አንድ
ለምንድነው ቀይ ቀለም የፍቅር መግለጫ የሆነው? የቀለሞች ስነ አእምሮ(color psychology)ቀይ
ቀለምን ከፍቅር፣ከአደጋ፣ተመልካችን በቀላሉ ከመሳብ ወዘተ ያይዟል፡፡
እኔ ግነ በተፎጥሮየ ደማቅ ቀይ ቀለም አልወድም፡፡ቀይ
በቀይ የለበሱ ሰዎች ስመለከት ጥሩ ስሜት አይሰማኝም… ይሰቀጥጠኛል፡፡የእሳት ቃጠሎ፣አስከፊ አደጋ ደርሶ ደም በደም የሆነ ፍጡር፣
ቀይ ሽብር፣እጅግ አደገኛ የሆነ ነገር ወዘተ ያስታውሰኛል፡፡እኔ ባደግኩበት አከባቢ ቀይ ደሮና ቀይ በግ ዛር ለያዛቸው ሰዎች በጠንቋዮች
ለመድሃኒትነት የሚታዘዙ ናቸው፡፡ ቀይ ጥለት ያለበት ነጠላ፣መቀነት ወይም ቀሚስም እዲሁ የሚለብሱት ዛር(ጂኒ) ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ደብዳቤ
በቀይ እስኪርቢቶ አይፃፍም ይባላል፡፡
ሁለት
ባህላችን አይደለም፤ የምዕራባውያን መጤ ባህል ነው፡፡ባህል
የማንነት መገለጫ ነው፡፡ የክብረ በዓላት አከባበር፣ አለባበስ፣አመጋገብ፣ የሃዘንና ደስታ አግላለፅ የአንድ ማሕበረሰብ የማንነት
መገለጫዎች ናቸው፡፡የራስ ባህል ትቶ በሌሎች መሞዳሞድ ግን ማንነት ከመሽጥ አይተናነስም፡፡ቆይ መከተል ያሉብን ምርጥ ምርጥ ባህሎችን
እየተውን የማይረቡትን ላይ የምናተኩረው ለምንድ ነው? ለምሳሌ ልዩነታችንን ዲሞክራስያዊ በሆን መንገድ መፍታት ትተን እርሰ በርስ እየተናቆርን ለኛ የማይ
ጠቅሙ ነገሮች ላይ ጊዜ ማጥፋቱ አይታየኝም፡፡
ሶስት
ፍቅር እንደ ዓመት መለወጫ በዓመት አንዴ ብቻ የሚከበር
ሳይሆን በየሲኮንዱ መታሰብ ያለበት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ፍቅር በአመክንዮ የሚደረት አያደለም… ከልብ ትርታ ጋር አብሮ ትር ትር ይላል፡፡የልብ
ትርታ ሲያቆ ያቆማል፡፡ ታላቁ መፅሐፍ ቅዱስ‹‹ እምነት፣ተስፋና ፍቅር ለዘላለም ፀንተው ይኖራሉ፤ ከሁሉም ግን ፍቅር ይብልጣል››
ያለው ለዋዘ አይደለም፡፡እናም ለኔ እያንዳንዱ ቀን የፍቅርና የልደት ቀን ነው፡፡
በመጨረሻም ነጮች የሚያደርጉት
ሁሉ በጎ ነው ማለት አያቻልም፡፡ መጥፎ ባህል እንዳለ ሁሉ ጥሩ ባህልም አለ፡፡ ሰለዚህ የሚጠቅመንን ከማይጠቅመን እየለየን ቢሆን ደግ ነው፡፡
የሆነ ሁኖ ግን የፍቅረኞች ቀን ለምታከብሩ ወገኖቼ መልካም የፍቅር ቀን
እመኛለሁ፡፡
No comments:
Post a Comment