Friday, November 30, 2012

ይህች ዓለም የአምባገነኖች መነሃርያ ነች




ፍልስጤማውያን በእስራኤል አውሮፕላኖች የቦምብ ናዳ እየወረደባቸው ነው፡፡ ይሐው ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸው ሲሆን እስካሁን ድረስ የሐማስ ከፍተኛ የጦር አዛዥ ጨምሮ 80 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከእስራኤል በኩል ግን ሦሰት ሰዎች ብቻ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ 27 ፍልስጤሞች ለ 1 እስራኤላዊ  ማለት ነው ሒሳቡ፡፡
ባራክ ኦባማ አሁንም ለእስራኤል ድጋፋቸውን አረጋግጠውላታል፡፡ እስራኤል ራስዋን የመከላክል ሙሉ መብት እንዳላትም አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ የሐማስ አቅምን ያላገናዘበ መፍጨርጨርና አልሞት ባይ ተጋዳይነት የእስራኤል የደም ጥማት ከማርካት ውጪ እስካሁን ድረስ የፈየደው ነገር የለም፡፡ ለኔ ከድንጋይ ጋር እንደ መላትም ነው የሆነብኝ ነገሩ፡፡ እስራኤል እስከ አፍንጫዋ ድረስ የታጠቀች አገር(የጸረ ሚሳኤልም ጭምር) መሆንዋን እያወቁ ሐማሶች ድንጋይ የመወርወር ያህል አጉል ሮኬቶችን ያንጣጣሉ፡፡
ጥርስ አልባው( የስግብግብ ምዕራባውያን ስራስፈጻሚው)ባንኪ ሙን እስራኤል የልብዋን እስክትፈጽም ፀጥ ብለው ከርመው አሁን ለይምሰል መተንፈስ ጀምረዋል፡፡ ይህ ተግባር ግን እጅግ አሳዛኝና የዓለም ኢ-ፍተሃዊነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ትልቅ ዱላ ያለው በፈለገው ጊዜ በፈለገው ሰው ላይ ማሳረፍ ይችላል፡፡ እስኪደክመው ድረስም ደጋግሞ መነረት ይችላል፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ግን አንዱ ሌላውን የአምባገነንት መዓርግ ሲሸልመው ስትሰማ ነው፡፡ ሁሉም እኮ አምባገነኖች ናቸው፡፡ ልይነቱ የአቅም ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ታላቁ ዱላ የተሸው የአምባገነኖቹን አምባገነን ይሆናል፡፡ ልክ እንደ አመሪካ፡፡
አዎ! አመሪካ(የዓለም ታላቁ ዱላ ባለቤት) ከሆንክ በዓለም ለመጀመርያ ጊዜ በጃፓኖች ላይ የአቶሚክ ቦምብ ማዝነብ ትችላለህ፡፡ የሽንፈት ካባ እስክትከናነብ ደረስ ቬትናም ላይ ጦርነት ታውጃለህ፡፡ ቀጥለህ ኢራቅን ትወርና ሳዳምን ባስር ሳንቲም ገመድ ማንጠልጠል ነው፡፡ አፍጋኒስታን የጦር መለማመጃህ ትሆናለች፡፡ ልብያ ላይ የበረራ ማዕቀብ ትጥልና ኔቶን ልከህ ዶግ አመድ ማድረግ፡፡ ከዛም ደምህ ያፈላው ጋዳፊን ጨፈላልቀህ በደም ታጥበውና አስፓልት ላይ ዘርግተህ ይሐው ማለት ነው፡፡ ምን ይሳንሃል ጃል!በመላው ዓለም የጦር ስፈራ አለሃ፡፡
ምን ቀረህ? ኢራን! ቆይ ለስዋም መላ አይጠፋም፡፡ በኢኮነሚ ማዕቀብ ታሻትና ከተዳከመች በህዋላ እስራኤልን ልከህ እንዳልነበረች ታደርጋታለህ፡፡




No comments:

Post a Comment