ከአብርሃ
ደስታ ጋር በአንድ ነገር እንለያያለን፡፡እርሱ ታሪክ በማፍረስ ታሪክ መስራት ይፈልጋል፤እኔ ግን በተሰራው ታሪክ ላይ ሌላ ተጨማሪ
ታሪክ መስራት እንጂ የነበረውን እንዲፈርስ አልፈቅድም፡፡ህወሓት ደርግን የመሰለ ጭራቅ በማስወገድ ታሪክ ሰርቷል፡፡አብርሃ ያ
ታሪክ አፍርሶ ለመንገስት በመፍጨርጨር ላይ ይገኛል፡፡
የህወሓት
ተልእኮ ኤርትራን ማስገንጠል ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብን ከደርግ መንጋጋ መንጭቆ ማስወጣት ነበር፡፡በምትኩም ሁሉም ብሔር ብሔረ
ሰቦችና ህዝቦች በእኩልነትና በፍቅር የሚኖርባት ዴሞክራስያዊት ሃገር መገንባት፡፡የህም የሁሉም ገዢ የሆነው ህገ መንግስት
አዘጋጅቶ እንዲፀድቅ በማድረግ እውን አድርጎታል፡፡የኤርትራ መገንጠል የአፈፃፀም ችግር ነበረው ካላልን በስተቀር ህገ መንግሰቱ ተግባራዊ የሆነበት ከስተት
ነበር፡፡
ለምን ይሆን ታድያ አብርሃ ድስታና ‹‹ለኢትዮጵያ አንድነት›› ቆመናል እያሉ
ወናፈ የሚነፉ ተቃዋሚዎች ‹‹የህወሓት ተልእኮ ኤርትራን ማስገንጠል ነበር›› የሚሉት? ኧረ ከቶ ለምን ይሆን ህገመንግስቱ
ተግባራዊ በመሆኑም ተግባራዊ ሳይሆን በመቅረቱም አምርረው የሚቃወሙት?በደርግ ዘመን ሰብአዊና ዴሞክራስያዊ መሰሎችን መጠየቅ
ለሞት ይዳርግ መኖሩን ስለረሱት ነው? ደርግ የሚያደርገው ማንኛውም ነገር(በቀይሽብር ትውልድ መፍጀትም ምጭምር) መደገፍ እንጂ
መቃወም የማይታሰብ መኖሮን ረስተውት ነው? የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንደሚከተለው አስፍሬዋለሁና አብረን እንየው፡፡
እኛ
ኢትዮጵያውያን ታሪክ ከመስራት ይልቅ ታሪክ ማፍረስ በእጅጉ ይቀለናል፡፡ከሁለት ሶስት ሺህ ዓመታት በፊት ሃገራችን የዓለም ስልጣኔ ቁንጮ ከሚባሉት አንዷ ነበረች፡፡የያኔዎቹ ኢትዮጵያውያን ታሪክ
ሰሪዎች ነበሩ፡፡ምንጊዜም የማይደበዝዙ ዓሻራዎቻቸውም እንሆ ዛሬም በሃገራችን ቆሞው ይገኛሉ፡፡እነዝያ ከአንድ ቋጥኝ ተፈልፍለው የተሰሩ
የአክሱም ሃወልቶችና ላሊበላን ጨምሮ በየአከባቢው የሚገኙ ውቅር አብያተ ክርስትያናት የእዚሁ ተምሳሌት ናቸው፡፡
እነዚህ
ታሪካዊ ቅርሶች ዛሬ ደግመን መስራት አንችልም፤ እንዴት እንደተሰሩም የምናውቀው ነገር የለም፡፡ምክንያቱም ከዛኛው ዘመን ጀመሮ
የተሰሩትን ስናፈርስ እንጂ ስንገነባ አልኖርምና ነው፡፡በተሰሩት ላይ ተጨማሪ መስራት ሳይሆን የተሰሩትን ስናፈርስ ኖረናል፡፡ውጤቱም
ከዓለም የስልጣኔ ቁንጮነት በዓለም የድህነትና የኋላ ቀርነት እንዲሁም የርሃብ ተምሳሌት ወደ መሆን ተሸጋግረናል፡፡ልክ እንደካሮት
ቁልቁል ወርደናል፤ምንም ዓይነት የመሬት ስህበት ሳያደናቅፈን ዱብ ነበር ያልነው፡፡ፈረንጆቹ ‹‹free fall›› የሚሉት
አወዳደቅ ነበር የወደቅነው፡፡
በጣም
የቆየውን ይቆይልንና ከደርግ ዘመን እንጀምር፡፡ደርግ ሃገርና ህዝቦችዋን በማፍረስ ገናና ከሆኑ መንግስታት ግንበር ቀደም
ነበር፡፡የአንድ ትውልድ ወጣት በቀይሽብር አማካኝነት አርደዋል፤የተቀሩትንም በየጦርነቱ እየማገደ አስገድለዋል፡፡አፄ ሃይለስላሴ
የጀመሩት የወሎና የትግራይ ረሃብም እጅግ በጣም በከፋ መልኩ አባብሶት ሃገራችን በ1977 ዓ.ም ትግራይ ውስጥ በተከሰተው ረሃብ
በዓለም ደረጃ እንድትታወቅ አድርገዋል፡፡ያድርቅ በሚልዬን የሚቆጠር የትግራይ ህዝብ በረሃብ ፈጅተዋል፡፡
ደርግ
የ77 ዓ.ም ረሃብ እየተባለ ለሚጠራው የትግራይ ህዝብ እልቂት የእህል እርዳት በማቅረብ ከመከላከል ይልቅ እጅጉ እንዲባባስ
ነበር ያደረገው፡፡በሰፈራ ስም ህዝቡን በሃይል እያፈሰ ምንም ዓይነት መሰረተ ልማት ወዳልነበረበት ጫካ ስለወረወረው በወባና ሌሎች
ተላላፊ በሽታዎች እንደ ቅጠል እንዲረግፍ አድርጎታል፡፡እናትና ልጅ፣ ባልና ሚስት ወዘተ በጉልበት በመለያየት የህዝቡ መሰረታዊ
ንሮ አናግቶታል፡፡በአጠቃላይ ‹‹ዓሳን ለመያዝ ባህሩን ማድረቅ›› በሚል ስሌት የትግራይ ህዝብን አውድሞ የንግስና ዘመኑን
ለማራዘም ያልፈፀመው ጭካኔ አልነበረም፡፡
ህወሓት
የትግራይ ህዝብን ከዚሁ ነፍብሰ በላ አውሬ መንጋጋ
ፈልቅቆ ለማውጣት ነበር የታገለው፡፡አድርጎታል ደግሞ፡፡መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከአውሬው በማዳንም የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑን
አስመስክሯል፡፡ያኔ ደርግን በሚያውቀው ቋንቋ ከማናገር ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረም፡፡ከመተኮስ ውጪ ምንም አያውቅም ነበር፤
ተቃወምከው አልተቃወምከው በጠብ መንጃ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ማግባብያ አልነበረውም፡፡
ህወሓት
በሚገባው ቋንቋ አነጋግሮታል፡፡የትግራይ ህዝብ ደርግ በመደምሰሱ ነው እንደ ህዝብ ቀጣይነቱን ያረጋገጠው፡፡ከላዩ ላይ
እየተንከባለለ ደፍጥጦ ሊያጠፋው የነበረው ትልቅ ቋጥኝ ሲወርድለት እፎፎፎይ! ነብረ ያለው፡፡ዛሬም፣ ነገም ለወደፊቱም ህወሓት
ደርግን የመሰለ ጭራቅ በመደምሰሱ ሲሞገስ ይኖራል፡፡ከላይ እንደገለፀኩት ደርግ ከጦርነት ውጪ ሌላ የማያውቅ ዲዳ ነበር፡፡ኢድዩ፣መኢሶን፣ኢህአፓ፣ኦነግ
ወዘተ ሊግባቡት አልቻሉም፡፡የልቡ ህመም ያወቀለት ብቸኛው ህዝባዊ ድርጅት ህወሓት ነበር፡፡
ለነ
አብርሃ ደስታና ሸሪኮቹ ህወሓት የሰራው ታሪክ እንደ እግር እሳት እየለበለበ አላስቆም አላስቀምጥ ስላላቸው ካላፈራረሱት በስተቀር
መኖር አይችሉም፡፡ያ የህወሓት ታሪክ በማፍረስ ካለንበት አዘቅት መቀመቅ በማውረድ ታሪክ መስራት ይዳዳቸዋል፡፡ያቺ ‹‹አንድ ቋንቋ፣አንድ
ሃይማኖት፣አንድ ዓይነት ባህል፣አንድ ብየሔር …››ያላት አንዲት ኢትዮጵያን ተግባራዊ ማድረግ ነው የእነርሱ ተልእኮ፡፡ይህ
እንዲሳካም መቐለ በመቀሌ፣ አዳማ በናዝሬት፣ብሾፍቱ በደብረዘይት፣ ሃሮማያ በአላማያ፣ ሃዋሳ በአዋሳ ወዘተ መጠራት ይኖርባቸዋል፡፡ለምን
ቢባል ‹‹በአማርኛ ሲፃፉ›› እንደዛ መሆን ስላለባቸው ነው፡፡
ለእነርሱ
ብዝሃነት የኢትዮጵያ ፀር ነው፡፡ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ብዝሃነትን ማውደም ቁጥር አንድ ተልእኳቸው ነው፡፡ዘውዳዊው ስርዓትና
የድርግ አገዛዝ ብዙ መኩረው አልተሳካላቸውም፤ላይነሱ ወድቋል፡፡‹‹የአንድነት ሃይሎች›› ያ የከሸፈው ውጥን ከግቡ ለማድረስ ነው
ሽር ጉድ እያሉ ያሉት፡፡እነ አብርሃ ደስታ እያንገበገባቸው ያለው የዛሬው ህወሓት እየፈፀመው ያለው የአስተዳደር ብልግና ሳይሆን
‹‹የአንድነት›› ውጥናቸው ስላኮላሸባቸው ብቻ ነው፡፡ብሔር ብሔረ ሰቦችና ህዝቦች ሲባል በርረው መጥፋት ይዳዳቸዋል፡፡ፕሮፌሰርመስፍን እንዳሉት ቃሉ ሲጠራ ያቅለሸልሻቿል፡፡
‹‹የአንድነት
ሃይሎች›› ተልእኮ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረ ሰቦችን በማጥፋት በአንዲት ብሔር፣በአንዲት ሃይማኖት፣በአንዲት ቋንቋና ባህል የምትታወቅ
ሃገር መገንባት ነው፡፡ይህ ግን የነበረውን ማፍረስ እንጂ መገንባት አይደለም፡፡ሊሳካም አይችልም፡፡በዚነዚህ ምክንያቶች ነው ‹‹የህወሓት ተልእኮ ኤርትራን ማስገንጠል ነበር›› እያሉ መጮህ የሚያምራቸው፡፡ለዛም ነው የኤርትራ
ህዝብ ማን ነው ሳይሆን ‹‹ኤርትራ የማን ነች›› እያሉ እንዲጠይቁ የሚያስገድዳቸው፡፡የዓሰብ ህዝብ ማን ነው ምንስ ይፈልጋል ሳይሆን
‹‹ዓሰብ የማን ናት›› ነው የእነርሱ ጥያቄ፡፡ስለ ጋራ ሸንተረሩን እንጂ ስለህዝብ አይጨነቁም፡፡
በእነርሱ ስሌት ህዝብ ብዝሃነት ነው፤ ብዝሃነት ደግሞ የኢትዮጵያ እንድነት ፀር፡፡
የትግራይ ህዝብ ማንኛውም በዓለም አለ የሚባለው ክፉና ደጉን ሁሉ የቀመሰ፣ እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ የመጣ ህዝብ ነው፡፡በመሆኑም ማን በሾሉ ጥርሶቹን እየቀረጣጠፈው ሳለ የአዞ እንባ እንደሚያነባለት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ማን እንደሚደማለትና ማን እንደሚያደማው፣ ማን እንደሚያቆስለውና ማን እንደሚቆስልለት፣ማን እንደሚገድለውና ማን እንደሚሰዋለት አብጠርጥሮ ለመለየት የሚያዳግተው የለም፡፡በእነማን ላይ ቆፎው እንደ ተነካበት ንብ በንድነት ተነስቶ እንደሚረባረብ ነጮችም ጥቁሮችም ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡የትግራይ ህዝብ ሌሎችን አይተነኩስም፤ ከተነካ ግን ቅጣቱ መራራ ነው፡፡
በእነርሱ ስሌት ህዝብ ብዝሃነት ነው፤ ብዝሃነት ደግሞ የኢትዮጵያ እንድነት ፀር፡፡
የትግራይ ህዝብ ማንኛውም በዓለም አለ የሚባለው ክፉና ደጉን ሁሉ የቀመሰ፣ እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ የመጣ ህዝብ ነው፡፡በመሆኑም ማን በሾሉ ጥርሶቹን እየቀረጣጠፈው ሳለ የአዞ እንባ እንደሚያነባለት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ማን እንደሚደማለትና ማን እንደሚያደማው፣ ማን እንደሚያቆስለውና ማን እንደሚቆስልለት፣ማን እንደሚገድለውና ማን እንደሚሰዋለት አብጠርጥሮ ለመለየት የሚያዳግተው የለም፡፡በእነማን ላይ ቆፎው እንደ ተነካበት ንብ በንድነት ተነስቶ እንደሚረባረብ ነጮችም ጥቁሮችም ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡የትግራይ ህዝብ ሌሎችን አይተነኩስም፤ ከተነካ ግን ቅጣቱ መራራ ነው፡፡
እነ
አብርሃ ግን ይህን አያውቁም፡፡ለዛም እንደ ቀበሮ የበግ ለምድ ለብሰው ከበጎች መሃል በመሰግሰግ ግዳያቸውን ለመጣል
የሚፍጨረጨሩት፡፡ህዝባችን ግን በግና ቀበሮ ቀርቶ ሌላም ለይቶ የማወቅ ጥበብ የተካነ ነው፡፡እናም ለማያውቁትም በሰላው ጥበቡ
እንደሚያሳያቸው ቅንጣት ታህልም አልጠራጠርም፡፡

No comments:
Post a Comment