Friday, November 30, 2012

የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ናፍቆት

                          
አህጉራችን አፍሪካ አሁንም የተመዋላ ሰላም አላት ለማለት ያስቸግራል፡፡ የማሊ ስሜናዊ ግዛት በእስላማዊ ፅንፈኞች ቁጥጥር ስር ከወደቀ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ የዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ሰላምም ከድጡ ወደ ማጡ ሁነዋል፤ ሰሙኑን ጎማ የምትባል የግዛትዋ ከተማ ኤም ሃያ ሶስት ሚባሉ አማፅያን ተቆጣጥረዋታል፡፡የሶማልያ ነገር ሙሉ በሙሉ አልየለትም፡፡ ሶርያ በከባድ ጦርነት እየተናጠች ትገኛለች፡፡ የሰሙኑን የእስራኤልና ፍልስጤም አታካራ የአንድ መቶ አርባ ሰዎች ነፍስ መቅጠፉን ይነገራል፡፡የአፍጋኒስታን፣ ኢራቅና ሊብያ ሰላም አልፎ አልፎ ጉም እየጋረደው ይገኛል፡፡
በስልጣን ላይ ያለው በምርጫም ሆነ በጡጫ እጁ ላይ የገባውን ስልጣን ላለማጣት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡የስልጣን ጥማት ወይም አዙሪት የላባቸው ተቃዋሚዎችም ከተቻለ በምርጫ አሳብበው፣ ከልሆነ በህዝባዊ ዓመፅ፣ ይህን ካልተሳካ ደግሞ በጠብመንጃ አፈሙዝ ስልጣን ለመጨበጥ ይፈጨረጨራሉ፡፡የተቃዋሚዎችም ሆነ የባለ ስልጣኖች ግትርነት ወይም በፖለቲኮኞቹ አባባል አክራሪነት ጦስ ግን የሚተርፈው ለህዝቡ ነው፡፡ሁለቱም በግድም በውድም የመሪነት ህልማቸውን እውን ለማድረግ የማያድርጉት ነገር የለም፡፡ የዋሻሉ፣ነጩን በማጥቆር፣ ጥቁሩን በማንጣት የድጋፊዎችን ቀልብ ለመሳብ ይጣጣራሉ፡፡እኔ እሻላሎህ የሚለውን ጉንጭ አልፋ ዲስኩራቸውን በመደጋገም ያደነቁሩናል፡፡ ይህ ለአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ የሰላም ማጣት አንዱ ምክንያት ነው፡፡በዚማሃል ግን ህዝቡ ይሰቃያል፡፡የመልካም አስተዳደር ችግር ይነግሳል፤ሙስና ይስፋፋል፤ድህነትና መሃይምንት የሃገሮቹ መገለጫ የሆናሉ፡፡ይህ ደግሞ ስደትን ያስከትላል፣ለህገወጥ የሰው ዝውውር መስፋፋት በር ይከፍታል፡፡ለዚህም ነው ብዙ ወገኖቻችን እንደ እቃ በኮንቴነሮችን ውስጥ ታሽገው ለመጓዝ እስከ መወሰንና ለአሰቃቂ እልቂት ራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት እያስገደዳቸው የሚገኘው፡፡
ሰላም የዓለም ብርሃን፣የመፈቃቀርና አብሮ የመኖር ሚስጥር ነው፡፡ሰላም ከሌለ ግን ሁሉም ነገር የለም፡፡ ቢኖርም ሙሉ በሙሉ አይታይም፤ይደበዝዛል፣ይጨልማል፡፡ ምዕራባውያን አምባገነኖች በተለይም አሜሪካ ለዓለማችን የሰላም መስፈን እንቅፋት ናቸው፡፡ ሽብርተኝነት የነሱ እከይ ተግባር ውጤት ነው፡፡እነሱ የፈለጉት ሁሉ እያደረጉ(ንፁሃንን መጨፍጨፍና ለዓላዊ ሀገሮችን መውረርም ጭምር)ሌሎች እጅና እግራቸውን አጣጥፈው ቁጭ እንዲሉላቸው ይፈልጋሉ፡፡በአጠቃላይ ይች ዓለምና ህዝቦችዋ በተለይም አፍሪካውያንና ዓረቦች እነሱን ለማገልገል እንደተፈጠሩ አርገው ያስባሉ፡፡ ያስባሉ ብቻም አይደለም በተግባርም እያሳዩን ይገኛሉ፡፡ ዲስኩራቸው ሌላ ተግባራቸው ሌላ ነው፡፡ስለሰላም እየለፈፉ በላዓላዊ ሃገሮች ላይ ጦርነት ያውጃሉ፡፡  
የሚገርመው ነገር ግን በቅንነት፣በመፈቃቀድና በመፈቃቀር የተመሰረተ ግንኙነት በመፍጠር ዓለምን ገነት ማድረግም ይቻላል፡፡ አዎ! ክፉ መስራት ካላቃተን ጥሩ ነገር ማድረግ አያቅተንም፡፡ለሰው ልጅ ከአየር ቀጥሎ ሰላም ያስፈልገዋል፡፡እስኪ ለዓለማችን ሰላም ድርሻችንን እንወጣ፡፡ ሰላም ለመላው ዓለም እንመኝ ለተግባራዊነቱም እንትጋ፡፡
                                  ሰላም!

No comments:

Post a Comment