Sunday, December 14, 2014

ኢትዮጵያ የበይነ መረብ ነፃነትን በማፈን ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ መሆኗን በጥናት ተረጋገጠ



ምንጭhttp://mgafrica.com/
መቀመጫው አሜሪካ የሆነው ፍሪደም ሃውስ የተባለ ኢ-መንግስታዊ ገባሪ ሰናይ ተቋም ያካሄደው ጥናት እነደጠቆመው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ አፋኝ ስትሆን በዓለም ደሞ የአምስተኛ ደረጃ ተቆናጥጣለች፤ኢራን፣ሶርያ፣ቻይናና ኲባን በመከተል፡፡

ያለበይነ መረብ ነፃነት የፕረሰ ነፃነት አይታሰብም የሚለው ሲፒጀይ በበኩሉ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ቀጥላ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን ለእስርና ለስደት በመዳረግ ከአፍሪካ ቀዳሚውን ይዛ እንደምትገኝ መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡

የመረጃ ድህንነት አጄንሲው ኢንሳ በጣም የተወሳሰቡ የኢንተረነት(በይነ መረብ) መቆጣጠርያ ሶፍተዌሮችን ተጠቅሞ የዜጎች የመረጃ ልውውጥ ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠረና ከፍተኛ ስለያ እያካሄደ ይገኛል፡፡ባለፈው 2006 ዓ.ም የወጣው አዋጅ ፌስቡክና ትዊተርን ጨምሮ ማንኛውም የማሕበረሰበ ግንኙነት መረቦችን እንዲሰልል ሙሉ ስልጣን እንደሰጠው የሚታወ ነው፡፡

በአንፃሩ ደሞ፣ ኢትዮጵያ በበይነ መረብ ሽፋን 2 ከመቶ ብቻ በማስመዝገብ ከዓለምም ሆነ ከአፍሪካ የሚጨረሻው ደረጃ ይዛለች፤አፍሪካ ሜል አንደ ጋርድያን የተባለ ድረገፅ ፍሪደም ሃውስን ጠቅሶ እንደዘገበው፡፡ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኘው የተሌኮም አገልግሎት የመሰረተ ልማት ግንባታውን ለማስፋፋት ቢሞክርም ዘመኑ የሚዋጀውን ስኬት አልተቀዳጀም፡፡

ጋምብያ፣ ሱዳንና ዚምብባዌ በቅደም ተከተል የበይነ መረብ ነፃነትን በማፈን ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ደቡብ አፍሪካ፣ ከንያ፣ዩጋንዳና ማላዊ ደሞ በበይነ መረብ ነፃነት አፍሪካን እየመሩ ይገኛሉ፡፡


ፍሪደም ሃውስ መቀመጫው አሜሪካ ሲሆን ለዲሞክራሲ፣ለፖለቲካ ነፃነትና ለሰብአዊ መብቶች ጥብቅና በመቆም የሚታወቅ ግብረ ሰናይ ተቋም ነው፡፡

1 comment:

  1. Please let me know if you're looking for a article writer for your site.
    You have some really great articles and I feel I would be a
    good asset. If you ever want to take some of the load off, I'd really like to write some material
    for your blog in exchange for a link back to mine. Please send me an email if interested.
    Many thanks!

    My blog post game of war cheats and hacks

    ReplyDelete