| ቢዛ ፊልም |
በሬድዮና ቴሌቪዥን ዝግጅቶች የምናውቀው ብርሃነ ንጉሰ ወደ ፊልም ኢንዲስትሪው በይፋ መቀላቀሉን የሚያበስር ወሬ ይዞ
ብቅ ብሏል፤ቢዛ ፊልም፡፡በፖስተሩ ላይ ያሉ ተዋናዮች ስመለከት የልጅነት ጀግኖቼን አስታወሱኝ፡፡እነ ሻምበል ሮማን፣ እነ ጓል ዓይነታ፣ እነ ሲሳይ ገበል፣ እነ ጉማ፣ እነ ቀጭ ሕርሙ፣ ሽላ መረብ…
በተላይ ያቺ ሰላም ተስፋይ የሚሏት ልጅ ሳይ በጣም ነው የደነገጥኩት፡፡ያቺ
ገና ህፃን እያለሁ ‹‹ማንጅስ፣ ይህ ትግል ከግቡ የምታደርሱት እናንተ ናችሁ፤ ስጋ ብፆት›› የሚል ትንቢት የነገረችኝ ሻምበል ሮማን
በአካል ድቅን አለችብኝ፡፡በህይወት ትኑር አትኑር አላውቅም፡፡ምስሏና አነጋገሯ ግን በህይወት እስካለሁ ድረስ ከእኔ ጋር ይኖራል፡፡ይህ
እውነታ የእነ እንትና ጭሆት ሊፈቀው አይችልም፡፡በጭራሽ!
እነ ሻምበል ሮማን የታገሉት የደርግ ስርዓት አሁን ባለው ስርዓት
ለመተካት እንዳልነበረ በእርግጠኝነት መመስከር እችላለሁ፡፡ለዛም ነው
‹‹ትግሉን ከግቡ የምታደርሱት እናንተ ናችሁ›› ያለችኝ፡፡በእቅፏ አድርጋ ስስ ፀጉሬን እያሻሸች፣ በራሽን መልክ ተሰጠቻት ዳቦ በሻይ
ለእኔ አስረክባ፡፡ይህ መሆኑን ሁለት ጠላቶች እንዳፈራ ግድ ብሎብኛል፡፡ባንድ በኩል ሁሉንም ጠቅልሎ ሲያበቃ፣ ሁሉንም እንድናጣ የደረገን
ስርዓት መታገል ይኖርብኛል፡፡በሌላ በኩል ደሞ ይህ ስርዓት ሙሉ በሙሉ የጠቀለለውን ሁሉ በሃይል ለመረከብና ‹‹የጠቅላይ አግላይ››
አዙሪቱን ለማጦዝ የተዘጋጁትን መፋለም እንዳለብኝ ያሳብቃል፡፡
ብርሃነ ንጉሰም ሆነ ተዋናይዋ ሰላም ተስፋይ ተጋሩ ከመሆናቸው በስተቀር
ያጠፉት ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ቤዛ ፊልም፣ ምናልባትም አብዛኞቹ የህወሓት አክራሪዎች ላይደግፉት ይችላሉ፡፡የትግራይ ህዝብ ግን
ታሪኩ እንዳይዛባበትና ጥራቱ እንዳይበላሽበት ከመስጋት ውጪ ምንም ዓይነት ተቃውሞ እንደማይኖረው መመስከር ይቻላል፡፡የትግራይ ህዝብ
ቁጭት የታጋይ ልጆቹ ዓላማ ግብ አለመምታቱን ብቻ አይደለም እንደ እግር እሳት እየለበለበው ያለው፤ የልጆቹን ታሪክ ሳይበረዝ፣ ሳይከለስ
አለመዘገቡንና ለቀጣዩ ትውልድ አለመተላለፉንም ጭምር እንጂ፡፡
ምናልባት ግን እነ ብርሃነ ንጉሰ የአንደኛው ፅንፍ ጭኾት በጭኾት
ማድረጋቸው በሃገራችን ታሪክ ተስርቶ የማያውቅ ስኬታማ የፊልም ስራ መስራታቸው አመላካች ነው፡፡ ‹‹ጠላቶች አለሁ?›› ሲል ይጠይቅል
ዊኒስተር ቼርችል፣ ‹‹መልካም፡፡በህይወትህ ለአንድ ነገር መቆምህን ያመለክታል፡፡›› እንግዲህ፣ ብርሃነ ንጉሰና ሰላም ተስፋይ ከራሳቸው
በላይ ለሆነ ዓላማ የቆሙ ጀግኖች መሆናቸውን እያስመሰከሩ መሆን አለበት፡፡
የአግላይ ጠቅላዮች አዙሪት
የሃገራችን ፖለቲካ ድሮም ዘንድሮም ‹‹አግላይ ጠቅላይ›› ነው፡፡ልዩነትን አጥብቦ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን
ባካተተ መልኩ የሚጓዝ ሳይሆን የተለየ ምልከታ የሚያራምዱትን ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ፍፁም የበላይነት የሚያቀዳጅና ከቅንድባቸው
ርቀው በማያስቡ ወገኖች የሚዘወተር ነው፡፡(አግላይ ጠቅላይ የሚለው አባባል የሚያዘወትረው ወዳጄ ተስፋኪሮስ አረፈ ሲሆን አገላለፁ
ያለፉት ስርዓቶች ለመግለፅ እንጂ አሁን ያለው የ100 ፐርሰነት አንድ ዓይነት አስተሳሰብን ለመግለፅ ሲጠቀምበት አልታዘብኩም፡፡)
በኢትዮጵያችን ታሪክ፣ ‹‹እኔ ብቻ ነኝ ትክክል፤ሌላው ሁሉ የተሳሳተ ነው፡፡በመሆኑም፣ የእኔ
መንገድ መከተል አለበት፡፡ካልሆነ ግን፣ ከምድረ ገፅ ተጠራርጎ መጥፋት አለበት፡፡›› የሚል ግትር አቋም ያላቸው አክራሪዎች አንድ
ጠላት ብቻ ነበራቸው፡፡የተቀረው ወዳጃቸው፤ ቀኝ እጃቸው ነው፡፡አሁንም ያው ነው፤ የተለወጠ ነገር የለም፡፡
ከሁለት ፅንፎች የተለየ ምልከታ ያለው ኢትዮጵያዊ ግን ብያንስ በሁለት ጠላቶች ተጠልፎ ሲወድቅ
ማየት የተለመደ ነው፡፡በሃገሬው አባባል ‹‹መሃል ሰፋሪ›› ተብሎ ይፈረጃል፡፡ መሃል ሰፋሪ ደግሞ በሁለት ፅንፈኞች በተተኮሱ ጥይቶች ይመታል፡፡ይሄ፣ የኢትዮጵያችን ነባራዊ እውነታ ነው፡፡ለምሳሌ
ያህል፣ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉት የሃገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን መውሰድ እንችላለን፡፡እነዚህ ተቃዋሚ ፓረቲዎች፣ በአንደኛው ፅንፍ
በገዢው ስርዓት ጥርስ ተነክሶባቸው ነጋ ጠባ ሲታሰሩና ሲንገላቱ፣ ከሃገር ሲባረሩ እንዲሁም ሲገደሉ ይስተዋላል፡፡ለቁጥር በሚያታክቱና
ሰላማዊ ትግሉን ወደ ፅንፍ በሚገፋ መልኩ ባልዋሉበት ጥቀርሻ ሲለብሱ ማየት የተለመደ ነው፡፡በሌላኛው ፅንፍ ደሞ፣ ለትግል ያልቆረጡ፣
ገዢው ስርዓት ተቀባይነት (ሌጂቲማሲ) እንዲያገኝ ከማድረግ ውጪ ሌላ ፋይዳ የሌላቸው አስመሳዮች ናቸው ተብለው ይፈረጃሉ፤ ገዢውን
ስርዓት በጠብ መንጃ አፈሙዝ ለመደምሰስ በሚታገሉ ሃይሎች፡፡
ይህ አካሄድ ግን፣ ሃገሪቱን መቋጫ በሌላቸው ጦርነቶች፣ በድህነትና ኋላ ቀርነትና አዙሪት እንድትዳክር ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ እንደሌላው ታሪክ ምስክር ነው፡፡የአጼ
ቴዎድሮስ ራእይ አጼ ዮሃንስ 4ኛ ተረክበውት ቢሆን ኖሮ ዛሬ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የዕለት ጉርስ አጥተው የውጭ እርዳታ የሚማፀኑባት
ሃገር ለመረከብ አንገደድም ነበር፡፡የአጼ ዮሃንስ 4ኛ ህልሞች በአጼ ምኒልክ ተቀባይነት አግኝተው ቢሆን ኖሮ ዛሬ በሩቅ የምንናፍቃት ኤርትራ አትኖርም
ነበር፡፡ የእነ ቴድሮስ ካሳሁን ‹‹ዳህላክ››ና ‹‹ፍዮሪና››ም ያህን ያህል ጆሮ አይስቡም ነበር፡፡አጼ ሃይለስላሴም በደርግ አይገደሉም
ነበር፡፡ደርግም፣ ዛሬ ‹‹ሙሉ በሙሉ መደምሰስ አለበት›› በሚባልለት ስርዓት አይደመሰስም ነበር፡፡በአጠቃላይ፣ ምንጊዜም ከዜሮ ለመጀመር
አንገደድም ነበር፡፡ሁሉም ስርዓቶች መቶ ፐርሰንት ካላሸነፍኩ ምኑን አሸነፍኩ የሚል የአዳኝና ታዳኝ ፍጥጫ የተከተሉት፡፡ሲያሸንፉ
መቶ ፐርሰነት ነው፤ ሲሸነፉ እንዲሁ መቶ ፐርሰንት፡፡በመሆኑም ሃገራችን ሁሌም መቶ ፐርሰነት እንደተሸነፈች ነው፡፡
ካለ አግላይ ጠቅላዮች መሰረት የሌለው ስርዓት
የአግላይ ጠቅላዮች የምንጊዜም ጠላት እነሱ ከሚያራምዱት የተለየ
አስተሳሰብ የሚያራምድ ብቻ ነው፡፡የአሁኑ ስርዓትም አግላይ ጠቅላይ መሆኑን ከላይ ተጠቅሷል፡፡ግን በአንድ ነገር ይለያል፡፡ተቀናቃኞቹ
በህዝብ ላይ ሲዘምቱ እንደማየት የሚያስደስተው ነገር የለም፡፡በህዝብ ላይ ዘምቷል ብሎ ሊያስቆማቸው ሲሞክር መመልከትም ያልተለመደ
ተግባሩ ነው፡፡ይልቅ፣ በህዝብ ላይ እንዲዘምቱ ነው የተለያዩ ሴራዎችን የሚሸርበው፡፡ምክንያቱም፣ በህዝብ ላይ የሚዘምቱ ጠላቶች ከሌሉ
ህዝቡ ሆ ብሎ ለራሱ እንደሚውጠው ጠንቅቆ ያውቃልና፡፡በመሆኑም፣ የዚህ ስርዓት ሁነኛ ደጋፊ የትግራይ ህዝብ ሳይሆን እነ እነ አበበ
ገላው፣ ሄኖክ የሺጥላ፣ ሃይሉ ቢታንያ የመሳሰሉ አክራሪዎች ናቸው፡፡
የዚህ ስርዓት ዋነኛው መርሕ ‹‹Never interrupt your enemy when he is making a mistake›› በሚለው የNapoleon Bonaparte አባባል ስር ሊጠቃለል ይችላል፡፡በአንድ ህዝብ ላይ መዝመት የሽንፈቶች ሁሉ አልፋና ኦሜጋ ነው፡፡ለዛም ነው፣ የስርዓቱ ሁነኛ ደጋፊዎችና ተጠቃሚዎች የትግራይ ህዝብ ሲዋረድና ሲሰደብ ስድቦቹን አጋንነው ለህዝቡ ከመናገር ውጪ ሌላ ነገር ሲያደርጉ የማይስተዋለው፡፡እንድያ ከሆነማ ‹‹የኸው ደሞ መጡበህ፤ ታሪካዊ ጠላቶችህ በቁምህ ሊውጡህ አፋቸውን ከፍተው ወደ አንተ እየተንደረደሩ ነው›› የሚለው የምንጊዜም ነጠላ ዜማው አድማጭ አያገኝም፡፡
ይህ ነጠላ ዜማ አድማጭ አላገኘም ማለት ደሞ ጠላቶቹን ሳይታገል ማሸነፍ የሚችልበት መንገድ ተዘጋ ማለት ነው፡፡ይህ የትግል ስልት ግን ከስርዓቱ ተርፎ ሰርተው ከመብላት ውጪ
ምንም ያላጠፉት ባለሙያዎችም ሳይጠቅም አልቀረም፡፡ቤዛ ፊልም የህን የሚያስረግጥ ሁነኛ ተምሳሌት ነው፡፡
“The supreme art of war is to subdue the enemy without
fighting” Sun Tzu
No comments:
Post a Comment