Wednesday, October 9, 2013

የተስፋየ ገብረአብ ‹‹የስደተኛው ማስታወሻ›› የተባለው መፅሐፍ ህትመት ተቋረጠ







አማራው ከኦሮሞ፣ ኦሮሞው ከኦሮሞ፣ አማራው ከአማራው፣ትግራዋዩ ከአማራው፣ትግራዋዩ ከትግራዋይ፣ ትግራዋዩ ከኦሮሞው እርሰ በርስ ለማፋጀት በሚፅፋቸው መርዝ የተቀቡ መፅሐፎቹ የሚታወቀው ተስፋየ ገብረኣብ የኤርትራ ሰላይ መሆኑን አለማየሁ መሰለ በተባለ ኢትዮጵያዊ ‹‹አክቲቪስት›› መጋለጡን አውራምባ ታይምስ የተባለው ድረ ገፅ ያስታወቀው ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡
ተስፋየ ‹‹የስደተኛው ማስታወሻ›› የሚባል ሌላ አዲስ መፅሐፍ ለማሳተም እፍን ጭንቅ ሲል መሰንበቱን የሚታወቅ ቢሆንም የመፅሐፉ ህትመት መቋረጡን በፌስቡክ ገፁን ገልፀዋል፡፡ተስፋየ በፌስቡክ ገፁ የፃፈውን ማየት ያልቻላችሁ እንደሚከተለው ቃል በቃል አቅርቤላችኋለሁ፡፡

የስደተኛው ማስታወሻን ለማሳተም ከነፃነት አሳታሚ ጋር ውል ፈፅመን መፅሃፉ በህትመት ሂደት ላይ ነበር፡፡ በመካከሉ ግን መፅሃፉ ውስጥ ከተካተቱ ምእራፋት መካከል ምእራፍ 7 ተቆርጦ እንዲወጣ አሳታሚው ጠይቆኝ ነበር። የተጠየቅሁትን ማድረግ አልቻልኩም፡፡ በመሆኑም በኔው ፍላጎት ከአሳታሚው ጋር ያለኝ ውል ተቋርጦአል። ሆኖም መፅሃፉ በዚህ በጥቅምት ወር ለንባብ እንደሚበቃ ቃል የገባሁ በመሆኑ በዛሬው እለት በእዚሁ የፊስቡክ ገፅ ላይ እንደምለጥፈው እገልፃለሁ። መልካም ንባብ።

ነፃነት አሳታሚ ድርጅት ‹‹ምእራፍ 7 ተቆርጦ እንዲወጣ›› ተስፋየን ያዘዘው ምን ዓይነት መርዝ የተቀባ ፅሑፍ ቢፅፍ ነው? የተስፋየ ገብረአብ እንደ ማንኛውም የሻዕብያ ተኩላ ለኢትዮጵያውያን የማይተኛ ቢሆንም ‹‹የደራሲው ማስታወሻ››ን በ2002 ዓ.ም ያሳተመለት የዋሽንግተን ዲሲው ነፃነት አሳታሚ ድርጅት ነበር፡፡አሁን ግን አሳታሚ ድርጅቱ ‹‹ከአሁን በፊት በረጨኸው መርዝ ብዙ ተምረናልና ይብቃህ›› ሳይለው አልቀረም፡፡ደግ አደረጉ!!!


ለካህዳም ሰው ይህም ሲያንሰው ነው!!!

ተስፋየ ገብረአብ፣ ኢትዮጵያ ሁሉም ነገር አድርጋልሃለች፤አሳድጋሃለች፤አስተምራሃለች፤ብቃቱ ባይኖርህም ለትልቅ ስልጣን አብቅታሃለች፤ የአሁኑ የስነፅሑፍ ብቃትህ የተገነባው በኢትዮጵያ ነው፡፡አንተስ ምን አደረክላት? አንተማ ጡቷን ቀረጠፍከው! የበላህበት ወጭቷን እምሽክሽክ አድርገህ ሰባበርከው፡፡በፍቅር ተንከባክባ ላሳደገችህ ሃገር ጥላቻ ልትዘራባት፣እሾኅ አመኬላ ልትተክልባት የሻዕብያ ተላላኪ ሆንክ፡፡ኢትዮጵያዊ ነኝ እያልክ ብዙ ኢትዮጵያውያን አታለልክ፤በጣም ብዙ ዋሸኅ(የናዚው የፕሮፖጋንዳ ሹም ጆሴፍ ጎብልስን የሚስንቅ ግብዳ ውሸት)፤ ስለ አባት ሃገርህ ስለ ኤርትራ ግን ትንፍሽም አላልክ፡፡ኢሳያስ ጌታህ አይደል? አሁን የሻዕብያ(ኢሳያስ) ሰላይነትህ ይፋ ሆኗል፤ እንኳን ደስ ያለህ!
እምዬ ኢትዮጵያ ‹‹ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ›› እያለች ነው፤ ባንተ ክህደት ምክንያት፡፡እምዬ ኢትዮጵያን አመድ አፋሽ አድርገሃታል፡፡
ያንተ ክህደት ደጃዝማች ኃይለ ሠላሴ ጉግሳን ያስታውሰኛል፡፡እሳቸው የራስ ጉግሳ አራአያ ልጅ ሲሆኑ የአባታቸው(ራስ ጉግሳ አራአያ) ሞት ተከትሎ ምስራቅ ትግራይን እንዲያስተዳድሩ ተሸሞው ነበር፡፡ነገር ግን 1927 . እናት ሃገራቸውን ክደው የጣልያን ባንዳ በመሆን የመጀመርያው የኢትዮጵያ የልዑላን ቤተሰብ ናቸው፡፡በሙሶለኒ ‹‹የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት›› ተብሎ በተሸሞው ቪቶርዮ አማንዩኤልም የራስ መዓረግ ተስጥቷቸው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ጣልያን ከኢትዮጵያ ተባርሮ አፄ ኃይለስላሴ ወደ ስልጣናቸው ሲመለሱ ደጃዝማች ኃይለስለሴ ጉግሳ በሃገር ክህደት ተከሰው ታስሯል፡፡

አንተ ግን ተስፋየ ኢትዮጵያዊ አልነበርክም አይደለህምምና ህሊናህ ቢያስርህ እንጂ ማንም አያስርህም፡፡የእጅህን ያስጥህ እንጂ ሌላ ምን እንላለን?እናም ያንተ መፅኀፍ የኢትዮጵያውያን ንብረት በሆነው  በነፃነት አሳታሚ ድርጅት እንዳይታተም መደረጉ በመጠኑም ቢሆን እልኸኛነታችንን፣ ሃገራዊ አንድነታችንና ፍቅራችን ሳያሳይህ አልቀረም፡፡ግን ሲያንስብህ ነው፤ በጣም ሲያንስብህ፡፡የኤርትራውያን ባዶ ኩራት እንደ ባሉን መተንፈስ አለበት፡፡እናንተ እኮ ከአበሾች ብታንሱ እንጂ አትበልጡም፡፡የጣልያናውያን መረማመጃ መሆናችሁ ሊያሳፍራችሁ ሲገባ ከልክ በላይ አሳበጣችሁ፤ እናም አፍሪካውያን አይደለንም  ማለት ዳዳችሁ፡፡የዛሬዋን የአፍሪካ ሲንጋፖር በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብ ለመገንባት ያልፈነቀላችሁት ድንጋይ የለም፡፡ከአሁን በኋላ ግን በቃችሁ ለማለት እንገደዳለን፡፡ያንተ ኢያጎነትም ይብቃ!!!

ለካህዳም ሰው ይህም ሲያንሰው!!!

1 comment:

  1. አሪፍ ነው፣ ነገር ግን ስለ ደጃዝማች ኃይለ ሠላሴ ጉግሳ በጻፍከው አልስማማም፣ 1. የመጀመርያው ባንዳ ለውጭ ሀይል ያደረ ምንሊክ ነው፣ ቀጥሎ ተፈሪ መኮነን ጣልያን ድረስ ሄዶ 2. ደጃዝማች ኃይለ ሠላሴ ጉግሳ ስልጣን አለው ምን ፈልጎ ነው ብለህ መጠየቅ አለብህ፣ የኃይለ ሠላሴ ስርዓት አንገሽግሾን ነበር እና እሳቸውን ለመጣል ሌላም ቢደረግ አያስወቅስም።

    ReplyDelete