የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስተሯ ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ ዩጋንዳ በቅርቡ ያፀደቀቸው ፀረ ግብረ ሰዶማውያን ህግን አምርረውተቃውሞውታል፡፡ዩጋንዳ በቅርቡ ባፀደቀቸው ፀረ ግብረ ሰዶማውያን ህግ በእጅጉ የተከፉ የሚመስሉት ሚኒስተሯ በትዊተር ገፃቸው ዩጋንዳን
በመጠቆም ‹‹ማዳላትና ጥላቻ በእኔዋ ውድ አፍሪካ ቦታ የላቸውም፡፡የአለባበስ ስነ ስርዓት መጠበቅ ወይም ፀረ ግብረ ሰዶማውያን ህግ
ማፅደቅ የመንግስት ተግባር አይደለም›› ሲሉ ፅፈዋል፡፡
በሚኒስተሯ ስሌት መሰረት ግብረ ሰዶም የሚከለክል ህግ ማውጣትም ሆነ የእነርሱ ተግባር መቃወም መብት ሳይሆን እንደ
ጥላቻና ማዳላት ይቆጠራል፡፡በመሆኑም የእርሳቸው አፍሪካ ግብረ ሰዶማውያን እንዳሻቸው የሚፈንጩባት ህግ አልባ አህጉር መሆን አለባት፡፡የእርሳቸው
አፍሪካ የአዲስ አበባ ጎደና ተዳዳሪዎችን ሳይቀር ህፃናት ልጆችን አስገድደውም ይሁን በገንዘብ አታልለው እየደፈሩ ያሉት ግብረ ሰዶማውያንን
ሃይ ማለት የለባትም፡፡በዚሁ አቋማቸውም ነው የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስተር ሆነው ህፃናትና ወጣቶችን ሊታደጉዋቸው የሚችሉት፡፡
ይህንኑ ፅሑፋቸውን ተከትሎ ከተከታዮቻቸው ድጋፍና ተቃውሞ የጎረፈባቸው ሚኒስተሯ ከአንድ ቀን በኋላ የትዊተር አካውንታቸው
‹‹በሃከሮች›› እንደተሰረቀባቸውና በስማቸው የተለጠፈው የዩጋንዳ ህግን የሚቃወም ፅሑፉም የክብርት ሚኒስተሯ አለመሆኑን አስተባብሏል፡፡አያይዘውም
ችግሩን ለማስተካከል በጥረት ላይ መሆናቸውና ለጊዜው በአካውንታቸው የሚለቀቁ ፅሑፎች አፅንኦት ሊሰጣቸው እንደማይገባ አውታውቀው
ነበር፡፡አሁን ግን የትዊተር አካውንታቸው ሙሉ በሙሉ ተዘገቷል፡፡
በትዊተር ገፃቸው ያሰፈሩት ፅሑፍ ብዙ ያላሰቡበትና የዩጋንዳን ተግባር በስሜት ተሞልተው የገሰፁበት በመሆኑ ሳይፀፅታቸው
አልቀረም፡፡እሳቸው የሰጡት አስተያየት ግን በኢትዮጵያውያን ህግና ወግ ተቀባይነት የሌለውና በእርሳቸው ደረጃ የሚገኝ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ
ይፈፅመዋል ተብሎ የማይታሰብ አፀያፊ ፅሑፍ ነው፡፡በአፍሪካ ስም የአንዲት ላዓላዊት ሃገር ውሳኔ በዚሁ ስሜት መቃወማቸውም ተገቢ
አይመስለኝም፡፡እንዳውም በሌላ ሃገር የተፈፀመ ቢሆን ንሮ ስራቸውን እስከ ማጣት ያደርሳቸው ነበር፡፡
ባለፈው ህዳር በድረ ገፆች የበለፀገው አሜሪካዊ በለሃብት የህዝብ ግንኙነት ስራስክያጅ ሆና ስትሰራ የነበረችው ጀስቲንሳኮ የተባለች አሜሪካዊት በትዊተር ገፅዋ ‹‹ወደ አፍሪካ እየሄድኩኝ ነው፡፡ኤድስ እንደማይዘኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ስቀልድ ነው፤እኔ
ነጭ ነኝ›› ብላ በማሾፏ ከስራዋ ተባርራለች፡፡
የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 629ና 630 ግብረ ሰደማዊነትን ያወግዛሉ፡፡ ሰፈፅም የተገኘ ማንኛው ሰውም(ወንድም
ይሁን ሴት) ከአንድ እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል፡፡ኢትዮጵያው ግብረ ሰደማዊነትን አምርረው የሚጠሉ ህዝቦች የሚኖሩባት
ግምባር ቀደምት ሃገር ነች፡፡በባዕድ ሃገር ከሚመለሱ ዲያስፖራዎችና የውጭ ዜጎች በስተቀር በኢትዮጵያ ባህልና ወግ መሰረት ግብረ
ሰዶም የሰው ልጅ የመጨረሻውን ዝቅጠት የሚያሳይ ወራዳ ተግባር ነው፡፡
ተቀመጭነቱ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የሆነው ‹‹ፓው ግሎባል አቲቱድ›› የተባለ ተቋም 97 % ኢትዮጵያን ግብረ ሰደማዊነትንእንደሚፀየፉ በጥናቴን አረጋግጫለሁ ይላል፡፡ሆኖም ግን ‹‹የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች ነን›› ባዮቹ ምዕራባውያን የህንኑ የኢትዮጵያውያን
አቋም በኋ ላ ቀርነት የተሸበበ ወግ አጥባቂነት ነው ሲሉ ይኮንኑታል፡፡በእነርሱ
እምነት መሰረት ምዕርባውያን የሚያደርጉት ሁሉ ከጭዋነትና ዘመናዊነት የሚቆጠር ሲሆን ኤዥያውያንና አፍሪካውያን የሚቃወሙት ከሆነ
ደግሞ ከኋላ ቀርነት ጋር ያያይዙታል፡፡
በእኛ ሃገር የሰው ልጅ ይቅርና እንስሳትም ወንድና ሴት ለይተው ያውቃሉ፡፡ሁሉንም እንስሳት ሴትና ወንድ እንጂ ሴትና
ሴት፣ወንድና ወንድ ወሲብ ሲፈፅሙ ታይቶም ተሰምቶም ኣይታወቅም፡፡ታድያ ማሰብ የሚችል ውስብስብ አእምሮ የታደለው የሰው ልጅ ከእንስሳት
እንኳን ለምን አይማርም?ወይስ እንስሳትም ኋላ ቀር ስለሆኑ ይሆን ግብረ ሰዶም ሲፈፅሙ የማይታየው? ለምንስ እንስሳት ግብረ ሰዶም
ሆኖው አይፈጠሩም? ምዕራባውያን ያልተበረዘ ባህልና ቋንቋ እንደ እሾህ ይወጋቸዋል፤ለዛም ነው የራሳቸው ባህል አበላሽተው የኛንም
ለማበላሸት በየዓመቱ በሚልዮኖች የሚቆጠር ዶላር በመመደብ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት፡፡
እኔን በጣም የሚያስቀኝ ደግሞ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች ነን ማለታቸውን ነው፡፡ ከዲሞክራስያዊ ምርሖች
ሁሉ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ‹‹ብዙሐን ይመውኡ›› ወይም ብዙሐን ይመራሉ አናሳዎች ይከበራሉ የሚለውን ነው፡፡ያእብላጫ ድምፅ
ገዢ ህግ ሆኖ ይወጣል፤ ያአናሳዎቹ መብትም ይከበራል፡፡ከላይ በተጠቀሰው የጥናት ውጤት መሰረትም 97 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን
ግብረ ሰዶም የሚያወግዙ በመሆናቸው የእንርሱ ድምፅ ገዢ ህግ መሆን አለበት፡፡ምዕራባውያኖቹ ግን የባህል ወረራ ዘመቻቸውን እውን
ለማድረግ ሲሉ ህዝቡም መንግስቱም በጭፍን በማብጠልጠል ላይ ይገኛሉ፡፡
በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ የሃገራችን የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስተር 97 ከመቶ ኢትዮጵያውያንን በማይወክሉና
ሽንጣቸው ገትረው ለግብረ ሰደማውያን በሚከራከሩ እንደነ ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ ያሉ አስመሳዮች መመራቱን ነው፡፡ወይዘሮ ዘነቡ በዚህ
አካሂዳቸው ይቅር ለሃገራችን ሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጥብቅና ሊቆሙ ለራሳቸውም ክብር ያላቸው አይመስሉም፡፡ስለወጣቶች የሚጨነቁ መሆናቸውን
ለማሳየት የመኮሩትም በሊቨርፑልና በአርሴናል መካከል ለሚካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ ማናቸውን ያሸንፋሉ እያሉ በመብሰልሰል ነው፡፡




No comments:
Post a Comment