ጊዜ በልደት ቀኔ ‹‹…Happy birthday
to you
Happy birthday to you
Happy birthday
Happy birthday to you
Happy birthday to you
Happy birthday… ››የሚለው የስቲቪ ዋንደር ድንቅ የልደት ሙዚቃ ተጋብዣለሁ፡፡
Happy birthday to you
Happy birthday
Happy birthday to you
Happy birthday to you
Happy birthday… ››የሚለው የስቲቪ ዋንደር ድንቅ የልደት ሙዚቃ ተጋብዣለሁ፡፡
ከዛም…ለህፃኑ የተዘጋጀው መጠጥ ጠጥቻለሁ…ቆንጆ ምግብም ተመግቤያለሁ፡፡‹‹ፃድቃናት የዘነበ…›› እንደሚባለው፡፡
‹‹የድኻ ምርቃት ከእርግማን አይተናነስም፡፡›› ያለው ማን ነበር? ይህን እያሰብኩና ፈራ ተባ እያልኩ ‹‹ዳጊን ያሳድግልን፣
ለወግ ለማዓርግ ያድርስልን›› ብየ ወጣሁ፡፡ልጁ የግድ ማደግ አለበት፡፡ለወግ ለመዓርግ እንዲደርስም ከልቤ እመኛለሁ፡፡እንኳን እርሱ፣
በመሃል ሸገር፣ በተንጣለለ ግቢ ውስጥ ተወልዶ እኔም አድጌ ለዚህ ደርሻለሁ፡፡እርሱ በየዓሙት ድል ያለ ድግስ ይደገስለታል፡፡ቤተሰቦቹ
በጣም እንደሚወዱት እየነገሩት በፍቅር ያድጋል፡፡በአራት ዓመቱ ወደ ህፃናት ማሳደጊያ ይላካል፡፡ከይ.ጂ 1፣ 2፣3…እንዲሁም አንደኛ፣
ሁለተኛ፣ሶስተኛ፣…እያለ እስከ ዩኒቨርሲቲና ደክትሬት ይደርሳል፡፡
እኔም አደኩ፡፡በአራት ዓመቴ ከመዓት ከብትና ፍየሎች ጋራ ወደ በረሃ ተላኩኝ፡፡ቀን ቀን በእነ እንትና ቤት ልጆች
ያለኝ ኡንቅ፣ መልጎም(ቁልፍ)ና መርፌ ቁልፍ በሐይል እየተነጠቅኩ፣ ግልገሎቼ ቀበሮና ዝንጀሮ በበላብኝ ቁጥር እየተቀጠቀጥኩ ‹‹ኤኽ፣
ብሓፂርኻ ቅረይ!›› እየተባልኩ ነጋ ጠባ በልምጭና በቁንጥጫ እየተለበለብኩኝ፣ አንዳንዴም በበርበሬ እየታጠንኩ፣ አርግማኑ ምርቃት
አድርጎልኝ በትአምር አደኩኝ፡፡አዎ፣ እኔ ለዛሬ መብቃቴና ከእነዚያ ሰማይ ጠቀስ ተራሮችና ገበያ ላይ የተሰበሰቡ የሚመስሉ ሰማይ
ጠቀስ ጥቋቁር ድንጋዮች ለትንሽ አምልጬ አዲስ አበባ የሚገኙትን ፎቆች ለማየት መብቃቴ ራሱ ትአምር ነው፡፡የታእምሮቹን ሁሉ ትአምር
ግን ማንበብ መቻሌን ነው፡፡ማንበብ መቻል እንደጋና መወለድ ነው፤ በየሴኮንዱ፣ በየደቂቃው፣ በየስዓቱ፣ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ…ሁሌም
የልደት ቀን ነው፡፡ሃብትና ስልጣን ቢኖርህ እሰየው፤ የተቸገሩ ሰዎች ሲያጋጥሙህ ከንፈርህ መጠህ አታልፍም፡፡ትረዳቸዋለህ…ሰዎች ሲደሰቱ
እንደማየት የሚያስደስት አለ?ለዛውም የደስታቸው ምንጭ አንተ መሆንህን ስታውቅ! አህ!
አትቆጭኝ መሬት ቀስብየ ረግጥሻለሁ
የዘላለም ሰፈሬ መሆንሽን አውቃለሁ
በነገራችን ላይ፣ ለመጀመርያ ጊዜ የልደት ቀኔን በይፋ ያከበረልኝ ፌስቡክ ነው፡፡በርግጥ ህፃን
እያለሁ አንደኛ አመቴን ሲከበር በወገቤ ላይ ዳቦ ተቆርሶልኝ ይሆናል፤ ያደኩበት አከባቢ ባህል ስለሚያስገድድ፡፡በዚህ አጋጣሚ ለመጀመርያ
ጊዜ ስለእኔ መወለድ ተቁም ነገር ጥፎ እንኳን ተወለድክ ለመባል ያበቃኝ ፌስቡክን የፈጠረው ዙከርበርግን አመስግኑልኝ፡፡ከእናንተ
ጋር ያገናኘኝ እርሱ ነው፡፡እናንተም አመሰግናለሁ፡፡
ታላቁ ፈተና…
ገዢው ስርዓት የሚነቅፉ ፅሑፎች የምትፅፍ ከሆነ ለእስር ታጭተሃል
የገዢው ስርዓት ‹‹ታማኝ›› ከሆንክ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ያንተው ነች፡፡ለከፍተኛ ስልጣንና እስከ
ለሌለው ሃብት ታጭተሃል…ላንተ የሚመጥን ወንበር በማፈላለግ ላይ ናቸው፡፡እንደሚታወቀው የኢህአዴግ ስልጣን እስከ መቃበር ድረስ ነው…ድርጅቱ
እስካልተቀበረ ድረስ፡፡
ከዓመታት በኋላ በአካል የገኘኸው የቅርብ ዘመደህ ‹‹አንተ ልጅ ግን አልሰማም አልክ አይደል?
ተው ግን ተው!›› ይልሃል፡፡
መታወቅያ ሳወጣ ‹‹የአደጋ ጊዜ ተጠሪ›› ተብየ ስጠየቅ የእርሱ ስምና አድራሻ ሞልቻለሁ፡፡‹‹አስፋው
ሓወይ፣ እዚ ነገር እዙይ ግደፎ ኢለካ ኣለኹ ግደፎ፤ ከም ጥላሁን
ይግዛው ደመ ከልብ ኮይንኻ ከይትተርፍ፡፡እዙይ ዝበለካ ዘለኹ፣ ስለዝፀልአካ ከምዘይኮነ ኣፀቢቕኻ ትፈልጥ ኢኻ…ግዜኡ ፅቡቕ ኣይኮነን፡፡ካብ ስራሕ ክትባረር፣
ክትእሰር …ኢሉ እውን ክትቕተል ትኽእል፡፡ ተስፋኻ ኣይተፀልሞ…ዕደልኻ ኣይተበላሽዎ…ዕድመኻ ኣይተሕፅሮ…፡፡ከይፅሓፍኹ ክነበር ኣይኽእልን
እንተይልኻ ብናይ ብርዒ ስም ተጠቐም፡፡
(ይህ ነገር ተው ብየሃለሁ፣ ተወው፡፡እንደ ጥላሁን ይግዛው ደመ ከልብ ሆነህ እንዳትቀር፡፡ይህን
የምልህ፣ ስለምጠላህ እንዳልሆነ በደምብ ታውቃለህ…ጊዜው ጥሩ ኣይደለም፡፡ ከስራ ልትባረር፣ ልትታሰር…ብሎም ልትገደል ትችላለህ፡፡
ተስፋህን ኣታጨልመው…እድልህን ኣታበላሸው…እድሜህን ኣታሳጥረው…፡፡ ኣለመፃፍ ኣልችልም ያልክ እንደሆነ የብዕር ስም ተጠቀም፡፡)››
እናንተስ ምን ትላላችሁ? መካሪዎቼና አሳዳጆቼ እንደሚሉት መፃፍም ሆነ ማንበብ አቁሜ የኔ ያልሆኑ
የልደት ቀኖች በፌስቡክ ላክብር ወይስ ልቤ እንደፈቀደውና የውስጥ ስሜቴ እንደወደደውን እየተከተልኩ ልደቴን በየቀኑ ላክበር? “We cannot change the cards we are dealt, just
how we play the hand.”
― Randy Pausch, The Last Lecture
― Randy Pausch, The Last Lecture

No comments:
Post a Comment