![]() |
ሙሾና ጭፈራ |
በብዛት
ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሳፍራ በቀይባሕር በኩል ወደ የመን በመሻገር ላይ ነበረች ጀልባ በሃይለኛ ንፋስ ተንጣ በመስመጧ 70 ሰዎች
መሞታቸውን ቢቢሲ የየመን ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘገበ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ተጠሪ ደሞ ባለፈው ጥቅምት ብቻ 200 ሰዎች
ቀይባሕርን አቋርጠው የመን ለመድርስ በመጓዝ ላይ እያሉ ህይወታቸውን እንዳጡ አሳውቋል።
ብዙ
አፍሪካውያን ስደተኞች ሜዲትራንያንና ቀባሕርን አቋርጠው ወደ አውሮፓና ዓረብ ሃገሮች በጀልባ ለመሻገር ሲሞክሩ በተደጋጋሚ ህይወታቸውን
እንደሚያጡ የሚታወቅ ነው፡፡
በለፈውዓመት ወርሃ መስከረም 2006 ዓ.ም በብዛት ኤርትራውያን ስደተኞችን ጭና ከልብያ ወደ ጣልያን በመሻገር
ላይ ነበረች ጀልባ ሰጥማ ከ360 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ የሚታወስ ነው፡፡
ብዙዎቹ ደሞ በጎዞ ላይ እያሉ አስገድዶ መደፈርን ጨምሮ ኢሰብኣዊ ድብደባዎችእንደሚደርስባቸው የሚታወቅ ነው፡፡ህገ ወጥ ሰዎችን ሚያዘዋውሩ ዴዊኖች ስደተኞቹን ታስረው በማሰቃየት ውጪ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በሽዎች
የሚቆጠር ዶላር ልከው እንዲያስፈቷቸው እንደሚያስገደዱ ይታወቃል፡፡
ክልሆነ ግን ሆዳቸውን በመቅደድ ኩላሊቶቻቸው አውጥተው እንደሚሸጡት
የዓለም መገናኛ ብዙሓን በተደጋጋሚ የሚዘግቡት ቢሆንም የህገ ወጥ ዝውውሩ አሁንም አልቆመም፡፡
ሙሾና
ጭፈራ የተቀላቀለበት ቀን
በሌላ ዘይና ደሞ በዛሬው ዕለት( ህዳር 29 ቀን 2007 ዓ.ም) 9ኛው የብሔሮችብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንበቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በአሶሳ ‹‹በድምቀት
ሲከበር›› ኢቢሲ የቀጥታ ስርጭት እያስተላለፈ
ይገኛል፡፡ የባዓሉ መሪ ቃል ‹‹በህገ-መንግስታችን የደመቀው ኢትዮጵያዊነታችን ለህዳሴያችን›› የሚል ሲሆን
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በዓሉ ‹‹የብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትን መረጋገጥ መሰረት የጣለ ታላቅ ገፀ በረከት ነው›› ሲሉ አሞካሽተውታል ።
የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን በበኩላቸው ህገመንግስቱ የሁሉንም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ማድረጉን ገልፃዋል፡፡
------------------------------------------------------------------------
‹‹ዓለም
ደሮ ናት ላንዱ እንቁላል ሌላው ኩስ ትጥላለች›› እንደሚባለው በዛሬው ዕለት የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከአባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው
ጋር ‹‹እሰይ እሰይ እናምራለን…›› እያሉ
በመጨፈር ላይ ሲሆኑ በሃገራቸው ስረተው ለመኖር የከበዳቸው ወገኖቻችን ደሞ አደገኛው የባሕር መንገድ ለማቋረጥ ሲሞክሩ ህይወታቸውን
አጥቷል፡፡እንግዲህ በጭፈራ ላይ የሚገኙ ወገኖች ወደ ህሊናቸው ይመልሳቸው ዘንድ ስንፀልይ ህይወታቸውን ላጡ ወገኞች ደሞ መንግስተ
ሰማያት ያዋርሳቸው እንላለን፡፡

No comments:
Post a Comment