Wednesday, February 20, 2013

የኢትዮ ቴሌኮም ቀሽም ማስታወቂያ








ኢትዮ ቴሌኮም አሁንም እንደ ካሮት የቁልቁል እድገቱን ቀጥሎበታል፡፡እንሆ አሁንም ከወዳጅ ዘመዶቻችን ጋር ያለ መቆራረጥና የመስመር መጨናነቅ ሊያገናኘን አልቻለም፡፡ አሁን እማ ጭርሶ ብሶበታል፡፡በመክሲኮ የሚገኘው የደምበኞች የአገልግሎት መስጫ ቢሮው ዘግቶ ቁጭ ብሏል፡፡ይህም የፈረንጆቹ መሪዎቻችን የአመራር ብቃት ማሳያ መሆኑን ነው፤በጣም ያሳዝናል፡፡ኢትዮ ቴሌኮም(የሃራችን ብቸኛው የኮምኒኬሽን ሲስተም ሞነፖል)እንዲህ የሚል ከሆነ ባንኮችና ሌሎች ኮምፒተራይዝድ የሆኑ አግልግሎት ሰጪ ተቋማት ምን ሊሉ ነው?

ደግሞስ ደምበኞች ውድ ጊዜያቸውን ሰውተውና ወጪ አውጥተው ቢሮው ድረስ ከደከሙ በኋላ ‹‹ሲስተም ስለተቋረጠበን ለጊዜው አግልግሎት እየሰጠን ስላልሆነ…፡፡››የሚል መስታወቂያ መለጠፉ ምን ማለት ነው?ችግሩ አንዴ ተፈጠሯል፤ምንም ማድረግ አይቻልም…ከመጠገን ውጪ፡፡ነገር ግን በሌላው ጊዜ በፅሑፍ መልእክት እንደሚያጨናንቀን ሁሉ ችግር ስለመፈጠሩም እንዲሁ በያሉበት ማሳወቅ ነበረበት፡፡

መንግስታችን የቴሌኮምኒኬሽን የጥራትና ተደራሽነት ችግር ፈረንጆች‹‹Domino effect›› ብለው የሚጠሩት እንደ ወረርሽኝ በሽታ ወደ ሌሎች ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቀላሉ እንደሚዛመት አልተረዳም፡፡አዎ! ቴሌ፣መብራት ሃይልና የመንገድ ትራነስፖርት የሃገራችን የደም ስሮች ናቸው፡፡የአንዳቸው መጥፋት ወይም የጥራት መጓደል በሌሎቹ ላይ ተዛመጅ የሆነ ከባድ ጫና አለው፡፡እናም መንግስት በሶስቱም ተቋማት ላይ አፅንኦ ሰጥቶ ሌት ተቀን ሳይል ጠንክሮ መስራት ነበረበት፤አለበትም፡፡የእስካሁን ድረስ የተሰራው ስራ‹‹አበራታች ነው›› እያሉ ሪፖርት ለማሳመር የሚደረገው የቃላት ጨዋታ ስለተነቃበት ቢቆም ይሻላል፡፡የተበላበት ቀሽም አባባል መሆኑን ከተደረሰበት ስንበቷል፡፡

መንግስታችን ሰሙኑን ለሁሉ የሚባል የመብራት፣የውሃና የስልክ ክፍያ በአንድ መስኮት መፈፀም የሚያስችል ‹ሲስተም› ተግባራዊ ማድረጉን አስውቋል፡፡‹ሲስተሙ› በሐሳብ ደረጃ ይበል የሚሰኝ ነው፤ ነገር ግን አሁንም ‹‹የአፈፃፀም ችግሮች›› አሉበት፡፡የህ ‹‹ከ15 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ››የሶስቱም አግልግሎቶች ክፍያ ለማከናወን ያስችላል የተባለለት የአሰራር ስርዓት ከሩብ ሰዓት በነሰ ጊዜ ማስተናገዱን ይቅርና ከሰዓታት እንግልት በኋላም ደምበኞቹን በአግባቡ ሊያስተናግድ አልቻለም፡፡የፈረደባቸው ወገኖቻችን አሁንም አናት በሚበረቅስ ፀሐይ እየተቃጠሉ ከመሰለፍ ሊታደጋቸው አልቻለም፡፡



አረ ወዲህ በሉ ጎበዝ፡፡ምንድነው ነገሩ?የተጀመረው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ላይፈፀም፣የተፈፀመውም የታለመው ዓላማ በአግባቡ ላይከውን ድግምት አለበት እንዴ?


No comments:

Post a Comment