Thursday, February 7, 2013

ዓለማችን ቆሽሻለች: መጥረግያና መወልወያ ይዘን እናፅዳት







ዓለማችን ከልክ በላይ ቆሽሻለች ማለት ብቻም ሳይሆን የቆሻሻ ክምር ሆናለች ቢባል ከእውነት ያራቀ አደለም፡፡በየቤቱ፣በየአከባቢው፣በየሃገሩና አህጉሩ እነዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቆለለው የቆሻሻ መዓት ዓለምን ወደ ገሃንምነት እየቀየራት ነው፡ቆሻሻ በቆሻሻ ላይ እየተደራረበ ዓለምን በመርዛማ ንጥረ ነገሮች ተበክላ ሁሉም ነገር እየነተበና እየሻገተ ይገኛል፡፡ያልተበከለ ነገር ማግኘት ቅዠት እየሆነ ነው፡፡ንፁህ አየር፣ንፁህ ውሃ፣ንፁህ ምግብ ከሁሉም በላይ ደግሞ ንፁህ አስተሳሰብ፣ ንፁህ ህሊናና ቅን አስተሳሰብ እንደ ሞኝነት ይቆጠራል፡፡


የቆሸሸ ነገር ለማፅዳት ቆሻሻ መሆን የግድ ነው ያለው ማን ነው?መንግስት ቆሸሸዋልና ፀረ መንግስት የሆነ አቋም ያለቸው ተቃዋሚዎችም መቆሸሽ አለባቸው እንዴ? እሳትን በእሳት ፈጥፋት እንዴት ይቻላል?እንዴት ነው አሸባሪዎችን በአሸባሪዎች ማስወገድ የሚቻለው?ዓየነ ደረቅ ውሸታም፣አምባገንን፣ ዘረኛ፣ሙሰኛና ጨቋኝ መንግስት ልክ በእርሱ አምሳያ፣ አስተሳሰብና ተግባር የተቃኘ እንደውም በባሰ ሌላ ወሮበላ ለመተካት የህልም ውግያ ማወጅ ፋይዳው ምንድ ነው? የሰው ሂይወትና ንብረት በማውደም ድህነትና ኋላቀርነትን ከማባባስ ወደፊት ፈቀቅ አያደርገንም፡፡በዚህ አካሄድ የትም መድረስ አንችልም…ታሪክ ምስክሬ ነው፡፡ያረጀ ያፈጀውን ነገር በሌላ ዓዲስ ነገር የመተካት ዓላማ ካለን መጀመርያ ራሳችንን ማሳደስ አለብን፡፡ አስተሳሰባችንን ማፅዳት የግድ ይለናል፡፡ግድያን በግድያ ለማስቆም መውተርተር የመገዳደል ሱሰኞች ያደርገናል እንጂ የትም ደያደርሰንም፡፡

በቆሸሸች ሃገር፣ በቆሸሸች ዓለም መኖር ስልችቶናል፣አቅለሽልሾናል፣ እጅ እጅ ብሎናል አይደል? ታድያ እንዚህ ነገሮች አጥፍቶ ለማጥፋት የሚደረጉ የቆሻሻ አስተሳሰብ ወጤቶች ሰለሆኑ በመጥረግያና መወልወያ ድራሻቸውን ማጥፋት አለብን፡፡ ጊዜ ሳናጠፋ አሁንኑ እንጀምር፡፡ እናም መጥረግያ መወልወያ! መጥረግያ መወልወያ! መጥረግያ መወልወያ! እያልን በየቤቱ፣በየስፍራው፣በየመስራቤቱ፣በየሃገሩ በአጠቃላይ ቆሻሻ ባለበት ስፍራ ሁሉ እየዞርን እናፅዳ፡፡ቆሻሻው እኛን ከማፅዳቱ በፊት!ቆሻሻው እኛን ከማቆሸሹ በፊት እንቅደመው፡፡ቆሻሻን ቆሻሻ!በለን በመለየት ሃገራችንን ለማፅዳት በጋራ ካልዘመትን በቀር መፍተሔ አናገኝም፡፡የቆሸሸ ማንነታችን በቆሻሻ ክምር ላይ እያንከባለልን ‹ሻወርን› ማሰብ የአስተሳሰብ ዝቅጠት ነው፡፡

ካሁለት ዓመታት በፊት የዓረብ ሃገሮችን ሲያምስ የነበረው የሰላማዊ ሰልፎች ደግግሞች ‹‹የዓረቦች ትንሳኤ›› የሚል የሽፋን ስም ቢሰጠውም እስካሁን ድረስ ግን የታለመው መፍትሔ አላስገኘም፡፡በእርግጥ ቆሽሸዋል፣ አርጅቷ፣ አምባገነኖች ናቸው ወዘተ የተባሉት ግለሰቦች ለእስርና ለግፋዊ ግድያ ዳርጓል፡፡ሰላማዊ ሰልፎቹ ግን በሰላም ሳይሆን በጦርነት፣ውንብድናና ድህነትን ነው የተተኩት፡፡ግብፅ አሁንም በዜጎቿ ደም እየታጠበች ትገኛልች፡፡ሶርያ መቋረጫ በሌለው ጦርነት እየታመሰችና ወደ ማትወጣበት መድረሻው የማይታወቅ ግሃንማዊ ጉድጓድ በስጠም ላይ ነች፡፡የቀሩትም በእስላማዊ መንግስታት ተተክቷል እየተኩም ነው፡፡

 እናም እነዚያ ከኩረጃ በስተቀር ምንም የማያውቁ ድያስፖራ አክራሪዎች ያን የዓረቦች ብጥብጥ መንትፈው ወደ ሃገራቸን ለማስገባት ‹‹በቃ!›› የሚሉ ባዱ ጭሆቶች በየድረ ገፆችና እንደ ፌስቡክ ባሉ የማህበረሰብ መገናኛ ዘዴዎች(social networks)ማስተጋባት ጀመሩ፡፡በቆሸሸ አፋቸውና አስተሳሰባቸው የነተበ ዘረኛ መርዝ መርጨት ስራየ ብለው ተያያዙት፡፡ቢሄሮች በቢሄሮች ላይእንዲነሱ ለፈፉ፤ እኛም ባናዳምጣቸውም ታዘብናቸው፡፡በቆሻሻ አስተሳሰባቸውና አመለካከታቸውና አልተደነቅንም ከነቆሻሻ ጭሆታቹ ገደል መግባት ትችላላቹህ አልናቸው፡፡እናም ‹‹በቃው›› በዚሁ አበቃ፡፡

የበቃው ዘመቻ መክሸፉ የተገነዘቡት በጥላቻ ታውረው መጮህ የለመዱ ቆሻሻ ዲያስፖራዎች ሱሳቸውን ለማርካት ‹‹የበቃ›› አርበኞቻችን ይፈቱ በማለት የተለመደው የማደንቆር ዳንኪራቸውን ቀጠሉበት፡፡ አሁንም ሰሚ እንጂ የሚያዳምጥ ጀሮና የሚመለከት ዓይን መሳብ አልቻሉም፡፡ነገር ግን በመስማትና ማዳመጥ ያለው ልዩነት መለየት ስለተሳናቸው አሁንም‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› በሚል ሌላ የጭሆት መዓት መመርቀን ቀጠሉ፡፡ ‹‹ሃገር የጋራ ሃይማኖት/እምነት ግን የግል ነው፡፡›› እየተባለ ባለበት ዘመን‹‹አንዲት ሃገር በአንዲት ሃይማኖት!›› የሚል መፈክር አንግቦ ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› እያሉ ማደንቆር ስካር ነው ወይስ ዕብደት? አፍን ዋሻ አስመስሎ የኔ እምነት ከናንተ ይበልጣል፤ በይበልጥም የግድ መከተል አለባችሁ፤ ካልሆነ ግን አንገታቹህ ለገጀራ ስጋቹህም ለአሞራ ይዳረጋል እያሉ ማስፈራራት ጤንነት ሳይሆን የለየለት ዕብደት ነው፡፡

ታድያ ዕብደትን ዕብደት ይወልዷልና የህ የሙጃህዲኖች የቁም ቅዠት ዓለማችን በአራቱም አቅጣጫዎች ሰላሟን እየበጠበጠና እያሸበራት ይገኛል፡፡እነዚያ በምዕራባውያን ሃገሮች የሚገኙ ጅቦችም የስልጣንና የፍቅረ ንዋይ ጥማቸውን ለመቁረጥ ሲሉ ብቻ የጨሆው ሁሉ እየተከተሉ እንደ ውሻ ማላዘናቸውን ቀጥለውበታል፡፡እንዚህ ሰዎች ትናንት ሃገራችን ሲያደሙና የነበረንን ሁሉ ሲያወድሙ የነበሩ ከሃዲዎች በቆሸሸው ማንነታቸው ሌሎችን ከሃዲዎች ብለው ቢፈርጁ አይደንቀኝም፡፡ለነሱ ከነሱ ወድያ አስተዋይ፣ታማኝ፣ ጀግና ታጋይ፣ አርበኛ፣ ለሃገሩና ወገኑ ተቆርቋሪ የለም፡፡በጣም የሚያሳዝነው ግን የነሱ ሳይሆን የነዚያ በጀግኖች ወላጆቻችን፣ወንድሞችና እህቶችን ደምና ሬሳ እየተረማመዱ አሁን ባሉበት ከደረሱ በኃላ የማይረቡ ቆሻሾች መሆናቸውን ነው፡፡እናም ቆሻሻ ቆሻሻን አየሳበ ውዷ ሃገራችን የቆሻሾች መጫወቻ ሁና እንድትዘልቅ በዚህም በዚያም የዲያብሎሶች ጭሆት እያስተጋባ ነው፡፡

ህግን ጥሶ ‹‹ህግ የከበር›› የሚል ዲስኩር ማሰማት ብለጠት ነው ወይስ የአስተሳሰብ ዘቅጠት?ህግን አፍርሶ ምን ዓይነት ህግ ለማቋቋም ነው ይህን ሁሉ የገድል ማሚቶ የሚያስተጋባው? ከአሁን በፊት ስህተት ስለተሰራ እኔም በበኩሌ እንዚያ ስህተቶች በማባባስ ሽግሮችን ለማስወገድ ተነስቻሎሁና ‹‹ድሚፄን ስሙ፣ መንገዴንም ተከተሉ፣ጳጳሱም፣ሸኩም፣ንጉሱም እኔ ነኝ እናም ካለኔ በስተቀር ዓለምና መንግሰተ ስማያትና አትወርሱም›› እያሉ ማስረራራትና የፍጥጫ ስብከት መስበክ ምን የሚሉት እንዝህላልነት ነው?ዓይንህን ጨፍን ልሸውድህ!

በህክምናው ሳይንስና በሳይኮሎጂ ሶስተዮሽ የጨለምተኛ ብህርያት(Dark Triads)የሚባል ሐረግ አለ፡፡ ሶስት ተማሳሳይ የሆኑ የስብእና ችግሮች ያጠቃለለ ሲሆን የዚህ ዓይነት ችግር ያለው ሰው የስነ አእምሮና የስነ ልቦና ህክምና ያስፈልጓል፡፡‹‹ከራስ በላይ ንፋስ›› ለንደዚህ ዓይነት ሰዎች የተመሰል ሳይሆን አይቀርም፡፡እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡
1.              ናርሲሲዝም(Narcissism)፡ ራስን እንደ ተራራ አግዝፎ መመልከት፣ ከኔ ውጪ ሌላ ታማኝ አስተዳዳሪ፣መሪ፣አርበኛ የለም ብሎ መደምደም፣ ከመጠን በላይ ራሰ ወዳድነት፣ ደካማ አሳፋሪ የተጨማለቀ ማንነትን ተወዳዳሪ እንደ ሌለው አድርጎ ማሰብ ነው፡፡
2.              ማኬቨሊያኒዝም(Machiavellianism)፡ የፍልስፍናው አባት ጣልያናዊው ኒኮሎ ማኬቨሊ (1469-1527 ዓ.ም እ.አ.አ.)ነው፡፡ በፖሊቲካው ዓለም በጣም የታወቀ ሲሆን ‹‹ማንኛውም ዓላማ የሚለካው በውጤቱ ብቻ ነው›› የሚል ፍልስፍና ያራምድ ነበር፡፡ አካሄዱ የፈለገው ይሁን የግል ፍላጎትህ ለማሳካት ብቻ የቻልከውን ሁሉ ያለርህራሄ እንደትፈፅም የሚመክር አስተሳሰብ ነው፤ መሸወድ፣ማጭበርበር፣መዋሸት፣መስረቅ እንዲሁም መግደል(እናት፣አባት፣እህት ወንድም፣ሚስትና ባል ጭምር!) ይቻላል በዚህ አስተሳሰብ መሰረት፡፡ ፡፡ እናም በስነ አእምሮ እንደ ጨለምተኝነት ይቆጠራል፡፡
3.              ሳይኮፓዚ(Psychopathy):ሶስተኛው ይስነ አእምሮ ችግር ሲሆን ይህም ከመጠን በላይ ራስን መውደድ፣ ለጊዘያዊ እርካታና የግል ደስታ ሌሎችን ማሰቃየት፤እንዲሁም ሲሰቃዩ በመመልከት በደስታ መቦረቅ፣ለሌሎች ቅንጣት ታህል አለመጨነቅ፣ ስለ ሞራል፣ሰብአዊነትና ህግ አክባሪነት ድንታ አለመኖር፣ስህተትን አለማመንና እንዳውም እያወቁ ማጥፋት፣በጠፋው ጥፋትም አለመፀፀት ወዘተ ያጠቃልላል፡፡

እነዚህ  ባህርያቶች በሃገራችን ፖለቲከኞች በተለይም በአክራሪ ድያስፖራዎች የሚደጋገሙ ተግባራት ናቸው፡፡ ሞት የሰው ልጅ ፍፃሜ መሆኑን እያወቁ በሞተ ሰው ይደሰታሉ፣ይጨፍራሉ፣ እነሱ እንደገደሉ የፉከራና ቀረርቶ ዳንኪራ ይረግጣሉ፡፡ሰዎችን በዘር፣በአከባቢና በእምነት በመከፋፈል አንዱን ባልዋለበትና በላሰበው ይከሳሉ ይወነጅላሉ፡፡ለሌላው ደግሞ የማይገባው የአርበኝነት ካባያለብሳሉ፡፡የህ ታድያ ፍርደ ገምድልነት፣ጨለምተኝነት በአጠቃላይ የአስተሳሰብ መቆሸሽ አይደለም? እኛን ደግፍ፣እኛን እንጂ ሌላ እትስማ፣ እኛ ከምንጠላቸው ሰዎች ጋር ብትቀርብ አብረህ ተወቀጣለህ የሚል ፅንፈኛ እምነት ማራመድ የማንነት መቆሸሽ ያመለክታል፡፡

ይህ የሻገተ አስተሳሰብ ለማፅዳት መጥረጊያ መወልወያ ይዞ በሕብረት መዝመት የግድ ይላል፡፡ያለፈውን አልፏል ከዚህ በኋላ ግን ይበቃል ማለት አለብን፡፡ከዘመነ መሳፍንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣብንና በስልሳዎቹና ሰባዎቹ የተጋጋለው እርሰ በርስ የመበላላት በሽታ መታከም አለበት… ላይመለስ፡፡ ያለፈውን ትውልድ ክፉም ይስራ ደግ ጊዜው ሲያልፍ አልፏል፡፡ ደግነቱ አብሮን እንዳለ ሁሉ ግን ክፋቱም እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ሁላችንም የዓመድ ክምር እያደረግን ስለሆን ተረባርበን እና ጥፋው፡፡እናም በጋራ መጥረግያ መወልወያ! መወልወያ መጥረግያ! መጥረግያ መወልወያ! እያልን የቆሸሸውን ለማፅዳት እንዝመት፡፡



No comments:

Post a Comment