![]() |
| በሳውዲዓረብያ በግፍ የተደበደበ፤የመኪና ጎማ እላዩ ላይ የጫነበት ወጣት |
አረቦች በተለይም ሳውዲ ዓረብያውያን በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈፀሙት ያለው ዘግናኝ ግፍ አህያን
ከመጫንና ፈረስን ከመለጎም በላይ ነው፡፡የሰሙንኑን የአረቦች ተግባር ከላይ ከተጠቀሰው አባባል በላይ ይሰቀጥጣል፡፡ ሰውን የሚያህል
ክቡር ፍጥረት እየደበደቡና እየገደሉ በደስታ መጮህ ከምር ያናድዳል፤ ያስቆጫል፡፡በሌላ መልኩ ግን የሳውዲ ዓረብያውያን ማንነትና
ተግባር ፍንተው አድርጎ ያሳየ ክስተት ነው፡፡
ሳውዲ ዓረብያ የአሸባሪዎች መጠለያና ቀንድ የገንዘብ ምንጭ መሆንዋን ዊኪሊክስ ያሳወቀው ከሶስትዓመታት በፊት ነበር 1፡፡ድሮ በተዘዋዋሪ ነበር ግብረ ሽበራውን የምታከናውነው፤ ዋህቢስቶችን በማስተማር፣በማስታጠቅና በገንዘብ
በመደገፍ ትታወቅ ነበር፡፡አሁን ግን ከመጠለያና ከገንዘብ መንጭነት አልፋ በጠራራ ፀሐይ ንፁሐን ሰዎችን
በመግደልና በመደብደብ ተጠምዳለች፡፡እናም ሽብርተኞችን ከማሰልጠንና ከማስታጠቅ አልፋ በግልፅ ወደ ግብረ ሽበራ ተሰማርታለች፡፡እናም ‹‹ከህግ ውጭ ወደ
ሃገሬ የገቡ የውጭ ዜጎች›› በሚል ሽፋን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ጨምሮ እየጨፈጨፈች ያለችው የግብረ ሽበራው አካል እንጂ ህግን
የማስከበር ጉዳይ አይደለም፡፡
የሳውዲ ዓረብያ ኢሰብኣዊ ጭካኔ ግን በውጭ ዜጎች ብቻ ያነጣጠረ አይደለም2፡፡ዓምና
የወጣው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ ሳውዲ ዓረበያ እስረኞች በሞት ፍርድ በመቅጣት ከዓለም አራተኛ ደረጃ
ይዛለች፡፡እጅግ የሚዘገንነው ደግሞ ዓምና በሞት ከቀጣቻቸው 79 ፍርደኞች ውስጥ 27 የውጭ ዜጎች መሆናቸውን ነው 3፡፡የምትገድላቸውም
በገጀራ አንገታቸውን በመቅላት ሲሆን በሞት ያልተቀጡትም ቢሆን እጃቸው ወይም እግራቸው ይቆራጣል፤ዓይናቸው ይፈሳል ሌላም ሌላም የአካል
ጉዳቶች ይደርስባቸዋል፡፡
አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ዓረብ ሃገሮች ለመድረስ ብዙ ውጣ ውረዶችን ማለፋቸው የግድ
ነው፡፡ አብዛኞቹ ህጋዊ ስደተኞች አይደሉምና ህጋዊ ባልሆኑ ደላሎች ተታልለው በብዙ ሽዎች የሚቆጠር ብር መክፈላቸው፣ የዓፋር በረሃዎች
ማቆራረጣቸው፣ቀይባህርን በጀልባዎች ተሻግረው የዓረብ ምድረ በዳ መድረሳቸው እንደ ትልቅ ድል ቆጥረውት ይሆናል፤ የአሁኑ በመንግስት
ደረጃ ድጋፍ ያለው ኢሰብአዊ ድብደባና ግድያ ሳይደርስባቸው በፊት፡፡
ሳውዲ ዓረብያ ከደረሱ በኋላ ግን ህጋዊ ቢሆኑም ባይሆኑም ይህግ ከለላ አይኖራቸውም፤ ባሮችእንጂ ሰዎች አይደሉም4፡፡ምክንያቱም እዛው ሲደርሱ ፓስፖራታቸውን ይነጠቃሉ፡፡ከዛም እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ርካሽ
የቤት እቃ ይቆጠራሉ፤ዓረቦቹ ጉልበታቸውና ደማቸውን እንደ መዥገር ይመጡባቸዋል፡፡ መብት አልባዎቹ ዓረብ የቤት እመቤቶች የምሬቶቻቸው
ሁሉ መወጣጫ ያደርጉዋቸዋል፡፡እንደ አህያ እየደበደቡ ይገዙዋቸዋል፤ይተፉባቸዋል... በአጠቃላይ እንደ ቡጢ መለማመጃ እቃ ይጠቀሙባቸዋል፡፡
እነዝያ ሁሉ መከራዎች አልፈው ሰርታችሁ ያልፍላችኋል በተባሉበት ሳውዲ ዓረባ ከደረሱ በኋላ
ህልማቸው እንደ ጉም በኖ ሲጠፋ ግን ስሜታቸው ምን ያህል ሊጎዳ እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ ብዙ ሳውዲ ዓረብያውያን አሰሪዎችለሰራተኞቻቸው የአንድ ዓመትና ከዛበላይ ደሞዝ ላለመክፈል ሲሉ በህጋዊ መንገድ ‹‹እስፖንሰር›› በመሆን የተቀበሉዋቸው ሰራተኞችንከቤት በማባረርና ጠፍቷል ብለው ለፖሊሶች በማሳወቅ የልፋታቸው ዋጋ እያሳጡዋቸው ይገኛሉ 5፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ
ብዙ ወገኖቻችን ከመንፈሳዊ፣ቁሳዊና አካላዊ ጉዳት አልፎ መተክያ የሌላት ህይወታቸውን አጥቷል፡፡የሳውዲ ፖለቲሶች ምስኪን ወገኖቻችንንአስረው እየተጋገዙ በመደብደብ ሲያሰቃዩዋቸው ማየት በጣም ይሰቀጥጣል፤አቅመ ቢስነት እንዲሰማህ ያደርጋል6፡፡
ግን ይህን ሁሉ መከራ መቼ ነው የሚያበቃው?ምንጩስ ምንድን ነው መፍትሔውስ?
እውን ዓረቦች ጠላቶቻችን ናቸው? ዓረቦች ኢትዮጵያን በሀይል ለመውረርና በሸሪዓ የምትተዳደር እስላማዊት ሃገር
ለማድረግ ከአምስት ጊዜ በላይ ጦርነት ከፍተውብናል፡፡በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር ሃገራችንን ለማተራመስ፣ እርሰበርሳችን ለማፋጀትና
ብሎም የመከላከል አቅማችን በማሳጣት በቀላሉ ለማሸነፍ ለዘመናት ሲለፉ ንረዋል አሁንም እየለፉ ይገኛሉ፡፡
ይሁን እንጂ ዓረቦች ከከፈቱብን ጦርነቶች ሁሉ የከፋው ከማያላውስ የድህነት ማቅና ኋላ ቀርነት ቅንበሮች እንዳንላቀቅ
የሚያደርጉት ደባ ነው፡፡ምክንያቱም ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ካሸነፍን እንደማይችሉን ያለፈው ታሪክ በማያወላዳ መልኩ ያስረዳቸዋል፡፡
እናም መሪዎቻችን ‹‹ቁጥር አንድ ጠላታችን ድህነት ነው›› ብለው ከወጁ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ሆኖም ግን ይህ
ክፉ ጠላት ለማሸነፍ ብዙ፣ እጅግ በጣም ብዙ ይቀረናል፡፡
ቁጥር አንድ ጠላታችን ድህነት ቢሆንም የድህነታችን ምንጭ ደግሞ ኋላ ቀርነት ነው፡፡የኋላ
ቀርነታችን ምንጮችም የባዕድ ሃይማኖቶች ናቸው፤ ከርስትናና እስልምና በአራተኛውና በሰባተኛው መቶ ክፍለዘመናት ከዓረበ የመጡ የባእድ
እምነቶች ሲሆኑ የተረፍሉን ነገር ቢኖር የስደት አድናቂዎች እንድንሆን ማድረግ ነው፡፡የክርስትናው እምነታችን የሰለሞናዊ ስርወ ንግስነትና
የእስራኤል ናፋቂነት አተረፈልን፡፡በግብፅ እየተሾሙ ሲላኩልን የኖሩ ጳጳሳት እጅና እግራችን አስረው ለድህነት ሰጡን፡፡ዛሬም ድረስ
እዮርሳሌምን እንደ ቅደስት ከተማ ቆጥረን ሃይማኖታዊ ጉዞ እየተባለ በየዓመቱ ብዙ ገንዘብ ፈሰስ እናደርጋለን፡፡የእስልምና እምነታችንም
ሜካን እንደ ቅድስት ከተማ ቆጥረን በየዓመቱ ሂጂራ እየተባለ ብዙ ገንዘብ ባክኖ ይቀራል፤ ሳውዲ ዓረብያም እንደ ጀነት እንድናያት
አድርጎናል፡፡
እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ እንዚህ ከተሞች የተቀደሱም ይሁኑ የተረገሙ ለእኛ ምናችንም አልነበሩም፤
አይደሉምም፡፡ወደ እንዚያ ከተሞች የሚደረጉ ጉዘዎች እንድንፀድቅ ሳይሆን ራሳችንን አሳንሰን ባዕዳንን እንደናመልክ የሚያደርጉ ናቸው፡፡የራሳችን
ባህልና አኗኗር ትተን የዓረቦችን እንድንወርስ እያደረጉን ነው፡፡ከዓረቦች እየወረስን ያለነው ጥበብና ዘመናዊነት ሳይሆን አክራሪነት
ነው፤ የአስተሳሰብ አድማሳችን የሚያሰፉ ጥበቦች ሳይሆን እንደ ቁምጣ የሚያሳጥሩ ናቸው፡፡ከልክ በላይ ፂም ማስረዘምና ሱሪ ማሳጠር
የዘመናዊነት መገለጫ ሳይሆኑ የኋላ ቀርነት ተምሳሌት ናቸው፡፡በመሆኑም ድህነታችን ከምንጩ ለማድረቅ በኋላ ቀርነት ላይም መዝመት
የሚጠበቅብን ይመስለኛል፡፡
ዋቢ ምንጮች
[1]. Zakaria:
The Saudis Are Mad? Tough!:http://content.time.com/time/magazine/article/0,9171,2156259-1,00.
html

No comments:
Post a Comment