የሰው ልጅ “ጥረህ ግረህ ብላ” ተብሎ እስከ
ተረገመበት ቀን ጀምሮ ያልወጣው ዳገት ያለወረደው ቁልቁለት የለም፡፡አሻፈረኝ አልታዘዝም በማለቱ ከገነት ወደ መሬት ተሽቀንጥሮ መወርወሩ
ይነገራል፡፡ከዛም መሬት ወርዶ ብዙ ተንገላትተዋል፣ወንዝ ተሻግረዋል፣ባሕር አቁዋርጠዋል፣ ሰማይና መሬትን አዳርሶዋል፡፡ባጋጣሚ ግን
ትልቅ ዋሻ አገኘ፡፡ እዛውም ተጠልሎ ድንጋይ ለይ እየተኛና እንደመሳርያ እየተጠቀመ መኖር ጀመረ፡፡ ያ ዘመንም ዘመነ ድንጋይ ብሎ
ሰየመው፡፡እንዲህ እንዲህ እያለ መሬትን ብቁጥጥር ስሩ ማስገባቱ ካወቀ በሁዋላ እንደገና ደግሞ ወደ ሌሎች ፕላኔቶችን እያመራ ይገኛል፡፡ስራውን
ለማቃለልና ንሮውን ለማሻሻል ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልዘየደው ዘዴ አለ ለማለት ያሰቸግራል፡፡ ከዘመነ ድንጋይ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ
ብዙ ዓይነት መሳርያዎችን ሰርተዋል እየሰራም ይገኛል፡፡ከነዚህ መሳርያዎች አንዱ ሮቦት ነው፡፡ግን ሰው እንዴት ሮቦት መስራት ቻለ?
ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡መፅሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር
የሰው ልጅን በራሱ አምሳል ሰራው” ይላል፡፡በዚህ መሰረት ለመጀመርያ ጊዜ የኮረጀው እግዚአብሔር ሲሆን ሰውም ይህን የኩረጃ ጥበብ
ከፈጣሪውን ተምሮ ሮቦትን በአምሳሉ ሰራው፡፡እግዚአብሔር ሰውን የሰራው እንድያገለግለው ነው ይባላል፡፡ ለምን? መልሱ በትክክል ባላውቀውም
ምናልባት ግን መስራት ስለደበረው ሊሆን ይችላል፡፡ምክንያቱም ደግሞ ባይደብረው ንሮ እስካሁን ድረስ መስራት አያቆምም ነበር፡፡ነገር
ግን ለሰባት ተከታታይ ቀናት ወጥሮ ከሰራ በሁዋላ “መተካካት” የሚባል ፖሊሲ በማርቀቅ ለሰው ልጅ ተላላኪ አድርጎ ሸመው፡፡የመጨሻው
ከፍተኛ ስልጣን ግን ዛሬም ድረስ በእጁ ነው…የፈለገውን ማድረግ ይችላልና፡፡ምርጫ ቢኖርም ባይኖርም አሸናፊው ያው ራሱ ነው፡፡የደበረው
ስራ እንጂ ስልጣን አይደለምና፡፡ታድያ እግዚአብሔር መስራት ከደበረው የሰው ልጅ እንዴት አይደብረውም?በቃ ሰውም በተራው መስራት
ሰለቸውና ሮቦት ሰርቶ የተላላኪነት ስልጣኑን አሳልፎ ሰጠው፡፡ልክ እነደፈጣሪውም ራሱ የማይችለው ወይም መስራት የማይፈልገው ነገር
ሁሉ ቀንና ሌሊት እያሰራው ይገኛል… ያለምንም ዕረፍትና ክፍያ፡፡
እግዚአቢሔር አዳምና ሔዋንን ከፈጠራቸው በሁዋላ
“በዚህ ዓለም የፈለጋችሁትን ነገር ሁሉ ማድረግ ትችላለቹህ ፤ነገር ግን ያች ዕፀ በለሴን መብላት ይቅርና መንካት አትችሉም፡፡”
የሚል ጥብቅ ትእዛዝ ሰጣቸው፡፡ ይህ ነገር ለአዳምና ሔዋን በቀላሉ ሊዋጥላቸው አልቻለም፡፡እንዴት ባንዲት ዕፀ በለስ ምክንያት ሙሉ
ነፃነታችን እናጣለን? የሚል ጥያቄ በህሊናቸው መመላለስ ጀመረ፡፡አምፅ አምፅ ፣ሸልል ሸልል አላቸው፡፡ ባልና
ሚስት ብዙ ከተመካከሩ በሁዋላ “ነፃነት ወይም ሞት!” የሚል መፈክር አንግበው ወደ ዕፀ በለሰዋን ሄዱና እንክት አድርገው በሉዋት፡፡ወድያውም
ማንኛውም ነገር መክፈትና መዝጋት እንዲሁም በቀላሉ የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ፣ማየት፣ይዘው መግባትና መውጣት ቻሉ (የእግዚአብሔር ሴኩሪቲ
ሲስተም ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት)፡፡ነገር ግን እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን የሚያስቡትና የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ያውቅ ስለነበር እጅግ
በጣም ተቆጣ፡፡ ተቆጥቶም አልቀገረ “ይች ጥሬ ከደረች …” አለና በዱላ እየዠለጠ ከቀያቸውን አባረራቸው፡፡ ከዛማ ምን ይደረግ ሁሉም
ነገር አለቀ ደቀቀ…ሳይቀድሙት ቀደማቸው፡፡ማለቅያ የሌለው ስቃይና መከራ ደረሰባቸው፡፡ተንገላቱ አይቀጡት ተቀጡ፡፡አባታችን አዳም
ሳይወድ በግዱ እጁን ሰጠ ወንጀለኛ መሆኑንም አመነ፡፡ ከብዙ ጅንጀና በሁዋላ በአዳምና በጌታው መካከል ዕርቀ ሰላም ወረደና አዳም
ወደ ቀደሞ ሰራው ተመለሰ፡፡ ቢሆንም ግን ከዛች ጊዜ በሁዋላ የአዳም ዘር በሙሉ ማብርያና ማጥፍያ ያለው ሮቦት ሁኖዋል፡፡አንዴ ይበራል
(switch on) ይደረጋል ከዛም ይሰራል፣ሌት ተቀን ይሰራል፣ ግራና ቀኝ ይወራጫል፣ያን የነሳል ይህን ይጥላል፣ቀስ በቀስ እንደ
ሻማ ራሱን እያቀለጠ ያጠፋል፡፡የማይሰራ ሰነፍ ካለም ያው ተሎ ካገልግሎት ወጪ ይሆናል፡፡በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ ይጠፋል(switch
off) ይደረጋል፡፡ሰው የሰራቸው ምግቦች ካገልግሎት ውጪ እንደሚሆኑ ሁሉ እሱ ራሱም ካገልግሎት ውጪ ይሆናል…ኤክስፓየርድ ያደርጋል፡፡
ፈጣሪ
ለመጀመርያ ጊዜ ራሱን ኮፒ አድርጎ ሰውን ፈጠረ፡፡ያገልጋይነት(የበርነት ግዴታ)ስልጣንም ሰጠው፡፡ሰውም በተራው ከፈጣሪውን ኩረጃ
ተማረና ሮቦትን በራሱ አምሳል ፈጠረ፡፡ ነገር ግን ሮቦት ማንነቱን እንደማያውቀው ሁሉ ሰውም ማንነቱን አያውቀም፡፡ ሌላ ሰው ካልነገረው
በስተቀር መቸ እንደተወለደ አያውቅም፡፡ መቸ እንደሚሞትም እንዲሁ፡፡
No comments:
Post a Comment